Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 25, 2014

በህዝባዊ ሰልፉ ለ ኦሰካር ሽልማት ከታጨው አደባባይ ምን እንማር/The people demand the downfall of the regime-also in Ethiopia



                  ተቃውሞንም ሆነ ድጋፍን ለመግለጽ ወደ አደባባይ መውጣት የተለመደ ነገር ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ አበባው መስቀል አደባባይን ብንመለከት እንኳ ያላስተናገደው ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ክንውን የለም። እነዚህ ክንውኖችን በበላይነት የዘመሩባቸው የዘፈኑባቸው የቦተለኩባቸው ግለሰቦች የተለያየ በጣም የማይስማሙ ርዕዮተ አለማት አቀንቃኞች ነበሩ ናቸውም። የኮሚኒስት አስተሳሰብ የነበራቸው የቀድሞዎቹ መሪዎች ኮሎኔል መንግስቱና  መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ አንዱ አንዱን ረግመውበታል። በዝነኛው የ1997 ምርጫ ሚያዚያ 29 ኢህአዴግ በማግስቱ ሚያዚያ 30 ደግሞ ዋና ተፎካካሪ የነበረው ቅንጅት ማንነታቸውን አሳይተውበታል። አላማው ለየቅል ነበር።
               ከ አዲስ አበባ ወጣ ስንልም ህዝቡ  አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ወይም ተቃውሞን የሚገልጽባቸው አደባባዮች ሞልተዋል። የሚቃወመዉም ሆነ የሚደግፈው ሰው ግን ከዛ ቦታ የሚገኘው አንድ ቀን ለዛውም ለሰልፉ በተፈቀዱት ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው። የመስቀል ደመራ ተደምሮ  እሳቱን ለኩሶ እጣኑን አጭሶ ጸሎቱ ሰማይ ይድረስ አይድረስ ሳያረጋግጥ ተቃጥሎ ሳያልቅ ደመራው ወዴት እንደወደቀ  ሳያይ እሽቅድምድሙ ቶሎ ቤት ለመግባት ነው። ይህን በዩኔስኮ አለም ቅርስነት የተመዘገበ የመስቀል ደመራ በዓል ለማነፃፀሪያ ተጠቀሰ እንጂ  በዚህ ጽሁፍ ለመጠየቅ የምፈልገው  የፖለቲካ ጥያቄን ህዝቡ ለመጠየቅ ተሰብስቦ  አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ ሳያገኝ  አደባባዩን ለምን ሰው ይለቃል ለማለት ነው።
አስረጂ
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም  የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ  ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በቅርቡ ተደርጓል።
  “ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም”  “የኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል”  “የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነህ መኮንን ለፍርድ ይቅረቡ”  እና መሰል አገዛዙን ያስበረገጉ  መፈክሮች ተሰምተዋል። እጅግ የሚደነቅ ሰልፍ ነበረ።ጮሆ ግን ከመመለስ ይልቅ ቢያንስ ይሄ አፉ መረን የሌለው ሰው ከስልጣን ካልወረደ ህዝቡ ባህርዳሩ ሰልፍ አንበተንም  ቢልስ ለማለት ወደድኩ። ጠቅላላ መንግስቱ ይውረድ ብሎ መጠየቅም ባይሆን ይሄን አንድ ግለሰብ ከስልጣን የማባረር ስራ ክልሉ የሚቀል ሰለሆነ ከስራ ለጊዜውም ቢሆን አግደነዋል ካላላችሁን አንላቀቅም ማለት ይችል ነበር ህዝቡ። አንድን ተራ ግለሰብ ማባረር ከተላመድን ሌላውም ይቀጥላል።የቅርብ ስለሆን የሄንን ሰላማዊ ሰልፍ ተነሳ እንጂ ሌሎችን ያለፉትንም ዘላቂነት ያስፈልጋቸው የነበሩ ሰልፎችን ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
ምን ኣልባትም በሕዝባዊ ሰልፉ ቁጣ ደንግጠው ከቦታው ኣንስተነዋል  በማለት ደጋፊ ለማብዛት ይጥሩ ይሆናል። 
ከሆነ እሰየው ። ነገር ግን ሌሎች ከመቶ በላይ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችንን እስኪመልሱ  መቶ 23  ዓመታትን አንታገስም። ሌሎች ሃገራት  በፈጠነ መልኩ አምባገነን መሪዎችን በህዝባዊ አብዮት እንዴት እንደቀየሩ እንመልከት።
የቱኒዝያ ተሞክሮ
መንግስታቸው በሙስና ተጨማልቆ  የመናገር የፖለቲካ ነጻነት ተነፍጎት ስራ ዕጥነት ተንሰራፍቶ በኑሮ ውድነት ማቆ ይኖር የነበረው የቱኒዚያ ህዝብ የስርዓት ለውጥ ያመጡት ባንድ ወር  ጊዜ (10 December 2011 - 14 January 2011) ያለማቋረጥ ባዳረጉት ህዝባዊ አመጽ ነው።
የቱኒዝያን ተሞክሮ አይተው የተነሱት ሊብያውያን 42 ዓመት ጫንቃቸው ላይ የነበረውን ሙአመር ጋዳፊን ለማውረድ የፈጀባቸው  6 ወር ብቻ ነው።ትግሉ በ17 February 2011 ተጀምሮ በ 23 August 2011 ጋዳፊ ተገደለ።
በህዝባዊ ሰልፉ ለ ኦስካር ሽልማት የታጨው  “አደባባይ” 
ግብጻውያን ሆስኒ ሙባረክን ፌብራሪ 2013 ያስወገዱት 17 ተከታታይ ቀንና ሌሊት በካይሮ ታህሪር ስኩየር ባደረጉት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው። ሙባረክን አስወግዶ ስልጣን የያዘውንም ሙስሊም ብራዘር ሁድ ስብስብ ተረኞቹ ጁላይ 2013 ሲያስወግዷችውም በተቃውሞ የስልፍ ቦታቸው በታህሪር ስኩየር ቀን ተሌት ሳይለዩ ደጅ የጠኑት ከአንድ ሳምንት አይበልጥም። ይሄ ሁሉ ድራማዊ ሽግግር የመጣው ደሞ ሳይታክቱ በሰልፍ ቦታቸው በመገኘታቸው ነው።“ዘ ሰኩዬር”   የሚል ዶክመንታሪ ፊልም ተሰርቶለት (የታህሪር አደባባይ አብዮት) በቅርቡ  2014 ኦስካር ሽልማት የታጨውም በዚሁ ነው www.cnn.com/2014/02/11/opinion/egypt-revolution-anniversary  
በመጪው ማርች 2 2014 አካዳሚ አዋርዱን ከመቀበሉ በፊት  ፊልሙ ፒፕልስ ቾይስ ዶኩመንታሪ አዋርድ  ቶሮንቶ 2013 ኢንተርናናል ፊልም ፈስቲቫል   እና የ2013   ኦዲየንስ አዋርድ ሰንዱንስ ከተማ   አሸናፊ የሆነ ነው።

