Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 31, 2016

በኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የመከረው ስብሰባ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የመከረው ስብሰባ ተጠናቀቀ

Vision-Ethiopia-22
ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2008)
በቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጅ ታውን መሪየት ሆቴል ከማርች 26-27 2016 የተዘጋጀውና በኢትዮጵያ የወደፊት ሁኔታ በለውጥ፥ ዲሞክራሲና፣ የብሄራዊ አንድነት ላይ የሚመክር ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የስብሰባው አዘጋጆች ገለጹ። በስብሰባው የኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ የሚመለከቱ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ሲሆን በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ምሁራን፣ የሲቢክ ድርጅቶች እና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥናታዊ ጽሁፎቻቸውን ያቀረቡበትና የተሳተፉበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በኮንፈረንሱ አንኳር አንኳር አገራዊ ጉዳዮች እንደሚነሱ ሃሳባቸውን አንስተዋል። በኢሳትና በቪዥን ኢትዮጵያ ትብብር ተዘጋጅቶ በነበረው በዚሁ ኮንፈረንስ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት የተወከሉ ምሁራን በኢትዮጵያ ወቅታዊና የወደፊት አቅጣጫ ዙሪያም ሰፊ ውይይትን አካሄደዋል።
ከተለያዩ የሲቪክና የሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም የእምነት ተቋማት የተወከሉ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና የተረጋጋ ሰላምን ማምጣት በሚቻልበት ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፣ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠርም ብሄራዊ እርቅና ብሄራዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ሃገራትን ተሞክሮ በዋቢነት በማንሳት ለታዳሚ ገለጻን ያደረጉት ፕሮፌሰር አቻምየለህ ደበላ፣ በአህጉሪቱ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት አይነት ምርጫ አድርጎ መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ ብሎ ያወጀ መንግስት እንደሌለ አውስተዋል።
በጋና በናይጀሪያና በሌሎች ሃገራት በትምህርት ቆይታቸው የታዘቧቸውን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ለኮንፈርነሱ ያካፈሉት ፕሮፌሰር አቻምየለህ፣ በሌሎች የአህጉሪቱ ሃገራት ፖለቲካዊ ለውጦች መታየት ቢጀምሩም በኢትዮጵያ ያለውን አካሄድ ግን ገና ብዙ የሚቀረው እንደሆነም አስረድተዋል።
በኒው ዮርክ ሲቲ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ጆን ሀርብሰን በበኩላቸው, በኢትዮጵያ ከ1960 የአብዮት ፍንዳታ ጀምሮ ሃገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሊያደርጉ የሚችሉ አራት እድሎች ሳይሳኩ መቅረታቸውን ገልጸዋል።
በግንቦት 1977 የተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ትግሎችን ያወሱት ፕሮፌሰር ሀርብሰን፣ ከኢትዮጵያ ጋር በሽብርተኛ ዙሪያ ትብብር ያላት አሜሪካ በሃገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲያብብ ትብብር ማድረግ እንዳለባት ባቀረቡት ገለጻ አመልክተዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባት የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ሌንጮ ባቲ፣ በመንግስት የሚፈጸሙ የኢሰብዓዊ ድርጊቶች በዝርዝር ካስረዱ በኋላ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት በመሆን በስልጣን ላይ ያለውን ኢህአዴግ መስወገድ እንዳለበት ተናግረዋል።
በሃገሪቱ እየተፈጸሙ ስላሉ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ሰፊ ሪፖርትን ያቀረቡት አቶ ነዓምን የኢህአዴግ መንግስት ፌዴራላዊ፣ ዴሞራሲያዊ ወይም ሪፐብሊክ ተብሎ ሊፈረጅ እንደማይችል አክለው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የወደፊት ጉዳይ የሚመክረው ስብሰባ እሁድ እለትም በዚሁ በማሪየት ሆቴል ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በትግሉና በግጭት አፈታት እና ለዲሞክራሲ፣ አንድነት ዙሪያ ሴቶች የሚጫወቱት ሚና በሚል መድረክ ውይይት ተካሄዶበታል።
በሃዋርድ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ወ/ሪት ኤልሳቤጥ ላቀው ወደአሜርካ የፈለሱ አፍሪካውያን ሴቶችን ጉዳይ ከኢትዮጵያውያን ትግል አንጻር ትንተና ሰጥታለች። በመቀጠልም በኖርዌይ ሃገር የሚኖሩት ወ/ሮ ሰዋሰስ ጆሃንሰን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲንና ነጻነትን በኢትዮጵያ ለማምጣት በአንድነት መታገል እንዳለባቸውና ካወሱ በኋላ፣ አዲሲቷን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በመጀመሪያ እርቅ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል። በመቀጠል የተናገሩት በፍራንክፈርት የሚኖሩት የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ወ/ሮ አሳየሽ ታምሩ ሲሆኑ፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አጋርነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ወ/ሮ አሳየሽ፣ “ለልጆቻችን ማውረስ ያለብን ነጻነትን ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። በዚህ ፓነል መጨረሻ ላይ የተናገሩት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ሴቶች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ወ/ሮ ወሰን ደበላ ሲሆኑ፣ 51% የሚሆነውን የኢትዮጵያን የሚሸፍኑት ሴቶች ቢሆኑም፣ በአገራዊ ጉዳይ ተሳትፏቸው ግን እጅግ ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ወ/ሮ ወሰን የኢትዮጵያ ሴቶች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል። ፓነሊስቶቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ድምጽ እንዲሰማ ቪዥን ኢትዮጵያና መድረኩን በማመቻቸታቸው አመስግነዋቸዋል።
እሁድ ከሰዓት በኋላ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለመዳሰስ ስብሰባ ተካሄዷል። ስብሰባውን የመሩት አቶ ግዛው ለገሰ ናቸው። በመጀመሪያ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን ያቀረቡት አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሲሆኑ፣ በፓርቲዎችና በማህበረሰብ (ኮሚኒቲ) አባላት መካከል መተባበር አለመኖር ለለውጥ ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ ተናግረዋል። ለአጭር ይሁንም ለረጅም ጊዜ የጋራ ግብ በእነዚህ የማህበረሰብ አባላትና ፓርቲዎች መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ ትብብር እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። ዶ/ር መስፍን አብዲ በመሬት ጉዳይ ዙሪያ ትንተና ሰጥተዋል። በህወሃት አገዛዝ መሬት የገበሬዎች ሆኖ እንደማያውቅና ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ አያሌ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
አሁን ያለችዋን ኢትዮጵያ በማስመልከትም ያለፈው ታሪክ ሆኖ ያለፈ በመሆኑ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ሁሉም በእኩል አይን የሚታይባት አገር መሆን ይኖርባታል ብለዋል። ከዚህ ጋር በማያያዝም ኦሮምኛ የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሞና የአማራ ልሂቃንም በሁለቱ ህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር እንዲሰሩ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በመሬይ ስቴት ዩንቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰይድ ሃሰን በመሬት ነጠቃና ሙስና ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። ፕ/ር ሰይድ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና በአለም ላይ ከታዩት ሙስናዎች ለየት ያለ ነው ብለዋል። መሬት የስልጣን ምንጭ በመሆኑ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት መሬት ነጠቃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተንብየዋል። ሁሉም የኢትዮጵያ ተደራሽ አካላት ይህ ዘርፈ-ብዙ ውስብስብ ችግር ለመፍታት ተቀራርበው መነጋገር እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በኬተሪንግ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር እዝቅኤል ገቢሳ፣ የዲሞክራሲ፣ የእድገት፣ የሰብዓዊ መብት፣ የሰላም ማስፈን እሴቶችን ከውስጣችን መመልከት እንዳለብን የሚተነትን ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲ የምትሻገርበትን ብዙ እድሎችን ያጣችበትን አጋጣሚ የተነተኑት ፕሮፌሰር እዝቅኤል፣ ኢትዮጵያውያን ህወሃት ኢህአዴግን ከማስወገድ ባለፈ የወደፊት እቅድ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስረድተዋል። ፕሮፌሰር እዝቅኤል በገዳ ስርዓትና በኦሮሞ እሴቶች ላይ ትንተና ሰጥተዋል።
“ከዚህ በኋላ ወዴት? ያልተመለሱ ጥያቄዎች!” የሚለው የመጨረሻው ስብሰባ የተመራው በኮሎራዶ ሜትሮፖሊታን ስቴት ዩንቨርስቲ መምህር በሆኑት በፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ነው። ለዲሞክራሲ፣ ለለውጥና ለአንድነት ምን መደረገ እንዳለበት የመከረው ይኸው ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ለውጥ የሚያስፈልጋት አገር እንደሆነች ተናግረዋል። የኢትዮጵያውያንን ህይወት የዳሰሰ በምስል ያሳዩት ፕሮፌሰር ሚንጋ፣ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የዲሞራሲና የብልጽግና አቅጣጫ (Roadmap) ያስፈልጋታል ብለዋል። በመሆኑንም ከኤርትራ ጋር ያንዣበባት የጦርነት አደጋ፣ በኦሮሚያ፣ ኮንሶ፣ አማራ፣ ሶማሌ እና ጋምቤላ አካባቢዎች የሚታየው ግጭት ኢትዮጵያን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደከተታት ተናግረዋል። ከህወሃት/ ኢህአዴግ መወገድ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚተገበር አቅጣጫ መቀመጥም እንዳለበት ፕሮፌሰር ሚንጋ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር ተሾመ ከበደ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው ብጥብጥ የመንግስት የስልጣን ምንጭ እንደሆነ ለተሰብሳቢው ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ተሾመ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ እሴቶችን የምታከብር፣ በሉዓላዊነቷ የማትደራደር አገር እንድትሆን ማድረግ ሃላፊነት እንዳለብን ለታዳሚው ተናግረዋል። ሕወሃት/ኢህአዴግን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ እንዲደመሰስ ማድረግ ሳይሆን ዲሞራሲያዊ እሴቶችን እንዲቀበል ማስገደድ እንዳለብን ተናግረዋል። “አገራችን ችግር ላይ ናት፣ የእኛን እርዳታ ትሻለች” ሲሉ ለተሰብሳቢው ተናግረዋል።
ከዚህ ቀጥሎ የተናግሩት የህግ ባለሙያና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባት አባል የሆኑት ዶ/ር በያን አሶባ ሲሆኑ፣ ያለፉትና የአሁኑ አምባገነን መንግስታት በህዝቦቻችን ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ሌሎች ኢትዮጵያውያን በኦሮምያ እየተከሰተ ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ በጥርጣሬ መመከታቸውን ትተው እንዲደግፉት ጥሪ አቅርበዋል።
በካሊፎርኒያ ግዛት ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም የአምባገነን መንግስታት ባህሪ ነገሮችን መደበቅ ነው ብለዋል። በመሆኑም ህወሃት ኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይታወቅበት ኢሳትን በብዙ ሚሊዮን ብር በመክፈል በተደጋጋሚ በሞገድ ለማገድ መሞከሩን ለተሰብሳቢው ተናግረዋል። ሆኖም ህወሃቶች ለሰሩት ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ የሚሆኑበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ለተሰብሳቢው ገልጸዋል። ለዲሞክራሲና ለእኩልነት የሚደረገው ትግልም ህወሃት/ወያኔ ኖረም አልኖርም መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑን አስረድተዋል። አዲስ አቅጣጫ የሚያመላክት ህገ-መንገስትም መዘጋጀት እንዳለበት ተሰብሳቢውን መክረዋል።
በመጨረሻ የቀረቡት በዳይተን ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ናቸው። የተሻለው አቅጣጫ አሁን ያለውን በዘውግ የተከለለውን አስተዳደር መከተል መሆኑን አስመረው፣ ኢህአዴግ ቢወገድም የዘውግ ጥያቄ በቀላሉ የሚጠፋ አለመሆኑን ገምተዋል።
ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች በሁላ በርካታ ጥያቄዎች ለተሰብሳቢዎች የቀረቡ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከመድረክ መልስ ተሰጥቶባቸዋል። አንዳንድ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ወደ ፊት በሚካሄዱ ስብሰባዎች እንደሚነሱ ለማወቅ ተችሏል።


ይድረስ! የጥላሁን ገሠሠን ክብር ታሪክና ዝና ለመሸከም ሁነኛ ትከሻ ላጣሽው ለወ/ሮ ሮማን በዙ!


