Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 31, 2016

በካምፓላ የወያኔ ደጋፊዎች ተደናግጠዋል




ነሃሴ 19/2008 ዓ/ም በአንድ ወጣት ደራሲ የተደረሰ መጸሃፍ ካምፓላ ላይ ተመረቀ!
የካምፓላ ምንጮቻችን እንደነገሩን መድረኩም በእውነተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ ነበር። ምሽቱን ልዩ ያደረገው አጋጣሚ ቀንደኛ የወያኔ ወዳጆችም ሳይቀሩ በምረቃው ላይ ታይተዋል። “ወልቃይት የትግራይ ነው! መተማ ደሞ የሱዳን ነው ! “ያለው የወያኔ ቤተኛ ማርቆስ ጌትዬ ስደተኛ መስሎ መገኘቱ ታውቋል።የወያኔ ኤንባሲ ባደራጀውና ስደተኞች ሳይቀሩ አባል በሆኑበት የዲያስጶራ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ፀጋዬም ተሳትፏል።በምሽቱ ሃገር ወዳድ ወጣቶች ባቀረቡት ዝግጅት በርካቶች ደስተኞች እንደነበሩና አቶ ስለሺም በስሜት ተነስቶ በማንባት የፕሮግራሙን አዘጋጆች አመስግኗል። ከእንግዲህም ከወያኔ ኤንባሲ ጋር እንደዱሮው በወዳጅነቱ የማይቀጥልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም የዐይን እማኞች ተናግረዋል። የመጸሃፉ ደራሲ ናቲ ቪሎፒያ በሲዲ ጭምር ያዘጋጀው የጥበብ ስራውን በምሽቱ ያስመረቀ ሲሆን አክቲቪስት ታማኝ በየነ የላከው የቪዲዮ መልዕክት በምሽቱ ቀርቧል። በሃገር ቤት በወያኔ አጋዚ የተጨፈጨፉ ወገኖችንም ሻማ በማብራት ተዘክረዋል። ይህን ስብሰባ ተከትሎ የወያኔ ኤንባሲ በምሽቱ በመፀሃፍ ምረቃው ላይ የተገኙትን ወዳጆቹን በምስጢር ለሃሙስ ስብሰባ እየጠራ መሆኑንና በድርጊቱም መደናገጥና ብስጭት እንደሚታይባቸው ስልክ ተደውሎ ከተጠሩት መካከል የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥ ጀርባ እጁ ያለበት አቶ ንጉሱ ጥላሁን *የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ*


ላለፉት 25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥እስራት፥ስደት እና ወከባ ዋናዎች የህወአት ሰዎች ቢገኙም በተላላኪዎች እና በጉዳይ አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ግን በክልሉ ያሉ በብአዴን ስም የተሰገሰጉ የጥፋት ሀይሎች ናቸው።


ሰሞኑን በአማራ ክልል የሚካሄደውን ህዝባዊ ትግል ጥላሸት በመቀባት ሰላማዊ ሰልፉ ህጋዊ አደለም ከማለት ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ሳያወግዝ አለቆቹ ጽፈው የሰጡትን እንደበቀቀን የሚያስተጋባው የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በ14/08/2016 የተገደለውን ወጣት አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ለቀረበለት ጥያቄ ሰዎች የፈለጉትን መልበስ እንደሌለባቸው እና የተገደለው ወጣትም በአመጽ እና በቅስቀሳ ተግባር ስለተሰማራ ነው እንጂ ነጭ ስለለበሰ አደለም ሲል ግድያው ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል።ወደ ፊትም እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቋል።
ታዲያ እንዲህ አይነቱ ሰው ማን ነው?የኋላ ታሪኩስ ምን ይመስላል?እንዴት ወደዚህ ስልጣን መጣ ብሎ መጠየቅ ስለ ግለሰቡ የተሟላ መረጃ እንዲኖረን ፥መወሰድ ያለበት ቀጣይ ተግባርም ለመወሰን ስለሚረዳ እነሆ ተከታታሉኝ።
ንጉሱ ጥላሁን በ1998 አ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ በፔዳጎጅካል ሳይንስ የተመረቀ ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታው የተማሪዎች መማክርት ውስጥ ይሰራ ነበር።በዚህም ወቅት ከግቢው የተማሪዎች የምግብ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመመሳጠር ጥራቱ ያልጠበቀ ምግብ እንዲቀርብ፥ነጭ ጤፍ መቅርረብ ሲገባው ቀይ ጤፍ እና በቆሎ የተቀላቀለ፥ትክልት መቅረብ ሲገባው አተር ከክ ፥ወዘተ እያደረገ በተማሪው በጀት የግል ኪሱን ሲሞላ የነበረ ሰው ነው።የ97 ምርጫ ብጥብጥ ተከትሎ በዮኒቨርሲቲው ውስትጥ የነበሩ ተማሪዎችን እየጠቆመ ያሳስር የነበረ ሰላይ ነበር።
ንጉሱ ትምህርቱን ሲይጠናቅቅ ገና በይፋ የምስክር ወረቀት ዲፕሎማው በሬጅስትራር ተሰርቶ ብይፋ ለሁሉም ከመታደሉ በፊት በነበረው የባንዳነት ተግባሩ ዲፕሎማው ተሰርቶ ተሰጦት በዳሸን ቢራ ፋብሪካ ያለ ምንም ውድድር የተቀጠረ ሰው ነው።ከዚያም በቀጥታ ለአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊነት ተመደበ።
ለዚህ ሁሉ ተግባር ከንጉሱ ጀርባ ማን አለ?ንጉሱን ማን ወደ ዳሸን ቢራ አስገባው?
ቁልፍ ካድሬዎች ተመርጠው በሚቀመጡበት የኮሙኒኬሽን ቦታ ማን ንጉሱን አስቀመጠው ብለን ስንጠይቅ መልሱ ህወአት ሁኖ እናገኘዋለን።እንግዲህ ይህ ሰው ነው የአማራውን ትግል በሌሎች ብሂሮች ላይ ያነጻጸረ እያለ የህወአትን አጀንዳ በህዝባችን ላይ የሚያስፈጽመው።
ወገኔ ትግል ሩቅ አያስሄድም።ከጎናችን ብዙ ጠላቶች አሉ ትልልቁን ዛፍ መቁረጥ ከመጀመራችን በፊት ቅርንጫፉን መመልመል ተገቢ ነው።


