Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 30, 2016

3 Police Officers turn down K30 000 bribe and arrest 16 Prohibited Ethiopian immigrants

Lusaka Times




Zambia Police officers

Alert Security officers in Luangwa District have intercepted 16 prohibited immigrants who were trying to use the Luangwa border to go to South Africa.
Luangwa Police Officer In-Charge, Assistant Superintendent, Mataa Muleta confirmed the interception of the 16 Ethiopian immigrants who were supposed to cross the Zambezi river to Zimbabwe enroute to South Africa.



Assistant Superintendent Mulata said the 16 Ethiopian Nationals, who entered Zambia through Nakonde border post from Tanzania, traveling in a Toyota Hiace mini bus registration Number ALR 1026, were apprehended at the Council Checkpoint on the Luangwa D145 main road at around 06:00hrs on Friday last week.

Mr Mulata said the driver of the Mini bus, Lenda Tembo and his co- driver, Prince Mulyata together with the 16 Ethiopian nationals tried to bribe
three police officers with K30,000, but the officers refused and brought them to Luangwa Police station were they are currently detained.

The Officer In-Charge further said the two Zambian Nationals, Mulyata and Tembo are detained for suspected human trafficking while the 16 Ethiopians are in police custody for illegal entry into Zambia and that they will appear before the court soon.

Meanwhile Acting Luangwa District Commissioner, Jairos Simukoko also confirmed the arrest of the 16 prohibited immigrants and the two Zambians.

Mr Simukoko commended the security wings and urged them to continue with the good so that human trafficking is reduced in the area.

He further commended Government for sending Zambia National Service officers to Luangwa to beef up security in the District which has experienced an increase in the smuggling of mealie meal and fuel to neighbouring countries.

The Acting District Commissioner said the coming of the ZNS officers was a welcome move as it has further helped to improve security in the District which borders two countries, Zimbabwe and Mozambique.

ዘሃበሻ

Friday, April 29, 2016

የትግራይ ደንበር የት ላይ ነው? ከ ዶክተር አንዳላማው




ከርዕሱ ጋር በተያያዘ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ያቀረቡትን ጽሑፍ በቅርቡ እዚህ ገጽ ላይ ለጥፌው እንደነበር ያያችሁ እንደምትኖሩ እገምታለሁ፡፡ በዚያ ጽሑፍ መሠረት ወልቃይትና ፀለምት ወደ ትግራይ (በዚያን ጊዜው አጠራር ወደ ኤርትራ) የተጠቃለሉት በፋሽስት ኢጣልያ ውሳኔ እንደነበረና ዓላማውም በአካባቢው እየተጠናከረ የነበረውን የአርበኞች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር መሆኑን ተረድተናል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የተካሄደው ስብሰባ አጀንዳ ራሱ ውሳኔው ለጊዜው (temporary) እንደሆነ ይገልጻል፡፡
ኢትዮጵያን እንደገና ለማዋቀር... በብሔረሰብ ክልሎች በመክፈል የመጀመሪያውን እርምጃ የወሰዱት ጣልያኖች ስለነበሩ፤ ባቋቋሟቸው ክልሎች ውስጥ ደግሞ የኤርትራው ክልል ከፍ ያለ ቦታ የተሰጠው ስለነበረ ገና ከመጀመሪያው ይህን አካባቢ ለአማራ የሚተውበት ምክንያት የነበረ አይመስለኝም፡፡ ይህ ጽሑፍ ሃሰት ነው የሚል ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ “የቀዳማይ ወያነ እንቅስቃሴ ከተመታ በኋላ በንጉሡ ውሳኔ የትግራይ መሬቶች ለጎንደር ተሰጡ” የሚለው ትረካ ስህተት ነው ብለን መደምደም እንችላለን፡፡
ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ ህወሓት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በጣም አጨቃጫቂ ሆነው ከዘለቁት ጉዳዮች አንዱ ከሰሜናዊው ጎንደር ተቆርሰው ወደ ትግራይ የተካለሉት አካባቢዎች ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያየ አመለካከቶች እንደሚንፀባረቁ ማውራት ጥቅም ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ወገኖች ያልሰሟቸው ነጥቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ልጠቃቅሳቸው ፈለግኩ፡፡
1. በ1990 አካባቢ (ጊዜውን እርግጠኛ አይደለሁም) ባህርዳር ላይ ተደርጎ በነበረ የብአዴን ካድሬዎች ስብሰባ ላይ ተነሳ ተብሎ በከተማው የተናፈሰ ወሬ ነበረ፡፡ በዚህ ወሬ መሠረት ከስደት ተመላሽ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በመተማና በሁመራ መካከል እንዲሰፍሩ ይደረጋል፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከነዚህ መካከል አብዛኞቹ የትግራይ ልጆች ስለነበሩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ “ልጆቻችንን በትግርኛ ማስተማር ስለምንፈልግ መንግሥት ይህን አገልግሎት ያሟላልን” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ የብአዴን ካድሬዎች ጥያቄውን ይዘው በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ይገኛሉ፡፡ “ልጆቻቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለማስተማር ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ ነው፤ ይሁን እንጅ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ በአካባቢው የሰፈረው ሕዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ወረዳችን ወደ ትግራይ ይካለል ቢሉስ?” በሚል መልክ ያቀርቡታል፡፡ በዚያ ጊዜ ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንዳስነሳና በአመራሩና በካድሬዎች መካከል “አንተ፣ አንተ” እስከመባባል እንዳደረሰ ሰምተን ነበር፡፡
2. በ1992 ታኅሣስ ወር ጎንደር ላይ ከአሜሪካ የመጡ የአካባቢው ተወላጆችና የብአዴን አመራር አባላት የተሳተፉበት: በጎንደር ልማት ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ ከአሜሪካ ከመጡት የጎንደር ተወላጆች አንዳንዶቹ “የወልቃይት ጉዳይ መፍትሔ ሳያገኝ ስለጎንደር ልማት ማውራት ጥቅም የለውም” በሚል መንፈስ በምሬት የተሞላ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከብአዴን ሰዎች የተሰጣቸው መልስ “በእኛ አመለካከት የወልቃይት ጉዳይ የተዘጋ ርዕስ ነው፤ ሕዝቡ ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኑ በትግራይ ክልል ስር መሆኑ ትክክል ነው ብለን እናምናለን” የሚል ነበር፡፡ ጥያቄውን ለማርገብ ግን “'አይ፣ አከላለሉ የሕዝብን ፍላጎት አያንፀባርቅም' የሚል ወገን ታች ወርዶ ከሕዝቡ ጋር መወያየት፣ ካስፈለገም ሕዝበ-ውሳኔ እንዲካሄድ መጠየቅ ይችላል” የሚል ሃሳብ ተሰንዝሮ ነበር፡፡
3. በ1995 አካባቢ (ይህንንም ትክክለኛውን ጊዜ ዘንግቸዋለሁ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለክልሉ ሕፃናት ተጨማሪ ኢትዮጵያዊ ቋንዎችን ስለማስተማር ጥናት አካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሕዝብ አስተያየት ምን እንደሚመስል ለመቃኘት ጎንደር ላይ ስብሰባ ይጠራል፡፡ እንደሰማነው ለተሰብሳቢዎቹ የተወሰነ ገለጻ ከተደረገ በኋላ “ልጆቻችሁ ትግርኛ ቢማሩ ምን ይመስላችኋል?” የሚል ጥያቄ ይቀርባል፡፡ የሕዝቡ መልስ ቁጣ የተቀላቀለበት ነበር ተብሎ ተነግሮኛል፡፡ አነጋገራቸው “ዛሬ ወልቃይትን አስወሰዳችሁ፣ ነገ ደግሞ ጠቅላላዋን ጎንደርን በትግራይ ስር ልታደርጓት ፈልጋችኋል ማለት ነው” የሚል ነበር፡፡ ጉዳዩ ከፍተኛ ቁጣ ከማስከተሉ የተነሳ በጊዜው የነበረው የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በቪኦኤ የአማርኛ ክፍል ቃለመጠይቅ ተደርጎለት ነበር፡፡
4. አሁን በቅርቡም ‘ደንበር ተሻግራችሁ አረሳችሁ፤ ከዚህ ክልል ፈቃድ ሳታገኙ እዚህ ማረስ አትችሉም፣ ወዘተ.’ አይነት ውዝግቦች እንደተነሱና ደም እስከመፋሰስ እንደደረሰ ይወራል፡፡
በእኔ አመለካከት የነዚህ ችግሮች ምንጭ የፌዴሬሽኑ አወቃቀር ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ አካላት የሆኑት ክልሎች (ቢያንስ የተወሰኑት) የተመሠረቱት አንቀጽ 39ን ታሳቢ አድርገው ይመስለኛል፡፡ አንቀጽ 39ን ተግባራዊ ለማድረግ የመጀመሪያው ጥያቄ “የክልሉ ደንበር የት ነው?” የሚለውን መመለስ ስለሆነ ያንን ‘በሰላሙ ጊዜ’ መጨረስ ግድ ይላል፡፡ በተጨማሪም አንቀጽ 39ን አንድ ቀን ልጠቀምበት እችላለሁ ለሚል ክልል ‘አሁን ያለው ሁኔታ አገርነትን የመለማመጃ ጊዜ ነው ወይ’ የሚል ስጋትም አለ፡፡
መፍትሔ አለው?   ከ ዶክተር አንዳላማው
---------------------
የማያዋጣው የመፍትሔ ሃሳብ ውዝግብ በተነሳባቸው አካባቢዎች ሁሉ ውሳኔ-ሕዝብ ማካሄድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለምን ቢባል ውሳኔ-ሕዝብ ለማካሄድ መጀመሪያ ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸውን ወገኖች መለየት ስለሚያስፈልግ ጥያቄው በዚህ ላይ ተቀርቅሮ እንደሚቀር አያጠያይቅም፡፡ (የሞሮኮና የምዕራብ ሰሃራን ምሳሌ ማየት ይበቃል፡፡ ውሳኔ ሕዝቡ እስካሁን ያልተካሄደው ሞሮኮና ፖሊሳሪዮ ማን ድምፅ ይስጥ በሚለው ላይ ስላልተስማሙ ነው፡፡) በበኩሌ ‘ገምት’ ብባል እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ መካለላቸውን የሚቃወሙ ወገኖች ‘ከ1983 በኋላ ወደ አካባቢው የመጡ ሰዎች ድምፅ የመስጠት መብት ሊኖራቸው አይገባም’ እንደሚሉ አስባለሁ፡፡
ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው የመፍትሔ ሃሳብ….
1. ቋንቋን ብቻ መሠረት ያደረገውን የክልሎች አመሠራረት በጥልቅ ፈትሾ የተሻለ አደረጃጀት መፍጠር (የድሮዎቹን ክፍላተ ሃገር መነሻ ማድረግ የሚቻል ይመስለኛል፡፡)
2. በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የአንድ ብሔረሰብ አባላት የሚገናኙበት የባህል ማዕከላት ማቋቋም፡፡ እነዚህ ማዕከላት የየብሔረሰቡን ባህልና ቋንቋ የማጥናት፣ የመንከባከብና የማዳበር ዓላማ ቢኖራቸው ይጠቅማል፡፡
3. ‘ለአንድ ብሔረሰብ አንድ ክልል’ የሚለውን መነሻ ሃሳብ መሰረዝ (ከስዊትዘርላንድ መማር እንችላለን)
4. እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቋንቋው የመጠቀም፣ በአካባቢ መስተዳድሮች በመራጭነትም ሆነ በተመራጭነት ያለገደብ የመሳተፍ መብቱን ማስከበር
5. ወላጆች “ልጆቻችን በዚህ ቋንቋ ይማሩልን” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ያንን ማሟላት የመንግሥት ግዴታ መሆኑን መቀበል፡፡
6. ክልሎች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪዎቹ የሚጠቀሙባቸውን ቋንቋ/ዎች መሠረት አድርገው የየራሳቸውን የሥራ ቋንቋ/ዎች አውጀው መጠቀም፡፡ (ይህ አሁንም መሬት ላይ ያለ አሠራር ነው፡፡)
7. በፌዴራል ደረጃ ተጨማሪ ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ የሚሆኑበትን ዘዴ መቀየስ፡፡
-------
የያዘውን የወረወረ… በሚለው እሳቤ ያቅሜን ያህል ይህችን ሃሳብ አቅርቤያለሁ፡፡ የእናንተን ለመስማት ደግሞ ጓጉቻለሁ፡፡ በሰከነ መንፈስ እንደምንወያይ ተስፋ በማድረግ አስተያየቶቻችሁን እጠብቃለሁ፡፡