የራስጌ ማስታወሻ፡
ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ክብሪት ሆኖ ያነሳሳኝ ለኳሽ ምክንያት መስፍን በዙ የሚባል ሰው በጥላሁን ገሠሠ ስም በተከፈተ ቴሌቪዥን እየሰራ ያለው ነገር ከአርቲስቱ ሙያዊም ሆነ ግለሰባዊ አመለካከት ጋር የማይገናኝ የመሆኑ እንቆቅልሽ ነበር።
በመሆኑንም እንቆቅልሹን ለመፍታት የሚያግዙ መጠይቆችን አወጣጥቼ አንድ ሁለት እያልኩ ስጓዝ ለመጠይቆቼ የማገኛቸው መልሶች ደግሞ እንደ ክር እየተረተሩ ወደ ቱባው ጉዳይ ወሰዱኝ። ወደ ወይዘሮ ሮማን በዙ!።
እናም ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝን መስፍን በዙን ተውኩና በወይዘሮ ሮማን ላይ አነጣጠርኩ። ዋናው ባለጉዳይ እያለ በጉዳይ አስፈጻሚው ላይ ጊዜ ማጥፋት አልፈለኩም። ጥቂት ከማትባል ጥናትና ክትትል በኋላም እንሆ የጥላሁን ገሠሠን ክብር ዝና ለመሸከም ሁነኛ ትከሻ ላጣሺው ለ “ወሮ ሮማን በዙ” በሚል ርዕስ እጽፍ ዘንድ ብዕሬ ፈቀደ፦በግልባጭም የተወዳጁ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ወዳጅና አፍቃሪ ለሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይድረስልኝ ።
ወይዘሮ ሮማን ፡ በቅድሚያ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አንቱታን ከመጠቀም ይልቅ “አንቺ” እያልኩ የምጠራሽ በእድሜ ብዙም እንደማንበላለጥ ካለኝ ግንዛቤ እንጂ ከኢትዮጵያዊነት ባህልና ስነ-ምግባር ውጭ በሆነ የማሳነስ ወይም የንቀት ስሜት አለመሆኑን እንድትረጂልኝ እሻለሁ።
ስቀጠልም፡ ከላይ ለአንባቢያን ባስቀመጥኩት የራስጌ ማስታወሻ እንደገለጽኩት የዚህ ጽሁፍ ጽንስ “ቲጂ ቴሌቪዥን” አፍቃሪ-ወያኔ የመሆኑን እንቆቅልሽ ለመፍታት መነሳቴ ነው። ወንድምሽ በተወዳጁ አርቲስት ስም በተከፈተ ቴሌቪዥን እየሰራ ያለው ከአርቲስቱ ሙያዊም ሆነ ግለሰባዊ አመለካከት ጋር የማይገናኝ መሆኑ በእውነትም ለአብዛኛው ኢትዮጵ ያዊና አርቲስቱን ለሚያከብረው ዜጋ ሁሉ እንቆቅልሽ ነበር።ቢያንስ ቢያንስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ።
ይህ መሆኑ ያሳሰባቸው ጥቂት የማይባሉ ጸሃፊዎች በተለያዩ ግዚያት ለወንድምሽም ሆነ ላንቺ ምክርና ማሳሰቢያቸውን ጽፈው አንብቢያለሁ። (ማሳሰቢያ አንድ)  (ማሳሰቢያ ሁለት)  (ማሳሰቢያ ሶስት)
ይሁንና ወንድምሽ ከአሳፋሪ ድርጊቱ እንዲቆጠብ የተሰጠውን ምክርና ማሳሰቢያ ችላ ብሎ ጭራሽ ሃገርና ህዝብ አጥፊ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፤ ለዚህ ማን አለብኝነቱ ዋና ጉልበቱ ደግሞ አንቺ በመሆንሽ ይህ ጽሁፍ በሳምንት አንዴ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ ከሚቀበጣጥር ተቀጣሪ ሰው ይልቅ “የአርቲስቱ 6ኛ ባለቤት” የሆንሺውን አንቺን በተጠየቅ ይሞግታል።
ታዲያ መልዕክቴ ለአንባቢም ግልጽ እንዲሆን ያንቺንና ይህ መልዕክት በተቀጣሪነቱም ቢሆን የሚመለከተውን የወንድምሽን ማንነት ላስተዋውቅ።
ውድ አንባቢያን ወ/ሮ ሮማን፤ የክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ 6ኛ ሚስት የነበረች፤ በአሁኑ ሰአት ደግሞ በጥላሁን ገሠሠ ስም ማለትም “ቲጂ” ወይም (TG TV) በሚል መጠሪያ በአሜሪካን … ውስጥ  የሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለንብረት ስትሆን ይህ ቴሌቪዥን በወንድሟ መስፍን በዙ የሚንቀሳቀስና አፍቃሪ-ወያኔ አመለካከት ያለው፤ የወያኔን ብጹኡነት የሚሰብክና የሚያራምድ ነው።
ወደ መልዕክቴ ልግባ፦
/ ሮማን ሆይ! ውዱና አይተኬው ጥላሁን ገሠሠ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ማለት እንደሆነ በስርዓተ ቀብሩ ላይ ተገኝተሽ ያየሺው ይመስለኛል ። አንቺ ልትረጂው ያልቻልሺው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥላሁን ገሠሠ ምን ማለት እንደሆኑ ነው። ይህን ደግሞ አለመታደል ሆኖ እንጂ ከማንም በበለጠ አብረሺው ጎጆ የቀለሺው (በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ያልገባሽ 6ኛ ሚስቱ ብትሆኚም) ልታውቂው በተገባ ነበር።
አዎ ! ጥላሁን ለሃገሩና ለወገኑ ስላለው ፍቅር ጥቂት እንኳ ግንዛቤ ቢኖርሽ ኖሮ ፤ ዛሬ በጥላሁን ስም ከወንድምሽ ጋር እየሰራችሁት ያለው ነገር ሁሉ! እሱ ከ14 ዓመት እድሜው ጀምሮ የደከመለትን፤ የቆመለትን፤ እያለቀሰ ያዜመለትን ኢትዮጵያዊነት የሚያጠለሽ የክህደት ሥራ መሆኑን ከማለዳው መረዳት በቻልሽ ነበር።
የጥላሁን ህዝባዊነትና የቲጂ ቲቪ (TG TV) አቋም ምንና ምን ናቸው?
ወ/ሮ ሮማን ለመሆኑ (TG TV) ብላችሁ በንጉሱ ስም በከፈታችሁት ቴሌቪዥን የሚተላለፈው “አፍቃሪ-ወያኔ” የሆነ ዘገባ ከጥላሁን ገሠሠ ማንነት ጋር ምን ያገናኘዋል ነው?
እንደ ግለሰብ ያሻችሁን መደገፍም ሆነ መንቀፍ መብታችሁ ነው፡፤ የኢትዮጵያዊው ጥያቄ ለምን በጥላሁን ስም በተከፈተ ቴሌቪዥን የወያኔን መንግስት ማገልገል ተፈለገ? የሚል ነው።
በአርቲስቱ ስም እስከተከፈተ ድረስ ፕሮግራሙም በእሱውና ሰፋ ካለም በኢትዮጵያ ሙዚቃና አርቲስቶች ዙሪያ መሆን አይገባውም ነበርን? ቴሌቪዥኑ የተቋቋመበት አላማ ምንድነው ?
በነገራችን ላይ እንዲሁ ሳስበው፤ ትንሽም ቢሆን ፊደል የቆጠርሽ ይመስለኛልና ስለ ጋዜጠኝነት ሙያ ግንዛቤ እንደሚኖርሽ እገምታለሁ። በመሆኑም የወያኔ ባለስልጣኖችን ጭራና ዱካ እየተከተለ ሳይጠሩት አቤት፤ ሳይልኩት ወዴት የሚለው ወንድምሽ በቴሌቭዥን ጣቢያው በሚያቀርበው ፕሮግራም የምትሸማቀቂ እንጂ የምትኮሪ አይመስለኝም። ደግሞስ አሸከርነት ምን ያኮራል ብለሽ ነው?
ታዲያ! ወንድሟ ይህን የሚያሳፍር ስራ ሲሰራ እያየች ዝምታ መምረጧ ለምንድነው? ብዬም መጠይቄ አልቀረም። ባይገርምሽ ይህ ጣጠኛ ጥያቄ ነው ለመስፍን በዙ የታሰበውን ጽሁፍ አቅጣጫ አስለውጦ ላንቺ እንድጽፍ ያደረገኝ። መስፍን በዙ! ብዙነው መዘዙ …ሆነ መሰለኝ። ስለዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ።
ከላይ እንደገለጽኩልሽ ምንም እንኳ የውዱ አርቲስት የአንድ ወቅት ጎጆ ተጋሪ ብትሆኝም እንደ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥላሁን ገሠሠ ምን ማለት እንደሆኑ የተረዳሽ አይመስለኝም ። ስለዚህ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥላሁን ምን ማለት እንደሆኑ በመጠኑም ቢሆን ላመላክትሽ።
/ ሮማን አንቺንና የምትደግፊውን የወያኔ መንግስት የሚያመሳስላችሁ አንድ ነጥብ አለ። ወያኔዎች የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው እኛ ስልጣን ከያዝንበት ጊዜ ጀምሮ ነው ሲሉ አንቺም የጥላሁን ታሪክ የሚጀምረው እኔ ካገኘሁት ጊዜ ጀምሮ ነው ማለትሽ ነው።
/ ሮማን ጥላሁን የቀድሞውን ሰራዊት ዩኒፎርም ለብሶ ሰራዊቱን ለመቀስቀስ ሲሄድ መንደፈራ ላይ በፈንጂ ተመቶ መቁሰሉን ታውቂያለሽ ? ዳሩ ከጥላሁን ዝና እንጅ ከታሪኩ ምን አለሽ? ዝና እንጂ ታሪክ አይመነዘር።
ቴሌቪዥናችሁ ስለ ህውሃት 40ኛ ዓመት ተጋድሎና ጀግንነት ሲዘክርልን በአኳያው ደግሞ የቀድሞውን ሰራዊት  ፋሽሽትነት ሲያውጅልን እንደ ባላቤትነትሽ “ እረ ይሄ ነገር ደግ አይደለም! ከጥላሁን ገድልና ታሪክ ጋር ይጣረሳል ” ብለሽ ማሰብ የተሳነሽ ለምን ይሆን? ። (ይቅርታ ለካስ ጥላሁን ለናንተ ስም ነው)
TG TV, Mesfin Bezu
ወሮ ሮማን!  ጥላሁን “አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሰስላት፤
እንጂ ሃገሬን ጭራሽ አይደፍራትም ጠላት”
ያላት ሃገር ኢትዮጵያ ነች! በዜማው ብቻ ሳይሆን በተግባርም ደሙን አፍስሶላታል! አጥንቱን ከስክሶላታል! ።  ዛሬ ወንድምሽ ባስነጠሱ ቁጥር መሀረብ የሚቃጣላቸው ስመ-መንግስት የያዙትን ወንበዴዎች ለመፋለም ከዘመተው ጦር ጋር ዘምቶ መንደፈራ ላይ ነበር የቆሰለው።
አንቺም ራስሽ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ከሚታተመው ቁምነገር ጋዜጣ ጋር ባደረግሺው ቃለ ምልልስ ፦
“ጥላሁን የውልደት ቦታ ወይም የብሔር ነገር የሚያሳስበው ሰው አልነበረም፡ ፡ በተለያዩ ቦታዎች የሆነ ፎርም ሲሞላ እንኳ ብሔር ሲባል ኢትዮጵያዊ ብሎ ነበር የሚሞላው፡፡ ጥላሁን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡” (ቃል በቃል የተወሰደ)
ብለሽ እንደነበር አንብቢያለሁ ፡: በስሙ የከፈትሺው ቴሌቪዥን ጣቢያሽ ደግሞ ዘርን እንጂ ኢትዮጵያዊነት መስማት ለማይፈልገው የወያኔ መንግስት አገልጋይ መሆኑን እንዴት ታስታርቂዋለሽ?፡:
ወ/ሮ ሮማን ጥላሁን እንዲህም ሲል ያዜመው ለኢትዮጵያ ነው።
ለሀገሬ ስታገል ለድንበሯ
ወድቂ
ለሁ እኔ አፈሯ
ስለ
ድል ታሪኬ ስታነሱ
ቤተሰቦቼን ግን እንዳትረሱ
አየሽ..? ወሮ ሮማን! ጥላሁን ቤተሰቡን እንኳ አደራ ብሎ የተናዘዘው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አደራ ጠባቂ ህዝብ ነው። አሁንም ቢሆን የጥላሁንን የአብራክ ክፋዮች አክብሮና አፍቅሮ ይኖራል። የሚገርመው ግን ጥላሁን “ቤተሰቦቼን ግን እንዳትረሱ”  ብሎ ለህዝብ በሰጠው የአደራ ኑዛዜ ውስጥ በህዝባር እንኳ ሊጠቀስ የማይችለው ወንድምሽ ዝክር አውጭ ሆኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ነው።
ጥላሁን በዜማዎቹ “ኢትዮጵያ” ን ሲያነሳ እንባ ከጉንጮቹ ይቀዳ እንደነበር ሳስታውስና ዛሬ ደግሞ በስሙ በተከፈተ ቴሌቪዥን ያቺ የሚያነባላት ሃገሩን እያጠፉ ያሉ አረመኔዎች መወደሳቸውን ሳስብ፤ ሃዘኔ ይከብዳል!!!።
ጥልዬ፤ በህይወት ዘመኑ ህዝብን ሲያስደስት ቢኖርም የራሱ ህይወት ግን በብዙ መከራዎች የተሞላች ነበረች።  ሞቶም አትረፍ ቢለው ወራሽ ነኝ ባይዋ ክብሩን ታሪኩንና ዝናውን መሸከም ተሳናት።
/ ሮማን ሆይ እውነት! እውነት! እልሻለሁ የጥላሁን ገሠሰን ክብር ታሪክ ዝና የሚሸከም ትከሻ የለሽም!
ብዙ ጊዜ ሰዎች ዝናን ይወዳሉ፤ ብዙዎች በየሄዱበት መታወቅ፤ እከሌ መባል ያስደስታቸዋል። ፍላጎቱ ተፈጥሯዊ ነው። ዝናና ታዋቂነቱ በስራና ማህበራዊ አግባቡን ጠብቆ የተገኘ ከሆነ ማለቴ ነው። በሌሎች ትከሻ መታወቅን አልሞ መነሳት ግን ጸያፍ ነው.። አንቺም የፈለግሺው የጥላሁን ባለቤት እየተባልሽ በቀይ ምንጣፍ ላይ መራመድና በሁሉም ያገልግሎት መስጫ ቦታዎች ቅድሚያ ማግኘትን ነው። ትንሽ ተሳክቶልሽ ይሆናል፡፡ ጥላሁንን የሚወዱ ሁሉ በዩሉኝታም ይሁን በጥላሁን ፍቅር በመሸነፍ አንድ እርከንም ቢሆን ከፍ ሳያደርጉሽ አልቀሩም። ወሮ ሮማን አንድ ያልተረዳሽው ነገር የታዋቂ ሰው ሚስት መሆን ያውም የጥላሁን! ጓዙ ብዙ…. መሆኑን ነው። ወደ አደባባይ ስትወጭ ከፀጉር አሰራርሽ እስከ እግርሽ ቅርፅ ለእይታና ለትችት ይጋለጣሉ። አንዱ አይኗ ያምራል ሲል፤ ሌላው እግሯ ወፍሯል ይላል። ይሄ እንግዲህ ከዝናና አደባባይ ከመዋል ጋር የሚመጣ ነው።በዚህ ላይ ደግሞ ቴሌቪዥን ከፍታችሁ ሰውን ስታዋርዱ በአፀፋው የሚመልስ ሰው መኖሩን ያስተዋላችሁ አይመስለኝም ።
እንዳሁኑ ከጥላሁን ፍላጎት ጋር የማይዛመድ ነገር የመስራትሽ ዚቅ አደባባይ ሲወጣ ደግሞ በይሉኝታም የተሰጠሽ የክብር እርከን ይገፈፋል፡፤ ቁልቁል ተመዘግዝጎ ይወርዳል።ወ/ሮ ሮማን ያገባቺው ጥላሁንን ሳይሆን ዝናውን መሆኑን ህዝብ እንዳሁን ሲደርስበት ማለቴ ነው።  የጥላሁን ዝና ምንጩ ደግሞ ድንቅ ስብዕናውና የሃገር ፍቅሩ ነው፡፡ አንቺ ደግሞ ድንቅ ስብዕናውንና የሃገር ፍቅሩን አውልቀሽ ጥለሽ ዝናውን ብቻ ለመሸከም ፈለግሽ። ትከሻሽ ሁሉንም መሸከም ስላልቻለ የማይነጣጠሉ ነገሮች ነጣጠልሽ። አዲዎስ!!
ልቀጥል…..ወ/ሮ ሮማን
ጥላሁን ለሰው ህይወት ያለውን ክብርና ሰባዊነት በተለይም በህጻናት ላይ የሚደርስ እንግልት የሚያሰቃየው ሩህሩህና አዛኝ እንደነበር “በወሎ ድርቅ” ዘመን “ዋይ! ዋይ! ሲሉ የርሃብን ጉንፋን ሲስሉ” እያለ በርሃብ ሲሰቃዩ ለነበሩት ሕጻናት በእንባ እየታጠበ ያዜመላቸውን ዜማ ብቻ ማስታወስ በቂ ነው።
ዛሬ ደግሞ በዚህ ሩህሩህና አዛኝ አርቲስት ስም የተከፈተው የወሮ ሮማን ቴሌቪዥን የ14 ዓመት ሕጻን ጭንቅላት በጥይት የበረቃቀሱ አረመኔዎች ይወደሱበታል።ይሞገሱበታል።
TG TV, Mesfin Bezu
ወሮ ሮማን ባንክ ሊዘርፍ ሲል ተገደለ የተባለ ው የ14 ዓመት ህጻን ነብዩ ይህ ነው። ይህ ህጻን ዛሬ ቢኖር የ25 አመት አበባ ሊሆን እንደሚችል የምታስብ እናት ገዳዮቹን መደገፍ ቀርቶ ማየትም የምትፈቅድ አይመስለኝም።
ወሮ ሮማን በጥላሁን ስም የከፈትሺው ቴሌቪዥን ከሱነቱና ከብሄራዊ ስሜቱ ጋር ፍጹም የማይገናኝ ጭራሹኑ የሚቃረን ስለመሆኑ በቂ ማሳያ የጠቃቀስኩ ይመስለኛል። አነሰ ከተባለም መጨመር ይቻላል። እድሜ ተዝቆ ለማያልቀው የጥልዬ ገድልና ዝብርቅርቁ ለወጣበት የወንድምሽ ዘገባ …እያነጻጸሩ መዘርዘር ይቻላል፡፤ለጊዜው ግን የአንባቢን ጊዜ ሳልሻማ ወደ ቀጣዩ ጉዳይ ላምራ፦
በነገራችን ላይ ወንድምሽ መስፍን በዙ በቴሌቭዥኑ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ሲያጥላላቸው ከነበሩና እያጥላላቸው ከሚገኙት የወያኔ መንግስት ጠንካራ ተቃዋሚዎች መካከል ዋናውና ግንባር ቀደሙ አርቲስት ታማኝ በየነ ነው።
ወንድምሽ በታማኝ በየነ ላይ የሰራውን ከ8 ሰዓት ያላነሰ ዘገባ ተመልክቻለሁ። ይህን ያህል ሰአታት የፈጀው ዘገባ ጠቅላላ ይዘት በሁለት ክሶች ላይ ያጠነጠነ ይመስለኛል።
1ኛው ታማኝ ጥላሁንን አስቀይሞታል! ጥላሁን በታማኝ ምክኒያት አዝኖ ያለቅስ ነበር
2ኛው ታማኝ በጥላሁን የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ህዝብ እንዳይገባ አሳድሟል! የሚሉ ናቸው።
እነኚህ ክሶች ውስጤን ይከነክኑት ስለነበር ታማኝ በየነን አግኝቼ የምጠይቅበትን አጋጣሚ በጣም እጓጓ ነበር። ጉጉቴ በከንቱ አልቀረም። ከለታት አንድ ቀን ታማኝ በየነ ለኢሳት ዝግጅት እኔ ያለሁበት ሃገር መጣ።  አጋጣሚውን በመጠቀም እኔና እንደኔው ነገሩ የከነከናቸው ሌሎች ሁለት ሰዎችን ጨምሬ 3 ሆነን ታማኝን ለ30 ደቂቃ እንዲያገናኙን የኢሳት ዝግጅት አስተባባሪዎችን  ጠየቅን።  የአዘጋጆቹም የታማኝም ፈቃድ ሆነና ከታማኝ ጋር ተገናኘን። ከሰላምታ ልውውጥ በኋላ በቀጥታ ወደ ጉዳዩ በመግባት በመስፍን በዙ ስለሚቀርቡበት ክሶች ያለውን አስተያየት ጠየቅነው።
በመጀመሪያ እኛ የፈለግነው ለጋራ የሃገር ጉዳይ መስሎት ስለነበር የግል ጉዳይ ስናነሳበት  “አዬዬ….!’’ ካለ በኋላ ለተሰነዘረበት ነገር ብዙም ቁብ እንደማይሰጠው የሚገልጽ ፈገግታ አሳይቶን፤ ነገር ግን ለኛ ባለው ክብር ብቻ የሚከተለ ውን መልስ ሰጠን።
ሁለት ነገር ብቻ ልንገራችሁ፡
1 እኔ ጥላሁንን የወደድኩት በፈቃዴና በፍላጎቴ ነው። ሰውን ስትወድ ደግሞ ከነ ሁለመናው መሆን አለበት። ሰለዚህ ራሴን ለመከላከል ብዬ በሰላም ያረፈውን ንጉስ ከመቃብር እያወጣሁ በዚህ ምክኒያትእንዲህ ስለሆነ ..እያልኩ የጥላሁንን ክብር የሚነካ ክርክር አልከራከርም። እኔ ስለ ጥላሁን ያለኝን ስሜት ሶስታችን እናውቃለን እግዚአብሄር ጥላሁንና እኔሌላው ትርፍ ነው።
2 በጥላሁን ጉዳይ የሚጠይቀኝና የሚከሰኝ ከጥላሁን ልጆች አንዳቸው ቢሆኑ ኖሮ መለስ እሰጥ ነበር ለነዚህ ሁለት ሰዎች ግን ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢል አልመልስላቸውም ማን ናቸው ብዬ??? ይልቅ እናንተ  እውነትን የማወቅ ፍላጎት ካላችሁ ለምን ከጥላሁን  ልጆች አንዳቸውን አትጠይቁም??ነበር ያለን።
የታማኝ አጭርና ግልጽ መልስ በተለይ እኔን ለሌላ ነገር አነሳሳኝ። አዎ! እውነቱን ለማወቅ ከጥላሁን 6ኛ ሚስት ወንድም ይልቅ የአብራኩ ክፋዮች ይቀርባሉና ከጥላሁን ልጆች አንዱን ማግኘትና ማናገር ፈለኩ ።
ይህን ያሰብኩት ከታማኝ ከተለየሁ በኋላ ነበርና የጥላሁን ልጆችን የማገኝበትን መንገድ እንዲነግረኝ አለመጠየቄ ሲያስቆጨኝ ያየው አንደኛው ወዳጄ የጥላሁን ገሠሠ ሁለተኛ ልጁ “ንጹህብር ጥላሁን ገሠሠ” ስለታማኝና ጥላሁን አባትና ልጅነት የሰጠቺው ምስክርነት እንዳለ ነግሮኝ ቪዲዮውንም አሳየኝ(ቪዲዮውን ለማየት)። ይህን ካየሁና ካደመጥኩ በኋላ መስፍን በዙ የሚባል ሰው ርካሽነት ገዘፈብኝ!። ጉዳዩ በአንቺም እውቅና የሚካሄድ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው “የስም ማጥፋት ዘመቻ” መሆኑ ደግሞ በተከታታይ ባደረኳቸው ጥናቶች ግልጽ ሆነልኝ ።
ወሮ ሮማን በነገራችን ላይ! በታማኝ ላይ የምታነሱትን ክስ አንዱም የጥላሁን ልጅ አብሯችሁ የማያነሳው ለምን ይሆን? ጭራሽ አባታቸውን በድሏል የተባለውን ታማኝን የጣት ቀለበትን ያህል ክቡር ሽልማት እንዴት ሊሸልሙት ይችላሉ ? ለመሆኑ እናንተስ በቴሌቭዥናችሁ የጥላሁንን መታሰቢያ ፕሮግራም ስትሰሩ ከጥላሁን ልጆች አንዱን እንኳ ጋብዛችሁ ታውቃላችሁ? ታማኝ ባዘጋጀው የጥላሁን መታሰቢያ ላይ ደግሞ ካንቺ በስተቀር ሁሉም የጥላሁን ቤተሰቦች መገኘታቸውስ ምን ማለት ይሆን? ታዲያ ለጥላሁን የሚቀርበው ማን ነው?  …..ወደ ሌላው ለልፍ
ወ/ሮ ሮማን እዚህጋም አንድ ግዙፍ ቁምነገር የሳትሽ ይመስለኛል!
“አይተኬው የህዝብ ልጅ” ከዚህ አለም በሞት በተለየበት መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ባለቤቱ ስለነበርሽ የቁሳዊና የሌሎችም ተያያዥ ንብረቶቹ ወራሽ መሆንሽን የሚያረጋግጥ ወረቀት በነጋሪት ጋዜጣ አሳውጀሽ አግኝተሽ ይሆናል። ነገር ግን ትልቁን ሃብትና ንብረቱን “የህዝብ ፍቅር” ልትወርሺ አትችዪም። አልቻልሽምም፡፡
የጥላሁን ገሠሠ ሥራ፤ ታሪክና ማንነት ብቸኛ ወራሽ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ። ይህ የህዝብ መብት ደግሞ በጋዜጣ ታውጆ በዳኛ መዶሻ የሚጸድቅ መብት ሳይሆን አርቲስቱ በህዝብ ልብ ውስጥ በገባበት ቅጽበት የጸናና ይግባኝ የማይባልበት መብት ነው። እናም ኢትዮጵያዊው ሁሉ የጥላሁን …  ወራሽ ባለመብት ነው።
በጥላሁን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ባለመብት መሆኑን ደግሞ ብዕሩ የተባረከ ይሁንና ‹‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ምስጢር›› በሚል የውዱን አርቲስት ታሪክ ግሩም አድርጎ ጽፎ ለንባብ ያበቃው ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ በማያዳግም መልክ ያስገነዘበሽ ይመስለኛል።
ወሮ ሮማን! ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ የጥላሁንን ታሪክ ለመጻፍ ሲነሳ አርቲስቱን ከህጻንነት እስኪ እልፈቱ ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች በቅርብ የሚያውቁትን በርካታ ወዳጆቹንና ቤተሰቦቹን አነጋግሯል። አንቺን ግን አላናገርሽም። ማናገርም አልፈለገም። ለምን ይመስልሻል? የጥላሁን ታሪክ ወራሽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ አንቺም ሆንሽ ዘመድ አዝማዶችሽ አለመሆናችሁን ሲነግርሽ ነው።
የመጽሃፉ ደራሲ ዘካሪያ መሃመድ ከቁምነገር ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሎ ነበር፡
ቁም ነገር፡- የጥላሁን ቤተሰቦች ስለ መፅሐፉ ያውቃሉ?
ዘከሪያ፡- የግል ታሪክ መፅሐፍ እራሱ ነው የሚመራህ፤ የሰውየውን የህይወት ምዕራፍ ነው የምትከተለው፡፡ የአቶ ፈይሳ ሐሰና ሀይሌ የቤተሰብ ማስታወሻ ከተመለከትኩ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ታሪኮችን ለማሰባሰብና ለመተንተን የጥላሁንን ቤተሰቦችና የሱን የቅርብ ወዳጆችን አነጋግሪያለሁ፡፡ ከወዳጆቹና የስራ ባልደረቦቹ መካከል እነ መሐሙድ አህመድ፣ ደበበ እሸቱ፣ አቶ ከበደ ወጋየሁ፣ ወ/ሮ ቆንጅት፣ ወ/ሮ አድባሪቱ የመሳሰሉትን አነጋግሪያለሁ፡
ቁም ነገር፡- ከቤተሰቦቹስ?
ዘከሪያ፡- ወ/ሮ ማርታ፣ ወ/ሮ ሒሩትን እንዲሁም ልጆቹንም አግኝቻቸዋለሁ፤ ይህን ስራ እየሰራሁ እንደሆነ የማያውቁ አሉ ብዬ አላስብም፡፡ ልጆቹንና የትዳር አጋሮቹን አግኝቻቸዋለሁ፡፡
የጥላሁንን የትዳር አጋሮች ሁሉ ሲያነጋግር አንቺን ማናገር አልፈለገም። አንቺን ማማከር ያለመፈለጉ በራሱ የጸሃፊውን በሳልነት ያሳያል። ምክንያቱም አንቺን ካማከረ እያንዳንዷ የጥላሁን ታሪክ ጠብታና እንጥፍጣፊ አንቺና አንቺ ጎጆ ጣሪያ ላይ ብቻ እንድታርፍ ማድረግ እንደምትፈልጊ አውቋል። ይህ መሆኑ ደግሞ የጥላሁንን ታሪክ ያጠለሸዋል። እናም ጸሃፊው አንቺን አለማማከሩ የኢትዮጵያ ህዝብና የጥላሁን ድንቅ ባለውለታ ነው።እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስኩት ደግሞ ይህንኑ ታሪከኛ መጽሃፍ ካነበብኩ በኋላ ነበር። (ስለ መጽሃፉ ከተሰጡ አስተያየቶች አንዱ ይህን ይመስላል)
የሙዚቃውን ንጉስ እንደ ጆንያ ከሰል…
መስፍን በዙ በታማኝ በየነ ላይ ካነሳቸው ክሶች አንዱ፦”ጥላሁን በታማኝ ምክኒያት አዝኖ ያለቅስ ነበር” የሚል ነው። ለመሆኑ ጥላሁንን ያሳዘነው ማን ነው?
‹‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ምስጢር›› በሚል በጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ የተጻፈው የጥላሁን ታሪክ ጥላሁንን ማን እንዳሳዘነው በማያሻማ ምስክርነት አስደግፎ ያስነብበናል።
በመጸሃፉ ላይ ምስክርነታቸው የሚሰጡት ፕ/ር ኃይሌ የጥላሁን የረዥም ጊዜ ወዳጅ ናቸው። ጥላሁንን በተለያዩ ጊዚያት እቤቱ እየሄዱ ይጠይቁታል። አይዞህ! ይሉታል።
ፕ/ር ኃይሌ በአንድ አጋጣሚ ጥላሁን ቤት ሄደው ያስተዋሉትን ለጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ እንዲህ ብለው ገልጸውለታል። ቀጥሎ ያለውን የመጽሃፉን አንድ ገጽ ቁራጭ ኮፒ ያንብቡ
TG TV, Mesfin Bezu
ወ/ሮ ሮማን፡ ለመሆኑ የፕ/ር ኃይሌን ምስክርነት እንደምን ታይዋለሽ? መቼም ፕ/ሩ ፈጥረው ተናገሩ ብለሽ ለማስተባበል እንደማትሞክሪ እገምታለሁ። ታዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ “የሙዚቃው ንጉሥ” እያለ የሚያከብረውን ታላቅ ሰው “እንደ ጆንያ ከሰል” መኪና ውስጥ ክተቱት ብሎ እንግዳ ፊት ማበሻቀጥ በምን …. ሊገለጽ ይችላል? ምን የሚሉት ስነ-ምግባር ነው? … ጥላሁንን ይህ ያላሳዘነው! ይህ ያላስለቀሰው! ምን ሊያሳዝንና ሊያስለቅሰው ይችላል?
በዚህ ምግባርሽ  እንኳን  የጥላሁን  አፍቃሪ  ኢትዮጵያዊ  ይቅርና  ልጆችሽም  ይቅር የሚሉሽ አይመስለኝም!።
ወ/ሮ ሮማን የመጽሃፉ ደራሲ አንቺን ያልጠየቀበት ምክንያት ለማንም ግልጽ ነው። በቁሙ ያላከበርሺውን ሰው ከሞተ በኋላ የታሪኩም የክብሩም ሆነ የዝናው ተጋሪ የመሆን መብትም ሆነ የሞራል ብቃት ሊኖርሽ እንደማይገባ በማመኑ ነው። ትክክልም ነው። አንቺ ግን በሚገርም ይሉኝታ አጥነት የጆንያ ከሰልን ያህል ክብር የነሳሽውን ሰው “ በሱ ጉዳይ የሚያገባኝ እኔና እኔ ብቻ ነኝ!” ብለሽ ትናውዢያለሽ። ካንቺ የተረፈ ውርሰ-ዝና ካለም ወደ ዘር ማንዘርሽ እንዲፈስ ወንድምሽን የፍሳሽ አሸንዳ አርገሽ አሰለፍሽ። አይ የሰው ተፈጥሮ…..!?
ጥላሁን እውነትም ያልታደለ ሰው ነው!
በዚሁ ታሪካዊ መጽሃፍ ውስጥ የጥላሁን አምስተኛ ሚስት ወ/ሮ ማርታ ሲማቶስ ጥልዬን እንዴት ትንከባከበው እንደነበርና ለጤንነቱ ምን ያህል ትጨነቅ እንደ ነበር በስፋት ተገልጿል።
ወ/ሮ ማርታ ሲማቶስ ያገባቺው ጥላሁንን እንጂ ዝናውን እንዳልነበር፤ በተለይ በከፍተኛ ህክምና እግሩ ከመቆረጥ ተርፎ ነገር ግን ሲጋራ ማጨስና ህመሙን የሚያባብሱ ነገሮችን ሁሉ ካላቆመ፤ እግሩ መቆረጡ እንደማይቀር ከሃኪም የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተቀብላ፤ በከፍተኛ ትጋት እየተገበረች፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የጥላሁንን ጤንነት ፍጹም ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር መቻሏ በጥላሁን ልጆችም ሳይቀር ተመስክሮላታል።
እውነተኛ የትዳር ጓደኛ ማለት እንዲህ ነው።እንደ ወ/ሮ ማርታ…!
ወ/ሮ ሮማን ሆይ!  የጥላሁን ልጆች የሚያሳስባቸው የአባታቸው ደህንነትና ጤንነት ብቻ ስለነበር ወ/ሮ ማርታን አመስግነዋል።  አንቺንስ ለምን አላመሰገኑም?…. መልሱን ለአንባቢ ግንዛቤ ልተውና ወደ መጽሃፉ ይዘት ልመለስ፦
ማርታ ለጥላሁን ታደርግለት በነበረው እንክብካቤ ከተደሰቱት የጥላሁን ገሠሠ ልጆች አንዷ ንጹህ ብር ጥላሁን ገሠሠ በዚህ መልክ ነበር ለማርታ ምስጋናና ምስክርነቷን የሰጠቺው፡፤ አሁንም ከመጽሃፉ ኮፒ የተደረገውን ክፍል ያንቡት።
TG TV, Mesfin Bezu
TG TV, Mesfin Bezu
ይህን የንጹህ ብርን የምስጋና መልእክት ሌሎቹም የጥላሁን ልጆች እንደሚጋሩት ደራሲው አነጋግሯቸው እንዳረጋገጠ በዚሁ ምስል ግርጌ መጽሃፉ ላይ አብራርቶ ገልጾታል።
ታዲያ ይሄ አለመታደል አይደለም ትላላችሁ? “አንተ ንጉስ ነህ ከዙፋንህ አትውረድ!” ከምትለው የእናት ምትክ የትዳር አጋር ጉያ ወጥቶ እንደ ጆንያ ጫኑት ወደምትል “ዝና ብቻ” ወራሽ …መግባት። የህይወት መንገድ እንዲህ እንዲህ ነች! … ደልዳላውን መሬት አስትተው መቀመቁን የሚያስመርጡ አስመሳይና አሳሳች መሰናክሎች የበዙባት…
የሚጮህው ቁራ የሚበላው አሞራ!
ሌላው ታማኝ በየነ ላይ ያቀረባችሁት ክስ በጥላሁን ኮንሰርት ላይ ሰው እንዳይገባ አሳደመ የሚል ነው። ለመሆኑ በጥላሁን ገሠሠ ኮንሰርት ላይ ማንስ ቢሆን ማሳደም ይቻለዋልን? ጥላሁን ይዘፍናል ተብሎ አትግባ ቢባል እሺ የሚል ኢትዮጵያዊ አለን? ጥላሁን እኮ የመድረክ ጸሃይ ነው፡፡ ጸሃይ እንዳትወጣ ማሳደም ይቻላል እንዴ? እውነት እውነት እልሻለሁ ይህ ክሳችሁ “የሚጮኽው ቁራ የሚበላው አሞራ” እንዲሉ በሱ ድካም ልታገኙት የነበረው ጥቅም በሆነ ምክንያት ማነሱ ወይም መቅረቱ የፈጠረባችሁን ቁጭት ከመግለጽ ባሻገር ማንንም አያሳምንም።
ወሮ ሮማን ጥላሁን በህይወት እያለ በሰጠው አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ “የስኳር ህመምተኞችን የሚረዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር ማድመጤን አስታውሳለሁ። አላማውን ከግብ ለማድረስ ሳይችል ማለፉ ያሳዝናል። ይሁንና እሱ ቢያልፍም አላማውን ከግብ በማድረስ የሙት መንፈሱ እንድታርፍ ለማድረግ በአንቺ በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩንም ሰምቼ ደስ ብሎኝ ነበር። አሁንስ ምን ደረሰ ?…
እኛ እያየን ያለነው ግን የስኳር ህመምተኞችን ስትረዱ ሳይሆን  ፤ በስኳር ፋብሪካ ስም ህዝብን ከመሬቱ የሚያፈናቅ ለውን የወያኔ መንግስት አበጀህ! በርታ! እያላችሁ በአሽከርነት ስትባዝኑ ነው።ህዝብ እየታዘበ ያለው በአርቲስቱ ስም በከፈታችሁት ቴሌቭዥን ገዳዩን መንግስት እያገለገላችሁ የአርቲስቱን የሙት መንፈስ እረፍት መነሳታቸሁን ነው ።
ወሮ ሮማንና የወያኔ መንግስትን ምን አፋቀራቸው?
ወ/ሮ ሮማን የጥላሁን የመጨረሻ ሚስትነት በጋብቻ ቅደም ተከተል ብቻ ሳይሆን በህዝብ ዘንድ ባላትም ቅቡልነት ነው፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የግለሰቧ ሁሉን ለኔ ሁሉን በኔ ባይ ባህሪ ነው። በታሪክ አጋጣሚ ጥላሁን ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የጎጆው ተጋሪ መሆኗ የፈጠረላትን የተጠሪነት መብት ብቻዬን ካልያዝኩ ፤ የጥላሁን ክብርና ዝና እኔው ላይ ብቻ ካልተርከፈከፈ ማለቷ በጥላሁን ቤተሰብና ወዳጆች ብሎም ጥላሁን በሚያፈቅረው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ቅቡልነትን አሳጣት።
ምክንያቱ ደግሞ ጥላሁን የህዝብ መሆኑ ነው።ታሪኩም፤ ሥራውም ብቻ ሁሉም ነገሩ…..የህዝብ ነው፡፤ ከዚያም ቀረብ ሲል የአብራኩ ክፋይ ልጆቹ በሙሉ የሚጋሩት ይሆናል እንጂ የአንድ የመጨረሻ ሚስቱና የሷ ቤተሰቦች ሊሆን አይችልምና ነው፡፡
ወ/ሮ ሮማን በራሷ “ሁሉን በኔ” ባይ ባህሪ ያጣቺውን ህዝባዊ ቅቡልነት የወረቀት ህጉ በሰጣት መብት ለማካካስና የጥላሁን ብቸኛ ወራሽነቷን አድምቃ ለማሳየት ተነሳች ። ይህን እውን ለማድረግ ገባ ወጣ በምትልባቸው ቢሮዎች ፈጣን ግልጋሎት ታገኝ ዘንድ የወያኔ ድጋፍ አስፈለጋት። ወያኔ ደግሞ ሲፈጥረው ከህዝብ ፍላጎት በተቃራኒ የቆመ መንግስት ነውና ህዝብ  የጠላውን ሰው “በሰጥቶ መቀበል” መርህ እንዴት ማስተናገድ እንዳለበት ስለሚያውቅ በደስታ ተቀበላት። ብቸኛ የጥላሁን ገሠሠ ወራሽ ባለመብትነቷ ደምቆ እንዲታይ መድረኩን ሁሉ አመቻቹላት። በልደቱ … በሃውልቱ… በመጽሃፉ… በፋውንዴሹኑ ምን ቅጡ! ጥላሁን ሲነሳ ሮማንም አብራ እንድትወሳ ሆነ። ወያኔ ይህን ሰጣት!  እሷስ ለወያኔ … ? አዎ እሷም ደግሞ በጥላሁን ስም የተከፈተው ቴሌቪዥን ከኮምኒኬሽን ጽ/ቤት በሚደርሰው መመሪያ መሰረት እንዲያገለግል ፈቀደች፡፡ ወንድሟንም ቀለቡን ችለው እንዲጠቀሙበት መርቃ ሰጠች። ይህው ነው እንቆቅልሹ ሲፈታ።
እስከ ዛሬ መስፍን በዙ ለምን እንዲህ ያደርጋል? እያልን የምንገረመውና የምንጮኽው ሁሉ የባከነ ጩኽት ነበር። መስፍን በሰጥቶ መቀበል መርህ ወያኔና እህቱ ሮማን የተረካከቡት መገልገያ መሆኑን ካለማወቅ የሚነሳ ጩኽት።
መደምደሚያ፦ ወ/ሮ ሮማን ሆይ!  አሁን ምን ሁኔታ ላይ እንዳለሽ ጠንቅቀሽ የምታውቂ ይመስለኛል። አዎ! ጥላሁንን የሚወደው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ጀርባውን ሰጥቶሻል። ጥላሁን “ቤተሰቦችን ግን እንዳትረሱ” ሲል ለህዝብ ከሰጠው “የአደራ ኑዛዜ” ላይ ፍቆሻል። ለምን? ብለሽ እንደማትጠይቂም ተስፋ አደርጋለሁ።
አዎ! ለጊዜው የወያኔ መንግስት እስካለ ድረስ የጥላሁን መታሰቢያ ዝግጅት ላይ፤ ልደቱ ሲከበር፤ .. ብቻ የጥላሁን ዝክር ባለበት ቦታ ሁሉ የፊት ወንበር ተይዞልሽ በቴሌቪዥን መስኮት ልናይሽ እንችላለን። ይህም ቢሆን የሚቀጥለው ለጥቂት ጊዚያት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ መንግስት እስክትታደል! ያኔ! ከሃዲና ባንዳው አንድም ሲፈረጥጥ አልያም በተከሳሽ ሳጥን ሲቀመጥ፤  የጥላሁን እውነተኛ ወራሽና ቤተሰቦቹም በሰገነታቸው ላይ ይቀመጣሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም እንደገና አደራውን አድሶ ይቀበላቸዋል። አንቺና ወንድምሽም በጥፋት ዘመኑ የወያኔ የመንግስትነት ታሪክ ተገቢው ምዕራፍ አይነፈጋችሁም። “ህዝባዊውን አርቲስት የነገዱበት…” በምትል ርዕስ የክህደት -ገድላችሁ ይዘከራል። እስከዛው ግን ከአጥፊዎቹ ትዕዛዝ እየተቀበላችሁ ጥፋታችሁ ቀጥሉ….
ካፈርኩ አይመልሰኝ እንዲሉ፤- ቀጣዩ የመስፍን በዙ ሩጫ የተጋለጠውን የእህቱን ገመና ለመታደግ የጥላሁንና የወ/ሮ ሮማንን ትዳር ከአብርሃምና ሳራ ትዳር ለማመሳሰ መባዘን ነው፡፤ ከቻለ እንደ አለቆቹ የሰው ምስክር አሰልጥኖ በቃለ መጠይቅ መልክ ያቀርብልናል፡፤ ያም ካልሆነ የአፍላ ፍቅራቸውን ጊዜ የቪዲዮና የፎቶ ክምችት አቧራውን እያራገፈ ዘጋቢ ፊልም ያስኮመኩመናል ። እኛም “የዛሬን አያድርገውና ድሮማ …. ነበሩ” እያልን ለማየት ያብቃን። የፕ/ር ኃይሌ ትዝብት ግን ከጭንቅላታችን አይጠፋም፡፤”….ንጉሱን እንደ ከሰል ጆንያ ክተቱት አለች?” …እንቆጫለን እንገበገባለን! ።
ወሮ ሮማን! ለጥሞና ንባብሽ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለዛሬ መልዕክቴን በዚሁ ልቋጭ፤ በቅርቡ ሌሎችንም መረጃዎች አሰባስቤ በተመሳሳይ መልዕክት እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ። በጥላሁን ስም መነገዱ እስካልቆመ እኔም መቃወሜን አላቆምም…… ምኑ ተነካና…
TG TV, Mesfin Bezu
ውድ አንባቢያን ሆይ የሙዚቃውን ንጉስ ታሪክ ካላነበባችሁ ይህን የዘካሪያ መሐመድ መጽሃፍ እንድታነቡ አጥብቄ እመክራለሁ።
አለማየሁ ላቀው መኮንን ! ነኝ
ቸር ይግጠመን !  በመጨረሻም፦

ጎንደር ለሪፈር አንልክም የተባለች የወልቃይት ነዋሪ ህይወታ ማለፉ ተነገረ

ጎንደር ለሪፈር አንልክም የተባለች የወልቃይት ነዋሪ ህይወታ ማለፉ ተነገረ

የወልቃይት ነዋሪ የሆነችው የ30 ዓመቷ ወላድ እናት በኹመራ ሆስፒታል በ19/07/08 የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላት በሰላም ከተገላገለች በኋላ ተጨማሪ ህክምና የሚያስፈልጋት በመሆኑ የሆስፒታሉ ሐኪሞች የተሻለ ህክምና እንድታገኝ ወደ መቀሌ እንድትሄድ ሪፈር ሊጽፉላት ይዘጋጃሉ፡፡
በኹመራ ሆስፒታል የነበሩ የእንኩየውሽ ገሌ ቤተሰቦች ወደ መቀሌ ሳይሆን ወደ ጎንደር ሆስፒታል መውሰድ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶክተሮቹን ለጎንደር ሆስፒታል ይጽፉላቸው ዘንድ ይማጸናሉ፡፡ነገር ግን የካህሳይ አበራ ሆስፒታል ዶክተሮች የተጠየቁትን ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሶስት ቀናትን ‹‹ለጎንደር ሆስፒታል አንጽፍም ››በማለት ያባክናሉ፡፡
ከሶስት ቀናት ጭካኔ በኋላ ህመምተኛዋ እየተዳከመች መምጣቷን የተመለከቱት ዶክተሮች ለጎንደር ሆስፒታል ሪፈር ይጽፋሉ፡፡እንኩየውሽ ጎንደር ሆስፒታል በደረሰች በሁለት ሰዓታት ልዩነት ውስጥም ህይወቷ በማለፉ ይህችን አለም ተሰናብታለች፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተላለፈው ውሳኔ መሻሩን ኦዲትና ኢንስፔክሽን አስታወቀ