እንግዲህ የኛ መስቀል አደባባይ ሳይሆን የደመራ በዓል ነው ዩኔስኮ አለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው። ለምን  ሰለነጻነታችን ሰለሃገራችን አንድነት የምናቀነቅንበት ይኸው አደባባይ ሆኑ ሌሎች ብሶት መተንፈሻ ቦታዎቻችን ከምናደርገው እንቅስቃሴ ጭምር ለምን አለም አቀፍ ሽልማት አልታጨም? ዶክመንታሪ ፊልም ሆኖ የዶክመንታሪ ፊልም አዋርድ ማግኘቱ ይቅርና ሰልፋችንን መቅረጽስ ይፈቀድልናል ወይ? ውጪ አድናቂዎቻችን ፊልም ሊሰሩልን የሚመጡት እኛ እንደግብጻውያን ጣህሪር አደባባዮቻችንን ቀን ተሌት በማጨናነቅ ነጻነታችንን ስናፋጥን ብቻ ነው። ትንሹ አዳራሹ የምንደልቀው የነጻነት ዕጦት ድቤ እስከ ታላላቅ አደባባይ ተቃውሞ ነጋሪቶቻችን ድረስ ምን ያህሉ ገዢዎቻችንን ጆሮ በሱት? ምን ያህሉ አለም አቀፍ ተቋማት ሚዲያዎችን ቀልብ ሳበ?
አንድ ቀን ጩኸት ብቻ ሆኖ ማለፉ ሊያንገበግበን ይገባል። የተባለውን ብቻ የሚሰራው ሃይል ማርያም ደሳለኝ እኮ ነግሮናል ላንሰማ ነገር ለየ እሁዱ  ሰላማዊ ሰልፋች የፖሊስ ጥበቃ መመደቡ ሰለቸን ብሎ።
 ጸረ አማራ አቋም እንዳለው በግልጽ ስድብ ያሳወቀውን /ኢህ አዴግ በመቃወም አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ በጋራ የጠሩት የባህርዳር ደማቅ ሰልፍ ሰልፍ ብቻ ሆኖ በማለፉ ይበልጥም ኢህ አዴግ ተቃዋሚዎች በባህር ዳር አስፈራርተው ለቀቁኝ ብሎ ይደሰታል። ሆኖም ዛሬም በማግስቱ እዛው ሰልፋችንን ባናቋርጥ ከምር አገር ጥሎ ይጠፋ ነበረ ያልለመደው ጠንካራ ተቃውሞ ሰለሚሆንበት። 
የዩክሬን ተሞክሮ
ወቅታዊ ከሆነው አውሮፓ የዩክሬን ተቃውሞም የምንማረው ቀን ተሌት የሚታገሉለት ህዝባዊ አመጽ እያሸነፈ መምጣቱን ነው። በዋና ከተማው ኪየቭ በሚገኘው ኢንዲፐንደንስ ስኩየር ዩክሬናውያን አንድነት መንግስት ካልተለወጠ አንንቀሳቀስም ብለው ለነጻነታቸው ዋጋ ከፍለዋል። የህዝብ ተመራጭነቱን ያስመሰከረው ፓርላማ ያንኮቪችን ለማስወገድ የተስማማው ህዝቡ አንድ  ሳምንት ያህል ሳይታክት አደባባዩ ባሳየው መስዋዕትነት ነው።
   10 ዓመት በፊትም የቡርትካናማ አብዮት ተብሎ የሚታወቀውን ያካሄዱ ናቸው። የሚገርመው  ምርጫ በድጋሚ እንዲካሄድ በተጠራው  በዚህ ቡርትካናማ አብዮት  ለሁለት ወራት ከ22 ኖቬምበር 2004 እስከ 23 ጃኑዋሪ  2005  በዛው አደባባይ ጠይቀው ዛሬ ያስወገዱት ያንኮቪች ያኔ ምርጫውን ፍርድቤት አጽድቆለት  ሲያስተዳድራቸው የነበረ ነው። 
ህዝብ መሪውን አደባባይ ይመርጣል ህዝብ መሪውን አደባባይ ተቃውሞ ያባርራል።
ለማጠቃለል