  ከ ዶክተር አንዳላማው https://www.facebook.com/endalamaw.aberra?fref=ufi


ሕይወት፤ ሌስተርና ቼልሲ ናት! Written by ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ሕይወት፤ ሌስተርና ቼልሲ ናት!
Written by ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
“የሚሸነፍ ትግል የለም፤ የሚሸነፍ ሰው እንጂ”
Image result for chelsea and leicester cityImage result for chelsea and leicester city
ይገርምሃል ወንድሜ፤ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎች‘ኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ፤ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡ 
እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር። መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም› እንደሚባለው ሌሎቹ ቡድኖች ዋንጫውን በሩቁ ከማየት አልፈው ይወርሱታል ብሎ ማን ያስብ ነበር፡፡
ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ የተጨበጠ፣ የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ስታድየሙን ሞልተው የሚጨፍሩት እንግሊዞች፡፡ የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡ የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣ የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ አታያቸውም እንዴ እነ ማንቸስተር ዩናይትድና እነ ማንቸስተር ሲቲ ከአራቱ ውስጥ ለመግባት መከራቸው ሲያዩ? አታያቸውም እንዴ እነ አርሴናል ከቀበሮ አምልጦ ዛፍ ላይ እንደወጣ ዶሮ ካሁን አሁን ከአራቱ ወረድን እያሉ ሲጨነቁ? አላየኸውም እንዴ ስንት ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የኖረው አስቶንቪላ ተሰናብቶ ከሊጉ ሲወርድ፡፡
ዓለም እንደዚህ ናት፡፡ ድል በታሪክ ቢሆን ኖሮ ከሊቨርፑል በላይ ማን ዋንጫ ይወስድ ነበር፡፡ ምን እዚያ ወሰደህ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ዋንጫ የጠነሰስን፣ የአፍሪካን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንስ የመሠረትን አልነበርንምን? ከብዙዎቹ ቀድመን ኳስ ተጫውተን፣ ከብዙዎቹ ቀድመን ዋንጫ አልበላንምን? ከብዙዎቹስ በፊት የአፍሪካን የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አልመራንምን? ዛሬ ግን የት ነን? ትዝታ ሆነናል፡፡ ዋንጫ እንደ መንግሥተ ሰማያት፣ ድልም እንደ ሰማይ ርቆናል፡፡
ሊቃውንቱ ‹ድል ማለት ጥረትና ዕድል የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣ አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡
አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ፤ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡ ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረኸዋል፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡ የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለም‘ኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡
ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡ ሌስተርን ተመልከቱ በላቸው። ሌስተር የት ነበረ፡፡ አምና ቼልሲ ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ፣ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ሦስትና አራተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፣ ሌስተር የት ነበር? እስከ ሰባት፣ እስከ ዐሥር ደረጃ ብትፈልገው ታገኘዋለህን? ፈጽሞ፡፡ ሌስተር ከወራጅ ቀጠናው በአራት ደረጃ ርቆ፣ ከወራጁ ከሁልሲቲ በ7 ነጥብ ብቻ በልጦ 14ኛ ደረጃ ላይ ነበረልህ፡፡
ዘመን መሰላል ነው፡፡ የወጣው ሲወርድ፣ የወረደው ሲወጣ ይገናኙበታል፡፡ በአንድ ዓመት ልዩነት የቸልሲን ቦታ ሌስተር፣ የሌስተርንም ቦታ ቼልሲ ይዞ አየነው። እንዳያርግ ስንፈራው የነበረው ቼልሲ እንዳይወርድ ተሳቀቅንለት፡፡ ‹የናቁት ይወርሳል› እንደተባለው አራቱን ኃያላን ገፍቶ ሌስተር መጣና እንደ ሽሮ ቅቤ በአናት ተቀመጠ፡፡ ‹ይሞታል ያሉት ተርፎ፣ ይቀብራል ያሉት ሞተ› ሲባል አልሰማህም?
እናም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ግፋ፣ ጣር፣ ታገል፣ ሥራ፣ ሞክር፣ ድፈር፤ ድል ይጠራቀማል፡፡ አንድ ቀን ከላይ ያየሃቸው ኃያላን እንደ ቼልሲ ደክመው፣ እንደ አርሴናል አርጅተው፣ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀልብ ርቋቸው፣ እንደ ሲቲ ነገር ዓለሙ ዞሮባቸው ታገኛቸዋለህ፡፡ ያኔ እንደሌስተር ገፋ ገፋ አድርገህ ከላይ ቁጢጥ ነው፡፡ ሰውን መናቅ እንጂ በሰው መናቅ አይጎዳም፡፡ ሰውን መናቅ ትዕቢትን ወልዶ ስንፍናን ያመጣል፡፡ በሰው መናቅ ግን እልህን ወልዶ ትግልን ይፈጥራል፡፡ እናም አሸናፊነትህ የሚወሰነው ሰዎች ባንተ ላይ ባላቸው አመለካከት አይደለም፤ አንተ በሌሎች ላይ ባለህ አመለካከት እንጂ፡፡ እንዴት ያዩኛል? ብለህ አትጨነቅ፡፡ እንዴት አያቸዋለሁ? ብለህ ግን አስብ፡፡ እያሸነፍክ ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡ የበለጠ ወደ ማይክራፎኑ በተጠጋህ ቁጥር የበለጠ ድምጽህ ይሰማል፡፡
እንዲያውም ሲንቁህ መልካም ነው፡፡ ጫና አይበዛብህም፤ ጠላት አይበዛብህም፤ ተገዳዳሪ አይበዛብህም፤ ጉልበትህን ለሥራህና ለዓላማህ ብቻ እንድታውለው ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ሰዎች ዓይናቸውን ቼልሲ ላይ ያርጉልህ፣ ማንቸስተር ላይ ይጣሉልህ፣ ሲቲ ላይ ያኑሩልህ፣ አርሴናል ላይ ያትኩሩልህ፡፡ አንተ ዝም ብለህ ሥራና እንደ ሌስተር እየገፋህ ና፡፡ መንደርህ ትንሽ ናት? ስምህን የሚያውቀው የለም? ገንዘብህ ጥቂት ነው? የተሰጠህ ግምት አነስተኛ ነው? ባንተ የሚተማመኑ የሉም ወይም ጥቂት ናቸው? እነዚህ ሁሉ ካልለወጡህ ልትለውጣቸው ትችላለህ፡፡
እንደ ንሥር ታድሰህ፣ እንደ እባብ አፈር ልሰህ፣ እንደ ከራድዮን ራስህን ለውጠህ እስካልመጣህ ድረስ እንደ ቼልሲ ትናንት ዋንጫ በልተህ ዛሬ መውረድህ የማይቀር ነው፡፡ ወደ ላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው፡፡ ጊዜ ይለወጣል፣ ሐሳብ ይለወጣል፣ ወዳጅ ይለወጣል፣ አሠራር ይለወጣል፣ እሴቶች ይለወጣሉ፡፡ አንተም ትናንት የሠራኸውን ብቻ እየዘፈንክ፣ የትናንቱንም ታሪክ ብቻ እየተረክህ፣ ‹ትናንት እንዲህ ያደረግኩት እኔ ነኝ› ብለህ እየፎከርክ መኖር አደገኛው አኗኗር ነው፡፡ ‹ሆ› ብለው ያወጡህ ‹ውይ› ብለው እንዳያወርዱህ፣ ‹ጀግና› ብለው የሰቀሉህ፣ ‹ፈሪ› ብለው እንዳይጥሉህ፤ ‹ጉሮ ወሸባዬ› የዘፈኑልህ፣ ‹ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ› እንዳይሉህ፣ ‹ያለ አንተ› ያሉህ ‹ካንተ በቀር› እንዳይሉህ፡፡ የኮሩብህ እንዳያፍሩብህ፣ ‹እዩኝ እዩኝ› ብለህ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› እንዳትል ከፈለግክ መንገዱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የትናንቱን ለታሪክ ተወውና ለዛሬው የሚያስፈልግህንና የሚገባህን ሥራ ሥራ፡፡ ከታሪክ ተማር እንጂ ታሪክ ላይ አትተኛ፡፡
አታይም፤ እዚህ ሀገር እንኳን የሊቨርፑል ዘመን አልፏል፡፡ ዛሬ በሃምሳዎቹና በስድሳዎቹ ውስጥ ያሉ የኳስ አፍቃሪዎች በዘመናቸው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የእነርሱ ልጆች እንኳን ሊቨርፑልን አይደግፉም፡፡ ያማ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መጥቶ፡፡ ዘመን ተቀይሮ፤ ደጋፊም ተደጋፊም ተቀይሮ፡፡ አዲስ ጀግና መጥቶ፣ አዲስ ተከታይ አፍርቶ፡፡ ያም ዘመን አለፈ፡፡ የነማንቸስተርና የነአርሴናልም ዘመን መጣ፡፡ እርሱም ሊያልፍ ነው መሰል፣ ደግሞ የነ ሌስተርና የነ ቶተንሐም ዘመን መጣ፡፡
‹በቃ ጨርሻለሁ› ወይም ‹በቃ ተጨርሻለሁ› አትበል፡፡ ‹አለቀ›ም ‹አለቀልኝ›ም አትበል፡፡ ካንተ በፊት ሌሎች ነበሩ፡፡ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ። ‹ታግለን ጨርሰናል› ያሉ እንደ ቼልሲ ቦታ እየለቀቁ፣ ‹ገና ይቀረናል› የሚሉ ታጋዮች እንደ ሌስተር ቦታውን እየተረከቡ ይሄዳሉ፡፡ ሕይወት ሌስተርና ቼልሲ ናት፡፡