የሰማያዊ ፓርቲ የስነ ስርዓት ኮሚቴ በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትን ጨምሮ የስነ ስርዓት ግድፈት ፈጽመዋል ያላቸውን ማባረሩንና ማገዱን መግለጹ አይዘነጋም፡፡
አቶ ይልቃል ጌትነትንና የቀድሞውን የፋይናንስ ኃላፊ ከፓርቲው አባርሪያለሁ ያለው የስነ ስርዓት ኮሚቴው በሌሎች ሁለት የፓርቲው አመራሮች ላይ የሁለት ዓመት እግድ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡የስነ ስርዓት ኮሚቴውን ውሳኔ በመመርመር ውሳኔ እንደሚሳልፍ ሲናገር የቆየው የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ በፓርቲው አመራሮች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ህገ ወጥ መሆኑን በመጥቀስ ተባረሩና ታገዱ በተባሉ የፓርቲው አመራሮች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ መሻሩን አስታውቋል፡፡
የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የስነ ስርዓት ኮሚቴውን ውሳኔ የሻረበትን ምክንያት ሲያስረዳም ‹‹ውሳኔው ለተከሳሾቹ ከመድረሱ በፊት በማህበራዊ ድረ ገጾች እንዲሰራጭ በመደረጉ፣የፓርቲውን የመተዳደሪያ ደንብ ያልተከተለና የቅጣትና የስነ ስርዓት ዓላማን ባለማገናዘቡ››ማለቱን በመግለጫው ይነበባል፡፡
የስነ ስርዓት ኮሚቴው ውስጥ የፓርቲው አባላት ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ገብተዋል የሚል ወቀሳ በስነ ስርዓት ኮሚቴው ሰብሳቢ ላይ ሲቀርብ ቢቆይም በዚህ ጉዳይ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ ያለው ነገር የለም፡፡
በበማህበራዊ ድረገጾች የፓርቲው አባላት ከዚህ መግለጫ መውጣት ጀምሮ በቃላት መወራረፍን እንዲያቆሙም ኮሚቴው አስጠንቅቋል፡፡
የስነ ስርዓት ኮሚቴው በአመራሮቹ ላይ አሳልፎት የነበረው ቅጣት በመነሳቱም አመራሮቹ በነበራቸው ተሳትፎ እንደሚቀጠሉ ይጠበቃል፡፡የኦዲትና ኢንስፔክሽን ጠርቶት የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ የተደረገው ጥረትም አልተሳካም፡፡
komishenu

ኢሳት ዜና-------ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አምባሳደሮችን እየተማጻኑ ነው


tewedrosየህወሃቱ አመራር አባልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለተመድ የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ቦታ ለመወዳደር የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን መንግስታቸውን አሳምነው ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጉላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ መሆናቸው ታውቁዋል።
ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን አምባሳደሮች መንግስቶቻቸው በምርጫው ድጋፋቸው እንዲሰጡዋቸው ያደርጉላቸው ዘንድ ሲማጸኑ ተሰመቱዋል። አምባሳደሮቹም በዲፕሎማሲ አነጋገር የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ገልጽውላቸዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በአሁኑ ወቅት መደበኛ ስራቸውን በመተው በመንግስት በጀት በምረጡኝ ቅስቀሳ የኤምባሲዎችን ደጅ እየጠኑ ሲሆነ፣ ዶ/ሩ እኔ ብመረጥ አፍሪካም ጭምር ትጠቀማለች በሚል የቅስቀሳ ዘዴ ድጋፍ እየጠየቁ ሲሆኑ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የዳይሬክተርነት ቦታ በተለይ እንደአሜሪካና እንግሊዝ ያሉ የሀያላን ሀገራት ደጋፍ ማግኘት ካልቻሉ በስተቀር የማለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው።
በአሁኑ ወቅት የጤና ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር ማርጋሬት ቻን በሀገራቸው ሆንግኮንግ የጤና ሚኒስትር ሆነው ከመስራታቸውም በላይ በአለም የጤና ድርጅትና በሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶች በከፍተኛ ሀላፊነት የሰሩ መሆናቸው ሲመዘን፣ በብቃትም ጭምር ዶ/ር ቴዎድሮስ ለቦታው እንደማይመጥኑ ከወዲሁ አስተያየት እየተሰጠባቸው ነው። ዶ/ሩ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 አመታት ለተፈጸሙት የሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ ናቸው በሚል፣ እርሳቸው እንዳይመረጡ በማህበራዊ ሚዲያ ቅስቅሳ ሲደረግ ቆይቶአል።
ዶ/ር ማርጋሬት እ ኤ አ ጁን 30/2017 ሀላፊነታቸው ስለሚያበቃ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብስቦ በእሳቸው ምትክ አዲስ ዳይሬክተር አወዳድሮ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢሳት ዜና

ተስፋሁን አለምነህ በህይወት ባይኖር ምን ልናደርግ ነው?በዳዊት ሰለሞን if there is no Tasfahun in life


Tsefahun-Alemenehew-G7-768x576
በዳዊት ሰለሞን
የቀድሞው የመኢአድ የህዝብ ግኑኝነት ተስፋሁን አለምነህ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የነበረውን የጸና እምነት በመቀየሩ ሳይሆን መንገዱ በስርዓቱ አንጋሾች ፈጽሞ ዝግ መሆኑን በሂደቱ በመሳተፍ በመመልከቱ ስርዓቱን በሚገባው ቋንቋ ለማናገር ወደ ኤርትራ በረሃ ወርዷል፡
ተስፋሁን በተለይም መኢአድና አንድነት ባህር ዳር ከተማ አድርገውት ከነበረ ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በኋላ በጣም የቅርቤ የምለው ጓደኞዬ ወጥቶት ነበር፡፡ለፓርቲው፣ለፕሮፌሰር አስራትና ለአገሩ የነበረውን ፍቅር አሁን በኮምፒውተር ኪቦርድ ለመተየብም እቸገራለሁ፡፡
ወጣቱ ፖለቲከኛ ከሰላማዊ ትግል ይልቅ የብረት ትግል እጅግ ቀላሉ ስለመሆኑም ከመናገር ተቆጥቦ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡በብረት በሚምሉ ወታደራዊ ገዢዎች ፊት እንደ አስራት፣አንዱዓለም፣ናትናኤል፣እስክንድርና ብዙ ሺህዎች ባዶ እጅን በፍቅር ተሞልቶ እንደመፋለም ፈታኝ ነገር እንደሌለም አጥብቆ ይናገር ነበር፡፡
ኢህአዴጎች በብረት ተወልደው በብረት ስልጣን በመያዛቸውም ያለ ብረት የሚደረግባቸውን ትግል መቋቋምና እንዴት ሊቀርቡት እንደሚገባም ባህሪውን ስለማያውቁት በለመዱት የኃይል መንገድ ጨካኝ ሆነው መገለጣቸው ተስፋሁንን ያስቆጨውም ነበር፡፡
በኢትዮጵያ በ2007 ለሚደረገው ብሄራዊ ምርጫ ከፓርቲው ጋር ብዙ ተስፋን ሰንቆ የነበረው የህዝብ ግንኙነቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት በመቅረብ ገዢውን ግምባር በሰላማዊ መንገድ እንዲፋለሙት ለማድረግ የቻለውን ያህል ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡ያሰበው አለመሆኑና ኢህአዴግም ከብረቱ ለመነጠል አለመፍቀዱን የምርጫውን ውጤት ጠቅልሎ በመውሰድ በማሳየቱ ተስፋሁንን ወደሌላኛው የትግል ጫፍ ገፋው፡፡
ተስፋሁን ኤርትራ ወርዶ በዚያ የሚገኙ የቀድሞ የትግል ጓዶቹን በመቀላቀሉ በቁርጠኛው ወጣት ድርጊት አላዘንኩም፡፡ያዘንኩትና እጅግ ያፈርኩት የትጥቅ ትግሉን በር ወለል አድርጎ በከፈተው ኢህአዴግ ነው፡፡ከተስፋሁን አጠገብ ቁጭ ብለው ኢህአዴግን በመወከል በምርጫ ወቅት የተከራከሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት የተስፋሁንን በረሃ መውረድ ሲሰሙ በረሃውን እጅግ ቅርብ ማድረጋቸውን በማሰብ መደበቂያ ጥፍር መፈለግ ይኖርባቸዋል ባይ ነኝ፡፡ራሴን በእነርሱ ጫማ ባስቀምጠውም ይህንኑ ለመናዘዝ የምደፍር ይመስለኛል፡፡
እርግጥ ነው ስርዓቱ ስልጡኑን የፖለቲካ መንገድ በጉልበቱ ዘግቶ ካበቃ በኋላም ቢሆን በተስፋሁን ካምፕ ተሰባስበው የነበሩ ስልጡኖችን ‹‹በምትፈልጉት ቋንቋ አናግራችኋለሁ ፣ወንድ ከሆናችሁ ጫካ አትወርዱም››እያለ የወንድ የሚለው መንገድ እርሱን ብቻ አራት ኪሎ የሚያደርሰው መስሎት ብዙዎችን ገፍቷል፡፡ብርሃኑ ተ/ያሬድና ሌሎችም በሰፊው መንገድ ለመሄድ መነሳታቸውን እዚህ ማስታወስ ተገቢ ይመስለኛል፡፡
እነተስፋሁን የመረጡት መንገድ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳዝን አይደለም፡፡በኢትዮጵያ የሚገኘው ስርዓት ዋነኛው የትጥቅ ትግል ሰባኪ ነው፡፡እውነቱን ለመናገር ማዘን የሚገባን ፈጽሞ ዝግ በተደረገው መንገድ አምባገነኑን ስርዓት ለመታገል የሚነሱ ፍጹም ሰላማዊያን ዜጎችን ስንመለከት ነው፡፡ላለፉት 25 ዓመታት በተናጠልም ይሁን በቡድን ተሰልፈው ህግና ህጋዊነትን ተስፋ አድርገው የተነሱ ዜጎች ተስፋ ባደረጉበት ህግ ተጠልፈው ከመንገድ ቀርተዋል፡፡
የስርዓቱ ጅቦችም ከብዕር፣ከወረቀትና ከመግለጫ ጋር ያገኟቸውን ነፍጥ አልባዎች በጭካኔያቸው ከልባቸው የሰላማቸውን እርግብ ለመግደል ወረቀት የማይችለውን በደል አድርሰውባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሰላማዊ ትግል በበኩሉ በየዓመቱ የሚነሱለትን አብሪዎች በጨለማ እያስዋጠ እንደገና ወደመጀመሪያው ይመለሳል፡፡ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ፡፡በዚህ መንገድ ለማለፍና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ አንዳች ቡዳ የበላቸው ወጣቶች፣ዕድሜ ጠገቦችና የቀድሞው ትውልድ ቅሪቶች መስዋዕትነታቸውን የሚለካላቸው አካል ሳያገኙ እንኳን ሲላቸው አገር አልባ፣ህይወት አልባ፣ነጻነት አልባ ሆነው ይደበዝዛሉ፡፡
ተስፋሁን በዚህ እንዲታሰብና ‹‹አንድ ትንታግ ወጣት ፖለቲከኛ ነበር››እንዲባልለት ባለመፍቀዱ ገዢው ግምባር ወደከፈተው የትግል መስመር ወጣ፡፡ጤነኛ አእምሮ ያለው አካልስ በተስፋሁን የትግል ምርጫ እንዴት ቂም ሊቋጥር ይችላል? እረ እንዴት ተስፋሁንን ከተራራ ላይ እንደወደቀ ስባሪ ሊቆጥረውስ ይዳዳዋል?
አገር ወዳድና ልበ ሙሉ የነበረው ተስፋሁን ኤርትራ ከወረደም በኋላ ረዘም ላሉ ወራቶች በፌስ ቡክ አካውንቱ  ይጠቀም ስለነበር የወዳጅነታችንን መነጋገራችን አልቀረም ፡፡ለትግል ወርዶ በማህበራዊ ገጹ ስለመጠቀሙ ስጠይቀውም ‹‹ገና ስልጠና ባለመጀመሩ እንዲጠቀም እንደተፈቀደለት ይነግረኝ ነበር፡፡ከማህበራዊ ድረ ገጽ ሳጣውም መጥፋቱ ስለሌሎች ነገሮች እንዳስብ አላደረገኝም፡፡
የሆነስ ሆነና ተስፋሁን ተገድሏል ወዘተ የሚሉ ድምጾችን በማህበራዊ ድረ ገጾች መመልከቴ አልቀረም፡፡ይህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥርም ለምን ይሆን ሰዎቹ ስለተስፋሁን ለማወቅ የተጨነቁት የሚል ጥያቄ ውጥር ያደርገኛል፡፡ተስፋሁን እንዳሉት (አያድርግበትና)ተገድሎ ቢሆን እነዚህ ጠያቂዎቹ ምን ሊያደርጉ ነው?ተስፋሁንን መፈለጋቸውን ይነግሩናል እንጂ ለምን እንደፈለጉት አንዳቸውም እንኳን እስካሁን አልነገሩንም፡፡
ተስፋሁን በእኔ እምነት ቢገደልም በህይወት ቢኖርም ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡ይህን ትንታግ ወጣት ሻዕቢያ ገደልኩት ቢለኝ እንኳን በተከሳሾች ወንበር ልናቆመው የሚገባን ገዳይ ኢህአዴግ እንደሚሆን ይሰማኛል፡፡በህይወት ኖሮም ዘመኑን በበረሃ ቢያሳልፍ ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበት ወታደራዊው ስርዓት ነው፡፡
እናም የሚሻለው ተስፋሁንና ሌሎች ብዙ ሺህዎችን ‹‹ውለድ››ብለን ኢህአዴግን እንጠይቀው፡፡ከሚያውቁት ኢህአዴግ በማያውቁት ሻዕቢያ ወደምትመራው ኤርትራ ያመሩት እኛ እዚህ ቁጭ ብለን ስለሻዕቢያ ማሰብ የምንችለውን እነርሱ ማሰብ ባለመቻላቸው አይደለም፡፡ከሁለቱ መጥፎዎች አንዱን መጥፎ በመምረጣቸው እንጂ፡፡
ሌላው የተስፋሁን ፈላጊዎች አጥብቀው የፈለጉት ዜና ‹‹ሞቱን››ይዞላቸው ቢመጣ እንኳን ይህ የተስፋሁንን መንገድ ስህተተኝነት ሊያሳያቸው አይችልም፡፡ብዙ ተስፋሁኖች እኮ በረሃ ሳይወርዱ በስርዓቱ ተገድለዋል፡፡እናስ የእነርሱ መሞት ሰላማዊ ትግል እንደማይሰራ ማሳያ ሊሆን ነው?
በተረፈ ተስፋሁንን አሳዩን ያላችሁ ሰዎች ‹‹ለምን ተስፋሁንን ማየት እንደፈለጋችሁ›› ንገሩን እስኪ፡፡

ተስፋሁን አለምነህ የት ነው ያለው ? – ግርማ ካሳ Where is Tesfahun


Tesfahun-Alemneh
ተስፋሁን አለምነህ
ተስፋሁን አለምነህ ወዳጄ ነበር። በሰላማዊ ትግል ዉስጥ በመንቀሳቀስ ብዙ አስተዋጾ ያደረገ ነው። የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሆኖ ሰርቷል። በጣም ጠንካራ ልጅ ነው። ሆኖም አገዛዙ በሰላማዊ ታጋዮች ላይ በሚያደርሰው ግፍና ከፍተኛ ወከባ፣ ተስፋ ቆረጠ። በሰላም ወያኔ አይወርድም ብሎ ሸፈተ። ወደ ኤርትራ በረሃ ሄደ። መሳሪያዉን አንግቦ የተነሳዉን ፎቶ አየን። ወደ ኤርትራ ሲገባም ከዚያ ከኤርትራ ደዉለው የኢሳት ጋዜጠኞች፣ እንደ ህብር ራዲዮ ያሉ ቃለ መጠይቅ አርገዉለት ነበር።
ወደ ኤርትራ በመሄዱ በግሌ በጣም ነበር ያዘንኩት። ተስፋ እንደቆረጠ ይነግረኝ ነበር። እኔም በትግል ዉስጥ መዉደቅ መነሳት ያለ ነው እለው ነበር። በኢሳት በኩል የግንቦት ሰባት ተቀላቀሉን ቅስቀሳ ሰለባ እንደሆነ ገባኝ። በኤርትራ በኩል የሚደረገው ትግል ላለፉት 20 አመታት ምንም ያመጣው ነገር እንደሌለ፣ እዚያ የሄዱ ብዙዎች ቀልጠው እንደቀሩ፣ በአንድ በኩል ወያኔዎችን እየተቃወምን የወያኔዎች አሥር እጥፍ ጭራቅ የሆነውን ሻእቢያ መተማመን አስቸጋሪ እንደሆነ የሚታወቅ ነው።
እንደዚያም ሆኖ ተስፋሁን አለምነህ አድራሻዉን ኤርትር አደረገ። ያ ዉሳኔ ስህተት የነበረ ቢሆንም፣ ያን ያደረገው ለአገር ፍቅር ስላለው በመሆኑ፣ ያለኝ አክብሮት አልነፈኩትም። ማን ነው ለአገርን ለሕዝብ ለመሞት ወስኖ በረሃ የሚገባው ? እና ዉሳኔዎቹ ትክክል ባይሆኑም ሞቲቩ ግን አገር ወዳድነት ነበር።
ይኸው ተስፋሁን ወደ ኤርትራ ከሄደ ወደ ዘጠኝ ወራት አልፎታል። አንድ አስደንጋጭ ዜናም በሶሻል ሜዲያው እያነበብን ነው። ተስፋሁን በሻእቢያ እንደተገደለ። መጀመሪያ ላይ ወሬው ዉሸት ነው ብለን ለወሬው ትኩረት አልሰጠንም ነበር። ግን የዉሸት ወሬዉን የሚያስተባባል ብንፈልግ ልናገኝ ባለመቻላችን፣ የተወራው ወሬ እዉነት ሊሆን ይችላል የሚል ሀሳብ ዉሳጣችን እየገባ ነው። በተለይም የተስፋሁንን ወደ በረሃ መግባት የነገሩን ሜዲያዎች ለጉዳይ ትኩረት አለመስጠታቸው አስገርሞናል።
ተስፋሁን የተቀላቀለው የአማራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( አ.ሕ.ዴ.ን) ነው። አሕዴን ከግንቦት ሰባት አርበኞች እና ከደሚት ጋር፣ በጋራ ለመስራት የአገር አድን ንቅናቄ መመሰረታቸውና አሕ.ዴን ያለበት የአገር አንድ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶር ብርሃኑ ነጋ መሆናቸው ይታወቃል።
የአገር ንቅናቄ ዉጊያዎች አድርጎ ተስፋሁን በዉጊያ ላይ ሞቶ ነው ? ከሆነስ የትኛው ዉጊያ ? ለመሆኑ ከኤርትራ ተነስተው የመረብ እና የተከዜን ወንዝ ተሻግረው ዉጊያ ላለፉት አንድ አመት ቢያንስ ዉጊያ ያደረጉ አሉን ? …ከሆነስ በወልቃይት ጠገዴ፣ ሁመራ ፣ ሰሜን ጎንደር እዚያ ኤርትራ አፍንጫ ሥር ባሉ ቦታዎች ህዝቡ፣ ገበሬው ትንቅንቅ ይዞ ኤርትራ ጦር አለን የሚሉት ደብዛቸው የት ነው ያለው ?? ? ተስፋዉን ሞቶ ከሆነ በምንም መልኩ ከወያኔዎች ጋር ሲዋጋ አይደለም የሞተው።ለምን የተደረ ዉጊያ ስለሌለ።፡
ያ ካልሆነ ተስፋሁን አለመነህ የት ነው ያለው ?
ኢሳቶች ወደ ኤርትራ ሲገባ ቃለ መጠይቅ እንዳደረጉለት፣ ያኔ እርሱን ባገኙበት መስመር፣ ሁኔታውን አጣርተው ቢያሳወቁን በጣም ጥሩ ነው። ይህ ወጣት ከላይ እንዳልኩት የወሰደው አቋም ስህተት ቢሆንም፣ ያደረገው ለአገርና ለሕዝብ ሲል ነው። እንደሌሎች ወጣቶች ሁሉንም ትቶ ኑሮዉን መኖር ይችል ነበር። ግን ለአገሬ፣ ለሕዝብ ብሎ በረሃ ሲገባ፣ በወያኔዎች ሳይሆን ወያኔን እንቃወማለን በሚሉ ኃይላት ወዳጅ ባደረጉት በሻእቢያ ተገደለ የሚለው በቀላሉ የሚታይ አይደለም። እየተወራ ባለው ሁኔታ ሕይወቱ ጠፍቶ ከሆነ ህዝብ ማወቅ አለበት።
እዚህ ላይ የሚሊታሪ ሚስጠር እንዲወጣ አይደለም እየጠየኩ ያለው። ግን የምናከበረው ወንድማችን የት እንዳለ ነው ለማወቅ የፈለግነው። ምንም ቢሆን ወንድማችን ነው።
( እዋጋለሁ ብሎ ጠመንጃ ያነሳው ተስፋሁን ከኤርትራ ፖስት አድርጎት የነበረ ፎቶ ነው።)

የሃገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተግዳሮቶች (ገለታው ዘለቀ)

የሃገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተግዳሮቶች (ገለታው ዘለቀ)