የቱኒዚያ የግብጽ ዩክሬን ህዝብ መጀመሪያ ለሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው  ይጠይቁና ሲቀጥል ወደ ህዝባዊ አመጽ አምርተው ከሚሰበሰቡበት አደባባይ ላፍታም ውልፍት ሳይሉ ስለታገሉ መሪዎቻቸውን ቀይረው የየጊዜውን ነፃነት ምን እንደሚመስል አወዳድረዋል።እኛ 40 ዓመት በላይ ያወዳደርነው አለመታደል ሆኖ ክፉና አምባገነን ገዠዎችን ነው   ዲሞክራሲያዊ ስረዓት በ ሃገራችን ለመገንባት ከ ሰላማዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ አመጽ በተጨማሪም ህዝባዊ አድማ እና ህዝባዊ እምቢተኛነት ልንከተለው የሚገባን ቀላል የትግል ስልቶች ናቸው።
ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት የሚያካሂዷቸው ሰልፎች ላይ ፍት ሃዊ መልስ ካላገኙ አደባባይ ባይነቃነቁ መንግስት ያልተለመደ ነገር ስለሚሆንበት ይደነግጣል፥አለም አቀፍ ትኩረትም እናገኛለን።
ኢትዮጵያውያን በውጪ አገር ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው፥ መንግስት አንቀጥቅጥ ምክክር አዳራሹ ማሰማታቸው እንኩዋን ሌላ አለም አቀፍ ትኩረት ሊያገኝ በዛው ሃገር ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥሪውን የማይሰሙበት ሁኔታ አለ።የተቀናጀ የተደራጀ ፖርታል ማስፈለጉ ይሰመርበትና በሰው ሃገር ምላሸ እስከምናገኝ ሳንታክት ማሳሰብ ያሰፈልጋል።
የጎን ጥቆማ 
          አለም አቀፍ ትኩረት የሳበው አውሮፕላን ጠለፋ እንኳ አእምሮው በተነካ ግለሰብ ድርጊት ነው ብለው የስዊዝ ሚድያዎች አራግበውታል። ጥያቄው ምን ያህል ተከላክለነዋል ነው። በሚሉትም መንገድ ቢሆን የሃገር ቤቱ የመኖር የመንቀሳቀስ ነጻነት ዕጦት ጨርቅ ያስጥላል ለማለት ማፈር የለብንም።  ማራገብ ከተነሳ ፓይለቱ ኮምፒተሩን ሲከፍት ካሜራውን የሚሸፍነው የወያኔ ደህንነት በሚያደርገው የኢንተርነት የኮምፒተር ስለላ ግራ በመጋባት  ነው ማለት ይቻላል
             በአሜሪካና  ንግሊዝ ያሉ የፖለቲካ አቀንቃኞቻችን ጋዜጠኞቻችን ኮምፒተር ወያኔ ቫይረስ ሲጋለጥ ለምን የተቃውሞ ሰልፍ እንዳልተጠራ ይገርማል።ለ አዕምሮ ጭንቀት የዳረገውም የነዚህ ወገኖቹ ና የሱም መሰለል ይመስላል። ጉዳዩን ያጋለጡት ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል እና ሲተዘን ላብ የተባሉ አለም አቀፍ ተቋማት ምስክርነታቸውን የሰጡን ሰለሆነና የተጀመረውን ክስ ለማገዝ  ከተቻለ ለብቻው ሰልፍ ይጠራበት ካልሆነም በሌላው ሰልፍ ታከን ድምፃችንን እናሰማ የኛንም የቴክኖሎጂ ነጻነት የኛንም ደሕንነት ጠብቁልን ለማለት ያመቻል ፊንፊሸር ስፓይ እና ፊንስፓይን ለፀረ ህዝብ መንግስታት የሚሸጠው ጋማ  ግሩፕ ካምፓኒን ሆነ በሰው ሃገርም የሚሰልለንን ወያኔን ለመቃወም ቦታው ምቹነቱ  በውጪ ባሉ ኢትዮጵያውያን ያደላል። ነግ በኔ ብለን ድርጊቱን አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀውና እንዲያወግዘው ማድረግ አለብን።
አብርሃም  