Thursday, April 28, 2016

የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ


የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ






የአዲስ አበባ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት፣የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅናውን የሰጠው፥ ዛሬ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንደኾነ የማሳወቂያ ቅጹ ያመለክታል፡፡
“የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ባገኘው ዕውቅና ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም.በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍያደርጋል፡፡
የማኅበሩ አመራር እና የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከመጋቢት 15 እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በዚያው በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብር ባልተለመደ ሕግና አሠራር እክል ከገጠመው ደቂቃ ጀምሮ፥ የአዲስ አበባ አስተዳደርንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ሓላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በትዕግሥት ሲያካሒድ ሰንብቷል፡፡
ውይይቶቹ በተካሔዱባቸው አጋጣሚዎች ኹሉ፣ መርሐ ግብሩን ለማስተጓጎል በማሰብ የአዲስ አበባ አድባራት አማሳኞች ያወጡትንና በሌላቸው ሥልጣን ለክልል መንግሥታት ሳይቀር ያሰራጩትን መግለጫ መግፍኤ በሚገባ ለማጋለጥ ወዲያውም ደግሞ፤ የማኅበሩን ዓላማና የአገልግሎት ስልቶች በጥልቀት ለማስገንዘብ መልካም አጋጣሚ የተፈጠረ ሲኾን፤ የማኅበሩ አመራርም፤ በመጨረሻ፣ ለ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ የከተማው አስተዳደር ለሰጠው ዕውቅና ምስጋናውን አቅርቧል፡፡


ኦርቶዶክሳዊው ምእመን፥ ትምህርተ ሃይማኖቱን፣ ሥርዐተ እምነቱን፣ ክርስቲያናዊ ትውፊቱንና ታሪኩን ተረድቶ ከሐዋርያዊት፣ ኵላዊትና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን መስተጋብር እንዲያጠናክር ብሎም ድርሻውን ተገንዝቦ የበኩሉን እንዲወጣ የማድረግ ዓላማ ያለውና “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ፣ የማኅበሩ ስትራተጅያዊ ዕቅድ አካል ሲኾን፤ በመደበኛው አሠራር፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በወቅቱ ተገቢውን ድጋፍና ዕውቅና አግኝቶ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ለመታየት የሰዓታት ዕድሜ ሲቀረው መታገዱ ይታወሳል፡፡