ገለታው ዘለቀ
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ለማንሳት ስነሳ በ1994  ዓ.ም  የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት ውስጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ሲወያዩ አንድ ምሁር የተናገረው ነገር ትውስ አለኝ። ትዝይላችሁ እንደሆነ የዚህ ምሁር ንግግር ብዙዎችን ኣስደምሞ ነበር። ለማስታወስ ያህል ይህ ምሁር ለራሳቸው ጠቅላይ ሚንስትር ለነበሩት ለአቶ መለስ እንዲህ ነበር ያለው።
“እዚህ አገር ሌላ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ተመስርቶ፣ ገበሬው ውስጥ ገብቶ ፋይዳ ያለው ለውጥ አይኖርም እርስዎ እያሉ። አይኖርም። ምክንያቱም እርስዎ እንዳይኖር ያደርጉታልና ነው። እስካሁን በዚህ ተሳክቶልዎታል በሚቀጥሉት ሃያ ኣመታትም ይህንኑ  ያደርጋሉ።”
የሚገርመው ይህ ምሁር ምንም ውስብስብ ነገር አልተናገረም። ብዙ ምጡቅ   አሳቦች በዚህ ስብሰባ ላይ ተነስተው ነበር። ይሁን እንጂ በተለይ የዚህ ምሁር ንግግር ግን ከተማሪው እስከ ምሁሩ፣ ከነጋዴው እስከ ሰራተኛውና ገበሬው ድረስ ኣስደንቆ ነበር። ለምን ብየ ጠይቄ አውቃለሁ። ሰው ሁሉ ይህን ምሁር ያደነቀበት ዋና ነገር ሁሉም በልቡ ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዲህ ነበር የሚያውቃቸውና ነው። እሳቸው እያሉ መድብለ ፓርቲ አይኖርም የሚል እምነት በዚህ ሁሉ ሰው ልብ ውስጥ ስለነበር ነው።  አሁን ይህ ምሁር በሃቀኝነት ይህን ስሜት መግለጽ ሲችል ሁሉም እዎ!  አገኘኸው ኣይነት ነው የተደመመው። አንዳንዴ የውስጥን ስሜት በቅንነት  የሚገልጽ ሰው ሲገኝ ደስ እንደሚለን ነው ነገሩ። ምሁሩ እንዳለው አቶ መልስ ቅንነት  የጎደላቸው ናቸው ብሎ ህዝብ ያዝን ስለነበርም ነው። በርግጥ ከዚህ ምሁር የወጣው ይህ ቃል ቅንነትንና እውነትን ይዞ ስለነበር የብዙዎችን ስሜት በቀላሉ መግዛት ችሎ ነበር።
ያ ምሁር “እርስዎ እያሉ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አይኖርም” አለ። አሁን አቶ መለስ ከዚህ ዓለም የሉም። ይሁን እንጂ ኣሳባቸውና ያፈሯቸው ደቀመዛሙርት ልክ እንደሳቸው ስለሆኑ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላም እነሆ ዛሬ ድረስ የዚህ የመድብለ ፓርቲ ጉዳይ እክሎች በዝተውበት ይኖራል። አቶ መለስ በኣካል ባይኖሩም አሉ ማለት ነው።
ያ ምሁርም ሆነ ብዙው ኢትዮጵያዊ በዚህች አገር በዚህ መንግስት ስር መድብለ ፓርቲ አድጎ ነጻ ምርጫ ተካሂዶ በውነት ያሸነፈው ስልጣን ይይዛል የሚለው እምነት በብዙዎች ዘንድ የወረደ ቢሆንም ግን ያሉትን ፓርቲዎች ወይ ተቀናጅተው ወይ አንድ የተሻለ ፓርቲ ጠንክሮ ወጥቶ ለመብታቸው እንዲያታግላቸው ይፈልጋሉ። እናም ዛሬ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሆነው ጉዳይ ለምን አንድ ጠንካራ ድርጅት አይኖርም….? ለምን ተቃዋሚዎች ይበታተናሉ….? ለምን ህብረት አቃተን……? የሚል ነው። እንዴውም በአንድ ወቅት ህዝቡ ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ እያለ ብስጭት የተሞላበት ስሜትም አንጸባርቆ ነበር። በርግጥም መቶ የሚሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች የቀፈቀፍን እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን በረከት አንለውም። ወደዚያ እሚታጠፈው ታጥፎ የሚከስመው ከስሞ የተወሰኑ ፓርቲዎች ይበቁናል። መቶ ፓርቲ ስሙንም ሸምድደን አንዘልቀው።
ከዚህ ከብዛቱም በላይ ግን የኢትዮጵያ መድብለ ፓርቲ ስዓት ጉዳይ ከፍ ያሉ ችግሮች አሉበት።  በዚህች በዛሬዋ ጽሁፌም የገጠሙንን ለእኔ የታዩኝን ኣራት ጉዳዮች አንስቼ ችግሮቻችንን ለመዳሰስ እፈልጋለሁ።
ከዚያ በፊት ግን የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ሃይላት ደካማዎች ናቸው ይላል። ለምን? ሲባል አንዱ ኣዘውትሮ የሚያነሳው ጉዳይ አማራጭ ፖሊሲ የላቸውም የሚል ነው። ሌሎች አንዳንድ ሰዎችም በርግጥ ይህን አሳብ ይጋራሉ። እውነቱን ለመናገር መንግስት ግን ይህን አዘውትሮ የሚገልጸው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይመስለኝም። ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ለዲፕሎማቶች ነው። መንግስት ተቃዋሚዎች ኣማራጭ ፖሊሲ የላቸውም ብሎ ለህዝቡ ቢናገር ህዝቡ ጥያቄው የአማራጭ ኣሳብ ጉዳይ እንዳልሆነ ያውቃል። ኣማራጭ ኣሳብ የሚባለው ነገር በመጀመሪያ እውነተኛ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ይጠይቃል። እውነተኛ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ባለበት ኣገር ኣማራጭ ኣሳቦች ህዝብ ጋር ወርደው በሃሳብ የበላይነት የያዘው የህዝብን ቀልብ ስቦ ተመራጭ ይሆናል። የህዝብን ቀልብ ስቦና ኣስደምሞ ስልጣን በማይያዝበት ኣገር ጥያቄው የህግን የበላይነት የማያከብሩ ስብስቦች ይውረዱና ለውጥ ይምጣና ደሞ ሌላውን እንሞክረው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ራሱ በሚያወጣቸው ህጎች ስለማይገዛ፣ ህግን ስለማያከብር፣ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ የሰባዊ መብቶችን ራሱ መንግስት እንደፈለገ ስለሚጥስ ለውጥ እንፈልጋለን የሚል ነው። በመሆኑም ተቃዋሚዎች በነጻነት በማይንቀሳቀሱበት ኣገር ኣማራጭ ኣሳብ የላቸውም የሚለው ክስ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ሳይሆን ከፍ ሲል እንዳልኩት ለውጭው ዓለም ይሆናል።
ለነገሩ እኮ ኣንዳንዶቹ የተጠናከረ ባይሆንም ኣማራጭ ኣሳቦች ኣሏቸው።አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ጥሩ አማራጭ ኣሳቦች አሏቸው። መንግስትን በመሬት ፖሊሲ ዙሪያ ሲቃወሙና መሬት በመንግስትም በህዝብም በግልም መያዝ ኣለበት ሲሉ ኣማራጭ ኣሳብ ማለት ይሄ ነው።
በኣስራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ምርጫ ወቅት ቅንጅት ያን ያህል ህዝባዊ ተቀባይነት ያገኘው ህዝቡ የቅንጅትን ማኒፌስቶ ኣንብቦ ስለጨረሰ ኣይደለም። በዚያች ስድስት ወር ውስጥ ቅንጅት ሰፊ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ስለሰራም ኣይደለም። ህዝቡ በሃይል ለውጥ ፈልጎ ነበር። በኣንዳንድ ቦታዎች በቅንጅት ተወካይና በኢህዓዴግ ተወካይ መካከል ምርጫ ሲካሄድ ህዝቡ ለመመረጥ ኢህዓደግ ኣለመሆን ብቻውን በቂ ነው ይል ነበር። ይሄ የሚያሳየው ለውጥን በጣም ከመሻት የመጣ ምርጫም ነበር። አንደኛው ይሄ ነው። ሌላው ደግሞ የለሂቁ ክፍፍል መቀነስና ዘግይቶ የታየው ህብረት ነበር የኢትዮጵያን ህዝብ በተስፋ ባህር ላይ እንዲያ ያንሳፈፈው።
ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንቅፋቶች እንመለስና ርግጥ ነው ተቃዋሚዎች ብዙ መሰናክል ኣለባቸው። ጥንካሬና ህብረት ተስኗቸዋል። አቶ መለስ ቢሞቱም የመድብለ ፓርቲ ጉዳይ እያደር ቁልቁል ሆኗልና ለዚህ መሰረታዊ ችግሮች ናቸው ያልኳቸውን ዝቅ ሲል እኔም ላቀብል።
  1. የህወሃት የጠለፋ የትግል ስልት
ህወሃት (ኢሃዴግ) ተቃዋሚዎችን የሚያጠቃበት ስልት በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ የመድብለ ፓርቲ የማሰናከያ ድንጋይ ነው። ህወሃት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ደርግን ለመጣል ይጠቀም ከነበረባቸው ዘዴዎች መካከል ሰርጎ መግባት፣ ማታለል፣ መደለል፣ የስነ-ልቡና ጦርነቶችን ማድረግ ዋና ዋና  ዘዴዎቹ ነበሩ። እነዚህን ስልቶች ዛሬም መድብለ ፓርቲ ስርዓት መስርቻለሁ በሚልበት ስርዓት ውስጥ ይጠቀምባቸዋል። ህወሃት ኣዲስ ኣበባን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ሌላ ቀዝቃዛ ጦርነት ከፍቶ ነው የሚኖረው። ዋናው ኣንዱ ችግሩ ህወሃት ራሱን እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን የሚያየው እንደ ዘውግ ተቆርቋሪ ማህበር በመሆኑና ለኢትዮጵያ የሚበቃ ወይም ኢትዮጵያን የሚሸፍን ዓላማ ስለሌለው በመድብለ ፓርቲ ውስጥ የውነት መጫወት ኣይችልም። ብሸነፍም ልሸነፍ ብሎ ለመወሰን ቢያንስ ኣገራዊ ድርጅት መሆንን ይጠይቃል። የሌሎቹ “የኢህዓዴግ” ኣባል ፓርቲዎችም ለህወሃት ተገዢ ከመሆን ባሻገር እንደዚሁ ተመሳሳይ ተፈጥሮ ነው ያላቸው። ለዚህ ነው እነዚህ ድርጅቶች የህይወት ታሪክ ውስጥ ጥርት ያለ ርእዮት የማይታየው።
በመሆኑም ኣውራው ፓርቲ ህወሃት ፖለቲካን ከማህበራዊ ማንነቱ ጋር ኣጣብቆ ስለያዘ በቀላሉ ለሃሳብ ፍጭት እጅ ስለማይሰጥ ተቃዋሚ የሚባሉትን ሁሉ በጠላትነት ያያቸዋል። እናም በደርግ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረውን ስልት ተግባራዊ እያደረገ ተቃዋሚዎች እንዳያድጉ ያደርጋል። ከተራ ኣባል እስከ ኣመራር ድረስ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ዘንድ ሰላይ እየሰገሰገ ህብረት እንዳያድግ፣ ህዝባዊ ሰላማዊ ትግሎችን እንዳይመሩ እያደረገ ያሸመደምዳቸኣል። ህወሃት ለብዙ ዓመት የዳበረ የጠለፋና ቆረጣ ልምድ ስላለው ተቃዋሚውን በቀላሉ ይጠልፈዋል። ኣንዱና ትልቁ ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች ኣለመጠንከር ምክንያት ይሄ ነው። በነገራችን ላይ ህወሃት እንዳይጠነክሩ የሚያደርገው ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ብቻ ኣይደለም። ኣጋር ድርጅቶቹንም ነው። እነ ብዓዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴግ ጠንካራና በራስ የሚተማመኑ እንዲሆኑ ኣይፈልግም። ይህን ቢያደርግ የሃገሪቱ የፖለቲካ ኣቅጣጫ እስካሁን ይቀየር ነበር። ነገር ግን እነዚህን ኣጋር ድርጅቶቹንም ጠልፎ ይዟቸዋል። ኢሃዴግ የተባለው ድርጅት እውነተኛ ማንነቱ ይታይ ቢባል ህወሃት ነው። ኢሃዴግ የህወሃት የፌደራል ስም ነው። ይሄ ማለት የኦህዴድ የደህዴግና የብአዴን ኣባላት ጨዋዎች ናቸው ማለት ኣይደለም። እነሱ ለግል እድሎች (Opportunities) መስፋት ሲሉ የህወሃትን የበላይነት ተቀብለው በሃገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳያድግ እያደረጉ ያሉ ናቸው። ተራው ኣባል ግራ ቢጋባም ከላይ ያሉት ግን በተለያየ ስልት የተያዙና ለህወሃት የበላይነት የሚሰሩ ናቸው። በኣጠቃላይ ህወሃት በስልጣን ለመቆየት ኣሳብን ወይም በኣሳብ በልጦ መገኘትን መሰረት ኣድርጎ ኣይኖርም። ዋናው እምነቱ ጠለፋ ነው። ኣጋር ድርጅቶችን መጥለፍና በራሱ እዝ ስር ማድረግ፣ ፕሬሱን መጥለፍ፣ ሰላማዊ ትግሉን መጥለፍ፣ ውጭ ያለውን ተቃዋሚ መጥለፍ…..ሁሉንም መጥለፍ…. ነው አዋጭ የትግል ስልት አድርጎ የሚኖረው። ስለዚህ በሃገራችን መድብለ ፓርቲ ስርዓት ኣድጎ እንዳናይ የሚያደርገን ይሄ የጠለፋ ጉዳይ ነው። ኢሃዴግ “ንብ” ነኝ ሲል የንብን የህብረት ስራ ያስታውሰናል። ኣውራው ኣለ። ሌሎች ደግሞ ውሃ ቀጂና ዘበኞች ናቸው መሰለኝ። ኣውራው ህወሃት ቢሆን እነ ኦህዴድ ብአዴንና ደህዴግ ዘበኞችና ውሃ ቀጂዎች ሆነው ይኖራሉ። ይሄ መለወጥ ኣለበት። በዚያች ድሃ ኣገር፣ ሁላችን ድሆች ሆነን እንዲህ ያለ ጅማሮ የትም ኣያደርሰንም።በህብረተሰቡም ውስጥ ይህ ነገር የተለየ ኤነርጂን እየፈጠረ ወደአልሆነ አቅጣጫ ስለሚመራን ቶሎ መቆም አለበት።
  1. የፖለቲካ ውቅር (Political setup)
ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ የፖለቲካው ውቅር ነው። በመሰረቱ ኢትዮጵያ በብሄር ላይ የተመስረተ ፖለቲካ ካማራት በኮንፌደራል የመንግስት ውቅር ነው መተዳደር ያለባት። በርግጥ ይህ ጥያቄ የማንም እንዳይደለ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በብሄር ላይ የፖለቲካ ቤትን ኣቁም እንደገና መድብለ ፓርቲ ስርዓትን ኣራምዳለሁ ማለት ኣንዱን በሬ ወዲህ ኣንዱን በሬ ወዲያ ኣጣምዶ እርሻ ልጀምር እንደማለት ይቆጠራል። መድብለ ፓርቲ ስርዓትና የብሄር ፖለቲካ ኣብረው ኣይሄዱም። የብሄር ፖለቲካ ባለኣንድ ፓርቲ ገዢነትን የሚያበራታት ስሜት ያለው ነው። ሰማኒያ የሚሆኑ ብሄሮች ሰማኒያ የፖለቲካ ድርጅት ኣቋቋሙ ማለት መድብለ ፓርቲ ስርዓት እውን ሆነ ማለት ኣይደለም። መድብለ ፓርቲ ስርዓት ማለት በኣንድ ብሄራዊ የፖለቲካ ማንነት ስር የተሰባብሰቡና የጋራ ትልቅ ግብ ያላቸው ነገር ግን በፖሊሲና በኣይዲዮሎጂ የሚለያዩ ድርጅቶች ኣሳብ እያፋጩ በፖሊሲ ብልጫ እየተመረጡ የጋራ ኣገር የሚያሳድጉበት ስርዓት ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሁን የለም። ብሄራዊ ማንነት በኣካባቢ የፖለቲካ ማንነት እንዲዋጥ ስለሚደረግ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ኣይኖርም። መንግስት ለኣንዳንድ የህብረ ብሄር ድርጅቶች ፈቃድ ሰጥቶና እድገታቸውን አየከረከመ የሚያኖራቸው ኣንዱ በስልጣን ላይ ያቆየኛል የሚለው እምነቱ ስለሆነ ነው። ብዙሃኑን ለመያዝ፣ ግጭቶችን ለመቀነስ ነው። ከዚህ ውጭ ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰዓት መድብለ ፓርቲን የሚያስተናግድ ሲስተም ኣልቀረጸችም።  ብሄራዊ ድርጅቶች የቆሙት ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ ስላላቸው እንጂ ሲስተሙ እየጠለፈ የሚጥል ነው።
  1. የፖለቲካ ባህላችን
በእኔ እምነት ይህም የተወሰነ ተጽእኖ የፈጠረ ቢመስለኝም እንደ ዋና ችግር ግን ኣላየውም። በርግጥ ነው በተለይ ቀደም ያለው ትውልድ እስካሁን የግራው የፖለቲካ ተመክሮ ተጽእኖ ፈጥሮበት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የተለወጡና በኣዲስ መንፈስ የተነሱ ደግሞ አሉ። ያልተለወጡትና ዛሬም በድሮ በሬ ለማረስ የሚሹቱ አነሱ በርግጥ እርስ በርስ ሲጠላለፉ ይታያል። ይሄ መቀረፍ ያለበት ችግር ነው። ለኢትዮጵያ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መሽመድመድ ግን እንደ ዋና ምክንያት ኣይታይም። ያም ሆኖ ግን የፖለቲካ ባህላችን ሊያድግ የሚገባው ብዙ ነገር ኣለውና በመድብለ ፓርቲው ስርዓት እድገት ላይ የተወሰነ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል። ከዚያ ውጭ መንግስት ራሱ ተቃዋሚውን የፖለቲካ ባህላችን ደካማ ነው እያለ ቅስማቸውን ለመስበር እንደሚሰራ ይታወቃልና ፓርቲዎች ባህላችን ጥሩ ኣይደለም እያሉ ራሳቸውን ማፍረስ ለመንግስት እድሜን ከመጨመር ሌላ ኣይጠቅምም።እሚስተካከለውን ማስተካከል መድብለ ፓርቲን የሚሸከም ልብና ትከሻን ማዳበር ያስፈልጋል።
  1. የግል ዝንባሌዎች
ኣንዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ኣለመጠናከር አስተዋጾ ያደረገው ጉዳይ ደግሞ  ፖለቲካ በሃገራችን ውስጥ ሙሰኛ ስለሆነ ነው። ከፍተኛ የሚባሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድሎችን ሁሉ ዘርፎ ይዟል። በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የትምህርት እድልን ሳይቀር ዘርፎ የወሰደ በመሆኑ ፖለቲካው ሙሰኛነቱ ጫፍ ረግጧል። ስኮላርሺፕ ለማግኘት፣ በስራ ላይ እድገት  ለማግኘት፣ የተሻለ ኑሮ ለመኖርና በተሰብንና ዘመድን ለመርዳት፣ ወደ ፖለቲካ ጠጋ ማለት ኣዋጭ ነው። ፖለቲካው እነዚህን ኦፖርቹኒቲዎች መዝረፉና ሙሰኛ መሆኑ ያመጣው ኣንዱ ችግር እድሎች በጠበቡበት ድሃ ኣገር የሚኖሩ ዜጎችን እድል ፍለጋ ሳያምኑበትም ቢሆን ወደ ፖለቲካ እንዲሳቡ ያደርጋል። ከመንግስት ጋር ኣጎብድደው እየሰሩ የተሻለ ትምህርት ለማግኘት ይጥራሉ። ኣንዳንዶች ደግሞ ገዢው ፓርቲ ደመወዝ እየቆረጠላቸው በተቃዋሚ ስም መንግስትን የሚደግፉም ይኖራሉ። ይህ ችግር በሰፊው በአገር ደረጃ ሲታይ ፖለቲካችን ጥሪ ባላቸው ኣስተዳዳሪዎች ብቻ ሳይሆን በብዙ እድል ፈላጊዎች የተጠቀጠቀ ሰሚያደርገው ኣጠቃላይ ፖለቲካችንን ጨዋታውን ኣበላሽቶብናል ይመስለኛል። ፖለቲካው ከመንግስትም በላይ ሆኖ ፓርቲ መንግስትን ሳይቀር ውጦ በሚኖርበት ኣገር፣ ፖለቲካው እንዲህ በሰፊው እድሎችን ሁሉ ከየሲቪል ሰርቪሱ ሰርቆ በሚኖርበት ኣገር፣  መድብለ ፓርቲ ኣፈር ይበላል። ፖለቲካም ኣያድግም።
ማጠቃላያ
እነዚህ ከላይ የጠቃቀስኳቸው ችግሮች ለሃገራችን መድብለ ፓርቲ ስርዓትና ለፖለቲካችን  እንቅፋቶች ናቸው ብለናል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ብዙዎቻችን ጠንካራ ፓርቲ ባለመኖሩ በጣም እናዝናለን። ለምንድነው ጠንካራ ፓርቲ የፈለግነው?  በአሁኑ ሰዓት ለምን ጠንካራ ፓርቲ ፈለግን? ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲስ ማለት ምን ማለት ነው?። መድብለ ፓርቲ ስርዓት በጠፋበት ኣገር ጠንካራ ፓርቲ ስንል በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ጽህፈት ቤት እየከፈተ የጦፈ የቢሮ ስራ የሚሰራ፣ ብዙ ኣባላት የመዘገበ ወዘተ ከሆነ  ስህተት ነው። ላም በሌለበት ኩበት ለቀማ ማሰብ ነው። እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ የሚያስፈልገው መድብለ ፓርቲ ስርዓት ባለበት ምህዳሩ ባለበት ኣገር ነው። የኣሁኑ ትግል ከዚህ ይለያል። ትግሉ የነጻነት ትግል ነው። መድብለ ፓርቲ ስርዓትን ከምር ለመጀመር ነው ትግሉ። ለዚህ ደግሞ ብዙ ኣባል የመዘገበ ብዙ ቢሮ ያለው ድርጅት ሳይሆን የሚያስፈልገን ኣንድ ሰውም ሊበቃን ይችላል። ትግልን የሚመራ ኣንድ የነጻነት ታጋይ ሊበቃ ይችላል። በአሁኑ ሰዓት የተነሳውን የኦሮምያ ኣመጽ የትኛው ጠንካራ ፓርቲ ነው የቀሰቀሰው? ማንም ፓርቲ ኣይመራውም። ህዝብ ነው ያስነሳው።
አሁን እኛ ጠንካራ ፓርቲ የምንለው በምርጫ ያሸንፍልናል ሳይሆን ሰላማዊ ትግልን ይመራል ብለን ኣስበን ከሆነ ትክክል ነው። ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው ከድርጅታዊ ጥንካሬው በላይ የጥቂት ኣመራሮቹ ቁርጠኝነት ይበልጥብናል። እነዚህ ድርጅቶች ኣባላት ምዝገባ ላይ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም። ሁሉም በልቡ ኣባላቸው ነው። ለዚህ ነው ኣንድ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ሲጠራ ያን ያህል ሰው የወጣው። በልቡ ኣባል ሆኖ የጨረሰውን ሰው ፎርም ካላስሞላን ብሎ ጊዜ ማጥፋቱ ዋጋ የለውም። ይልቅ ህዝቡን በሰላማዊ መንገድ ለመብቱ እንዲታገል ማድረግ ነው። ይህን ግፍ የጠገበ ህዝብ ስለነጻነት ልናስተምረው፣ ስለለውጥ ጥቅም ልናስተምረው ኣያሻም። የሚያስፈልገው ትግልን የሚመሩ የነጻነት ታጋዮችን ማፍራት ነው።
ጠንካራ ፓርቲ ቢኖረን መልካም በሆነ። ነገር ግን በተለይ በሃገር ቤት ይህን ኣይነት ፓርቲ በኣሁኑ ሰዓት መጠበቅ ችግር ኣለው። ዋናው ማወቅ ያለብን ነገር ተቃዋሚዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ኣላቸው። ባይመዘግቡትም፣ የድርጅት ኣባል ኣድርገው መታወቂያ ባይሰጡትም ህዝቡ ኣባል ሆኖ ጨርሷል። በመሆኑም ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁኑ ፈጣን ምልሽ የሚሰጠው ሰፊ ህዝብ ኣለ። ህዝባዊ ተቃውሞዎችን መምራት የሚችል የተሰጡ መሪዎች ያሻናል። በዚህ ጊዜም ጠንካራ ፓርቲ ስንል የላይኛውን መሪዎች የመስዋእትነትና የቆራጥነት መንፈስ የሚመለከት ነው። ጠንካራ መሪዎች ብቅ ሲሉና ተቃውሞዎችን ሲመሩ ህዝቡን ለመብቱ ሲያታግሉት ያን ጊዜ ብዙዎችን ውጦ ጠንካራ ፓርቲ ወጣ ይባላል። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን ማድረግ ያለብን መልካም ራእይ ያላቸውን ፓርቲዎች ውጤት ተኮር እንዲሆኑ መከታተል ጠቃሚ ነው። መቼም ጠንካራ ፓርቲ ሁሌም እንሻለን። ይሁን እንጂ የአሁኑ አንገብጋቢ ጥያቄያችን የህዝቡን መብት የሚያስመልሱ ቆራጥ የነጻነት ትግል መሪዎችን ነው። ስለዚህ ህዝቡ መረዳት ያለበት ነገር ጣንካራ ፓርቲ መጠበቁ ጊዜ ይወስዳል። የፓርቲውም ቁጥር ገና ሊጨምር ይችላል። አሁን የሚያስፈልገው ዜጎች ለነጻታቸው፣ ለመብታቸው በራሳቸው መቆምን ነው። ህዝባዊ እምቢተኝነቶች መሪዎችን ያፈራል። ታላቁ መሪ ማርቲን ሉተር ኪንግ የነጻነት ትግል ውጤት ነው፣ ከህዝብ ትግል መሃል የወጣ ነው። ማርቲን ሉተር ሳይሆን ትግሉን ያፈራው ትግሉ ነው ማርቲን ሉተርን ያፈራው። ኔልሰን ማንዴላ በራሳቸው አንደበት እኔ የደቡብ አፍሪካዉያን የትግል ውጤት ነኝ ብለዋል። መሪ የሚያፈራ ትግል ማድረግ አለብን። ኢትዮጵያን በተሻለ አቅጣጫ መምራት የሚችሉ ብዙ ልጆች አሉ። ጭቆና ተጭኗቸው ይሆናልና እነዚህን መሪዎች የህዝብ ትግል ያወጣቸዋል። በሌላ በኩል ፓርቲዎችም በቆራጥነት ትግሉን ምሩ፣ ህዝቡን ለመብቱ አታግሉት። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።
አስተያየት ካለዎት በዚህ ኢሜየል ይጻፉልኝ
geletawzeleke@gmail.com

ሰበር ዜና! የመለስ ፋውንዴሽን ተዘጋ! (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)


ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ
ይህን የመለስን ፋውንዴሽን መዘጋት በሚመለከት “ዜና ላድርገው ወይንስ መጣጥፍ?” ብዬ ብዙ ተጨነቅሁ፡፡ ዜናም ላድርገው መጣጥፍ መቼም እስካሁን የቀደመኝ እንደማይኖር ተስፋ አለኝ፡፡ ወደሰበር ዜናው ላምራ፡፡
የሕዝብ ዋይታ የፈጠረው ዕንባና ያፈሰሰው የንጹሓን ደም ፈጣሪ ዘንድ ጮኸው ባመጡት የጸሎት መልስ ለገሠ ዜናዊ – በፖለቲካዊ የብዕር ስሙ መለስ ዜናዊ – የሚባለው ሽፍታ  የዛሬ አራት ዓመታት ገደማ ከሥሩ ተግነድሶ አይሞቱ አሟሟት መሞቱ የሚታወስ መሆኑን የገለጸልን ይህን ሰበር ዜና ያደረሰን ግለሰብ በመቀጠልም በዚህ ዱርዬ ሀገር አጥፊ ስም ተቋቁሞ የነበረውና ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ፋውንዴሽን ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን ጠቁሟል፡፡
አቶ ነፃነት ዘለቀ የሚባሉ – ባጋጣሚ ሆኖ የዜናውም ዘጋቢ እርሳቸው ናቸው – የአዲስ አበባ ኗሪ ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም – በዕለተ ኪዳነ ምሕረት – ከቤታቸው ወደ ሥራቸው ለመሄድ ዝምቡን እንኳን እሺ የሚልለት ሰው ሳይኖር ኦናውን ተገትሮ በሚውለው በዚያ ፋውንዴሽን አጠገብ ሲያልፉ የተመለከቱት ነገር ከባድ ምልኪያዊ ገጽታ እንዳለው የደረሱበት መሆኑንም አልሸሸጉም፡፡
ዝርዝሩን በተመለከተ እንዲህ በማለት ገልጸዋል – አቶ ነፃነት፡፡ “ዌል፣ እኔ ኖርማሊ ጧት ጧት ወደ ሥራ የምሄደው በዚህ የመለስ ፋውንዴሽን በሚሉት መንገድ አስታክኬ ነው – ብዙም የምታከክ ደግሞ እንዳይመስልህታዲያ፤ እናንት ጋዜጠኞች አንድን ነገር ኤግዛጀሬት እንደምታደርጉና ነገሮችን እንደምታዛቡ አውቃለሁ፡፡ እርግጥ ነው አክቹዋሊ እዚያ አካባቢ ስደርስ ወደፋውንዴሽኑ ማየትን አልወድም፡፡ ሰውዬው በቁሙ ያስጠላኝና የእናቴ ገዳይ ያህል እቆጥረው ስለነበረ በዚያ የማልፈው ደሜ እየተንተከተከ ነው – ዩዥዋሊ፡፡ ዛሬ ግን ለየት ያለ ነገር ታዘብኩና የመኪናየን ፍጥነት በረድ አድርጌ በመስኮት በኩል ስመለከት ከዐድዋ ድልድይ አቅጣጫ የመጣ የሚመስል አንድ ላንድክሩዘር በመናኸሪያ ሆቴል አቅጣጫ በኩል ከሚገኘው የፋውንዴሽኑ ዋና መግቢያ የበሩ ኮለን ጋር በመጋጨት በሩን ዘግቶ ቆሞ አየሁ – በትዕዛዝ በሩን ለመዝጋት የቆረጠ ይመስላል፡፡ ወደግቢው የሚወስደውን መንገድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዘግቶታል፡፡ ከሰው በቀር ወደግቢ መኪና አያስገባም – ለነገሩ ከዚያች ውሻ ሴት በስተቀር ሌላ ሰው ማን ሊገባ እንደሚችል አላውቅም – (ውሻ ማለቴን በዜናህ እንዳታቀርበው ታዲያ ፤ እናንተ እኮ አትታመኑም – አደራህን ኤዲት አድርገህ አውጣው ኦኬ?) ብዙ ሰዎችም ዙሪያውን ቆመው ጉድ ጉድ ይላሉ – “ድ” እንደማይጠብቅ አንባቢዎችህን ንገራቸው – አለበለዚያ ምን ድግስ ኖሮ ነው ‹ጉድ ጉድ› (አሁን ‹ድ› ይጠብቃል) የሚሉት እንዳይሉህ፡፡ እንደምገምተው ብዙዎቹ ሳይደሰቱ አልቀሩም፤ ግን በላይ ያዘኑ መስለው ሊፓቸውን ይመጣሉ – ‹እምጵ› እያሉ፡፡ ግጭቱ ከባድ ቢመስልም የተጎዳ ሰው ግን እንደሌለ አንገቴን በመስኮት አስግጌ የጠየቅሁት አንድ ሰው ነግሮኛል፡፡” በማለት ፋውንዴሽኑ ቢያንስ ያ ላንድክሩዘር እሰኪነሳ ድረስ ተዘግቶ እንደሚቆይ አስረድተዋል፡፡
“በዚህ በፋውንዴሽኑ መዘጋት ምን ተሰማዎት?” ተብለው የተጠየቁት አቶ ነፃነት ሲመልሱ “ኦፍ ኮርስ ምንም አልተሰማኝም ልልህ አልችልም፡፡ ግጭቱ ባይደርስ ደስ ይለኛል፡፡ በተለይ ከመጠነኛ የንብረት ዲስትራክሽን ውጭ የሰው ላይፍ ላይ ምንም ሃፕን ያደረገ ነገር ባለመኖሩ ደስ ብሎኛል፡፡ በት ኦን ዚአዘር ሃንድ ላንድ ክሩዘርን የመሰለ ሚጢጢየ ካር ኦር መኪና ኢፍ ዩ ላይክ ሳይሆን የሆነ ዩ ኖው የፋውንዴሽኑን ግቢ ብቻ የሚያህል ሜቴዎሮይድ ቢወድቅበትና ድራሽ አምላኩ ቢጠፋም የምጠላ ፐርሰን አይደለሁም – ኤግዛክትሊይ ኤ ካይንድ ኦፍ ዛት፡፡ ቱ ዩር ሰርፕራይዝ ይሄ ላንድክሩዘር በሩን እንዲህ ልክክ አድርጎ በግጭት ምክንያት መዝጋቱ ኢት ኢዝ ሪሊ ኦሚነስ – ማለቴ ምልኪያዊ ነው፡፡ ይህ ያልተጠበቀ ክስተት ግቢው በቅርቡ እንደሚዘጋና ለሌላ ፍሬያማ ተግባር እንደሚውል ይጠቁማል፡፡ ሶሪ እቸኩላለሁ፡፡ ሌላ ነገር ባትጠይቀኝ ደስ ይለኛል” በማለት ወደ ሥራቸው ለመሄድ ማቆብቆባቸውን በሰውነት እንቅስቃሴያቸው ቢጠቁሙም የያዛቸው ጋዜጠኛ ቀላል ባለመሆኑ “ጥሩ ነው፣ በንግግርዎ ጣልቃ እንግሊዝኛን የሚጠቀሙት ለምንድነው?” ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ መልሳቸውም “ሂድና ኢቲቪን ጠይቅ፣ ሂድና ወያኔን ጠይቅ፣ ሂድና በየስብሰባውና በየዐውደ ጥናቱ በእንግሊዝኛና ዐማርኛ ጉራማይሌ በቅጹ ሳያውቅበት እያወለጋገደ የሚንተባተበውን ምሁርና ካድሬ ጠይቅ፣ ሂድና ስሙን ሲጠየቅ ባላስፈላጊ ሁኔታ ሳይቀር ‹አክቹሊ ስሜ ገረመው ነው› የሚል ዓይነት ጉራማይሌ ሠርክ የሚነገርባቸውን ኤፌሞች ጠይቅ፣ ሂድና የተማርኩ ነኝ የሚለውን ዜጋ በሙሉ ጠይቅ፣ ‹የሠራተኞች መጓጓዣ› ማለት አቅቷቸው አይደለም እንዴ ዐማርኛን በመጸየፍ ‹ፐብሊክ ሰርቪስ› የሚል የዐማርኛ ጽሑፍ ሰማያዊ አውቶቡሶች ላይ ለጥፈው የሚያስቁን? እኔስ ታዲያ ከማን አንሳለሁ? ሁ ማይነስ ሁ አንተ!?” በማለት በንዴት መልሰዋል፡፡ አሁን የቸኮልኩት እኔ ጋዜጠኛው ሆንኩ – እርሳቸው እንደሆኑ ሥራቸውንም ረስተው ከኔ ጋር ሲያወሩ ቢውሉ ደስተኛ ይመስላሉ፡፡
በተዋዛ አቀራረብ ላደረስንላችሁ ጮማ ሰበር ዜና ምሥጋና እንደሚገባን በሾርኒ በመጠቆም በሌላ – ከተገኘ – ሰበር ዜና እስክንገናኝ ደህና ዋሉ በማለት የምሰናበታችሁ –
ከመለስ ፋውንዴሽን ቅጽር ግቢ ውጪ የተጠናቀረውን ዜና ያቀረብኩላችሁ ነፃነት ዘለቀ ነኝ ከአዲስ አበባ
ማሳሰቢያ፡- ይህንን ዜና በምስል ማስደገፍ ያልተቻለው በዚያ አካባቢ ፎቶግራፍ ማንሣት ከጤና አኳያ ጎጂ ሆኖ በመገኘቱ መሆኑን ከይቅርታ ጋር ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ጎመን በጤና፡፡ ለሥራ ያልደረሱ፣ ለምግብ ያላነሱ ልጆችን ቀፍቅፎ ከጅብና ከዓሣማ ጋር አላስፈላጊ ልፊያ ውስጥ መግባት ብልኅነት አይደለም፡፡
By andualem sisay
Hundreds of Ethiopian migrants have been evacuated from war torn-Yemen in the past 10 days.
The International Organisation for Migration (IOM) said in a press statement it had evacuated 485 vulnerable Ethiopians, including 122 women, 261 men, a child and 101 unaccompanied minors from Yemen.
The voluntary repatriations, the statement explained, was supported by the governments of Yemen, Djibouti, Ethiopia and Saudi Arabia.
“This has followed IOM’s earlier repatriation of 4,222 Ethiopians from Yemen in an operation that was suspended in September 2015 due to lack of funding. The same operation provided post-arrival assistance to another 3,319 Ethiopians fleeing Yemen,” it said.
Other partners
The new repatriation from the Hodeidah seaport to Djibouti and on to Ethiopia by bus, targets a total of 1,212 stranded migrants.
IOM’s migrant assistance and protection operations in Yemen were also being supported by other partners such as the US State Department and the UK’s DfID.
The arrivals confirmed the desperate situation of many migrants, hence the urgency for the evacuation.
Ethiopians
Ahmed (not his real name), a 22-year-old barber, explained that he left Ethiopia in search of a better life in Saudi Arabia.
“After paying smugglers to take us to Yemen, we were promised that we would be on our way to Saudi Arabia to make a lot of money. But we were intercepted by kidnappers as soon as we got off the boat in Yemen,” he said.
Beaten to death
“We saw two individuals beaten to death. They were hang upside down and beaten to death; we watched them die.”
Ali (name changed), a 25-year-old khat shop owner, narrated how he was also kidnapped and held to ransom. Family members in Saudi Arabia had to pay the kidnappers a total of $2,700 (Saudi Riyals 10,000) for his release. He considers himself fortunate, given the cruelty he witnessed.
“We saw the kidnappers melt plastic on the backs of some of them. We saw one young man beaten so badly till his arm and ribs were broken and then dumped onto the streets.
Were raped
“If you don’t have the money to pay the ransom demanded, you die. We also saw many women who were raped,” he told IOM.
The migrants who either managed to escape or were released by kidnappers following ransom payments, were given refuge at IOM Yemen shelters. However, they represent a small percentage of all those in need of repatriation, according to the IOM Migration Management Programme Coordinator in Ethiopia, Ms Fumiko Nagano.
Umbrella law
“According to UNHCR and the Regional Mixed Migration Secretariat, over 92,000 migrants arrived in Yemen in 2015. Some 89 per cent of those are believed to be Ethiopian nationals,” she said to IOM.
The Director-General of the Middle East Affairs Directorate at the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs, Mr Siraj Reshid, said the latest returnees from Yemen further underlined the need to strengthen the fight against human traffickers.
“The Government of Ethiopia has already ratified an umbrella law and we are working on its implementation to promote regular channels for those who seek job opportunities abroad,” he told IOM.
- See more at: http://www.zehabesha.com/hundreds-of-ethiopians-evacuated-from-war-torn-yemen/#sthash.qV1IH3QJ.dpuf
By andualem sisay
Hundreds of Ethiopian migrants have been evacuated from war torn-Yemen in the past 10 days.
The International Organisation for Migration (IOM) said in a press statement it had evacuated 485 vulnerable Ethiopians, including 122 women, 261 men, a child and 101 unaccompanied minors from Yemen.
The voluntary repatriations, the statement explained, was supported by the governments of Yemen, Djibouti, Ethiopia and Saudi Arabia.
“This has followed IOM’s earlier repatriation of 4,222 Ethiopians from Yemen in an operation that was suspended in September 2015 due to lack of funding. The same operation provided post-arrival assistance to another 3,319 Ethiopians fleeing Yemen,” it said.
Other partners
The new repatriation from the Hodeidah seaport to Djibouti and on to Ethiopia by bus, targets a total of 1,212 stranded migrants.
IOM’s migrant assistance and protection operations in Yemen were also being supported by other partners such as the US State Department and the UK’s DfID.
The arrivals confirmed the desperate situation of many migrants, hence the urgency for the evacuation.
Ethiopians
Ahmed (not his real name), a 22-year-old barber, explained that he left Ethiopia in search of a better life in Saudi Arabia.
“After paying smugglers to take us to Yemen, we were promised that we would be on our way to Saudi Arabia to make a lot of money. But we were intercepted by kidnappers as soon as we got off the boat in Yemen,” he said.
Beaten to death
“We saw two individuals beaten to death. They were hang upside down and beaten to death; we watched them die.”
Ali (name changed), a 25-year-old khat shop owner, narrated how he was also kidnapped and held to ransom. Family members in Saudi Arabia had to pay the kidnappers a total of $2,700 (Saudi Riyals 10,000) for his release. He considers himself fortunate, given the cruelty he witnessed.
“We saw the kidnappers melt plastic on the backs of some of them. We saw one young man beaten so badly till his arm and ribs were broken and then dumped onto the streets.
Were raped
“If you don’t have the money to pay the ransom demanded, you die. We also saw many women who were raped,” he told IOM.
The migrants who either managed to escape or were released by kidnappers following ransom payments, were given refuge at IOM Yemen shelters. However, they represent a small percentage of all those in need of repatriation, according to the IOM Migration Management Programme Coordinator in Ethiopia, Ms Fumiko Nagano.
Umbrella law
“According to UNHCR and the Regional Mixed Migration Secretariat, over 92,000 migrants arrived in Yemen in 2015. Some 89 per cent of those are believed to be Ethiopian nationals,” she said to IOM.
The Director-General of the Middle East Affairs Directorate at the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs, Mr Siraj Reshid, said the latest returnees from Yemen further underlined the need to strengthen the fight against human traffickers.
“The Government of Ethiopia has already ratified an umbrella law and we are working on its implementation to promote regular channels for those who seek job opportunities abroad,” he told IOM.
- See more at: http://www.zehabesha.com/hundreds-of-ethiopians-evacuated-from-war-torn-yemen/#sthash.qV1IH3QJ.dpuf
By andualem sisay
Hundreds of Ethiopian migrants have been evacuated from war torn-Yemen in the past 10 days.
The International Organisation for Migration (IOM) said in a press statement it had evacuated 485 vulnerable Ethiopians, including 122 women, 261 men, a child and 101 unaccompanied minors from Yemen.
The voluntary repatriations, the statement explained, was supported by the governments of Yemen, Djibouti, Ethiopia and Saudi Arabia.
“This has followed IOM’s earlier repatriation of 4,222 Ethiopians from Yemen in an operation that was suspended in September 2015 due to lack of funding. The same operation provided post-arrival assistance to another 3,319 Ethiopians fleeing Yemen,” it said.
Other partners
The new repatriation from the Hodeidah seaport to Djibouti and on to Ethiopia by bus, targets a total of 1,212 stranded migrants.
IOM’s migrant assistance and protection operations in Yemen were also being supported by other partners such as the US State Department and the UK’s DfID.
The arrivals confirmed the desperate situation of many migrants, hence the urgency for the evacuation.
Ethiopians
Ahmed (not his real name), a 22-year-old barber, explained that he left Ethiopia in search of a better life in Saudi Arabia.
“After paying smugglers to take us to Yemen, we were promised that we would be on our way to Saudi Arabia to make a lot of money. But we were intercepted by kidnappers as soon as we got off the boat in Yemen,” he said.
Beaten to death
“We saw two individuals beaten to death. They were hang upside down and beaten to death; we watched them die.”
Ali (name changed), a 25-year-old khat shop owner, narrated how he was also kidnapped and held to ransom. Family members in Saudi Arabia had to pay the kidnappers a total of $2,700 (Saudi Riyals 10,000) for his release. He considers himself fortunate, given the cruelty he witnessed.
“We saw the kidnappers melt plastic on the backs of some of them. We saw one young man beaten so badly till his arm and ribs were broken and then dumped onto the streets.
Were raped
“If you don’t have the money to pay the ransom demanded, you die. We also saw many women who were raped,” he told IOM.
The migrants who either managed to escape or were released by kidnappers following ransom payments, were given refuge at IOM Yemen shelters. However, they represent a small percentage of all those in need of repatriation, according to the IOM Migration Management Programme Coordinator in Ethiopia, Ms Fumiko Nagano.
Umbrella law
“According to UNHCR and the Regional Mixed Migration Secretariat, over 92,000 migrants arrived in Yemen in 2015. Some 89 per cent of those are believed to be Ethiopian nationals,” she said to IOM.
The Director-General of the Middle East Affairs Directorate at the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs, Mr Siraj Reshid, said the latest returnees from Yemen further underlined the need to strengthen the fight against human traffickers.
“The Government of Ethiopia has already ratified an umbrella law and we are working on its implementation to promote regular channels for those who seek job opportunities abroad,” he told IOM.
- See more at: http://www.zehabesha.com/hundreds-of-ethiopians-evacuated-from-war-torn-yemen/#sthash.qV1IH3QJ.dpuf