 February 2014

L'Ethiopie va renégocier avec l'Egypte, son projet de barrage sur le Nil

APA-Addis Abeba (Ethiopie)
Le ministre éthiopien de l’Hydraulique et de l’irrigation, Alemayehu Tegenu, a déclaré que son pays collaborait avec le Soudan pour reprendre le dialogue avec l’Egypte au sujet de l’utilisation des eaux communes du fleuve Nil.


Tegenu qui s'exprimait mardi à Addis-Abeba, a confié aux journalistes qu'il recherchait un appui au niveau de la région pour son projet dénommé ‘Great Ethiopian Renaissance Dam' (Grand barrage de la renaissance éthiopienne, GERD) d'un coût estimé à 4,7 milliards de dollars et qui est actuellement réalisé à près de 34%.

Il a précisé que les pourparlers avec les voisins de l'Ethiopie au sujet d'un rapport du groupe d'experts internationaux sur les effets du GERD sur les pays en aval étaient en bonne voie quand l'Egypte décida de quitter la table des négociations.

Il a indiqué qu'au bout du compte, le barrage serait bénéfique pour les trois pays riverains du Nil et ne ferait pas de mal aux pays en aval, comme l'avait fait croire le rapport des experts.

Le barrage éthiopien sur le Nil, près de la frontière avec le Soudan, considéré comme étant l'un des projets hydroélectriques les plus imposants au monde, va arroser 1.680 km² de forêt dans le nord-ouest de l'Ethiopie (une zone quatre fois plus vaste que la superficie du Caire) et déplacer près de 20.000 personnes.

Une fois réalisé, le projet devrait également créer un réservoir de près de 70 milliards de mètres cubes d'eau, soit l'équivalent du flux annuel du Nil bleu, le long de la frontière soudanaise, avec une capacité attendue de 6.000 mégawatts.

Le projet a cependant causé quelques clapotis entre l'Ethiopie et l'Egypte, avec l'ex-dirigeant égyptien destitué, Mohammed Morsi, qui menaçait de déclarer la guerre à Addis-Abeba pour protéger les intérêts de son pays dans le Nil.

Morsi avait déclaré que l'Egypte tirait du fleuve Nil, plus de 80% de l'eau qu'elle utilisait.

Les menaces de l'Egypte d'user de la force avaient ralenti l'exécution du projet dont la fin des travaux était prévue pour 2017.
- See more at: http://www.apanews.net/news/fr/article.php?id=509118#sthash.qbEshYEi.dpuf

wanted officials