Wednesday, April 27, 2016

በዘውዲቱ ሆስፒታል የእንቅርት ታካሚዋ ለሃሞት ጠጠር በስህተት ህክምና ሆዷ ተከፈተ

– የህክምና ስህተቱን የፈፀሙት ሃኪም ከሥራ ተባረዋል

– “የሃሞት ጠጠሩ በነፃ ስለወጣልሽ ዕድለኛ ነሽ” ሲሉ ዋሽተዋታል
በዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በተፈፀመ የህክምና ስህተት ሣቢያ እንቅርት ለማስወጣት የሄደችው ታካሚ በስመ ሞክሼ በተፈጠረ ስህተት ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ። ታካሚዋ ከሁለት ዓመታት ወረፋ ጥበቃ በኋላ ተራዋ ደርሶ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት ነበር ወደ ሆስፒታሉ የሄደችው፡፡
ሠላም ደሞዜ የተባለችው ታካሚ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት አስፈላጊውን ምርመራ አድርጋ በሆስፒታሉ አልጋ ትይዛለች። በሌላ በኩል ሰላም ኪሮስ የተባለች ታካሚ ደግሞ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ወረፋ ጠብቃ ቀጠሮዋ በመድረሱ ነበር ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው፡፡ ወጣቷ በቀዶ ህክምና ከህመሟ ለመፈወስ አስፈላጊውን ምርመራ አከናውና በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ እንድተኛ ይደረጋል፡፡
d12b6b68b6e00bc55cb887af84ad0b45_XL
ባለፈው ረቡዕ ሁለቱም ህሙማን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ ከቆዩ በኋላ ለእንቅርት ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው ሰላም ደሞዜ በቅድሚያ ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል ትገባለች። የእንቅርት ታካሚዋ በቀዶ ህክምናው ክፍል ከገባች በኋላ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ሆዷ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ በታካሚዋ ሃሞት ውስጥ ለቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር አለመኖሩን ያስተዋሉት የቀዶ ህክምና ባለሙያው፤ ሆዷን መልሰው በመዝጋት የእንቅርት ማውጣት ህክምናውን ያደርጉላታል፡፡
ጉዳዩ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረባቸው ሃኪሙ፤ በወቅቱ ስለተፈፀመው ሁኔታ አንዳችም ነገር ሳይናገሩ የቀዶ ህክምና ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ። ከስፍራው ያገኘናቸው ምንጮች እንደገለፁልን፤ የሀኪሙ ረዳቶችና በስፍራው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ችግሩን ለመሸፈንና የተፈጠረውን ስህተት ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ ታማሚዋ ለእንቅርት ቀዶ ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም የሃሞት ከረጢት ጠጠር ችግር ስለተገኘባቸው ህክምናው በነፃ እንደተደረገላቸውና በዚህም ዕድለኛ እንደሆኑ በመንገር ቤተሰቦቻቸውን ለማሳመን ጥረት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የታማሚዋ ቤተሰቦች ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የህመም ምልክት ባልታየበት፣ ምርመራና ቅድመ ህክምና ባልተደረገበት ሁኔታ በድንገት ለሃሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር ሊፈጠር አይችልም በሚል ከሆስፒታሉ አስተዳደርና ከህክምና ባለሙያዎቹ ጋር ውዝግብ ይፈጥራሉ፡፡ ጉዳዩ የሆስፒታሉ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ደርሶም እንዲጣራ ከተደረገ በኋላ ትልቅ የህክምና ስህተት መፈጠሩ ታምኖበት፣ የህክምና ባለሙያዎቹና አስተዳደሩ ቤተሰቦቿን ይቅርታ በመጠየቅ ለታካሚዋ የቅርብ የህክምና ክትትል እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን የቀዶ ህክምና ባለሙያውና ረዳቶቹ ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፤ የህክምና ስህተቱ መፈፀሙን አምነው ስህተቱ የተፈፀመው በወቅቱ የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ሃኪምና ረዳቶቻቸው ታካሚዋ በትክክል የመጣችው ምን ዓይነት ህክምና ልትፈጽም መሆኑንና ሌሎች ሁኔታዎችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ ህክምናውን በመጀመራቸው ነው ብለዋል፡፡
አንድ ሰው የቀዶ ህክምና ከማድረጉ በፊት በአግባቡ ሊደረግ የሚገባው “ሰርጂካል ሴፍቲ ቼክ ሊስት” መኖሩን የጠቆሙት ዶ/ር ተረፈ፤ በዚህች ወጣት ታካሚ ላይ ይህ ጥንቃቄ ሳይደረግ በመቅረቱ ስህተቱ መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
የስህተቱ መፈፀም ሳያንስ በወቅቱ ስህተቱ አምኖና ስለ ሁኔታው ለቤተሰቦቿ ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ የነበረ ቢሆንም ይህም አለመደረጉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
“አሁን ታካሚዋ ለህይወቷ የሚያሰጋት ምንም አይነት ችግር የሌለባት መሆኑ በህክምና ባለሙያዎች በሚገባ ስለተረጋገጠ ስለጉዳዩ ለቤተሰቦቿ በቂ መረጃ በመስጠት ይቅርታ ጠይቀናቸዋል፡፡ ታማሚዋ ግን ከሆስፒታሉ እንድትወጣ በሃኪሞቿ ቢፈቀድላትም ሁለት ቀዶ ህክምና በማድረጓ በቅርብ ሆና የጤናዋን ሁኔታ እንድንከታተላት ስለፈለግን አሁንም በሆስፒታሉ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የጤናዋ ሁኔታ ግን በጣም ጥሩ ነው” ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፡፡ ስህተቱን የፈፀሙት የቀዶ ጥገና ሃኪም በኮንትራት የተቀጠሩ መሆናቸውን ያመለከቱት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፤ ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ በማድረግ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ትልቁ ስህተት የቀዶ ሃኪሙ ቢሆንም ሥራው ላይ የተሳተፉት የሀኪሙ ረዳቶችም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠቁመው እነሱም የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ፡፡
\
Source: አዲስ አድማስ ጋዜጣ

የኢትዮጵያዊቷ ሞደሊስት የዘር ሐርግ ፍለጋ ከአሜሪካ እሰከ ኦሞ ወንዝ የተደረገ የጉዞ ቅኝት (ታምሩ ገዳ)






“እነዚህ ድንቅ ጎሳዎችን በስልጣኔ ሰም ከመጥፋታቸው በፊት መጎብኘቴ ትልቅ እድል ነው”ሞዲሊስት ፋጡማ ስይድ

እውቋ ሞደሊስት ፋጡማ ሰይድ የሁለት እህቶቿን በሶማሊያው የአርስ በርስ ጦርነት ካጣች በሁዋላ ከአስራ ሶስት አመቷ ጀምሮ በሰደት ያደገችበት የአሜሪካኑ የቦስተን ከተማን በተለይ ደግሞ ዛሬ ብዙዎች የሚያውቋት የኒዮርክ ከተማን “ቤቴ ነው “ብትለውም በውስጧ አንድ የጎደላት ነገር እንዳለ ከተረዳቸው ክረምረም ብላለች። እርሱም የማንነቷ ጥያቄ እና የዘር ሐረጓ ከየት እንደ ተመዘዘ ጠንቅቆ ማወቅን ነበር ።

ከኢትዮጵያዊ አባቷ እና ከሶማሊያዊ እናቷ በመጸነስ የዛሬ 29 አመት ወደዚህ አለም ብቅ ያለቸው ፋጡማን ብዙዎቹ ምእራባዊያን የፋሺን አዘጋጆች እና ስፓንሰሮች የሚያውቋት በ ጥቁር ፣እንቁ እና ሞደሊስትነቷ በኒዮርክ፣በፓሪስ፣በሎንዶን፣በሚላን ፣ በአቴንስ እና በመሰል መደረኮች ላይ ውብ ምስሎቿን እንጂ ከየተኛው ምድር እንደ በቀለች እራሷም ብትሆን ከልጅነት ምናቧ ውጪ በቅጡ የምታውቀው አትመሰልም ነበር።

ለዚህም ይመሰላል በቅርቡ ከምትኖርባት የኒዮርክ ከተማ በመነሳት የሰው ልጆች መገኛ ከሆነቸው ከምድረ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የወላጅ አባቷ የዘር ሐርግ ከሚመዘዘባት እና በዘመናዊ ስለጣኔ ስም (ለሸንኮራ አገዳ ተክል ልማት እና ለግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀችት ሲባል) ከ200 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀያቸው የመፈናቀል አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል አሊያም የተፈጥሮአዊ የአኗኗር ኡደታቸው ሊቋራጥ ግድ ይላል ተብሎ የሚሰጋላቸው በጥንታዊ እና ማራኪ የአኗኗር ስልታቸው የበርካታ ጎብኘዎች እና የተመራማሪዎች ቀልብን የሚስቡት ከ 12 የሚበልጡ የተለያዩ ጎሳዎች የሚገኙበት ከኦሞ ወንዝ አቅራቢያ (ከደቡባዊው የአገሪቱ ክልል) ነበር የተጓዘችው።የፋጡማ የደቡብ ኢትዮጵያ ጉብኘት የዘር ሐረጓን ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በስልጣኔ ሽፋን ከአይናቸን ሊጠፉ የሚችሉትን የኦሞ ወንዝ ያፈራቸው ኢትዮጵያዊያኖችን በግንባር እና በአይኗ ተገኘታ ለመቃኘት ሲባል “ከጊዜ ጋር የተደረገ እሸቅድምድም” መሆኑን አስረግጣ ተናግራለች።


ከዘመናችን እውቅ ሞዲሊስቶች መካከል አንዷ የሆነችው ፋጡማ የኢትዮጵያ ምድርን ስትረግጥ እነዚያ ብዙ ምእራባዊያን የምጣኔ ባለሙያዎች የመሬት ሽያጩ እርሷ ከከተመችበት ከኒዮርክ ከተማ እጅግ የናረባት የ አ/አ ከተማ እና ዘመናዊ ህንጻዎቿን ብዙም ሳትቃኝ በበነጋታው የዘር ሐርጓ ትስስርን ለመፈለግ ወደ ደቡባዊ ኢትዮጵያ ያደረገችው ጉዞን በተመለከተ በአለም ታዋቂ ሞደሊስቶች ፣የፋሺን ዲዛይነሮች ፣አደናቂዎች እና የመሳሰሉት ዙሪያ የሚያውጠነጥነው “ቮጎስ” የተባለ ታዋቂው መጽሄት ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 9/2016 እኤአ ሲዘግብ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ደም ሰላላት እውቋ ሞዲሊስት ፋጡማ ሲዘግብ ፋጡማ በኢትዮጵያ ቆይታዋ የልጅነት ጊዜዋን ባሳለፈችው አርብቶ አደሮች በሚበዙበት በጎረቤት ሶማሊያ (በእናቷ አገር) የነበረው ኑሮ በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ከሚኖሩ ጋር ተመሳስይነት እንዳለው ለመረዳት መቻሏን ተናግራለች።