አንድ ሰሞን ከሙኒኮች ጋር (በኤፍሬም ማዴቦ) Ginbot 7 Patriot Efrem Madebo in Munich

አንድ ሰሞን ከሙኒኮች ጋር (በኤፍሬም ማዴቦ)

 Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters

በኤፍሬም ማዴቦ
አባባ . . .  አባባ . . . . ስማ አባባ ረሳህ እንዴ አለኝ ያ ባለፈዉ ነኃሴ ወር ስንለያይ ያስለቀሰኝ ልጄ።  ምኑን አልኩት።  ቅድም ምሳ ላይ የነገርኩህን . . . እንዴ!  እሱንማ እንዴት እረሳለሁ። Please don’t አባባ! …… I will not! ሲረጋጋና ደስ ሲለዉ ታየኝና ልቤን ደስ አለው። ልጄ ኮሌጅ የሚገባበት ቀን እኔ ደግሞ ከትግል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት ቀን ናፍቆናል። አባባ Good luck አለኝ። እኔም ይቅናህ አልኩት። Good luck እና ይቅናህ የተባባልነው እኔ እሱ የሚመኘዉ ኮሌጅ እንዲገባ እሱ ደግሞ እኔ በድል ኢትዮጵያ እንድገባ ነበር። ሁለታችንም ይቅናን . . . አሜን!!!
አዉሮፕላን ዉስጥ ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ኢር ፎኑን ጆሮዬ ውስጥ ሰክቼ አይፎኔ ላይ “Play” የሚለዉን ስጫነዉ ጥላሁን ገሰሰ “አራዊቱ ሁሉ መጥቶ ቢከበኝ” እያለ ጀመረኝ። የምወደው ዘፈን ነበርና ደጋገምኩት። ጥላሁንኮ ድምጻዊ ብቻ አይደለም ነቢይም ነዉ፤ የዛሬ ስንትና ስንት አመት በአራዊቶች እንደምንከበብ ተንብዮ ነበር። የሚቀጥለው ዘፈን ገና ሲጀምር ምን መሆኑ ታወቀኝና. . . . . ኧረ በፍጹም. . . እንዴት ተደርጎ አልኩና አይፎኔን ዘግቼዉ ኪሴ ዉስጥ ከተትኩት። “መለያየት ሞት ነዉ” የሚለዉን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ብወደዉም የጠነከረዉ ሆዴ እንዲባባ በፍጹም አልፈለኩም። አይፓዴን አወጣሁና የአስናቀች ወርቁን ሰዉነት እየሰረሰር ገብቶ አንጀት የሚያርስ ክራር መኮምኮም ጀመርኩ። አስናቀች ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ቦታ ወሰደችኝ፤ ደግነቱ ዬትም ትዉሰደኝ ዬት መልሳ መላልሳ እዚያዉ አዉሮፕላኑ ውስጥ ታመጣኝ ነበር . . .  አለዚያማ!
አዉሮፕላኑ ወንበር ላይ አንደተኛሁ ከአንድ ጎኔ ወደ ሌላዉ ጎኔ ስገላበጥ ሁለት የተለያዩ ድምጾች ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገቡ። ከአይፓዴ የሚወጣዉ ድምፅ “እልም አለ ባቡሩ” ይላል፥ የአዉሮፕላኑ ድምጽ ማጉያ ደግሞ “Welcome to Munich” ይላል። እንቅልፋም አይደለሁም፥ እንቅልፌን ሳልጨርስ የሚቀሰቅሰኝ ሰዉም ሆነ ምንም አይነት ድምጽ ግን ጠላቴ ነዉ። ደግሞም የእንቅልፍ ነገር ሆኖብኝ ነዉ እንጂ ሙኒክ መድረሴን ወድጄዋለሁኮ።
እኔንና ሌሎች ከ180 በላይ መንገደኞችን የጫነዉ ዩናይትድ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 106 አዉሮፕላን ጎማዎች ከሙኒክ አዉሮፕላን ማረፊያ ወለል ጋር ሲላተሙ ያ ለካሳ ተሰማ ዘፈን አልበገር ያለዉ እንቅልፌ ዳግም አይመጣ ይመስል እልም ብሎ ጠፋ። እኔም የምን እንቅልፍ አልኩና ሙኒክን ለማየት ቸኮልኩ። ሙኒክ ሲባል ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማለሁ እንጂ እቺን ዉብ የባቫሪያ ከተማ ሳያት የመጀመሪያዬ ነበር። አይፎኔን አወጣሁና ከአስመራ አሜሪካ ከገባሁ ጀምሮ ስልክ እየደወለ ሙኒክ ካልመጣህ እያለ ለሚጨቀጭቀኝ የአገሬ ሰዉ ስልክ ደወልኩ. . . .  ጋሼ ደረስክ እንዴ አለኝ። አዎ እናንተን እየጠበኩ ነዉ አልኩት። ጋሼ እኛ መግባት አንችልም ስትወጣ ታየናለህ አለኝ። ሁለት ተንጠልጣይ ሻንጣዎቼን ግራና ቀኝ ትከሻዬ ላይ አንጠልጥዬ ሻንጣ የጫንኩበትን ጋሪ እየገፋሁ ወደ መዉጫዉ አመራሁ። የሁለቱ ሻንጣዎች ክብደት ትከሻዬን ሲያጎብጠዉ ግዜ ሁለተኛ ለማንም ሰዉ ዕቃ አላደርስም ብዬ ማልኩ። ሁሌም እየማልኩ የምረሳዉ መኃላ ቢኖር ይህ ብቻ ነዉ። ወደ መዉጫዉ ስጠጋ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ። ታክሲዉና አዉቶቡሱ፤ ሸኚዉ፤ እንግዳ ተቀባዩ፤ እኔን መሰሉ ወደ ሙኒክ የሚመጣዉና ሙኒክን የሚለቀዉ መንገደኛ እዚህም እዛም ይተራመሳል። ከዚህ ሁሉ የሰዉና የመኪና ትርምስ ዉስጥ አይኔ ተሽቀዳድሞ ያረፈዉ በዚያ በዉበቱና በድምቀቱ የባንዲራዎች አዉራ በሆነዉ የአገሬ ባንዲራ ላይ ነበር። ሊቀበሉኝ የመጡ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ያንን በትንሽነቴ “ደሙን ያፈሰሰ” ብዬ የሰቀልኩትንና ማታ “ተጣማጅ አርበኛ” ብዬ ያወረድኩትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲመጡ አየሁና ተጠጋኋቸዉ። ሰንደቅ አላማዉ “አምባሻ” ስለሌለበት አመንኳቸዉ። አለዚያማ ፊቴን አዙሬ ጉዞዬን ወደ አስመራ እቀጥል ነበር እንጂ አምኜ አልጠጋቸዉም ነበር። ወይ ጉድ …… ዘመን አያመጣዉ ነገር የለም. . . . . .  የምንተነፍሰዉንም አየር መጠርጠር ጀመርንኮ!
ሙኒክ የገባሁት ሐሙስ ጧት አስር ሰአት ተኩል ላይ ነበር። እሁድ ጧት ለስራ ጉዳይ ሲዊዘርላንድ እስክሄድ ድረስ ከሁለት ቀን ተኩል በላይ ሙኒክ ዉስጥ ቆይቻለሁ። ግን እንኳን ሁለት ቀን ተኩል ግማሽ ቀንም የቆየሁ አልመሰለኝም። ነገሩ ምንድነዉ ብዬ ተገረምኩ። ሚስጢሩ የገባኝ አስመራ ገብቼ ከእንቅልፌ ስነቃና የቀረብኝን ሳዉቀዉ ነዉ። ሙኒኮች በልቼ የምጠግብ፥ ጠጥቼ የምረካ አይመስላቸዉም። ያገኙኝ ሰዎች ሁሉ ብላ፤ጠጣ፤ እንሂድ፤ እንዉጣ፤ ምን እንግዛ፤ ምን እናምጣ፤ ምን ትፈልጋለህ፤ ምን አነሰ ነዉ ጥያቄያቸው። የሙኒክ ወገኖቼ ከኑሯቸዉ በላይ ሲያስቡልኝና ከራሳቸዉ በላይ ሲሳሱልኝ አይቼ እንደ ዐለት የማይነቃነቅ ደጀን አለኝ ብዬ ተመክቼባቸዋለሁ። በተለይ ሙኒክ ውስጥ ያየኋቸዉ ሴቶች እህቶቼ መጥተን እንቀላቀላችሁ እንጂ ከተማ ዉስጥማ ምን እናደርጋለን ነበር ጥያቄያቸዉ። የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ የቀረዉን የመጨረሻ የፍርሃት ጠብታ ጠራርገዉ ሲወስዱት ታወቀኝና ድፍረቴ ከአናቴ አልፎ ሲያንሳፍፈኝ ተሰማኝ። እቴጌ ተዋበች ለቋራዉ አንበሳ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ለዳግማዊ ምንሊክ ጉልበት፤ ብርታትና ጽናት እንደሆኗቸው ሁሉ ለኔም የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ ገብተዉ ብርታት፤ ልቤ ዉስጥ ገብተዉ ጽናት ሆኑኝ። አደራ. . . .  ሴት የላካዉ ሞት አይፈራም ብላችሁ ለቆራጥ እህቶቼ የምሰጠዉን ምስክርነት እንዳታሳንሱብኝ። የሙኒክ ሴቶች የልብ ልብ የሰጡኝ ዕቃችንን ጠቅልለን ካልተከተልንህ እያሉ ነዉ እንጂ አይዞህ በርታ አለንልህ እያሉ ብቻ አልነበረም።
ቀኑን እንደ ደዋሪ ከወዲህ ማዶ ወዲያ ማዶ ስሽከረከር ዉዬ ስለደከመኝ አርብ ዬካቲት 26 ቀን (Feb 26) አልጋዬ ዉስጥ የገባሁት በግዜ ነዉ። ከሆቴሉ ሰራተኛ ቁልፍ ተቀብዬ መኝታ ክፍሌ ስደርስ አልጋዋ እንኳን ሙሉዉን ኤፍሬም አንድ እግሩንም ተሸክማ የምታድር አልመሰለችኝም። ትንሽዬ አልጋ ናት። ሽንት ቤቱና መታጠቢያ ቤቱም እንደዚሁ። ብቻ ምን አለፋችሁ አዉሮፓ ዉስጥ ትልቅ ነገር ያለም አይመስል። መንገዱ፤ መኪናዉ፤ ሀንጻዉና መኖሪያ ቤቱ ሁሉም ነገር ትንሽ ነው። አዉሮፓዉያን አንድ ነገራቸዉ ግን ትልቅ ከትልቅም ትልቅ ነዉ። ለሀይል ቁጠባና (Energy Conservation) ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጡት ቦታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። አዉሮፓ ስሄድ ሁለት ጉዳዮች ነበሩኝ። አንደኛዉ የሙኒክ ኢሳት ቤተሰቦች ባዘጋጁት የገንዘብ ማሰባሰብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የትግል ጓደኛዬን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር ነዉ።
አርብ ማታ በግዜ ቆጤ ላይ ስለተሰቀልኩ ቅዳሜ ዬካቲት 27 ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ እንደልማዴ እየደጋገመ አላዛጋኝም ወይም ተኛ ተኛ አላሰኘኝም። ፈጣን ሻወር ወስጄ ልብሴን ለባበስኩና ያደርኩበት ሆቴል በነጻ ብላ ያለኝን ቁርስ መቆርጠም ጀመርኩ። ከቁርሱ ይልቅ የጣመኝ ቡናዉ ነበርና አንዴ ደግሜ ሶስተኛዉን ይዤ ጠረቤዛ ቀየርኩና አይፓዴን ከፍቼ ዜና መቃረም ጀመርኩ። ኦሮሚያ ዉስጥ ከሦስት ወራት በፊት የተቀሰቀሰዉ ሀዘባዊ ቁጣ አለመብረዱ፤ የአዲስ አበባዉ ታክሲ ሾፌሮች አድማና ጎንደር ዉስጥ በየቦታዉ የሚፈነዳዉ ህዝባዊ አመጽ ትኩረቴን ከሳቡ ዜናዎች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። ዜና ማንበቡን ጨርሼ ቀና ስል ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞና ጓደኛዉ መጡና . . . ጋሼ ምሳ እንብላ እንጂ ብለዉኝ ተያይዘን ወጣን።
ፉጨቱ፤ ሆታዉ፤ መዝሙሩና አዳራሹ ዉስጥ በየማዕዘኑ የሚዉለበለበዉ ሰንደቅ አላማችን ገና ስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ሳልገባ በሩቁ የአዳራሹን ስሜት ነገረኝ። አዳራሹ ዉስጥ ያሉት ኢትዮጵያዉያን አላማቸዉ አላማዬ ምኞታቸዉ ምኞቴ እንደሆነ ካውቅኩ ቆይቷል። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ስሜታቸዉን ሳይ ግን ልባቸዉ ከልቤ ተገናኘና ደሜ ደማቸዉ፤ ሞቴ ሞታቸዉ መሆኑ ዉስጤ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ። ከሰዉነቴና ከሰዉነታቸዉ የአካል ፍላጭ ወጥቶ አዲስ አካል ሲፈጠር ታወቀኝ። አዎ. . . ዜግነት መሰረቱ፤ እኩልነት ማዕዘኑ፤ ነጻነት ጣራዉ፤ ፍትህ ወለሉ፤ አንድነትና ዲሞከራሲ ድርና ማጉ የሆነ ፍጹም አዲስ አካል ሲፈጠር ተሰማኝ። ፍጹም ልዩ ስሜት ነበርና ወደድኩት። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ብዙም ሳልቀመጥ እኛ በህይወት እንድንኖር የሞት መስዋዕትነት ለከፈሉልን ጀግኖች የሂሊና ጸሎት እናድርስ ሲባል አዳራሹ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ በሙሉ ከመቀመጫዉ ተነሳ። አዳራሹ ላንዳፍታ ሰዉ የሌለበት ኦና ቤት መሰለ። ያንን ሰው የሞላበት የስብሰባ አዳራሽ የዝምታ ጽላሎት ዋጠዉ። ሁላችንም በአንድ አፍንጫ እንተነፍስ ይመስል ትንፋሻችን እራሱ አንድ ሆነ።
ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች አፈወርቅ አግደዉና ሀይሉ ማሞ ማይክሮፎናቸዉን ጨብጠዉ መድረኩ ላይ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዋል። አዳራሹን የሞላዉ ህዝብ እነሱን እነሱ ደግሞ ህዝቡን ያዩታል። ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞ ለእለቱ ጨረታ የቀረበዉን ዉብ የኢሳት አርማ ለተሰበሰበዉ ህዝብ ሲያሳይ ያ የሂሊና ፀሎት ሲደረግ ዝምታ የዋጠዉ አዳራሽ በጭብጨባ ጩኸት የፈረሰ መሰለ። ጨረታዉ በአንድ ሺ ዩሮ ተጀመረ። አፈወርቅ አግደዉ መድረክ ላይ ወጣና በዚያ ጀት ድምጹ ንግግሩን ሲጀምር አዳራሹ ዉስጥ ኢሳት ቴሌቭዥን የተከፈተ መሰለኝ። ከጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ አፍ እንደ አብሪ ጥይት እየተወረወሩ የሚወጡት ቃላት አድራሻቸዉ ጆሮ ሳይሆን የተሰበሰበዉ ሰዉ ኪስ ዉስጥ ይመስል ሁሉም እየተነሳ ያለዉን ይለግስ ጀመር። በአንድ ሺ ዩሮ የተጀመረው ጨረታ ብዙም ሳይቆይ አምስት ሺ ዩሮ ደረሰ። አዳራሹ ዉስጥ የነበርኩት ብቸኛ የበረሃ ሰዉ ጨረታዉ አምስት ሺ ዩሮ ላይ የሚቆም መስሎኝ ነበር። ምን ላድርግ እዉነቴን ነዉ። በረሃ ዉስጥ ብቸኛዉ የገንዘብ ቋንቋ ናቅፋ ብቻ ነው።  አምስት ሺ ዩሮ ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቅፋ ነዉ። ለሁሉም ጨረታዉ እኔ እንዳሰብኩት አልቆመም፤ እንዲያዉም የማሸነፍ እልህ ዉስጥ በገቡ ከተሞችና ግለሰቦች መካከል ፉክክር ፈጠረና 6 ሺ፤ 7 ሺ፤ እና 8 ሺ እያለ ቀጠለ።
የሙኒክ ጨረታ ትዉስታቸዉ በበጋው ፀሐይና በክረምቱ ዝናብ የማይደበዝዝ ሶስት ትዝታዎች ጥሎብኝ አልፏል። ለወትሮዉ እኔ ጨረታ የማዉቀዉ ግለሰቦች በቡድን ወይም በግል ሲጫረቱ ነዉ። የሙኒኩን ጨረታ ለየት ያደረገብኝ አንዱ ነገር የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ሙኒክ፥ በርሊን፥ ፍራንክፈርትና ኑረምበርግ. . .  ወዘተ እያሉ በከተማ ጭምር ያደረጉት ጨረታ ነዉ። እንግዲህ ይታያችሁ አዉሮፓ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጨረታ በተካሄድ ቁጥር የሚጫረቱት በግል፥ በቡድንና በከተማ ጭምር ከሆነ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ለፍትህና ለነጻነት ለሚደረገዉ ትግል የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከሌሎቻችን ይበልጣል ማለት ነው። ሌላዉ የሙኒክ ትዝታዬ የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለማጥፋት በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረጉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን በነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ርእዮት አለሙ፤ እስክንድር ነጋ፤ ኡስታዝ አቡበከር፤ በቀለ ገርባና አንዱአለም አራጌ . . . ወዘተ ስም መጫረታቸዉ ነዉ። በእነዚህ ጀግኖች ስም የተደረገዉ ጨረታ የጀግኖቹ ስምና ህያዉ ስራቸዉ ከልባችን እንዳይጠፋ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን የእነሱን ፈለግ እንድንከተል የሚገፋፋ ነበርና ለሙኒኮች ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው። Dank u München!
ሶስተኛዉ ትዝታዬ ሙኒክን ለቅቄ አስመራ ከገባሁ ከሶስት ሳምንታት በኋላ አሁንም ፊቴ ላይ አለ። ካሁን በኋላም ቢሆን እየረሳሁ ብዉልና ባድር ሶስተኛዉን ትዝታዬን የምረሳ አይመስለኝም። ይህ እንደ አፍላ ፍቅር ልቤ ዉስጥ ተተክሎ የቀረዉ ትዝታ የሶስት ሰዎች ትዝታ ነዉ። በአንድ በኩል ፊት ለፊት የመጀመሪያዉ ረድፍ ላይ ተቀምጦ ከተሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ የሚል ዶክተር አለ። በሌላ በኩል ደግሞ አዳራሹ ኋላ ሆነዉ አንሸነፍም ብለዉ የመሸጉ ባልና ሚስት አሉ። እነዚህ ሶስት ሰዎች ኋላና ፊት ተቀምጠዉ ያካሄዱት ለሰአታት የዘለቀ ፉክክር ተሰብሳቢዉን እንደ ልብ ሰቃይ ድራማ ከፍና ዝቅ ያደረገ ልዩ ትርዕት ነበር።
ዶክተሩ የህክምና ዶክተር ነዉ። ታላቄ ነዉ ሆኖም በቁመት እንጂ በዕድሜ ብዙ አንበላለጥም። የምፈልገዉን ነገር አድርግልኝ ስለዉ ያደርጋል፤ ና ስለዉ ይመጣል። ከሙኒክ ሲዊዘርላንድ እንሂድ ስለዉ ሳያቅማማ ስራዉን ጥሎ ነዉ የተከተለኝ። ቀልዱ፥ጨዋታዉና ቁምነገሩ አይጠገብም፥ በተለይ ከአፈወርቅ አግደዉ ጋር ሲተራረቡ የአራት ሰአቱ የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ እንኳን ያለቀ የተጀመረም አይመስልም ነበር። ብቻ ምን ልበላችሁ ዶ/ሩ ለኔ የነበረዉ አክብሮትና ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር በኔ ደካማ ብዕር የሚገለጽ አይደለም።
ባልና ሚስት ናቸዉ፥ የተቀመጡት አዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ ላይ ነዉ። አይቸኩሉም ደግሞም አይዘገዩም። ፈጣሪ ያደላቸዉ ስጦታ ነዉ መሰለኝ ትክክለኛዉን ግዜ ያዉቁታል። ሲማከሩ ጆሮና አፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ። ሲስማሙ ስምምነታቸዉን የሚናገረዉ ባልየዉ ነዉ። የእነዚህ ባልና ሚስት ፍላጎት ጨረታዉን ማሸነፍ ሳይሆን ኢሳትን መርዳት መሆኑን የሁለቱም ፊት በግልጽ ይናገራል። ከላይ ባስተዋወቅኳችሁ ዶክተርና በእነዚህ ባልና ሚስት መካከል የተደረገዉ የጨረታ ፉክክር አዳራሹ ዉስጥ የተሰበሰበዉን ኢትዮጵያዊ ልብ ሰቅዞ የያዘ ፍጹም ልዩ ድራማ ነበር። ፉክክሩ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና እኛነት የታየበት እንዲሁም የማይቀረዉን ብሩህ የአገራችንን ተስፋ ከወዲሁ በናሙና መልክ ፈንጥቆ ያሳየ ዉብ መድረክ ነበር። በገንዘብ አስተዋጽኦ መልኩም ቢታይ ባልና ሚስትና ዶክተሩ ያደረጉት ፉክክር የጨረታዉን ጣሪያ ከሃያ ሺ ዩሮ በላይ አድርሶታል። በነገራችን ላይ እዚህ መጣጥፍ ዉስጥ ስማቸዉን ጠቅሼ ብጽፍ ደስ የሚለኝ ብዙ ኢትዮጵያዉያን አሉ። የማላደርገዉ ክፉ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ደንቆሮ የሆነ ጠላት ስላለን ነዉ። ይህ ጠላት የደደብነቱ ብዛት የሥልጣን ክልል ያለዉም አይመስለዉም፤ አዉሮፓና አሜሪካ ዉስጥ የጻፈ፥ የተናገረና ሀሳቡን የገለፀ ኢትዮጰያዊ ላይ እድሜ ልክ እስራት ይፈርዳል። ደሞስ ጭንቅላታቸዉ በንፍጥ ብቻ የተሞላና ሰዉነታቸዉ በተዘረፈ ሀብት የደለበ ሰዎች ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
ከሙኒክ የሲዊዟ መናገሻ ቤርን ድረስ የአራት ሰአት መንገድ ነዉ። በረጂም በረራና በቅዳሜዉ የአዳራሽ ዉስጥ ቆይታ የተዝለፈለፈዉ ሰዉነቴ እየከዳኝ ቢሆንም የግድ ሲዊዘርላንድ መሄድ ነበረብኝና ተንገዳግጄ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ የአራት ሰአቱን መንገድ ተያያዝኩት። የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ የሚያልፈዉ በኦስትሪያ በኩል ነዉ። ከጀርመን ወጥቼ ኦስትሪያ መግባቴን ያውቅኩት ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ የቆሙትን ፖሊሶች ስመለከት ነዉ፤ ለዚያዉም ባይነገረኝ ኖሮ አላዉቅም ነበር። መኪናዉ ዉስጥ እንቅልፍ ብጤ ሞካክሮኝ ነበር ግን የጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉና የዚያ ደግ ዶክተር ጨዋታ እንኳን እንቅልፍ ሌላም ነገር የሚያስረሳ ነበርና ጨዋታቸዉ እንቅልፌን አባረረዉ። የመኪናዉ ዉስጥ ቀልድ፥ ተረብና ጆክ ከአካባቢዉ የተፈጥሮ ዉበት ጋር ሆነዉ መንፈሴን እያደሱት ድካሜን አስረሱኝ። አፈወርቅን የምትወዱት በቴሌቭዥን መስኮት ዉስጥ ብቻ አይታችሁት ከሆነ ብዙ ገና ብዙ ይቀራችኋል . . . ምኑን አያችሁና። አፈወርቅ ሲቀርቡት ጨዋታዉ፤ ቀልዱና ቁም ነገሩ አይጠገበም። ስለምንም ነገር ሲናገር የራሱ የሆነ ልዩ ዜማና ቃና አለዉ። ታሪክ ሲናገር በታሪኩ ዉስጥ ይዟችሁ ያልፋል። የታሪኩን መቸትና የተዋንያኑን ስም ከአባት ስም ጋር ሲናገር መጽሐፍ የሚያነብ እንጂ በቃሉ የሚናገር አይመስልም። የአማርኛ ቋንቋ በተለይ የቅኔ ችሎታዉ ይኸ ሰዉ ዋልድባ ነዉ ጋሙጎፋ ተወልዶ ያደገዉ ያሰኛል።
ከሙኒክ ተወጥቶ ኦስትሪያ እስኪገባ ድረስ ከመንገዱ ግራና ቀኝ የሚታየዉ ዘመናዊ እርሻ ከሳንሆዜ ሳንታክላራ ሲኬድ የሚታየዉን ሜካናይዝድ እርሻ አስታወሰኝ። የአዉሮፓና የአሜሪካ መመሳሰል ገረመኝ። በሃሳቤ ረጂም ርቀት ወደኋላ ተጓዝኩና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስማር ከአዋሳ አዲስ አበባ በአዉቶቡስ ስጓዝ አዉቶቡሱ ቆቃን እንዳለፈ አርሲ ነጌሌ እስኪደርስ ድረስ አልፎ አልፎ  የማያቸዉ ትናንሽ እርሻዎች ፊቴ ላይ መጡ። አስናቀች ወርቁ “እንደ መቀነቴ ዞሬ ዞሬ እዚያዉ” ብላ የተጫወተችዉ ዘፈን ትዝ አለኝና ሆዴ በቁጭት ተሞላ። አዎ የኛ ነገር ዞሮ ዞሮ እዚያዉ ነዉ። እርሻው እዚያዉ፤ ገበሬዉ እዚያዉ፤ ፋብሪካዉ እዚያዉ ባጠቃላይ የኑሮ ደረጃዉ እዚያዉ ነዉ። እዚያዉ ድሮ የነበረበት ቦታ። ወደፊት እናያለን እንጂ ወደፊት አንሄድም። ይህንን ሳስብ ተቆጨሁ . . . ተናደድኩ።  ለምን አልናደድ ለምንስ አልቆጭ . . .  እኛና ድህነት፤ እኛና ኋላቀርነት፤ እኛና እየረገጡ ከሚገዙን ጋር መሞዳሞድ ሞት ካልለየን በቀር ላንለያይ የቆረብን ይመስላልኮ!
እኛ ኢትዮጵያውያን ከአዉሮፓና ከአሜሪካ ለምንድነዉ ይህን ያህል የምናንሰው ብዬ እራሴን ጠየኩና መልሳ ሳጣ የአዉሮፓን ዉበት ማድነቄን ቀጠልኩ። እዉነቱን ለመናገር የኋላ ቀርነታችን ምክንያት ጠፍቶኝ አይደለም። ለምን መናጢ ደሃዎች እንደሆንም ጠፍቶኝ አይደለም።  ችግሩ. . .  የኋላ ቀርነታቸንን ምክንያት ባሰብኩ ቁጥር ከዚህ አሳፋሪ ኋላ ቀርነት ለመላቀቅ የምናደርገዉ ጥረት እምብዛም መሆኑን ስለማዉቅ ማሰቤን አቆምና ንዴትና ቁጭት ዉስጥ እገባለሁ። የኔ ነገር ደግሞ ጉድ ከጉድም ጉድ ነው፤ አራሴን ስጠይቅ የማገኘዉ መልስ ቁጭትና ንዴት ነዉ። ቁጭትና ንዴት ደግሞ እንደገና ጥያቄ ያጭሩብኛል። ይገርማል .…  አገሬ ከድህነት ኡደት እኔ ከጥያቄ ኡደት ላንላቀቅ የተማማልን ይመስላል። የራሱ ፊደል፥ ስነጽሁፍና የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር ያለዉ ሀዝብ እንዴት ያልሰለጠነ ህዝብ ተበሎ ይጠራል? አባይን፤ አዋሽን፤ ሸበሌን፤ዴዴሳን . . . ወዘተ ይዞ አገር እንዴት ይራባል? አክሱምን፤ ላሊበላንና ፈሲለደስን የገነባ ህዝብ ለምን ከኋላ ቀሮች ተርታ ስሙ ይጻፋል? ለምን? ለምን? ለምን?
ኦስትሪያ ስደርስ እርሻዉ፤ መኪናዉ፤ ከተማዉ፤ የሰዉ መልክና ቋንቋዉ ምንም አልተለየብኝም። ልዩነት አለ ቢባል ጀርመንን ለቅቄ ኦስትሪያ የሚባል አገር መድረሴ ብቻ ነዉ። ኦስትሪያን ለቅቄ ሲዊዘርላንድ ስገባም ፊት ለፊቴ ላይ ጉብ ጉብ ብለዉ ከሩቁ ከሚታዩኝ  ተራራዎች ዉጭ ከተማዉ የጀርመንን ከተሞች ይመስላል፤ ብዙዎቹ መኪናዎች ጀርመን ዉስጥ የተሰሩ መኪናዎች ናቸው፤ ቋንቋዉም ጀርመንኛ ነዉ። ከአሜሪካ ተነስቼ ሲዊዘርላንድ እስክደርስ ድረስ በአራት አገሮች ዉስጥ አልፍያለሁ (አሜሪካ፥ ጀርመን፥ ኦስትሪያና ሲዊዘርላንድ) – ማነህ ተብዬ ፓስፖርት የተጠየኩት አሜሪካንን ስለቅና ሙኒክ ስገባ ብቻ ነው።
ሽፍታዉ ልቤ መሸፈት አይታክተዉ ነገር አሁንም ሸፈተ። ደግሞስ ይሸፍት አንጂ. . . . ለምን አይሸፍት?  የተወለድኩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉኮ! እኛ ሰዎች እግዚአብሄር በአምሳያዉ እኩል አድርጎ ፈጥሮን አንዱ መሪዉን መርጦ ሲሾም ሌላዉ በገዛ መሪዉ ሲጎሸም፤ አንዱ በልቶ ጠግቦ ሲያምርበት ሌላዉ የሚበላዉ አጥቶ ህይወት ሲከዳዉ፤ አንዱ ሁሌም አሳሪ ሌላዉ ሁሌ ታሳሪ፤ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሲሆን እንኳን የሰዉ ልብ ከሳር ዉጭ ሌላ የማያዉቀዉ በሬም ይሸፍታል። ጀርመንን፤ ኦስትሪያንና ሲዊዘርላንድን ሳይ በገዛ አገራቸዉ ማናችሁ እየተባሉ በየኬላዉ የሚጉላሉት ምስኪን ወገኖቼ ትዝ አሉኝ። ቤንች ማጂ ዉስጥ ወደ ክልልህ ተመለስ ተብሎ የተገፋዉ ወገኔ በርቀት ታየኝ። ቤኒሻንጉል ዉስጥ አለክልልህ ምን ታደርጋለህ ተብሎ ንብረቱን ተቀምቶ እየተረገጠ የተባረረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ትዝ አለኝና ሆዴን አመመኝ። ጋምቤላ ዉስጥ የአያት ቅድም አያቶቹ መሬት ጠመንጃ ባነገቱ ጉልበተኞች ተቀምቶ ሲታርስ እሱ ተመልካች የሆነው አኝዋክ ወገኔ ትዝ አለኝ።
ከጀርመን ሲዊዘርላንድ ስንጓዝ መኪናዉ ዉስጥ የነበርነዉ አምስት ሰዎች ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን። አዉሮፓ ዉስጥ አገሮችን በሚያሳስብ ደረጃ ከፍተኛ የስደተኛ ቀዉስ አለ። ሆኖም ከጀርመን ወጥተን በኦስትሪያ በኩል ሲዊዘርላንድ እስክንደርስ ድረስ አንድም ግዜ ማናችሁ የሚል ጥያቄ አልቀረበልንም። ተመልሰን ጀርመን ስንገባም እንደዚሁ። እትብቴ በተቀበረባትና የዚህ አለም ጉዞዬን ስጨርስ የመጨረሻ ማረፊያዬ እንድትሆን በምፈልግባት ምድር እንደ ቆሻሻ ነገር የሚረገጠዉ መብቴ በባዕድ አገር ሲከበር አየሁና  “ኢትዮጵያዊነት” ምን ያደርጋል ብዬ አማረርኩ። ችግሩ ኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቆርጠዉ በተነሱ ከሃዲዎች ላይ መሆኑ ገባኝኛ እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ አለኩ። አዎ!  እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ ። “ማጥፋት” አለብኝ ሲባል አባባሉ በተግባር ካልተተረጎመ የባዶ ቃላት ጫጫታ ወይም የሞተ ሰዉ ዛቻ ነዉ። አንተ/አንቺ አንባቢ አስተዉል/አስተዉይ። ነፃነትና ፍትህ የሌሉበት አገር ሁሉ የአጥፊዎችና የጠፊዎች መድረክ ነዉ። ጠፊና አጥፊ ባሉበት ቦታ ደግሞ ሁለቱም ያጠፋሉ። አጥፊ ስራዉ ማጥፋት ነዉና ያጠፋል። ጠፊ ደግሞ ላለመጥፋት የሚያደርገዉ ምንም ነገር ስለሌለ እራሱን በማጥፋት ከአጥፊዉ ጋር ይተባበራል። የኛ የኢትዮጵያዉያን ችግርም ይኼዉ ነዉ. . .  ጠፊዉም አጥፊዉም እኛዉ እራሳችን ነን። ከዛሬ በኋላ ግን እኛ አጥፊዎች ጠላታችን ጠፊ መሆን አለበት። ተፈላሲፌባችሁ ከሆነ ይቅርታ . . . እንደዚህ የሚያንበለብለኝ ዉስጤ ያለዉ ላለመጥፋት የማጥፋት ፍላጎት ነዉ። ሲዊዘርላንድ መናገሻ ቤርን መድረሴን ያወቅኩት መኪናዋ ቆማ . . . ጋሼ እንዉረድ ስባል ነው።
የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጅ የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ለማክበር ሲዊዘርላንድ ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጰያዊ ከያለበት ተሰባስቧል። አዳራሹ ከመሙላቱ የተነሳ መቀመጫ ያጣዉ ሰዉ ያዳራሹን ዳር ዳር አጨናንቆታል። በየማዕዘኑ የሚወዛወዘዉ የኢትዮጰያ ሰንደቅ አላማ ለአዳራሹ ልዩ ዉበት ሰጥቶታል። የእንኳን ደህና መጣህ ጩኸቱ፥ ጭብጨባዉና ፉጨቱ አዳራሹ የእግር ኳስ ስታድዩም እስኪመስል ድረስ ቀለጠ። አጠገቤ የቆመው ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ ጭብጨባዉ ለኔ ነዉ ላንተ ብሎ ጠየቀኝ . . . ለኛ ነዉ አልኩት። ሳቅ አለና ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ተሰብሳቢዉ እንዲቀመጥ ተማፀነ። እኔም እጆቼን ዘርግቼ አብሬዉ ተማፀንኩ። ከእግራቸዉ ጣት እስከ ጸጉራቸዉ ጫፍ ድረስ ፍቅር በፍቅር የሆኑት የሲዊዝ ኢትዮጵያዉያን የምን መቀመጥ አሉና ሆታዉና ጭብጨባዉ ቀጠለ። ጧት ሙኒከን ስለቅ ድካም በድካም የነበረዉ ሰዉነቴ ዉስጥ አዲስ ሀይል እየገባ ሲያጠነክረኝ ተሰማኝ። ለካስ እኛ ሰዎች ምናብ ለምናብ ስንናበብ ዉጤቱ ፍቅር፥ ሀይልና ብርታት ነዉ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሲዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያን እንደ ሲዊዝ ቸኮለት የሚጣፍጥ የአገር ልጅነት ፍቅር አቀመሱኝና በወገን ፍቅር ሰከርኩ። ሲዊዞች፥ ቸኮለታቸዉና ፍቅራቸዉ በጣም ተመቸኝ…….. ግን ብዙ ስራ ስላለብኝ የአንዲን ልደት ሻማ አብርተንና ኬኩን ቆርሰን “መልካንም ልደት” አንዲ ብለን ከዘመርን በኋላ ተለያየን። ጉዞ እነሱ ወደ ቤታቸዉ እኔ ወደ ሙኒክ ሆነ።
ረቡዕ መጋቢት 2 (March 2) ቀን በጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከአዲሶቹ የሙኒክ ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ጉዞ ወደ ኦሎምፒክ መንደር ሆነ። ሙኒክ ኦሎምፒክ ልጅነቴን ይዞ የሚመጣ ብዙ ትዝታ አለዉ። የሜክሲኮዉ ኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ማሞ ወልዴ የመጨረሻዉን የኦሎምፒክ ማራቶን፤ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ የመጀመሪያዉን የኦሎምፒክ ሩጫ የሮጡት ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነዉ። ምሩዕ ይፍጠር ሙኒክ የሄደዉ ለ10ሺና ለ5ሺ ሜትር ዉድድሮች ሲሆን በ10ሺ ሜትር ሦስተኛ ከወጣ በኋላ የ5ሺ ሜትር የመጨረሻዉ ዉድድር ከተጀመረ በኋላ በመድረሱ ያሸንፋል ተብሎ በጉጉት ይጠበቅ በነበረዉ ዉድድር ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ሙኒክ ኦሎምፒክ አሳዛኝ ታሪክም አለዉ። ጨለማዉ መስከረም (Black September) በመባል የሚታወቀዉ የፍልስጥኤማዉያን አክራሪ ቡድን ኦሎምፒክ መንደር ዉስጥ አሸምቆ ገብቶ በእስራኤል አትሌቶች ላይ አደጋ ያደረሰዉ በዚሁ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1964 ዓም በተካሄደዉ ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነበር። በነገራችን ላይ ሙኒክ ኦሎምፒክ የተካሄደዉ ጥቁር አሜሪካዊዉ ጆዜ ኦዉንስ በርሊን ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያዎች አሸንፎ የናዚ ሂትለር መሪዎች ጥቁር ስለሆንክ ከኛ እጅ ሜዳሊያ አትቀበልም ካሉት ከ36 አመታት በኋላ ነበር።
ሙኒክ ዉስጥ በመጨረሻ የጎበኘሁት ከከተማዋ 19 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘዉንና በ1944 ዓም የተሰራዉን የዳሁ ናዚ ማጎሪያ (Concentration Camp) ነበር። ዳሁን ጎብኝቶ ለመጨረስ ወደ ሦስት ሰአት አካባቢ ፈጅቶብኛል። እነዚህ ሦስት ሰአቶች ወደፊትም ወደኋላም እየወሰዱኝ ዳሁ የጭካኔና የእልቂት ቦታ የመሆኗን ያክል የይቅርታና የመማማሪያ ቦታም እንደሆነ አሳይተዉኛል። ዳሁ ለሰዉ ልጅ ቁስሉም መድኃኒቱም ሰዉ መሆኑ የታየበትና የሰዉ ልጆች ጭካኔ መድረስ የሚችልበት የመጨረሻዉ ከፍታ ላይ የደረሰበት ቦታ ነዉ። ዳሁ አሁንም ድረስ ሲያዩት ጣረ ሞትን የሚጣራ የጨለማና የብርህን፤ የሞትና የህይወት፤ የጭካኔና የምህረት ቦታ ነዉ። ዳሁ የናዚ ግፍና ጭካኔ እማኝ ነዉ። ዳሁ የዘግናኝ ታሪክ ቅርፊት፡ የብሩህ ዘመን ትዉፊት፥ ቂምና ጥላቻን አብናኝ ይቅር ብሎ ይቅርታ ለማኝ ቦታ ነዉ። ዳሁ አይዋሽም . . . እንኳን ሊዋሽ  ጭራሽ ዉሸት የሚባል አያዉቅም። ዳሁ ከአንዱ ክፍል ወጥተን ወደ ሌላዉ ክፍል በገባን ቁጥር የሚነግረን እዉነት ግን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ያሰኛል። ያቆስላል፤ ያደማል፤ ልብ ይሰብራል፤ ሆድ ይቆርጣል። እስረኞች ከመኝታ ቤታቸዉ እየተነዱ ገላችሁን ስለምትታጠቡ ልብሳችሁን አዉልቁ ተብለዉ ወደ ሌላ ክፍል ይወሰዳሉ። የሚቀጥለዉ ክፍል ዉስጥ የሚጠብቃቸዉ የመታጠቢያ ገንዳ ሳይሆን የመርዝ ጋዝ ገንዳ ነዉ። እስረኞቹ በመርዝ ጋዝ ከተገደሉ በኋላ እሬሳቸዉ ወደሚቀጥለዉ ክፍል ይወሰድና አገር የሚያክል ምድጃ ዉስጥ እየተጣለ ይቃጠላል። ይህ ግፍና ጭካኔ የተፈፀመዉ በሰዉ ልጆች ላይ ነዉ፤ ይህንን ግፍና ጭካኔ የፈፀሙትም የሰዉ ልጆች ናቸዉ። ጀርመንና ፖላንድ ዉስጥ ስላሉ የናዚ ጀርመን ማጎሪያ ካምፖች ከሰማሁ ቆይቷል። ይህንን በተለያዩ መጽሐፍት ላይ ያነበብኩትን ታሪክ ታሪኩ የተፈጸመበት ቦታ ላይ ቆሜ ስመለከት ግን አእምሮዬ ማሰብ አቆመና በድን ሆኜ ቀረሁ። ሁለት እጆቼን ዘርግቼ አማተብኩና . . . . . እንዲህ አይነት ክፉ ጭካኔ ዬትም ቦታ መደገም የለበትም ብዬ የዳሁ ጉብኝቴን ጨረስኩ።
ጀርመን፥ ኦስትሪያ፥ ሲዊዘርላንድና ዳሁ ስለ አሁኗና ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በየራሳቸዉ መንገድ የሚነግሩን ብዙ ነገር አለ። ዳሁ በሚባለዉ የናዚ ሂትለር ማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ የተፈጸመዉን ግፍና ጭካኔ የፈጸሙት እኛን የመሰሉ የሰዉ ልጆች ናቸዉ እንጂ ከጥልቅ ባህር ዉስጥ የወጣ ዲያብሎስ አይደለም። ጀርመን፥ ኦስትሪያና አራት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሲዊዘርላንድ ድንበር፤ ቋንቋ፤ባህልና ሐይማኖት ሳያግዳቸዉ ከአንዱ አገር ወደ ሌላዉ እንዳሰኛቸዉ እየተዘዋወሩ በኤኮኖሚ ተሳስረዉ በሰላም የሚኖሩት አርቆ አስተዋይ መሪዎቻቸዉ በወሰዱት መልካም እርምጃ ነዉ እንጂ እግዚአብሄር ከሰማይ ወርዶ የልዩነት ግድግዳቸዉን አፍርሶላቸዉ አይደለም። ክፉዉም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ፥ መልካሙም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ምርጫችን ምንድነው? አዉሮፓ ዉስጥ ሰዉ ከአባቱ ገዳይ ጋር ተስማምቶ ሲኖር እያየን እኛ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር በሠላም ጎን ለጎን መኖር ለምን አቃተን? አዉሮፓዉያን በየአገሮቻቸዉ መካክል ያለዉን ድንበር አፍርሰዉ በአንድ ገንዘብ ሲገበያዩ እኛ በአንድ አገር ዉስጥ ለዘመናት አብሮ በኖረ ህዝብ መካከል አጥር የምንሰራዉ ለምንድነዉ?
ሙኒክ ከመሄዴ በፊት አሜሪካ ሜሪላንድ ዉስጥ አንድ ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። እዚህ ስብሰባ ላይ የእምነት አባቶች፤ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች፤ አባቶች፤ እናቶችና ወጣቶች ተገኝተዉ ነበር። የሁሉም ፍላጎት አንድ፤ አንድና አንድ ብቻ ነበር። እሱም ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። አዉሮፓ መጥቼ ጀርመንና ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ስገናኝ የተሰማኝ ስሜት አሜሪካ ዉስጥ ከተሰማኝ ስሜት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩበት የአለም አካባቢ ሁሉ ፍላጎታቸዉ ፍትህ፥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉ። ግን ፍትህና ነጻነትን ስለፈለግናቸዉ ብቻ አናገኛቸዉም። የተናጠል ትግል ደግሞ ተራ በተራ የወያኔ ምሳና ቁርስ ያደርገናል እንጂ ነጻነታችንን አያስገኝልንም።  በእርግጥ ነጻነት ስንደሰትበት ደስታዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ፤ ሆኖም ነጻነታችንን ጠላት እንዳይቀማን የምንጠብቀዉና ከተቀማንም ታግለን የምናስመልሰዉ በጋራ ነዉ። ስለዚህ ጽኑ የሆነዉ የፍትህና የነጻነት ፍላጎታችን ጽናት ባለዉ የጋራ ትግል ካልተደገፈ ያለን አማራጭ እየተረገጥን መኖር ብቻ ነዉ።
ወያኔ የበላይ በሆነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደዳሁ አይነት በሰዉ ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊፈጸም አይችልም የምንል ሰዎች ካለን ወደ ኋላ ዞር ብለን አኝዋክንና ኦጋዴንን ልንመለከት ይገባል። ዛሬ ወያኔ ኦሮሚያ ዉስጥ መብቴ ይከበር ብሎ በጮኸ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚወስደዉ ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ እርምጃም የሚያሳየን ወያኔ የስልጣን ገመዱ ባጠረ ቁጥር የማያደርገዉ ምንም ነገር እንደሌለ ነዉ። የወደፊቷ መልካም ኢትዮጵያ የምትናፍቀን ኢትዮጵያዉያን ከጀርመን፥ ከኦስትሪያ፥ ከሲዊዘርላንድና ከዳሁ የምንማረዉ ጠቃሚ ትምህርት አለ። ዛሬ በማድረግ ወይም ባለማድረግ የምንፈጽማቸዉ ብዙ ስህተቶች አሉ። እነዚህ ስህተቶች የጠላታችንን የወያኔን የሥልጣን ዘመን ማራዘማቸዉ ብቻ ሳይሆን ወያኔ ከተወገደ በኋላም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል። ለምሳሌ ኦሮሚያ ዉስጥ ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት በሌላ አገር የሚካሄድ ይመስል ብዙዎቻችን ከጎን ቆመን ተመልክተናል። ይህ አጉልና የማያዋጣ ቸልተኝነት ነገ በአማራ፤ በሲዳማ፤ በሃዲያና በኮንሶ … ወዘተ አካባቢዎች የሚነሱ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ኦሮሞዉ በቸልተኝነት እንዲመለከት ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ አማራዉ ለኦሮሞ ካልጮኸና ኦሮሞዉ ከአማራዉ ጋር አብሮ ካልታገለ አማራዉ፤ ኦሮሞዉ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ባርነት ነፃ አይወጣም። ወደድንም ጠላን ታሪክ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሲዳማን በወላይታ፤ ጉጂን በጌዲኦ፤ ትግሬን በአማራ፤ አማራን በኦሮሞ . .  ወዘተ አዉድ ዉስጥ ጠቅልሎ አስቀምጦናል። ከዚህ ጥቅልል ዉስጥ በተናጠል አንዱ ብቻዉን ነፃ መሆን አይችልም። ወያኔ ጨፍልቆ የሚረግጠን አንድ ላይ ነዉ፤ ነፃ የምንወጣዉም አንድ ላይ ነዉ። ኢትዮጵያና አንድነቷ አደጋ ላይ ወድቀዋል። ኢትዮጵያዊነት የምንለዉ ክቡር ማንነትም ከፍተኛ አደጋ ላይ ነዉ። እነዚህን ጣምራ አደጋዎች  ማቆም የዚህ ትዉልድ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነዉ። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳሁን የመሰለ የመታሰቢያ ቦታ እንዲኖራት በፍጹም መፍቀድ የለብንም። ይህ እዉን የሚሆነዉ ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን እጅ ለእጅ ተያይዘንና ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከእልቂት አድነን የነገዋን ኢትዮጵያ በፍትህ፤ በነጻትና በዲሞክራሲ መሰረት ላይ መገንባት ከቻልን ብቻ ነዉ። ሌላ ምንም መንገድ የለመልኩም። ቸር ይግጠመን።
አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር – ebini23@yahoo.com

ወልቃይትና ጠገዴ በአጼ ዮሓንስ ዘመንም ትግራይ ውስጥ አልነበሩም ( የሰነድ ማስረጃው ይሄው) Abraham


***************************************************************
ከዚህ በላይ በጻፍኩት ሐተታ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በ አጼ ቴዎድሮስ ዘመን ወልቃይትና ጠገዴ በትግራይ ስር እንዳልነበሩና : ይተዳደሩ የነበሩት በጎንደር በጌምድር ስር መሆኑን በመረጃ አይተናል:: ደሚቀጥለው ከመሻገራችን በፊት ለህሊናዎ ይሄንኑ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ መረጃ ይመልከቱ
( http://library.si.edu/digital-libra…/…/routesabyssinia00cook)
እዚህ ሊንክ ላይ ቢጫኑ መጽሓፉን በነጻ ያገኙታል( ጽሁፉን በጉልህ ለማንበብ Control + ይጫኑ) :: ከገጽ 188 ጀምሮ በማያሻማ ሁኔታ እንደተጻፈው ዋልድባ : ወልቃይት ጠገዴ በቀድሞው በጌምድር ባሁኑ ጎንደር ስር እንደነበሩና የትግራይ ግዛት እንዳልነበሩ ነው::
አሁን ከአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ወደ አጼ ዮሐንስ ዘመን እንጓዝና ወልቃይትና ጠገደ በማን ስር እንደነበሩ እንይ:: በተልይም አሁን ያሉ የትግራይ ብሔርተኞች የሚያነሱት ክርክር
” ወልቃይትና ጠገዴ እንዲሁም የሰሜን ወሎ ግዛቶች :በአጼ ዮሃንስ ዘመን በትግራይ ስር ነበሩ” የሚል ነው::
የኣጼ ዩሓንስ የልጅ ልጅ የሆኑት ራስ መንገሻ ሥዮም በግልጽ ይህ ትክክል አለመሆኑን : የትግራይ ድንበር ተከዜ እንደሆነና ተከዜን ተሻግሮ ያለው ወልቃይት የትግራይ አካል እንዳልነበረ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል::
በአጼ ዮሐንስ ዘመን ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያን ካርታ አንስቶ የሄደው ፈረንሳዊው የካርታ ባለሙያና የዓለሙ የካርታ ድርጅት በ18ኛው ክፍለ ዘመን ያሳተመውም መጽሓፍ የሚያረጋጝጠው ይሄንኑ ነው:: Elis Reclus የተባለው ፈረንሳዊ የካርታ ስራ ና የጂኦግራፊ ባለሙያ The Earth and its Inhabitants : North East Africa በሚለው መጽሃፉ ወልቃይት : ጠገዴ ና ጠገዴ ን በስም እየጠቀሰ የበጌምድር ግዛቶች ( ያሁኑ ጎንደር) እንጂ የትግራይ ግዛቶች እንዳልነበሩ በማያሻማ መልኩ ጽፎታል:: ይህ የካርታ ባለሙያ መጽሓፉን ያሳተመው በኣጼ ዮሓንስ ዘመን ነው:: ኢትዮጵያ ድረስ መጥቶ አጼ ዮሐንስና መኳንቶቻቸውን አናግሮ : ኢትዮጵያን ዞሮና ተመራምሮ ያገኘው የወቅቱን እውነት ነው ያሰፈረው:: መጽሓፉን ለማግኘት ይሄንን ሊንክ ተጭነው ገጽ443 ያንብቡ::
https://play.google.com/store/books/details?id=Y4WbCSAU7kQC
ምናልባት ጎግል አካውንት ከሌላችሁ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሃፉን ማውረድ ይቻላል:: ይህ መጽሓፍ ከተጻፈ ከመቶ ዓመት በላይ ስለሆነው በማይክሮ ፊልም አርካይቭ ውስጥ ገብቷል:: ለማንበብ ካስቸገሮ ኮንትሮል ፕላስ እየተጫኑ ከገጽ 443 ጀምሮ ያለውን ያንብቡ
https://archive.org/stream/cihm_40198#page/n568/mode/1up
ይህም ካልተቻለ ከዢህ ጽሁፍ በታች ( ኮሜንት ላይ) ገጹን ስለለጠፍኩት ማየት ይቻላል::
እነ ዶክተር ገላውዴዎስ ” ወልቃይት ከጥንት ጀምሮ በትግራይ ስር አልነበረችም የሚለው ያታሪክ መሰረት የለውም :: ስህተት ነው:: … እነዚህ ሰዎች ከጀርባቸው ሌላ አካል አለ:: ” በማለት ያለተጻፈ የሚያነቡት ከየት አምጥተው ይሆን? ዘረኝነት ይሄን ያህል ሰውን ያሳውራል?
ይቀጥላል

Netsanet Beqalu's photo.