እራሰቸውን በተለያዩ መንገዶች ከሚገልጹት ከሙርሲዎች (ከንፈራቸውን በትልቅ ሸክላ የሚወጥሩት) ፣ከዶርዚዎች (በሸማ ፣በ ፈትል ሰራ እና በድንቅ የጎጆ ቤት አሰራር የተካኑት)፣ ከ ከሮዎች (እራሳቸውን ነጭ አፈር በመቀባት የሚያሰወቡት) ጎሳዎች ጋር ለመገናኘት ከመቻሏ በተጨማሪ ወንድ ልጆች ለጉርምሳና ለመድረሳቸው መለኪያ/መፈተኛ የሆነው በርድፍ በቆሙ የቀንድ ከብቶች/ሰንጋዎች ጀርባ ላይ መዘለል ፣ ታዋቂው የምሽት ጭፈራን ( ኢቫንጋዲን) ከማየት በመለጠቅ በዶርዜዎች ቤት ተገኝታ በልጅነቷ ታደርገው የነበረው ለእናቶች ውሃ የመቀዳት ባህልን በተግባር ተወጥታለች ፣የሸማ ሰራ/ ጥጥ የመፍተል ስልጠናን ወስዳለች ፣ የማህበረሰቡን ከብቶችም ጠብቃላቸዋልች ።በስተመጨረሻም ከደሳሳ ነገር ግን በፍቅር ከተሞላው ጎጆዋቸው ተጋብዛ ቡና በጋራ ለመጠጣት በቅታለች። ዘውትር ቢቀርቧቸው እና ቢጎበኙ ከማይሰለቹት የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች እና ተፈጥሮ የደለቸው መልካ ምድሯ ጉብኝት መልስ በአ/ አ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቿ ጋር በዚያ በመከረኛው እና ትወልድ ገዳይ በሆነው በጫት እና ሺሻ(ሁካ) ዙሪያ እንደተገናኘች ፣ለማሰታውሻነት የተለያዩ ኢትዮጵያ ነክ አልባሳትን እና ጌጣ ጌጦችንም እንደገዛች የመትናገረው ፋጢማ የኢትዮጵያ ጉዞዋ ከአይምሮዋ የማይረሳ ትዝታ እንደጣለባት እና የምስራቅ አፈሪካ ቁርኝቷን ይበልጥ ያጠናከረላት መሆኑንም ሳትገልጽ አላለፈችም።

ፋጡማ በደቡብ ኢትዮጵያ(የኦሞ ወንዝን ብቸኛው ተገናቸው እና እስትንፋሳቸው ያድረጉ) ወገኖቻቸን ማየቷን በተመለከተ “በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ከምላቸው ክስተቶች መካከል ጉልሁ እና አንዱ ነው “ በማለት ከጉዞዋ መልስ በቲዊተር አካውንቷ ላይ ያሰፈረቸው ሲሆን የእነዚህ ዝርያቸው በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮአዎ ክስተቶች ሳቢያ በመመናመን እና በመጥፋት ላይ ያሉት ጎሳዎች የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይን በተመለከተ የተለያዩ የሰበአዊ መብት እና የአካባቢያዊ እንክብካቤ ተቶርቋሪዎችም ጭምር ስጋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ሲያሰተጋባ ይሰማል። በተቃራኒው ደግሞ “ቱሪዝምን ጨምሮ በሁሉም መሰክ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ እሆናለሁ” የሚለው (ባለ ራእዩ) አገዛዝ ጩሀቱን እና ውግዘቱን በተመለከተ “ተቃውሞው ለዜጎች ዘላቂ መብት ከሚቆረቆሩ ወገኖች ሳይሆን ፈርንጆችን ለማሰደሰት ከሚዳክሩ ቡድኖች የመነጨ ወቅሳ ነው”በማለት ስጋታቸውን ያጥላላል። ታዲያ እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ የኦሞ ወንዝን መከታ ያድረጉት ቀደምት እና በአለማችን ላይ እጅግ ውብ የሆነ የአኗኗር ስልት ካላቸው ጎሳዎች የሚጠቀሱት ወገኖቻቸንን ባሕላቸውን፣ እኗኗራቸውን እና ቀያቸውን ሳይቀይሩ ህይወታቸው የሚሻሻልበትን መንገድ መቀየስ ወይስ በዘመናዊነት ምክንያት “ነበሩ”ሚለውን ብሄልን ማፋጠን? የሚሉ የሁለት የክርክር መድረኮች ተከፍተዋል

Tuesday, April 26, 2016

የሰርቆ አደሮች ስብሰባ— ዳንኤል ክብረት



የሰርቆ አደሮች ስብሰባ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል ‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና ‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት ስም ትክክል አይደለም፡፡ ገጽታችንን የሚያበላሽ ነው› ሲል አስተያየት ሰጠ፡፡ ጭብጨባ አዳራሹን ሞላው፡፡
‹ታድያ ምን ይሁን፤ መቼም ሌባ መሆናችን ርግጥ ነው› አሉ ሰብሳቢው፡፡
‹ጠየም አድርጉት፤ እንደ ባለጌ ጥፊ ድርግም አይደረግም› አሉ ሌላ አስተያየት ሰጭ፡፡

‹እኮ ምን እንባል› አሉ ሰብሳቢው፡፡
‹ሌሎቹ ሠርቶ አደር፣ አርብቶ አደር፣ ወቶ አደር፣አርሶ አደር ከተባሉ እኛም ‹ነጥቆ አደር› ነው መባል ያለብን›
ይኼው ጸደቀ፡፡

‹የሕዝቡ ምሬት ጨምሯል፡፡ ሕዝቡ በሌቦች መማረሩን በተደጋጋሚ እየገለጠ ነው፡፡ አንድ ቀን መሣሪያ ቢያጣ እንኳን አካፋና ዶማ ይዞ መነሣቱ አይቀርም፡፡

ከተንተከተከ እሳቱ ጨምሮ
ክዳኑን ይገፋል የፈላበት ሽሮ
ሲባል አልሰማችሁም፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ ለሁላችን መግቢያ ቀዳዳው ጠባብ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛው ራሳችን መፍትሔ ማምጣት አለብን› አሉ ሰብሳቢው፡፡

‹ስንናገር ለይተን መናገር አለብን፡፡ ሌባ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ኩሩ ሌባና ልክስክስ ሌባ፤ ጨዋ ሌባና ባለጌ ሌባ፤ ሸቃጭ ሌባና ኢንቨስተር ሌባ፤ ነጥቆ ሂያጅና ነጥቆ ገንቢ፤ ገፋፊ ሌባና ለካፊ ሌባ፣ እየተባለ የሚዘረዘር ብዙ ዓይነት ሌባ ነው ያለው፡፡ በስመ ሌባ ሁላችንም መሰደብ የለብንም› አሉ አንድ የታወቁ ሌባ፡፡

ሰብሳቢው የተገረሙ ይመስላሉ፡፤ አገጫቸው በእጃቸው ይዘው ‹እኔም የእናንተን ያህል ባይሆንም መቼም በዚሁ ስም ተጠርቼበታለሁ፡፡ አሁን የዘረዘርከው ግን ምንድን ነው?› አሉት፡፡

ሰውዬው ዕውቀት በመጠየቁ ወንበሩ ላይ ተገላብጦ ተቀመጠና፣ ጉሮሮውን ጠራርጎ ‹መቼም ዕውቀት ማካፈል ደስ ይለኛል፡፡ ኩሩ ሌባ ማለት ከሚሊዮን በታች የማይነካ፤ ዝም ብሎ በመቶውም በሺውም የማይልከሰከስ ነው፡፡ ልክስክስ ሌባ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ጨዋ ሌባ ማለት ደግሞ ሲሰርቅ በሕጉ መሠረት የሚሰርቅ ማለት ነው፡፡ ሰነድ አዘጋጅቶ፣ ጨረታ አጫርቶ፣ ማስታወቂያ አሠርቶ፣ ቃለ ጉባኤ አያይዞ፤ ዕቃ ገቢ አድርጎ የሚሰርቅ ማለት ነው፡፡ ባለጌ ሌባ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢንቨስተር ሌባ ገንዘብ የሚቦጭቀው ከትላልቅ ኢንቨስትመንቶች ብቻ ነው፡፡ መጉመድ እንጂ መጉረስ የማያውቅ ቆፍጣና፡፡ መጉረድ እንጂ መቁረጥ ያልለመደ ጀግና፤ መቦጨቅ እንጂ መንጨት የማያውቅ ሆደ ሰፊ ማለት ነው፡፡ ሸቃጭ ሌባ ግን ከገቢውም፣ ከወጭውም፣ ከሱቁም፣ ከኅብረት ሱቁም የሚቀነጣጥብ ቀነጣጣቢ ነው፡፡ ነጥቆ ሂያጅና ነጥቆ ገንቢ ስለሚባሉት የሌባ ዓይነቶች በደንብ መግለጥ አለብኝ፡፡ ‹ነጥቆ ሂያጅ ሌባ› ማለት ካገኘ በኋላ እዚህ ሀገር የማይቀመጥ ሌባ ነው፡፡ ይኼ ዓይነቱ ሌባ ለሀገሪቱ ዕድገት ዕንቅፋት ነው፡፡ የሀገርን ገቢ ወደ ባዕድ ሀገር የሚያሸሽ ከሐዲ ሌባ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ስሜት ፈጽሞ የሌለው ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ መብላት ሲገባው ሀገሩን ከድቶ ወጥቶ የሚበላ፡፡ እኛ ‹ወጥቶ በል ሌባ› ብለነዋል፡፡ ‹ነጥቆ ገንቢ ሌባ› ግን አገር ወዳድ ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ ፎቁንም፣ ፋብሪካውንም፣ ሆቴሉንም፣ እርሻውንም ይገነባል፡፡ ለሀገሩም አጥብቆ ያስባል፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ የሚሊዮን ብሩን መኪና ያሽቃብጠዋል፤ እዚሁ የመቶ ሺ ብር ውስኪ ያወርዳል፡፡

ነጥቆ ገንቢ ሌባ ደግ ሰው ነው፡፡ ሃይማኖተኛ ከሆነ ከነጠቀው ገንዘብ ወይ ለቸርች ወይ ለገዳም ይሰጣል፡፡ ነዳያን ያበላል፡፡ ድኻ ይረዳል፡፡ ሃይማኖተኛ ካልሆነ ደግሞ ለወጣት ማኅበራት ይለግሳል፤ ለቀበሌ ቲሸርት ያሠራል፤ በዓል ስፖንሰር ያደርጋል፤ እንዲህ ያለው ነጥቆ ገንቢ ሌባ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ ግን ምን ያደርጋል የሀገራችን ሕግና የኢንቨስትመንት ዐዋጁ በቂ ማበረታቻ ለዚህ ሀገር ወዳድ ሌባ አይሰጥም፡፡

በመጨረሻ የማብራራላችሁ ‹ገፋፊ ሌባና ለካፊ ሌባ› ስለሚባሉት ነው፡፡ ገፋፊ ሌባ ማለት ሥጋ ሲበላ አጥንት የማያስቀር፤ እንጀራ ሲበላ ሞሰብ የማይተርፈው፤ ሻይ ሲወስድ ከነ ብርጭቆው፤ የደራሲውን ድርሰት ወስዶ የደራሲው ስም የሚያጠፋ፤ ሚስቱን መንጠቁ ሳያንሰው ባሏን የሚገል፤ በመሬትህ ላይ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሊሠራ አንተን በዘጠነኛው የኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የሚወረውርህ፣ ሃምሳ ዓመት የኖርክበትን ቤት ወስዶ ከከተማው ሃምሳ ኪሎ ሜትር አውጥቶ የሚጥልህ ማለት ነው፡፡ ለካፊዎቹ ሌቦች ዝም ብለው ነው፡፡ እዚህም እዚያም ለኮፍ ለኮፍ ነው የሚያደርጉት፡፡›
ሰውዬው ማብራሪያውን ሲጨርስ አድናቂዎቹ እየሳቁ አጨበጨቡ፡፡ ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ይባል የለ፡፡
‹ታድያ አሁን መፍትሔው ምንድን ነው› አሉ ሰብሳቢው ነገሩ ውስብስብ ብሎባቸው፡፡ አንዱ እጁን አወጣ፡፡

‹ለችግሩ መባባስ ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ከመሐልና ከታች ያሉት ሌቦች ናቸው፡፡ አሁን እኔ ኩሩ ሌባ ነኝ፡፡ ልስረቅ አልስረቅ ሰፊው ሕዝብ አያውቅም፡፡ እይውልዎት፣ መንደር መንገድ ላይ ያለችውን ዛፍ የሚቆርጠውን እንጂ ደን ውስጥ ያለውን ዛፍ የሚቆርጠውን ማንም አያየውም፡፡ አሁን ለኛ ችግር የሆኑብን የመንደር ዛፍ ቆራጮች ናቸው፡፡ ለካፊ ሌቦች ከስኳሩም፣ ከጨውም፣ ከድንቹም፣ ከሸማቾቹም ይቀነጣጥቡና ሕዝቡን ያነሣሡታል፡፡ ሕዝቡኮ ስኳሩ ወደ ሸማቾች ከገባ በኋላ አለቀ ሲሉት እንጂ መጀመሪያውኑ ወደ ሸማቾች ባልመጣው ስኳር ላይ አይበሳጭም፡፡ ሃምሳ ኩንታሉን ወስደን ሃምሳውን ኩንታል ሩብ ሩብ ኪሎ ብናከፋፍለው ‹ተመስገን› ብሎ ነው ወደ ቤቱ የሚሄደው፡፡ ሥራው ግልጽነት ያለው እንዲመስል ደግሞ የመጣውን ሃምሳ ኩንታል ከሴቶች፣ ከወጣቶችና ከአዛውንት የተመረጡ ኮሚቴዎችን አሰልፎ እኩል እንዲያካፍሉ ማድረግ ነው፡፡

‹ልክ ነው፡፡› አለ አንዱ ሰርቆ አደር ኢንቨስተር ‹ሰው መብራት ተቆራረጠብን አለ እንጂ የመብራቱን ኬብል እነማን ናቸው ከውጭ የሚያስገቡት ብሎ ጠየቀ? ዱቄቱ ወደ ሸማቾች በብዛት አልመጣም አለ እንጂ ዱቄቱን እነ እገሌ ብቻ ለምን ከውጭ ያስመጣሉ? ብሎ ጠየቀ፤ አልጠየቀም፡፡ ኮንደሚኒየም በትክክል አልደረሰኝም አለ እንጂ እነ እገሌ የከተማ ቦታ በካሬ 300 ሺብር የሚጫረቱት ብሩን ከየት ቢያመጡት ነው ብሎ ጠየቀ፤ አልጠየቀም፡፡ ‹እገሌና እገሌ የተባሉ ዋና አከፋፋዮች ለምን አስወደዱብን፣ ለምን አሳነሱን› አለ እንጂ ‹ግን እነርሱ የውጭ ምንዛሬ ከየት እያገኙ ነው ዕቃውን ከውጭ የሚያመጡት?› ብሎ መች ጠየቀ፤ ስለዚህ ችግሩ እታች ያሉት አቀባባይ ሌቦች አሠራሩን ስላላወቁበት ነው ማለት ነው፡፡ አያችሁ ሕዝቡ የዋሕ ነው፡፡ በጥፍርህ ስትቧጭረው ‹ጥፍሩን ቁረጡልኝ› ነው የሚለው፡፡ ሰውዬውኮ የቧጨረው ጥፍር ስላለው አይደለም፡፡ በጥፍሩ እንዲቧጭር የሚያዝ ጭንቅላት ስላለው ነው፡፡ ሕዝቡ ‹ጥፍሩን አስቆርጦ› ወደ ቤቱ ይገባል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ቧጫሪው ዝም ይላል፡፡ ቆይቶ ግን ጥፍሩ ሲያድግ መቧጨሩን ይቀጥላል፡፡ መጀመሪያ ጥፍሩን ያሳደገው፤ ተቧጨር ብሎ መብት የሰጠው ማን ሆነና፡፡ አሁንም ያስቸገሩን ራሶቹ አይደሉም፡፡ ጥፍሮቹ ናቸው፡፡› እንደ ድጓ አድራሽ በሊቃውንት ፊት ዕውቀቱን ያስመሰከረ መስሎት ትከሻውን ሰበቀ፡፡

ሰብሳቢው ግራ እየገባቸውም ቢሆን ‹ሐሳቡን እንጠቅልለው፤ የመቋጫ ሐሳብ አምጡ› አሉ፡፡

ሁለት ሰዎች ተረዳድተው ያዘጋጁትን የአቋም መግለጫ ይዘው ወጡ፡፡ እነርሱ የአቋም መግለጫውን ሲያቀርቡ ተሰብሳቢዎቹ ወረቀትና ስክርቢቶ አዘጋጁ፡፡

አንደኛ፡- ኅብረተሰቡ ስርቆትን እንዲጠየፍ ስለ ስርቆት በመገናኛ ብዙኃን ትምህርት ይሰጥ(ይኼ ሲነበብ አንድ አምስቱ በቲቪና ሬዲዮ የሚቀርበውን ማስታወቂያ ለመሥራት እንዴት ከባለ ሥልጣናቱ ጋር እንደሚሠሩ ተንሾካሾኩ፤ አንድ ሁለቱ ደግሞ በእነርሱ ሬዲዮ ጣቢያ ይህን ፕሮግራም ለመሥራት የስፖንሰር ገንዘብ ሲቦጭቁ ታያቸው)

ሁለተኛ፡- በየቀበሌውና በየደረጃው ሕዝቡ ሌቦችን እንዲያጋልጥ ይደረግና ርምጃ ይወሰድ(የተወሰኑት ተሰብሳቢዎች ለቀበሌ ስብሰባዎች ሞንታርቦ፣ ውኃና ኮፍያ ያለ ጨረታ ለማቅረብ ተጠቃቀሱ)

ሦስተኛ፡- ሌብነትን የተመለከተ ዜማ በታዋቂ አርቲስቶች እንዲዘጋጅ ይደረግ (አርት ነክቶናል የሚሉ ነጥቆ አደር አርቲስቶች የሚዘጋጀውን የፀረ ስርቆት ቅስቀሳ ከእነርሱ እንዳይወጣ ዘየዱ)

አራተኛ፡- ስለ ስርቆት አስከፊነት የሚያስተምር ቢል ቦርድ በመላ ሀገሪቱ ይተከል (የማስታወቂያ ድርጅት ያላቸው ተሰብሳቢዎች ይቺ ፕሮጀክት ከኛ አታልፍም ብለው ማሉ)

አምስተኛ፡- የፀረ ስርቆት ቀን በየዓመቱ ይከበር፡፡ (ቲሸርትና ኮፍያ፣ መድረክና መስተንግዶ የሚያቀርቡ ተሰብሳቢዎች ዓመታዊ ገቢ ተገኘ ብለው ጮቤ ረገጡ፡፡)