ወያኔ መሞቻውን፤ ­­­­እኛ መሰንበቻውን

ይገረም አለሙ
እኔ ከምኑም የለሁበት ተቀዋሚም ደጋፊም አይደለሁም  በሚል ጭንብል ተሸፍኖ የሚኖረው ክፍል ሲቀር ሌላው በሁለቱ ጎራ ይመደባል፡፡ በወያኔ ጎራ ያለው ወገን ለአባልነትም ይሁን ለደጋፊነት ያበቃው ምክንያት ምንም ይሁን ባለው አቅም  በሚችለው መንገድ የወያኔን  ዕድሜ ለማራዘም ያስችላል ብሎ ያመነበትን ይሰራል፡፡ እንደውም አንዳንዱ ያለ ወያኔ መኖር አንደማይቸል ራሱን አሳምኖ ሞቴን ከወያኔ ጋራ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በዚህ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሆነ ብለው አቅድው ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ናፍቀው የወያኔን እድሜ በሚያሳጥር ተግባር ላይ አይሰማሩም፡፡ የውስጥ አርበኞች ካልሆኑ በስተቀር፡፡
በአንጻሩ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ለተቀዋሚነት የበቃበት ምክንያትና አንዴትነት የመለያየቱን ያህል ተግባሩም የዛኑ ያህል የተለያየ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ መቋሰል መጓተቱን፤መወነጃጀል ጣት መቀሳሰሩን ወደ ጎን አስቀምጦ  አንድ ወጥ በሆነ መንገድ ለወያኔ እድሜ ማጠር መስራት አልቻለም፡፡  ይህም በመሆኑ ወያኔ በጥንካሬው ሳይሆን በድክመቱ፣ በእውኑ ሳይሆን በሙቱ ሲገዛ ኖሯል፣. አሁንም እየገዛ ነው ምን አልባትም ወደፊትም! ( መበስበሳቸውን ከነገሩን በኋላ በእኛ ድክመት ህይወት ዘርተው ስንት አመት ገዙን ?)
ከወያኔ ጎራ የተሰለፉት ሥልጣን ሽተውም ይሁን በዘር ተስበው፤ስኳር ልሰውም ይሁን መሬት ብናገኝ ብለው፤አያያዙን አይተህ ወደሚያደላው ብለው መስሎ ተመሳስሎ መኖርን መርጠውም ይሁን ብቻ ባሉበት በተሰለፉበት ለወያኔ ይበጃል ያሉትን በተናጠልም ይሁን በመተባበር ሲሰሩ አኛ ለተያያዝነው ትግል ይበጃል የምንለውን ምን ሰራን ብለን ራሳችንን ከመጠየቅ ይልቅ እነሱ ማውገዙ በእጅጉ የቀለናል፡፡ ዓላማው ምንም ይሁን ምን ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመስለው ተባብሮ በራሱም ተጠናክሮ በጽናት የሚሰራ ይደነቃል፡፡ ዓላማየ የሚለውን ያውም በቃል ሲነገር የተቀደሰ አላማ ያንን ተግባራዊ ለማድረግ የማይጣጣር  የማይተባበር መወገዝ መወቀስ ካለበት እርሱ ነው፡፡
የተቃውሞው ጎራ ዥንጉርጉርነት በራሱ አልሞ አቅዶና ታግሎ ውጤት ማምጣት አይደለም ጊዜ የሚፈጥራቸውን አጋጣሚዎች ለመጠቀም እንኳን  የማይችል አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ወያኔ ለሥልጣኔ ማቆያ ይበጃኛል እያለ በሚፈጽመው ኢ- ሰብአዊ ኢ- ህጋዊና  ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ በሆነ ተግባሩ በየግዜው ከህዝብ እየተጣላ መሞቻውን ሲያፋጥን በአንጻሩ ተቀዋሚው መሰንበቻውን ያመቻችለታል፡፡ ( የወያኔን ዕድሜ የሚያራዝም ተግባር ይፈጽማል፡፡)

እንደ ተቀዋሚ ድርጅቶቹ ብዛት  እንደ መሪዎቹ ማንነት ለታቃውሞ የተነሱበት ዓላማና ምክንያት ይለያያል፡፡ ነገር ግን በወርቃማ ቃላት የተሸፈነ ድብቅ አጀንዳ እስከሌለ ድረስ የወያኔን አንባገነናዊ አገዛዝ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገድና ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ማድረግ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ነው፡፡ ( በድርጅት ደረጃ ከዚህ የተለየ የተጻፈና በአደባባይ የሚናገሩት ዓላማና ግብ የነበራቸው እድሜ አስተምሮአቸው መከራ መክሮአቸው  ተመልሰዋል፡፡)

በመሆኑም አደረጃጀታቸው ቢለያይ፤ የመረጡት የትግል ስልት ሊዛመድ የማይችል ቢሆን ከላይ በተጠቀሰው ግብ ተስማምተው  ቢችሉ ተባብረው ካልሆነም ሁሉም በየራሱ የትግል ስልትና መንገድ ወደ ግቡ መጓዝ አንጂ አንዱ የሌላኛው እንቅፋት ሲብስም ጠላት ሆኖ መሰለፍ ፍቺ ያጣ አንቆቅልሽ ነው፡፡ ይህ አንቆቅልሽ የሆነ ተግባር ነው እንግዲህ ወያኔ መቃብሩን ሲቆፍር ተቀዋሚዎች እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት እንዲሆኑት ያደረገው፡፡እናም ወያኔ መሞቻውን እኛ መሰንበቻውን እንሰራለን ለማለት ያበቃኝ፡፤
ብዙ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ  ወቅታዊውን ሁኔታ እንመልከት፡፡ ከሁለት አመት በፊት ተቃውሞ አስነስቶ የብዙ ወጣቶችን የህይወት መስዋእትነት አስከፍሎ ለብዙ ወጣቶችም እስር እንግልትና ስደት ምክንያት ሆኖ ተግባራዊነቱ የቆመውን የኦሮምያና የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎች የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ አናደርገዋለን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትንም ልክ እናስገባቸዋለን ብሎ ለህዝብ  ያላቸውን ንቀት ባሳየ መልኩ መናገር እድሜ ማሳጠሪያ እንጂ ማራዘሚያ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ወያኔ ሞቱን የጠራበት የአቶ አባይ ጸሀየ ንግግር ግን ለፖለቲከኞቹ የተገለጠላቸው ህዝቡ ለተቃውሞ አደባባ ወጥቶ በጥይት መውደቅ  ከጀመረ በኋላ ነው፡፡
በኦሮምያ በአብዛኛዎቹ ዞኖች የታየው ግድያ፤ የግፍ ደብደባና የገፍ እስራት የተጠቀመበት አልተገኘም እንጂ ወያኔ መሞቻውን ያመቻቸበት ነበር፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ ሕዝብን ጋኔን፣ ሰይጣን ጠንቋይ በማለት የተናገሩትም ሆነ የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንቱ  አቶ ሙክታር ከደር  የወያኔው ገዳይ ቡድን በኦሮምያ ክልል ተሰማርቶ የፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ሁሉ ተገቢና ትክክል እንደነበረ ገልጸው ይህን በማድረጋችሁ ትመሰገናላችሁ በማለት በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ያስተላለፉት አድናቆትና ምስጋና ለወያኔ መሞቻው አንጂ መሰንበቻው ሊሆን የሚችል አልነበረም፡፡ አንዲህ አይነት ግራ ገብ ነገር ሲገጥማቸው ሟች ሞልቶ ነበር ገዳይ ጠፋ እንጂ ነው የሚሉት አበው፡፡

የሱዳኖችን መሬት ድንበር አልፈው ሄደው የያዙ ሽፍቶች በማለት የሀገሩን ዜጎች ከመወንጀል አልፎ  የኢትዮጵያን መሬት የሱዳን ነው በማለት በአደባባይ ለመመስከር የተበቃው ከማን አለብኝነት ንቀት በመነጨ ቢሆንም ይህ ሞቱን ሊያፋጥኑ ከሚችሉ በርካታ ተግባሮቹ አንዱ የሆነው ድርጊት ያደረሰበት ነገር አለመኖሩ ሲታይ በርግጥም የናቀን አይቶ ገምቶ ነው ያሰኛል፡፡ ያስናቁን ደግሞ በመግለጫ እንጂ በተግባር የማይታዮ ቁጥረ ብዙ ድርጅቶች ናቸው፡፡
በሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ ፈንድቶ የወጣ ቁጣ በሚታይበት ወቅት አዲስ አበባ ዝም በማለቱ ለአመታት ተግባራዊ ያላደረጉትን የመንገድ ሥነ- ሥርዓት ህግ ተግባራዊ እንደርጋለን ብለው የታክሲ ሾፌሮችን ለስራ ማቆም አድማ የዳረጉበትን ድርጊት ማንም ጤነኛ የወያኔ አባልና ደጋፊ ለእድሜ ማራዘሚያ የተደረገ ነው ሊለው አይችልም፡፡ ዝም ያለውን ለመቆስቆስና ተቃውሞውን አዲስ አበባ ላይም ለማቀጣጠል  የውስጥ አርበኞች የፈጸሙት ነው ከተባለ ሊያስማማን ይችላል፡፡ ነገር ግን በማንም ተፈጸመ በማን ከሌሎች ድርጊቶች ጋር ተደማምሮ  የወያኔን መሞቻ ሊያፋጥን የሚችል ድርጊት ነበር፡፡ በነበር ቀረ እንጂ፡፡
በሀገር ውስጥ ያሉትም ሆኑ በወጪ የሚገኙት ፖለቲከኞች እነዚህና ሌሎች በርካታ  ወያኔ ራሱ የፈጸማቸውን ሞቱን የሚያፋጥኑ ድርጊቶች  ሊያነሳሱዋቸውና ሊያስተባብሩዋቸው ቀርቶ እንደ ዓላማና አደረጃጀታቸው በየራሳቸው መንገድ    ተንቀሳቅሰው ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር ያደረጉት ነገር ባለመኖሩ እሱ ሞቱን ቢያፋጥነውም እነርሱ እስትንፋስ ሰጥተውት መሰንበት ችሏል፡፡ መሰንበቱን ሲያረጋግጥ ደግሞ  ይቅርታ የሚባል የእድሜ ማረዘሚያ መድሀኒት ራሱ ለራሱ አዞ እየወሰደ ይገኛል፡፡ ይህን ተከትሎም አንዳንዶቹ ፖለቲከኞች በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የታያቸው ባይታወቅም ይቅርታ በተባለው እንክብል ወያኔ ሙሉ ፈውስ አግኝቶ ከደደቢት እምነቱ ይለወጣል ብለው ተስፋ እያደረጉ ነው፡፡
ወያኔ ከላይ ለአብነት የተጠቀሱትን ጨምሮ ለሀያ አምስት አመታት በቃልም በተግባርም መሞቻውን የሚያፋጥኑ ድርጊቶች ፈጽሟል፡፡በአንጻሩ ወያኔን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት ነው የምንታገለው የሚሉ ፖለቲከኞች ሀያ አምስት አመት ሙሉ ፓርቲ ሲያፈርሱ ሲገነቡ፤ አንደ አሜባ ራሳቸውን ሲያባዙ፤ርስ በርስ ሲወነጃጀሉ የጎንዮሽ ሲታገሉ ወያኔን ታግለው የሚያሸንፉ አይደለም ራሱ መቃብሩን እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን ገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ ባለመሆናቸው ወያኔ ነበረ አለ  እስከ መቼ አንደሆነ ባይታወቅም ይኖራል፡፡ አሳዛኝ አሳፋሪ!

ኢትዮጵያ ወዴት ነው የምትሄደው እና የማትሄደው? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን  ከተማ  (ዋሺንንግቶን ድሲ ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው፡፡)