ተሰብሳቢዎቹ ሰወጡ የአዳራሹ ዘበኛ በኀዘን ለጓደኛቸው ‹በሬ ሞተና ፍትሐት ሲፈታ ከበሮው ድምጹ እንዳይሰማ ‹ትሽ፣ ትሽ፣ ትሽ› ይል ጀመር፡፡ ከዚያ በፊት ‹እድም፣ እድም፣ እድም› ሲል ይሰሙት የነበሩት ጽናጽንና መቋሚያ ‹ምነው ዛሬ ያለወትሮህ ድምጽ እንዳይሰማ ‹ትሽ፣ ትሽ፣ ትሽ› ትል ጀመር› ብለው ቢጠይቁት ‹የሞተው በሬ፤ የሚመታው የበሬ ቆዳ ሆኖብኝኮ ነው፡፡ እንዴት ከበሬ ቆዳ ተሠርቼ በሬ ሞተ ብዬ ከበሮ ልምታ› አላቸው ይባላል ብለው ተረቱ፡፡

Monday, April 25, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሳምንታዊ ርዕስ አንቀጽ “መፍትሄው ትግሉን መቀላቀል ብቻ ነው”


የአርበኞች ግንቦት 7 ሳምንታዊ
ርዕስ አንቀጽ
አፕሪል 22 2016 
ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በህዝባችንና በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ አምናና ካቻምና የሆነውን እንኳ ትተን በዚህ በያዝነው አመት ብቻ በወገኖቻችንና በአገራችን ላይ ከተፈጸሙት ወንጀሎች ጥቂቶቹን ብናስታውስ የሚከተሉትን እናገኛለን ፤
በጎንደር በኩል አገራችንን ከሱዳን ጋር የሚያዋሰነውን ለምና ድንግል መሬት ቆርሶ ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ማራመጃ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተፈጸመውን ስውር ስምምነት የተቃወሙ በርካታ ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት ተፈጽሞአል።
ለዘማናት ተዋህዶ የኖረውን የቅማንትና የአማራ ህዝብ በማንነት ጥያቄ ለመከፋፈልና ለማጋጨት በተደረገው ደባ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ ተደርጎአል።
የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የማንነት ጥያቄ ለማዳፈን ሲባል ለዓመታት ወደ ክልሉ ተሰዶ በሠላም ሠርቶ የሚኖረውን የትግራይ ተወላጅ በማስታጠቅና በማነሳሳት በሁለቱ መሃል ጥላቻና ቂም እንዲረገዝ ተደርጎአል።
በደቡብ የአገራችን ግዛት የማንነት ጥያቄ ያነሱና ወያኔ ለሚያካሂደው የስኳር ምርት ከመሬታቸው አንፈናቀልም ባሉ የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎች ላይ ግዲያና እስር ተፈጽሞአል። በባሪያ ፈንግል ዘመን ይካሄድ በነበረ አዋራጅ ሁኔታ ዜጎች ራቁታቸውን እጅና አንገታቸውን በገመድ ታስረው በወታደር መኪና ሲጓጓዙ ታይቶአል።
በአርባምንጭ ፤ በቴፕና ማጂ በአገዛዙ ዘረፋና ሙስና የተማረሩና ተቃውሞ ያነሱ ዜጎች ሽብርተኛ ተብለው ተደብድበዋል፤ ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ ከሥራቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ተጥለዋል።
በብዙ ድካምና ጥረት ያገኙትን ገንዘብ አጠራቅመው ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው መጠለያ ቤት በአነስተኛ ቦታ ላይ የገነቡ በርካታ ዜጎች የሠሩት ቤት ለከተማ ውቤት አይመጥንም ተብሎ በላያቸው ላይ በቡልዶዘር እንዲፈርስ ተደርጎ ለበረንዳ አዳሪነት ተዳርገዋል።
በአፋርና በሱማሌ ክልሎችም እንዲሁ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ወንጀል ከመሬታችን አንፈናቀልም ያሉ ዜጎች ታስረዋል ፤ ተገድለዋል ፤ ለስደት ተዳርገዋል።
ሃሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ የሞከሩ፤ የአገዛዙን ዘረኛ አካሄድና ዘረፋ የተቃወሙ በርካታ ዜጎች በተቀነባበረ የሽብርተኝነት ወንጀል እየተከሰሱ ዝብጥያ ወርደዋል፤ እስር ቤት ውስጥ እያሉም በጨካኞችና አረመኔዎች አሰቃቂ ድብደባና ማሰቃያ እርምጃ ተፈጽሞባቸዋል።
ለወያኔ ባለሥልጣናት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ የሆነውን የመሬት ዘረፋ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሥም ለማካሄድ የተደረገውን እንቅስቃሴ ተቃውመው አደባባይ በወጡ የኦሮሚያ አካባቢ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጭፍጨፋ በአጋዚ ጦር እንዲካሄድ ተደርጎአል። በዚህም የተነሳ ከ400 በላይ ዜጎች ህይወት ተቀጥፎአል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከትምህር ገበታቸው ታድነው እስር ቤት ተወርውረዋል፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።
ህዝባችን ከፍተኛ የረሃብ አደጋ አንዣቦበት አለም አቀፍ ለጋሾች ህይወት ለማዳን በሚራወጡበት ወቅት ለባለሥልጣናቱ መኖሪያ ዘመናዊ ቪላ ለመገንባት ከመንግሥት ካዜና በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ እንዲሆን ተደርጎአል።
የወያኔ መሪዎች ከደሃው ህዝብ ጉሮሮ እየዘረፉ ወደ ውጪ ከሚያሸሹት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ውስጥ አምስት ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ በአንድ የወያኔ አባል በሻንጣ ተይዞ እንግሊዝ አገር ለማስገባት ሲሞከር ተይዞአል።
በቅርቡም በቻይና አየር ማረፊያ በተመሳሳይ መንገድ የተገኘ ብዙ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለሥርዓቱ ቅርበት እንዳለው በተገለጸ ሰው እጅ ተገኝቶ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ቦኋላ በባለሥልጣናቱ ጣልቃገብነት መለቀቁ ተዘግቦአል።
ይህ ሁሉ ሰቆቃና ግዲያ መንግሥት ነኝ በሚለው የህወሃት አገዛዝ በወገኖቻችንና በአገራችን ላይ መፈጸሙ አንሶ ድንበር አቋርጠው ገቡ የተባሉ ታጣቂ ሃይሎች ከሰሞኑ በጋምቤላ ክልል ከ230 በላይ ወገኖቻችንን ገድለው ከ150 በላይ ህጻናትን ከእናቶቻቸው ጉያ ነጥቀው ተሰውሮአል። በጣም የሚያሳዝነውና አገራችን ያለቺበትን የውድቀት ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው ደግሞ በሁለት ቀናት ዕድሜ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ በወገኖቻችን ላይ ፈጽሞ ወደመጣበት የተመለሰ የውጭ ታጣቂ ሃይል ማንነት እስከዛሬ አልታወቀም መባሉ ነው ።
ሌላው አሳዛኝ ክስተት በአገራቸው ተስፋ የቆረጡና ኑሮ የምድር ስኦል ሆኖባቸው በስደት የተለያዩ አፍሪካ አገሮች ውስጥ በመንከራተት ላይ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል በጀልባ ወደ አውሮጳ ለማምለጥ ሲጓዙ ከ200 በላይ የሚሆኑት ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ሰጥመው የአሳ እራት ሆነዋል። በታንዛኒያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ የተያዙ በርካታ ወጣቶች ለረጅም ወራት በታንዛኒያ እስር ቤት ውስጥ ሲማቅቁ ቆይተው ከተለቀቁ ቦኋላ የታንዛኒያ መንግሥት አገልግሎቱን እንደጨረሰ ዕቃ ኬንያ ጠረፍ ላይ ወስዶ አራግፎአቸዋል። በእርምጃው ደስተኛ ያልሆነው የኬንያ ፖሊስም ወጣቶቹን አፍኖ ወደ መጡበት ታንዛኒያ ምድር በመመለስ አውላላ ሜዳ ላይ አራግፎአቸው ተመልሶአል። አዛኝና ተቆርቋሪ መንግሥት የሌላቸው እነዚህ ወጣቶች በማያውቁት አገር ለጅብ እራት አሳልፈው ተሰጥተዋል ። ይህ ሁሉ መከራና ስቃይ በወገኖቻችን ላይ ሲፈራረቅ ህዝባችንን ለዚህ ሰቆቃ የዳረጉት ወያኔና ግብረአበሮቹ ከህዝብ በዘረፉት ገንዘብ ፎቅ ላይ ፎቅ በመገንባት በዶላር እያከራዩ ሃብት ላይ ሃብት ያከማቻሉ። ልጆቻቸውንና የቅርብ ዘመዶቻቸውን በዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ከአገር እየሸኙ ውድና ምርጥ በተባሉ ትምህርት ቤቶች ያስተምራሉ ።
አርበኞች ግንቦት 7 በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ፤ ግዲያ ፤ እስርና ስደት መቆም የሚችለው የአፈናው ፤ የግዲያው እና የስደቱ ምንጭ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ከህዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ መወገድ ሲችል ብቻ ነው ብሎ ያምናል። ለአገሩና ለወገኑ የሚቆረቆር ማንኛውም ዜጋ የዚህን ዘረኛና ከፋፋይ አገዛዝ የሥልጣን ዕድሜ ለማሳጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል አቅሙ በፈቀደ መንገድ ሁሉ እንዲያግዝና ትግሉን እንዲቀላቀል አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ጠንክረን በመታገል በአገራችንንና በወገኖቻን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ፤ ግዲያና ስደት ማስቆም እንችላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

11 U.S. Senators condemn human rights violations in Ethiopia


የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።


Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia.