“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡Quo Vadis Ethiopia: Where Are You (not) Going?
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከወራት በፊት በዚህ ጉባኤ ላይ እንድገኝ እና እንድሳተፍ ጥሪ ባቀረበልኝ ጊዜ ኢትዮጵያን ገጥመዋት ባሉት መሰረተ ሰፊ የተሳትፎ መድረክ፣ ውይይት እና ክርክር ጉዳዮች ሀሳብ እጅግ በጣም ነበር የተደሰትኩት፡፡ የቪዥን ኢትዮጵያን አርዓያ በመከተል ሌሎችም እንደዘሁ በርካታ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው እና የቪዥን ኢትዮጵያ አስተባባሪዎች በሙሉ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት እና ጉባኤው በስኬታማነት በመካሄዱ ያለኝን አድናቆት እና ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ ስለኢትዮጵያ እና ስለኢትዮጵያ ሕዝብ ያገባናል በማለት ይህ ጉባኤ ስኬታማ እንዲሆን የየበኩላችሁን ጥረት ላደረጋችሁ ወገኖቼ ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ ያለጥረት ለውጥ አይመጣምና፡፡
እንደዚሁም ሁሉ ይህ ጉባኤ ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆን ሰፊ ሽፋን በመስጠት ሲዘግብ ለነበረው ለኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ከንቱ ፕሮፓጋንዳ ተዳክሞ በነበረበት በዚያ አስከፊ ወቅት ከስድስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 ኢሳት አማራጭ የዜና፣ የመረጃ፣ የትንታኔ እና የመዝናኛ ምንጭ በመሆን ለኢትዮጵያውያን ወገኖቹ አዲስ ክስተት በመፍጠር ከሕዋ በመብረቃዊ ኃይል አለሁላችሁ በማለት ከተፍ አለ፡፡
የኢሳት የአማካሪ ኮሚቴ የመጀመሪያው ሊቀመንበር ሆኘ አገልግያለሁ፡፡ የተለያዩ የሙያ ስብጥር ካላቸው ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መስራት እጅግ በጣም የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡
በጨለማው ጎን በኩል ያሉት እና ስልጣናቸውን በፍርሀት፣ በቁጣ፣ በጥላቻ፣ በበቀል እና የኃይል እርምጃን በመውሰድ ለማቆየት የሚፈልጉ ኃይሎች የኢሳትን ስርጭት ለማቋረጥ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ቀጥለውበት እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ኢሳት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ተጋርዶ የሚገኘውን የጨለማ መጋረጃ የብርሀን እጀታ ባለው ጎራዴው እየበጠሰ እና እየበጣጠሰ ብሩህ ብርሀን ማሳየቱን ቀጥሎበት ይገኛል፡፡
የአምባገነኖች ዋና የጥፋት መሳሪያቸው ሚስጥራዊነት ነው፡፡
አምባገነኖችን ለማጥፋት የተሻለው መሳሪያ ደግሞ ነጻ ሜዲያ ነው፡፡
ለአምባገነኖች የተሻለው የጦርነት ሜዳ ዕቅድ እስከ ጥርስ ድረስ የእውነታን ዝናር ታጥቆ  እራቁታቸውን በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው በሚገኙት ጨቋኞች የተጠያቂነት ጨለማ ላይ አንጸባራቂ ብርሀን ማብራት ነው፡፡
ምንም ዓይነት ራዕይ በሌላቸው ጨቋኞች ጨለማ ላይ አንጸባራቂ ብርሀናችሁን በማብራታችሁ ኢሳትን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ  መረጃ በማቅረብ እና ሰፊውን ሕዝብ በማስተማር እያደረጋችሁ ላላችሁት ከፍተኛ ጥረት ኢሳቶችን በጣም አመሰግናለሁ፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ በመገኘት ምሁራዊ ክህሎት የታከለበት እና ቀስቃሽ የሆነ ጽሑፍ ላቀረባችሁ ወገኖቼ በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ካቀረባችኋቸው ምልከታዎች እና ዘርፈ ብዙ አመለካከቶች እና ሀሳቦች በርካታ ፍሬ ነገሮችን ተምሪያለሁ፡፡
በዚህ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በጉባኤው በመገኘት ተሳትፎ ያደረጋችሁትን ወገኖቼን በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ላቀረባችኋቸው ጠንካራ ጥያቄዎች እና ልዩ ምልከታ ለተንጸባረቀባቸው አስተያየቶቻችሁ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ የእናንተ ተሳትፎ ይህንን ጉባኤ በእጅጉ ፍሪያማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት ሁሉ አሁን በህይወይት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ አማጺዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ እንዲከፈት በማዘዝ በወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ እልቂት እንዲፈጠር ካደረገ በኋላ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ትግል ውስጥ ገብቻለሁ፡፡ በዚያ አሰቃቂ እልቂት ላይ 193 ንጹሀን ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአነጣጣሪ አልሞ ተኳሽ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በአደባባይ በየመንገዶች ላይ በግፍ የተገደሉ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ከ30 ሺ በላይ የሚሆኑ ንጹሀን ዜጎች ደግሞ ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡ እነዚህን መጠነ ሰፊ የተንሰራፉ የሰው እልቂት እና መብት ድፍጠጣ ኢሰብአዊ ወንጀሎችን የፈጸሙት 237 የፖሊስ ነፍሰ  ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ ያለምንም ተጠያቂነት ደረታቸውን ገልብጠው በየአውራ መንገዶች በነጻነት በመንገዳወል ላይ ይገኛሉ፡፡
ያ አሰቃቂ እልቂት በአሁኑ ጊዜም ቀጥሎ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ብዙሀኑን ሕዝብ በቁጥጥር ስር ማዋል እና በዜጎች ላይ ስቃዮችን መፈጸም በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎ ይገኛል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ በአምባገነኑ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) በኦሮሚያ ክልል በ270 ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ አሰቃቃ እልቂት ተፈጽሟል፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩት ወገኖቻችን ደግሞ በዘ-ህወሀት ድብቅ እና በሚታወቁ የማጎሪያ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የተገደሉትን እና በእስር ቤት ውስጥ በመሰቃየት ላይ የሚገኙትን ወገኖቻችንን ሌላ ማንም ሳይሆን እራሱ ዘ-ህወሀት ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ እነርሱ ግልፅነት የሚባል ነገርን በፍጹም አያውቁም፡፡ እነርሱ የሚያውቁት እና የተካኑበት ነገር ቢኖር መግደል እና በማጎሪያው እስር ቤት በጅምላ እና በተናጠል ዘብጥያ ማውረድን ነው፡፡
በኦሮሚያ ላይ እየተካሄደ ላለው የሕዝብ ቁጣ ዘ-ህወሀትን በመቃወም ከሕዝቡ ጎን አብሮ መሰለፍ ያለመቻል እና ተጨባጭነት ያለው ወገናዊ ድጋፍ ያለማሳየት አሳፋሪ እና በእራሱ የሞራል ስብዕና ኪሳራ ውጤት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞ ወገኖቻችን እየደሙ፣ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ እና በስውር እየታፈኑ ደብዛቸው እንዲጠፋ እየተደረጉ ባሉበት ሁኔታ ሌሎቻችን በዝምታ የምንመለከተው ከቶ ለምንድን ነው? እኮ ለምን?
የእራሴን ምልከታ ከማቅረቤ በፊት እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በአምባገነኑ መለስ በግፍ ላለቁት 193 ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች፣ ሌሎች ዘ-ህወሀት እልቂት ለፈጸመባቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች እና ምንም ዓይነት አጣሪ ኮሚሽን ሳይቋቋም ከይስሙላው የቅርጫ ምርጫ በፊት እና የማጣራት ስራ ከተሰራም በኋላ ምንም ዓይነት ፍትህ ሳያገኙ ደማቸው እንደ ውሻ ደም ተቆጥሮ ደመ ከልብ ሆኖ ለቀረው ወገኖቻችን፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በዘ-ህወሀት መጠነ ሰፊ የማን አለብኝነት የጭካኔ የኃይል እርምጃ በመውሰድ እልቂት ለፈጸሙባቸው 270 በመረጃ ተረጋግጦ ለተያዙ የእልቂት ሰለባዎች እና በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የፖለቲካ እስረኞች እያደረግሁት ላለው እልህ አስጨራሽ ትግል ከጎኔ ተሰልፋችሁ የበኩላችሁን ወገናዊ ግዳጃችሁን እንዲትወጡ እንድትቀላቀሉኝ በአጽንኦ እጠይቃለሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኢፍትሀዊነት በሆነ መልኩ በእብሪተኛው ዘ-ህወሀት ማን አለብኝነት በግፍ ታስረው በመማቀቅ ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን ለአንድ አፍታ እንድናስታውሳቸው ለማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ እነዚህም ብርቅየዬ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ጀግኖች በርካታ ናቸው፡፡ ሁሉንም ዘርዝሮ ለማቅረብ የሚቻል አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን እስቲ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እናስታውስ፡፡
እስክንድር ነጋን፣ አንዷለም አራጌን፣ በቀለ ገርባን፣ አህመድ ጀቤልን፣ አበበ ቀስቶን፣ እማዋይሽ ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን እና በርካታዎቹን ሌሎችንም እናስታውስ፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ወዴት እየሄድች ነው/quo vadis ?
ይህንን ጥያቄ በጥያቄ ለመመለስ የበለጠ ግልጽ በሆነ መልኩ በጥያቄው በእራሱ ላይ ጥያቄ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
“ኢትዮጵያ ወዴት ነው የምትሄደው?” ማለት እራሱ ምን ማለት ነው?
ለብዙ ሰዎች ይህ ጥያቄ ቀጥተኛ እና መልሱም ቀጥተኛ መስሎ ሊታያቸው እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህ ጥያቄ ለእኔ አእምሮን የሚበጠብጥ ውስብስብ ጥያቄ እና ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው መልሶች ያሉት ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡
በዘመናዊ ቋንቋ አጠቃቀም ኮአ ቫዲስ የሚለው ሀረግ ሮም ውስጥ በኔሮ ኬሳር በመስቀል መከንቸሩን በመፍራት በተሰደደበት ጊዜ ለደቀመዝሙር መላዕክ ቅዱስ ጴጥሮስ ወዴት እየሄድክ ነው የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር፡፡ ጴጥሮስም በሮም መውጫ አካባቢ እየሱስን አገኘው እና “ወዴት እየሄድክ ነው ብሎ ጠየቀው?” እየሱስም እንዲህ በማለት መለሰለት፣ “እንደገና በመስቀል ለመከንቸር ወደ ሮም እየሄድኩ ነው“
በተሰጠው መልስ በመደነቅ ጴጥሮስ ወደ ሮም ተመልሶ በመሄድ ስራውን ለመቀጠል እና በመስቀል ተዘቅዝቆ ለመሰቀል ወሰነ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ያንን በዓል ለምታከብሩት ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ፡፡
እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ አዲስ አበባ በነበርኩበት ጊዜ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያንን የላቲን ሀረግ (ኩአ ቫዲስ የሚለውን) ያወቅሁትና የተጠቀምኩበት ፡፡
ከአራት አስርት ዓመታት በፊት በአንድ በታወቀ በየወሩ በሚታተም የእንግሊዝኛ መጽሔት (?) እ.ኤ.አ በ1968-69 አዲስ አበባ ውስጥ አሁን ስሙን በማላስታውሰው እና ያለው ትውስታየ ትክክል ከሆነ “በእኔ እኩያ ያሉት ወጣቶች የዘመኑን የኑሮ ሁኔታ ያልተከተለ የአኗኗር ዘይቤ” በሚል ርዕስ እኔ የማምንበትን የላቲን ሀረግ ያለው ጥያቄ በመጠቀም አንድ ጽሑፍ አውጥቸ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የነበረውን አስቀያሚ ሁኔታ በመገንዘብ ወጣቶች ወዴት እየሄዱ ነው የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነበር፡፡
ከግማሽ ምዕተ ዓመት አካባቢ በኋላ እንደገና እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ አቀርባለሁ፣ “ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች ነው/Quo vadis, Ethiopia?“ እንዲህ የሚል ሌላ ጥያቄም ለመጨመር እወዳለሁ፣ “ኢትዮጵያ ወዴት ነው የማትሄደው?“
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንግዳ እና አስቂኝ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡
ከብዙ ዓመታት በፊት በወቅቱ ከነበሩት ለእኔ ጓደኞች ያቀረብኩትን ጥያቄ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ያንኑ ጥያቄ አሁን ላሉት ወጣቶች ማቅረብ ለእኔ እንግዳ እና አስቂኝ ነገር ነው፡፡
ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እድሜው ከ35 ዓመት በታች ነው ይባላል፡፡
ስለሆነም ጥያቄውን የበለጠ ግልጽ በማድረግ የመጀመሪያ ጥያቄ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ወዴት እየሄዱ ነው?” በሚል መልኩ ተቃኝቶ መቅረብ አለበት፡፡
ደረቁን እውነታ በመግለጽ የእኔን የጉማሬ ትውልድ ለማግለል ሙከራ እያደረግሁ አይደለም፡፡
ወጣቶች ወዴት እንደሚሄዱ እየጠየቅሁ ባለሁበት ጊዜ ለአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ እንዲህ የሚለውን አንድ የአፍሪካ ስለጉዞ ብልህ  ማስጠንቀቂያ አባባል  በማስመልከት የሰጠውን በማስጠንቀቂያነት ለማቅረብ እገደዳለሁ፣ “ወዴት እንደምትሄድ የማታውቅ ከሆነ ማንኛውም መንገድ ወደዚያው ይወስድሀል፡፡“
ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደመረጡት መድረሻቸው ለመጓዝ ከፈለጉ የሚመሩበት ዋና ዕቅድ (የመንገድ ጉዞ  ካርታ) ያስፈለጋቸዋል፡፡
ሌሎች ደግሞ እንዲህ ይላሉ፣ “ሁሉም መንገዶች ወደ ሮም ያመራሉ፡፡“
የሮም ግዛት እጅግ በጣም ሰፊ እና የፖለቲካ ስልጣኑ ከሮም በመውጣት ወደ ሌሎች ንጉሳዊ አገዛዞች ሁሉ የተሰራጨ ነበር፡፡
(እግረ መንገዴን እንዲህ የሚለውን የሙሶሊኒን ቅዠት ገልጨ ማለፍ እፈልጋለሁ፣ “ቤኒቶ ሙሶሊኒ አዲሱን የሮማን ግዛት ለመጀመር እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደውን መንገድ ፈልጎ አገኘ፣ እናም እንዲህ ብሎ በማወጅ ወራሪ ጦሩን ወደዚያው ላከ፣ “መጣሁ፣ አየሁ፣ እናም ድል አደረግሁ፡፡“ የእርሱ ቀደምቶች እ.ኤ.አ በ1896 ተመሳሳይ ድርጊትን በኢትዮጵያ ለመፈጸም ሙከራ አድርገው ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያንን ለሮም ወራሪዎች የሰጡት መልስ  አንዲህ ነበር ፣ “መጡ፣ አዩ፣ ከዚያም አይቀጡ ቅጣት ቀምሰው ጭራቸው ተቆርጦ በፍጥነት ወደ ሮም ተባረሩ ፡፡)
ሆኖም ግን ለኢትዮጵያ ወጣቶች የሚቀርበው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፣ “ሁሉም መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ ይወስዳሉን?“
“ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች ነው?” የሚለው ጥያቄ “ዘ-ህወሀት ወዴት እየሄደ ነው?” ከሚለው አባባል ጋር ተፈጥሯዊ ቁርኝት አለው፡፡
የዘ-ህወሀት የሙስና ግዛት መስራች ጌቶች ሙሶሊኒ እንዳደረገው ሁሉ አንድ ዓይነት አመለካከት አላቸው፡፡ ከጫካው ውስጥ እመር ብለው በመውጣት እንዲህ በማለት አወጁ፣ “መጣን፣ አየን፣ እናም ድል አደረግን፡፡“
ኢትዮጵያውያን ለዘ-ህወሀት እንዲህ የሚል ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል፣ “መጣችሁ፣ እልቂትን ፈጸማችሁ፣ ዘረፋችሁ፡፡ አሁን የንሳችሁን አይቀጡ ቅጣት ቀምሳችሁ ተመልሳችሁ ወደ ጫካችሁ የለደዳቺሁት ዱር ትሄዳላችሁ፡፡“ (ዱርዬዎች አልኩ አንዴ?)
ወጣቶችን ተከተሉ፣
ኢትዮጵያ ወዴት እንደምትሄድ ፈልጎ ለማግኘት ወጣቶችን ተከተሉ እላለሁ፡፡
ስለሆነም ጥያቄው እንደገና ተሻሽሎ እንዲህ በማለት ቀርቧል፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ኢትዮጵያን ፈልገው ለማግኘት እየተመለከቱ ነውን?“
አልበርት ኤንስታይን በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “አንድን ችግር ለመፍታት የአንድ ሰዓት ጊዜ የሚኖረኘ ከሆነ 55ቱን ደቂቃዎች በችግሩ ዙሪያ ላይ በማሰብ አጠፋዋለሁ፣ እናም አምስቷን ደቂቃ ደግሞ ለመፍትሄው አውላታለሁ፡፡“
ኤንስታይን ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሀሳባዊነት ከእውቀት የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ እውቀት ለሁሉም ውሱን ከመሆኑ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ሀሳባዊነት ዓለምን በሙሉ አቅፎ ይዟል፣ እናም ሁሉም ለማወቅ እና ለመገንዘብ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡“
ይህንን አባባል የበለጠ ግልጽ በማድረግ ጆርጅ በርናርድ ሻው እንዲህ ብለው ነበር፣ “ ነገሮችን ታያላችሁ እናም “ለምን” ትላላችሁ፡፡ እኔ ግን እንዲህ የሚሉትን እና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ነገሮችን አልማለሁ፣ “    “ለምን አይሆንም?“ እላለሁ፡፡
እንግዲህ እኔ እየተናገርኩለት ያለው ስለዚያ ዓይነት ሀሳባዊነት ዓይነት ጉዳይ ነው፡፡
ሁሉንም የኢትዮጵያ ችግሮች ለመፍታት 20 ደቂቃዎችን ተሰጥቼ ነበር፡፡ ስለሆነም 17ቱን ደቂቃዎች ስለችግሮች ማሰቢያነት ከእናንተ ጋር እጠቀማለሁ ፡፡ ቀሪዎችን 3 ደቂቃዎች ስለመፍትሄዎች ጠቃሚነት የማውላቸው ይሆናል፡፡
የአፍሪካን አባባሎች፣ የኤንስታይንን የትኩረት ማሰብ እና የሀሳባዊ የፈጠራ እሳቤን መንታ ሀሳቦች እና ሁሉም መንገዶች ወደ ሮም ይወስዳሉ የሚሉትን አራቱን አባባሎች በአንድ ላይ በመቀመር አራት ድሮችን ማድራት እችላለሁ፡፡
ለጉባኤው ዋና አስተባባሪ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው “ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች ነው?” የሚለው ነው፡፡
ይህ ጥያቄ በጣም ጠቃሚ ጥያቄ ነው ምክንያቱም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ ያለ ጉዳይ ነውና፡፡
ከጥያቄው ጋር ለተወሰነ ጊዜ ግብግብ/ልፊያ አድርጊያለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 በዋናው ካርታ ላይ ያለው የዴሞክራሲ ድልድይ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2012 ኢትዮጵያ፡ በሕገ መንግስታዊ የዴሞክራሲ ጎዳና ላይ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ጥር 2011 የአፍሪካ ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች ከወደቁ በኋላ በሚል ርዕስ በሳምንታዊ አምድ ላይ ትችት ጽፌ ነበር፡፡
ከዚህም በላይ በዚህ ጥያቄ ላይ በርካታ ትችቶችን ያቀረብኩ ሲሆን አሁን በቅርቡ በዚህ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የዘህወሀት የፍጻሜ ታሪክ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አእምሮ ለዚህ ጥያቄ ከፍት የሆነው ለምንድን ነው? ያንን ጥያቄ ለመጠየቅ በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡
ይህ ጥያቄ የተነሳበት ምክንያት የዘ-ህወሀት ውድቀት መጨረሻው ፍንትው ብሎ ሊታየን በመቻሉ ምክንያት ነውን?
ጥቂቶች ከኢትዮጵያ አድማስ ባሻገር ጥልቅ ጭቆና ያለ መሆኑን ስለሚያዩ እና ሌሎቹ ደግሞ ከዘ-ህወሀት አገዛዝ ዋሻ መጨረሻ የነጻነት ብርህን ፍንጣቂ እየታያቸው እና በኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች ሁሉ ፈጣን በሆነ መልኩ እየተለዋወጡ በመምጣታቸው ምክንያት ነው ሊሆን ይችላልን?
ለእኔ በጥያቄው ውስጥ ያሉት አራት ቃላት የተለያዩ ምላሾችን ይሰጡኛል፡፡
እነዚህን ቃላት በምሰማበት ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ህልቆ መሳፍርት የሌላቸውን  እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎችን እንዳነሳ ያደርጉኛል፡
1ኛ) ኢትዮጵያ ከዘ-ህወሀት ጋር ወዴት እየሄድሽ ነው? (ኢትዮጵያ ከዘ-ህወሀት ጋር ለመገላገል በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡)
2ኛ) ዘ-ህወሀት ከስልጣኑ ከተወገደ በኋላ ኢትዮጵያ ወዴት ታመሪያለሽ?
3ኛ) ኢትዮጵያ ዘ-ህወሀት ከስልጣኑ ከተወገደ በኋላ ስልጣኑን ተረክቦ የሚመራሽ ማን ነው?
4ኛ) ኢትዮጵያ ዘ-ህወሀት ከስልጣኑ ከተወገደ በኋላ ምንም ሳትታወቂ ድብቅ ሆነሽ ትቀጥያለሽን?
5ኛ) ኢትዮጵያ ላለፉት መቶ ዓመታት በጭቆና እና በፈላጭ ቆራጭነት አገዛዝ ስትገዢ እንደኖርሽው ሁሉ አሁንም ወደኋላ በመንሸራተት በዚያው ልትቀጥይ ትችያለሽን?
6ኛ) ኢትዮጵያ ላለፉት 25 ዓመታት ዘ-ህወሀት ሲገዛሽ በቆየበት መንገድ መገዛትሽን በመቀጠል አደገኛ ቅርቃር ውስጥ በመግባት ልትፈነጅ ትችያለሽን?
7ኛ) ኢትዮጵያ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት አዘቅት ውስጥ ልትዘፈቂ ትችያለሽን?
8ኛ) ኢትዮጵያ በመጨረሻው እልህ አስጨራሽ ትግልሽ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉት ወደ ነጻነት ወደሚያመራው ጉዞሽ ልትራመጅ ትችለሽን?
9ኛ) ኢትዮጵያ ወደ እውነት እና እርቀ ሰላም ጉዞ ልትራመጅ ትችያለሽን?
10ኛ) ኢትዮጵያ በእራስሽ ላይ ክልል እየተባለ ከሚጠራው የታጠረ የብረት (የበርት አልኩ አንዴ?) አጥር ሰብረሽ በመውጣት ከጎሳ ፖለቲካ፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከወሮበላ የዘራፊ አገዛዝ እግረ ሙቅ ሰንሰለት በመፈታት ነጻ መሬት ሆነሽ ልትቀጥይ ትችያለሽን?
እነዚህን ጥያቄዎች ማንም ቢሆን ለመመለስ ወይም ደግሞ ለመመለስ ሙከራ ማድረግ እንደማይፈልግ አውቃለሁ፡፡
እኔ እራሴ በእርግጠኝነት እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አልፈልግም፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች በጣም አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ አስፈሪ ጥያቄዎቸ ናቸው፡፡ ውስብስብ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ አእምሮን የሚበጠብጡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች አስቸጋሪ እና ምንም ዓይነት መፍትሄ ሊገኝላቸው የማይመስሉ የሚታዩ ናቸው፡፡ እጅግ በጣም ብሩህነት በሚታያቸው እና መልካም ሀሳብን በሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ላይ ጨለምተኝነትን የሚያላብሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እጅግ ልዩ የሆነ የፈጠራ ክህሎትን፣ ልዩ የሆነ ሀሳባዊነትን እና ልዩ የሆነ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡
ዘ-ህወሀት እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት አድርጎ እንደሚመልስ አውቃለሁ፡፡
ዘ-ህወሀት ከእነርሱ መመሪያ አውጭነት እና አመራር ሰጭነት ውጭ ኢትዮጵያ እንደ ሶሪያ እና ሊቢያ ዓይነት በሆነ መንገድ ላይ ትጓዛለች እያሉ ይነግሩናል፡፡ (ይኸ የእነርሱ የደስታ ምኞት ነው፡፡ ለእነርሱ ቁማር መጫወቻነት ኢትዮጵያን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ እስከመጨረሻው ትጥፋ ብለው ያስባሉ፡፡ (ከእኛ በኋላ የጥፋት ውኃ)፣ ወይም ደግሞ ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት “አህያ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው መሆኑ ነው፡፡ (አህዮች አላኩም ::)
አሁን በህይወት የሌለው እና የዘ-ህወሀት ጭንቅላት እየተባለ የሚጠራው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ እርሱ እንደሚመራት ካልሄደች እንደ ዩጎዝላቪያ ትበታተናለች እያለ ሟርት ያወራ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ለሰባት ሀገር ተበጣጥሳለች፡፡ አምባገነኑ መለስ ለኢትዮጵያ የነበረው ራዕይ ይኸ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት ራዕይ ይኸው ነው፡፡ እነርሱ ከሄዱ በኋላ ኢትዮጵያ በ 7 ወይም በ 9 መንገዶች ትግዋዛለች ይላሉ ፡፡
አምባገነኑ መለስ ለኢትዮጵያ ያሟረተው እጣ ፈንታ ለርሱ ደረሰው ፡፡ ኢትዮጵያ ግን በሕያው አለች ለዘላለመም ትኖራለች።
ዘ-ህወሀትም የመሪ ዉን እጣ  ፈንታ ካገኘ በህዋላ ኢትዮጵያ እንደዚሁ ትቀጥላለች፡፡
መንገዱ ከእነርሱ ውጭ እንደማይኖር በእብሪት ተወጥረው የሚናገሩት ሌላ ማንም ሳይሆን እራሳቸውን መላዕከት አድርገው የሰየሙት የዕኩይ ምግባር ስብስቦች ብቻ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የክልል የበረት አጥር ከዘ-ህወሀት ፍጻሜ ጋር አብሮ እንደሚወገድ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡
በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ ሲያከትም አፓርታይድም አብሮ አላከተመምን?
የጎሳ ፌዴራሊዝም (የጎሳ አፓርታይድ) ዘ-ህወሀት ተረግዞ የተወለደበት የማህጸን ውስጥ ፈሳሽ ነው፡፡
ክልላዊነት ዘ-ህወሀት በስልጣን ላይ ጠንካራ ሆኖ እንዲኖር የተወለደ ጉድ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከአፓርታይድ ውጭ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ እና ባንቱስታንስ መኖር እንደማይችሉ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ከጎሳ ፌዴራሊዝም እና ክልላዊነት ውጭ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘ-ህወሀት የሚባል ሰይጣን መኖር አይችልም፡፡
ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች ነው/Quo vadis የሚለውን ጥያቄ ጥልቅ ሀሳብን በተላበሰ መልኩ ለማሻሻል መርጫለሁ፡፡
በዚህም መሰረት ጥያቄው እንዲህ የሚል ይሆናል፣ “ዘ-ህወሀት ከተወገደ በኋላ ኢትዮጵያ ወዴት ትሄዳለች?“
ይኸ ጥያቄ ለእኔ አንድ በካንሰር በሽታ ተይዞ ሲሰቃይ የቆየ ሰው በድንገት ከካንሰር በሽታው ነጻ ቢሆን ምን ሊሆን ይችላል ከሚለው ጥያቄ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡
ለምሳሌ እንበል እና ለበርካታ አስርት ዓመታት ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጭ በእስር ቤት ታስሮ የቆየ ሰው ነጻ ቢሆን ያ ሰው ምን ስሜት ሊሰማው ይችላል?
እንደዚሁም ሁሉ ለአስርት ዓመታት በባርነት ቀንበር ውስጥ ተይዞ አሳር መከራውን ሲያይ የቆየ አንድ ህዝብ አንድ ቦታ ላይ ነጻ ነህ ቢባል ምን ሊሰማው ይችላል?
እነዚህን ጥያቄዎች በሌሎች ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡
በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት አፓርታይድ አገዛዝ ሲወድቅ እና እ.ኤ.አ በ1994 በብዙህን አገዛዝ ሲተካ አብዛኞቹ ደቡብ አፍሪካውያን ምን ዓይነት ስሜት ነበር የተሰማቸው?
ኔልሰን ማንዴላ እና በሺዎች የሚቆጠሩት ጸረ-አፓርታይድ መረዎች እና የፖለቲካ እስረኞች እ.ኤ.አ በ1991 ከእስር ቤት ሲለቀቁ አብዛኞቹ ደቡብ አፍሪካውያን ምን ዓይነት ስሜት ነበር የተሰማቸው?
በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያለምንም ምርጫ ማጭበርበር በነጻነት እና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ፣ እንደዚሁም የጥቂት ነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ምርጫውን መቶ በመቶ ማሸነፉ ቀርቶ የእራሳቸውን መንግስት ለመምረጥ የምርጫ ካርዶቻቸውን በመጠቀም ለሰዓታት ሰልፍ በመያዝ ቆመው መቆየታቸውን ሲመለከቱ አብዛኞቹ ደቡብ አፍሪካውያን ምን ዓይነት ስሜት ነበር የተሰማቸው?
አንግዲህ አፍጣጭ ጥያቄው ዘ-ህወሀት ተጠራርጎ ወደታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ከተወረወረ በህዋላ ምን ይመጣል ነው ?
የዘ-ህወሀት አምባገነናዊ የጭቃ ግንብ ከተደረመሰ እና የዘ-ህወሀት የመስታወት የቅዠት የመስታወት ግንብ በህዝባዊ ማዕበል ከተሰባበረ ወይም እየተንፏቀቀ በሚሄድ ተቃውሞ እየተናጠ ከሄደ በኋላ ኢትዮጵያ ወዴት ትሄዳለች?
ኢትዮጵያ እንደ አስቀያሚው ጋላቢ ከወደቀች እና ከፉኛ ከተጎዳች በኋላ እንደገና በንጉሱ ፈረሶች እና በሁሉም የንጉሱ ሰዎች አማካይነት ተነስታ መጓዝ ትችላለችን?
ወይም ደግሞ ኢትዮጵያ ከወደቀችበት የዘ-ህወሀት አመድ ላይ በመነሳት ታርጋለች ?
ዘ-ህወሀት ባንድ እግሩ አየተንገዳገደ የስልጣኑን ጊዜ በብድር ገዝቶ ተቀምጧል፡፡ የዘ-ህወሀት  ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ ዘ-ህወሀት በህዝቦች ጀርባ ላይ ታዝሎ ሊቆይ አይችልም በማለት ተናግሯል፡፡ እንደ ኃይለማርያም አባባል ዘ-ህወሀት ቀኖቹ አልቀዋል፡፡
ዘ-ህወሀት ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያነት እየተጓዘ ነው!
በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ወደየትም በማያስኬድ መንገድ ላይ እንደ ጅብራ ተገትሮ ይገኛል፡፡
ስለሆነም መመለስ ያለባቸው ሁለት ጥያቄዎች እነሆ፡
1ኛ) ዘ-ህወሀት ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት እስከሚጣል ድረስ እያደረሰ ባለው ሰብአዊ እና የማቴሪል ጉዳት ኪሳራ ምን መደረግ ይኖርበታል?
2ኛ) ዘ-ህወሀት ተጠራርጎ ወደ ታሪክ ማጠራቀሚያ ቆሻሻ ውስጥ እስከሚጣል እና ዘ-ህወሀትን የሚተካ ታሪክ እስከሚተካ ድረስ ምን መደረግ ይኖርበታል?
መፍትሄለረዥሙ የነጻነት ጎዳና ዋና ዕቅድ፣
እንዲህ ወደሚለው የአፍሪካውያን አባባል እንደገና እመለሳለሁ፣ “የት እንደምትሄድ የማታውቅ ከሆነ ሁሉም መንገዶች ከቦታው ያደርሱሀል፡፡“
ዋናው ዕቅድ ላድሲቷ የኢትዮጵያ አዲስ ሕገመንግስት ማዘጋጀት ነው፡፡
የዘ-ህወሀትን ሕገ መንግስት አጥንቸዋለሁ፡፡ የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት ልክ ከተለያዩ ሀገሮች የሽብርተኝነት ሕጎች እየተቆረጠ እና እየተለጠፈ እንደተዘጋጀው የጸረ- ሽብር ሕግ እየተባለ እንደሚጠራው የሸፍጥ ሕግ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ባልተቃኘ መልኩ ከሌሎች ሀገሮች ሕገ መንግስቶች የተውሶ ቋንቋ እየተቆረጠ እና እየተቀጠለ የተደረተ ድሪቶ ነው፡፡ (የተኮረጀ ነው አልኩ?)
ከዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት ለመሰብሰብ ያቻልኩትን ያህል በሁሉም በሚባል መልኩ ባየሁት ሁኔታ “ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች” የሚል እንጅ ኢትዮጵያ እየተባለች በምትጠራው ግዙፍ ምድር ላይ  ኢትዮጵያ የሚል አንድም ቃል አላገኘሁም፡፡
ምናልባትም እራሴን ማረም ይኖርብኛል ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በዕርቅ ሰበብ በሰሜናዊው ክፍል ለአንድ ወራሪ ኃይል የተሰጠው መሬት ተቀንሶ እና እንዲሁም 700 እና ከዚያ በላይ ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የሀገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት ተቆርሶ በድብቅ ለሱዳን ተሰጥቶ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የሚባል ግዙፍ ምድር በእራሱ ለመኖሩ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነውና፡፡
በዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት መንደርደሪያ መግቢያው ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ተጽፎ ይገኛል፣ “እኛ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች…“
በሕገ መንግስቱ ውስጥ ብሄሮች እና ብሄረሰቦች እንጅ እንደ ሀገር ኢትዮጵያ የሚል ምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡
ምን ለማለት እንደፈለግሁ ግልጽ ለማድረግ መንደርደሪያውን ወደ የዩናይትድ ስቴትስ ሕገመንግስት በመመለስ እንዲህ የሚለውን ይሰጠናል፡ “እኛ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሕዝቦች…“ የሚለውን ይፋ ያደርጋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ከሁሉም የዓለም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የመጡ የስደተኞች ሀገር ብትሆንም እንኳ በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ሕዝብ ብቻ (እኛ ሕዝቦች…) በማለት ነው በግልጽ የተቀመጠው፡፡
“እኛ ሕዝቦች…” የሚለው በሁለት ምዕተ ዓመታት ውስጥ ዕንከኖች የሉበትም ባይባልም ቅሉ ለዩናይትድ ስቴትስ ህልውና እና ብልጽግና ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡  (እንደ ዶናልድ ትሩምፓውያን በጥላቻ የተሞላ ፉዞ ቢኖሩበትም አላልኩም፡፡)
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ለሚዘጋጀው አዲስ ሕገ መንግስት የመንደርደሪያው ክፍል/Preamble እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣…“ በማለት እንደሚጀምር አምናለሁ፡፡
ሁለተኛ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግስት ከሚከተሉት አስተሳሰቦች ላይ ሊመሰረት ይገባል፡ “በሕገ መንግስቱ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ መንግስት ያልተሰጡ ወይም ደግሞ ለአካባቢ ግዛቶች ያልተከለከሉ ስልጣኖች እንደየአግባባቸው ለመንግስታት እና ለሕዝቡ የተተው ናቸው፡፡“  በሌላ አገላለጽ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲሱ ሕገ መንግስት ብሄራዊው ሕገ መንግስት ስልጣን ሲሰጠው ብቻ ነው ተፈጻሚነት የሚኖረው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከ10ኛው ማሻሻያ ያሜሪካ ህገ መንግስት ጀምሮ ለረዥም ጊዜ እስከቆየው ጽናት የተሞላው ሕገ መንግስት ድረስ ተመሳሳይ ቋንቋዎችን በጥቅም ላይ ሲውል ተመልክታችኋል፡፡
ሶስተኛ እና ቀጥተኘ በሆነ መልኩ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግስት እንዲህ የሚለውን የጋናን ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (4) ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አለበት፣ “ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ ብሄራዊ ባህሪ ያለው መሆን አለበት፣ እናም አባልነት በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በክልላዊነት ወይም ደግሞ በሌሎች ከፋፋይ ነገሮች ላይ ተመስርቶ መከናወናን የለበትም፡፡“
እነዚህ ሶስት ሕገ መንግስታዊ ዓላማዎች እውን የሚሆኑ ከሆነ የሚቀረው ነገር የማንዴላ ረዥሙ ጉዞ ለነጻነት የሚለውነው፡፡
በማንዴላ መንገድ የሚደረገውን የነጻነት ግልቢያ እናስብ፡፡
የማንዴላ መንገድ ምንድን ነው?
የማንዴላ መንገድ ከአእምሮ እስረኝነት እና ከዘር፣ ከጎሳ እና ኃይማኖት የጽንፈኝነት ጥላቻ ነጻ ማውጣት ነው፡፡
ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ለመውጣት ወደ ዋናው የእስር ቤት በር እየተጠጋሁ በሄድኩ ጊዜ ያ ወደ ሙሉ ነጻነት እንደሚወስደኝ የማውቅ ሲሆን ያንን አስከፊውን ጥላቻ እዚያው እስር ቤቱ ውስጥ ጥየው ካልወጣሁ አሁንም ቢሆን እዚያው እስር ቤቱ ውስጥ እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡”
ያድሲቷ የኢትዮጵያ አዲሱ ሕገ መንግስት ዕቅድ ሁሉንም ኢትዮጵያውን ከረዥም ጊዜ የአእምሮ እስረኝነት፣ ከጎሳ ጥላቻ እና በመልክዓ ምድራዊ ወሰን ታጥረው ከተቀመጡት እና ክልል እየተባሉ ከሚጠሩት የማጎሪያ በረቶች በማውጣት እውነት እና ብሄራዊ ዕርቀ ሰላም ወደሰፈነባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ እንደሚወስድ አምናለሁ፡፡
የማንዴላ የእውነት እና የዕርቅ መንገድ፣
በርካታ ሀገሮች ሩዋንዳን፣ አርጀንቲናን፣ ሴራሊዮንን፣ ሲሪላንካን፣ ኬንያን፣ ጋናን እና ሌሎችን ጨምሮ የእውነት እና የዕርቅ ሂደትን አከናውነዋል፡፡
ለእውነት እና ዕርቅ ተግባራዊነት በርካታ አቀራረቦች አሉ፡፡ መሰረታዊ ዓላማው ሀገሪቱ በአንድ በተወሰነ ጊዜ የሰብአዊ መብቶችን አጠባበቅ በመርገጥ ደርሶባት ከነበረው የፖለቲካ እና ማህበራዊ ምስቅልቅል ሁኔታ ቁስሉ እንዲሽር ለማድረግ ነው፡፡ መሰረታዊ ዓላማው በቀልን እና “ዓይን ላጠፋ ዓይን” በሚል የእብሪት አካሄድ በመነሳሳት ሌላ አዲስ ሀገር መገንባት እንደማይቻል ለማሳየት ነው፡፡ ይህንን መርህ በመጣስ የሚካሄድ ነገር ሁሉ ወደ ጨለማ ሀገር ህዝቦች የሚወስድ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የህጻናት መብት ድፍጠጣ ምስል የሚታይባት ሀገር ናት፡፡ ስለሆነም የድህረ ዘ-ህወሀት መወገድን ተከትሎ ኢትዮጵያ የእውነት እርቅ ሂደት እንዲከናወን ማድረግ ዋናው አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
የተሳካ ብሄራዊ የእውነት እና የዕርቅ ሂደት መካሄድ ለእውነተኛ የብዙሀን ፓርቲ ዴሞክራሲ መንገድ ይከፍታል፡፡
ስለብዙሀን ፓርቲ ዴሞክራሲ በመናገር ላያ ያለሁት የሕግ ልዕልና የበላይነትን፣ የሰብአዊ መብት አጠባበቅን፣ መልካም አስተዳደርን፣ ተጠያቂነትን እና ግልጽኝነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው፡፡
የብዙህን ፓርቲ ዴሞክራሲ ስል ጎሰኝነትን፣ ኃይማኖትን፣ ቋንቋን፣ ክልልን፣ ወዘተ መሰረት ባደረገ መልኩ ማለቴ አይደለም፡፡
መልካም አስተዳደር ሀሳቦቻቸውን በመግለጽ እና በፖለቲካ ሂደቱ ላይ በችሎታቸው ለመወዳደር በሚችሉት ግለሰቦች እና ቡድኖች ችሎታ ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ጠንካራ የብዙህን የፖለቲካ ፓርቲ ስርዓት ዜጎች በጉዳዮች ላይ እንዲሰባሰቡ እና ሀሳቦችን፣ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ለመልካም አስተዳደር ማስተባበር እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡ ጠንካራ የብዙሀን የፖለቲካ ፓርቲ ስርዓት ተመሳሳይነት ያላቸውን አስተያየቶች እና ሀሳቦችን በሚካፈሉ ሰዎች መካከል መተባበር እንዲችሉ እና በመንግስት ላይ ጫና ማድረግ እንዲችሉ ያረጋግጣል፡፡ በውድድር ላይ የተመሰረተ የነጻ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት ለፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት፣ የሲቪክ ማህበራት ቅሬታዎቻቸውን በግልጽ ለመግለጽ እና በገንቢ የፖሊሲ ክርክሮች እና በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲኖር ያስችላሉ፡፡ የብዙሀን መብለ ፓርቲ ስርዓት መኖር ከማህበረሰቡ ውስጥ የተገለሉ ቡድኖች በተለይም ወጣቶች እና ሴቶች እንዲካተቱ ያደርጋል፡፡
ስለሆነም ጥያቄውን አንድ ጊዜ እንደገና እንዲህ በማለት አነሳዋለሁ፣ ”ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች ነው?“
ኢትዮጵያ ከዘ-ህወሀት ክልላዊነት የአፈና አገዛዝ በመውጣት የሕግ የበላይነት ወደተረጋገጠበት እና ሰብአዊ መብቶች ወደሚጠበቁበት ሕገ መንግስት እየገባች ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከማስመሰል እና ተፈጥሯዊ ካልሆነው ክልላዊ አገዛዝ እየወጣች ወደ አንድ ብሄራዊት ኢትዮጵያ መኖሪያነት እየገባች ነው፡፡
እንዲህ የሚለውን የአፍሪካውያንን አባባል እስቲ አንድ ጊዜ ልድገመው፣ “ወዴት እንደምትሄድ የማታውቅ ከሆነ ሁሉም መንገዶች ወደዚያው ይወስዱሀል፡፡“
አሁን ግን ወዴት ለመሄድ እንደምንፈልግ እና የትኛው መንገድም ወደዚያ እንደሚያደርሰን በሚገባ እናውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በሁሉም ኢትዮጵያውያን እጆች እና እግሮች ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማንሳት ወይም ደግሞ ወደ ታች በመወርወር እንደብርጭቆ አንኮታኩቶ የመስበር ኃይል አላቸው፡፡ ወደ ነጻነት በሚወስደው ረዥሙ መንገድ አብረዋት መጓዝ ወይም ደግሞ ዘ-ህወሀት በገነባው በሚገፋ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ኢትዮጵያን ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ወዴት እንደምትሄድ ሌላ የማንም ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው፡፡
እንደገና አንድ ጊዜ ወደ ኤንስታይን እና ሻው ልመለስ፡፡
ኤንስታይን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሀሳባዊነት ከእውቀት የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ እውቀት ለሁሉም ውሱን በመሆኑ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ የምናውቀው እና የምንገነዘበው ጥቂት ነገሮችን ብቻ ሲሆን ሀሳባዊነት ግን ሁሉንም ዓለም ያካትታል፣ እናም ምንጊዜም ቢሆን ማወቅ እና መገንዘብ ይኖራል፡፡“
ኤንስታይን ማለት የፈለጉት የሰው ልጆች ዕጣ ፈንታ በምናውቀው ብቻ የሚወሰን አይደለም ሆኖም ግን ከዚህም ባለፈ መልኩ ጥልቅ በሆነ መንገድ በምናስበውም ጭምር ነው፡፡
እንዲህ የሚለውን እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነውን ሀሳባዊ ጥያቄ የጠየቁት ኤንስታይን ነበሩ፣ “አንዲትን የጨረር ፍንጣቂ በህዋ ላይ መጋለብ ብችልስ?”
በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነትን መሰረት ያደረገ እውነተኛ የመድብለ/ብዙሀን ፓርቲ ዴሞክራሲ ስርዓትን ለመመስረት ብናስብስ ?”
በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣንን በብሄራዊ እና በአካባቢ ግዛቶች መካከል መሰረት ያደረገ የፌዴራል መንግስት ስርዓት ለመመስረት ብናስብስ ?
ጎሳን፣ ኃይማኖትን፣ ክልልን፣ ቋንቋን፣ ወዘተ መሰረት ባላደረገ መልኩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማቋቋም ብናስብስ ?
የኢትዮጵያ ህዝብ ሰውነት ከዘ-ህወሀት ካንሰር ነጻ እንዲሆን ብናስብስ ?
የእኔ ሀሳብ በነጻ እና በጉጉት እንዲንሸራሽር እፈልጋለሁ፡፡ እንደ ሻው ሁሉ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀርባለሁ፣ “ነገሮችን ታያለህ፣ እናም እንዲህ ትላለህ፣ ለምን? ሆኖም ግን ቀደም ሲል ሆነው የማያውቁ ነገሮችን አልማለሁ፣ እናም ለምን አይሆንም?“ እላለሁ፡፡
ጥቂቶች በብርሀን ፍንጣቂ ለመጋለብ ሲያስቡና ሲመኙ እኛ ለምን ረዥሙን የነጻነት መንገድ ጉዞ መጀመር ማሰብ ይሳነናል?
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ወዴት እንደምትሄድ የተነሳው ጥያቄ በኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች እና ወንዶች አቦ ሸማኔ ትውልድ መሪነት በጉማሬው ትውልድ ድጋፍ ሰጭነት ተገቢውን ምላሽ ያገኛል፡፡ ለእኛ ነጻነት ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ ታጉረው በግፈኛው ስርዓት እየተሰቃዩ መስዋዕትነት እየከፈሉ ባሉ የፖለቲካ እስረኞች ተገቢውን ምላሽ ያገኛል፡፡
ሁሉም መንገዶች ወደ አዲሲቷ ኢትየጵያ ያመራሉ!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
መጋቢት 20 ቀን 2008 .

wanted officials