Whereas the first pillar of the 2012 United States Strategy Toward Sub-Saharan Africa is to strengthen democratic institutions, and the United States Agency for Inter- national Development Democracy, Human Rights, and Governance Strategy states that strong democratic insti- tutions, respect for human rights, and participatory, ac- countable governance are crucial elements for improving people’s lives in a sustainable way;

http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2016/04/DAV16554.pdf

AAU Students, Protested In front of US Embassy,Hearing–April 18/2016


http://ehrp.org

Oromo students from 4kilo, 5kilo and 6kilo campuses of Addis Ababa University, who were arrested for demonstrating in front of the Embassy of USA opposing Ethiopian government’s ongoing killings and human right abuses on peaceful protesters, appeared at Menagesha 1st instance court. Though the court session was appointed to hear prosecutor’s witnesses, no witness was present. Based on the prosecutor’s demand for another appointment, the case adjourned for April 27th 2016.

The court session was closed for attendance but after the hearing the defendants were taken to 5kilo and 6kilo (areas of the university campuses) on foot escorted by the police. The objective was to make other students see them while arrested and escorted. The defendants are also experiencing harsher treatment at kilinto prison. For example, while other prisoners are allowed to take in their charge files with them, these student defendants are not allowed to have their charge files. Thus,
AAU-students-protested
1. Since they don’t exactly know the prosecutor’s detailed charges and the evidences filed against them, the prosecutor can make any changes on evidence list without their knowledge

2. Their lawyers can not give them adequate legal advice because they do not have the charges on their hands and that is against the constitution and any criminal procedure laws

Though it has already been more than a month and ten days since the students protested, THE EMBASSY HAS NOT COMMENTED ANYTHING YET. And no person from the embassy and diplomatic community was observed to follow up the trial.

The following is the list of the names of the defendants

1 Soressa Deme 4th year Mechanical Engineering Student

2 Bilisuma Birhanu 2nd year Economics Student

3 Gudina Tesfaye 2nd year Management Student

4 Eshetu Dejene 2nd year Economics Student

5 Debela Feyisa 4th year Engineering Student

6 Batte Lemi 2nd Year Mathematics Student

7 Alemu Olani 2nd year Economics Student

8 tGemechu Kebede 1st year Afan Oromo Language

9 Ahmed Mohammed 5th year Electrical Engineering Student

10 Hinersamu Bogale 3rd year Accounting Student

11 Ejigu Qebeta 2nd year Economics Student

12 Sheleme Gemechu 2nd year Economics Student

13 Gemechu Hailu

14 Meresha Bayisa 2nd year Economics Student

15 Tesfaye Getu 3rd year Management Student

16 Teressa Asenaqe 2nd year Economics Student

17 Tesfaye Mekonnen 2nd year Economics Student

18 Daniel Abdisa 2nd year Chemical Engineering Student

19 Guta Bayisa 2nd year Chemical Engineering Student

20 Birhanu Bedada 1st year Public Administration Student

**************************************************

On another case of a charge file against Olana Kebede and et al, which was appointed at Lideta Higher Court 19th bench, the case as adjourned for July since the judges are said to be unavailable due to the training they are attending.

Sunday, April 24, 2016

11 የአሜሪካ ሴናተሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አፈና አወገዙ


የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።



በሕገመንግሥት የተረጋገጡ መብቶቻቸውን እየተጠቀሙ ተቃዋሞዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚገልፁ ሰልፈኞች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪል ኅብረተሰብ አባላት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ግድያ የታከለበት የኃይል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የገለፁ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤት አባላት አድራጎቱን በብርቱ እንደሚያወግዙ ያሳወቁበትን የውሣኔ ሃሣብ ነው ይፋ ያደረጉት።

ሰነዱን ያዘጋጁትና የሴናተሮቹን ተቃውሞ የመሩት ዴሞክራቱ የሜሪላንድ አንጋፊ ሴናተር ቤን ካርዲን እና ሪፐብሊካኑ የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ናቸው።



ሪፐብሊካኑ የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ /ፋይል ፎቶ/

የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የገባውን የደኅንነት ውል መልሶ እንዲፈትሽ ይጠይቃል።

የሴናተሮቹ የውሣኔ ሃሣብ መግለጫ ሰነድ ረቂቅ አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ የኃይል እርምጃዎችን እንዲያቆምና አጥፊዎች እንዲጠየቁ ያሳስባል።

በጋምቤላ ሕዝብ ለተቃውሞ ወጣ – “መንግስት ግድያውን ለፖለቲካ ፍጆታና ኦሮሚያን እና ጎንደርን ለማረጋጋት ተጠቅሞበታል” – ጋምቤላ አልተረጋጋችም


13076784_10205648164656023_6561978623060851611_n
(ዘ-ሐበሻ) በጋምቤላ “መንግስት የለም ወይ?” ያሉ ነዋሪዎች ሰሞኑን የተፈጸመውን ግድያ በማውገዝና መንግስትም ይህንን የሕዝብ ሞት ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ አዎሎታል በሚል ሕዝቡ በነቂስ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን ሲያሰማ መዋሉን ለዘ-ሐበሻ የደርሰው መረጃ አመለከተ::
“ልጆቻችን ይመለሱ…. በሃገራችን ሰላም አጣን… መንግስት በኛ ሞት የፖለቲካ ድል ማግኘቱን ያቁም…” እና ሌሎችንም መፈክሮች ሲያሰሙ የነበሩት የጋምቤላ ነዋሪ ሰልፈኞች መንግስትን ሲያወግዙ ውለዋል::
ሕፃናቱን ለማስለቀቅ ከብቤያለሁ እያለ ሲፎክር የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ወታደር እስካሁን ልጆቹን ባያስለቅቅም የትናንቱን ገድያ ተቃውመው ለሰልፍ የወጡትን ኢትዮጵያውያን ግን ዛሬ ጋምቤላ ላይ ሲቀጠቅጥና ለመበተንም ሲሞክር ታይቷል::
gambela
በጋምቤላ የተለያዩ ከተሞች በአሁኑ ወቅት መረጋጋት አለመኖሩን የሚገልጹት የአካባቢው ምንጮች ማን ከየት መጥቶ ገድሎ እንደሚሄድ እንደማይታወቅና ሕዝቡም እርስ በራሱ ተፈራርቶ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
በጋምቤላ ጉዳይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት የታህሳስ 13 መታሰቢያ ንቅናቄ ተወካይ አቶ ኦዶል ኦዶል ለዘ-ሐበሻ በሰጡት አስተያየት የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት የሰሞኑን ግድያ የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ አድርጎታል ብለዋል:: እንደ እርሳቸው አባባል መንግስት እየነገረን ያለው ትንሹን ግድያና በተለይም ሙርሌዎች ያደረሱትን እንጂ ከዛ በፊት ከ15 ቀናት በፊት ስለሞቱት ሰዎች የነገረን ነገር የለም ብለዋል::: እንደ ኦዶል ገለጻ መንግስት በኦሮሚያና በጎንደር የተነሳበትን ሕዝባዊ ቁጣ ለማብረድና ሃሳብን ለማስቀየር የሙርሌዎችን ግድያ ከመጠቀሙ በላይ ምንም ያደረገው ነገር የለም ብለዋል::
በተለይም በትናንትናው ዕለት በጋምቤላ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለተገደሉት 15 ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ጠይቀናቸው “ገዳዮች ናቸው የተባሉት ሰዎች የገደሉት አማሮችን እና ኦሮሞዎችን ብቻ መርጠው ነው; ይህም ማን ከበስተጀርባው እንዳለ ያሳየናል” ብለውናል::
አቶ ኦዶል ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት የጋምቤላ አክቲቭስቶች ሕዝቡ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ መረጃዎችን ለሕዝብ ቶሎ ቶሎ ማድረስ አለባቸው ብለዋል:: ሕዝቡ መንግስት የሚለውን ብቻ በመስማት መንግስት አሸናፊ እንዳይሆን መረጃዎችን ከፎቶዎች ጋር በማውጣት ማጋለጥ ይገባቸዋል ብለዋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት ጃዊ በተባለ የስደተኞች ጣቢያ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጋትሏክ ቱት ኩዃት ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የሞቱትን ቁጥር ወደ 10 አሳንሰውታል:: ለትናንቱ ግድያ መነሻም ሴቭ ዘችልድረን የተባለ የግብረሰናይ ድርጅት መኪና በስደተኞቹ ካምፕ ላይ በደረሰበት አደጋ የሁለት ስደተኞች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ነው ሲሉ ተናግረዋል:: ስደተኞቹ ከመኪና አደጋው ጋር ተያያዥነት በሌላቸው 10 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውንም ገልጸዋል::
ጋምቤላ ተወጥራለች…. ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘች ትመለሳለች::

wanted officials