ንጉሱ ጥላሁን የአማራው ጠላት
 Aseged Tamene photo

ወያኔ በሁመራ አና ሽሬ በጠራው ሰልፍ ላይ የትግራይ ህዝብ በነቂስ ወቶ ዋለ

ወያኔ በሁመራ አና ሽሬ በጠራው ሰልፍ ላይ የትግራይ ህዝብ በነቂስ ወቶ ዋለ ፡፡ በሰልፉም ላይ የሚሰሙት መፈክሮች ዝምታው በዛ ህወሓት በአማራ እና ኦሮሚያ ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት የሚሉ መፈክሮች ይዘው ወተዋል ፡፡ የኦሮሞ እና አማራ ህዝብ ለሞት ሽረት ትግል ራሱን ያዘጋጅ ..!??

ገና ብዙ ይላሉ ። አንዳድ ሰወች ወያኔ ማለት የትግራይ ህዝብ አይደለም ለምትሉ እውነታውን እያያቹ ነው። ማንኛውም የትግራይ ተወላጂ ኦሮምያም አማራ ክልል ያለውን እርምጃ መወሰድ አለበት አሊያም ወደሀገራቸው እዲህዱ ካልተደረገ ከህዝቡላይ ችግርም ይፍጥራሉ ኢፍርሜሺንም የምያወጡብን እነሱ ናቸው ማዘን አያስፈልግም ይህን የአማራውም የኦሮም ትግሉን የምያቀሳቅሱ አካሎች ይህን መመርያ ካላደረጉ ህዝባቸው ላይ ትልቅ ችግር ይፍጠራል በፍጥነት ትዛዝ መሰጠት አለበት ።

በኦሮምያም በአማራም ክልል በጣም ልንጠብቃቸው የምገቡ ቦታወች የመጠጥ እህወችን በጣም እጠብቃቸው የተለያዩ መርዞችን ለመጨመር እቅድ አላቸው ይህንም የምያረጉት የትግራይ ተወላጆች ናቸው ትኩረት ይሰጠው 

በጎጃም የደምበጫና አማኑኤል ሕዝብ በሕወሓት መንግስት ላይ ተነሳ | የቋሪት ሕዝብ የራሱን የጎበዝ አለቃ መረጠ

በጎጃም የደምበጫና አማኑኤል ሕዝብ በሕወሓት መንግስት ላይ ተነሳ | የቋሪት ሕዝብ የራሱን የጎበዝ አለቃ መረጠ
የጎጃም ሕዝብ የአማራ ተጋድሎ እንደቀጠለ ነው:: ዛሬ በጎጃም ደምበጫ እና አማኑኤል ከተሞች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ተነስቷል:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በም ዕራብ ጎጃም ደምበጫ ከተማ የጸረ ሕወሓት መንግስት ትግሉ አይሏል::
ደምበጫ ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት የትግራይ ተገንጣይ ሥርዓት ሃገሪቱን ጥሎ እንዲወጣ ጠይቋል:: ሕዝቡ በተቃውሞም ተምጫ ድልድይን የዘጋው ሲሆን ማንኛውም ትራንስፖርት በዚህ ድልድይ በኩል እንዳያልፍ አድርጎ ስር ዓቱን እየተቃወሙ ነው:: “ወልቃይት አመራ ነው; ሕወሓት ጸረ አማራ ነው” የሚሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው::
በሌላ በኩል አርሶ አደሮች ዛሬ የገበያ ቀን ቢሆንም ከተማ ውስጥ ከገቡ አብረው ሊበጠብጡ ይችላሉ በሚል የትግራይ ተገንጣይ መንግስት ወታደሮች ወደ ደምበጫ ከተማ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል::
በሌላ በኩል ቤተ አማራ እንደዘገበው በምስራቅ ጎጃሟ አማኑኤል ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በደ/ማርቆስ ትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ሰራዊት መኪና ላይ ከባድ መትረይሶችን በመደገን ያልተጠበቀ ሰልፍ ሊካሄድ ይችላል በሚል እሳቤ ከተማዋን ወረዋታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአዲስ ኣበባ የመጡ የህዝብ ባሶች ከኣማኑኤል ጀምሮ እየተደረገ ባለው ተቃውሞ ደብረማርቆስ እንዲያድሩ ተደርጓል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ደርግን ለመጣል ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው የቋሪት ሕዝብ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ስብሰባ በማድረግ የሚመራውን የጎበዝ አለቃ መምረጡ ተሰማ:: የቋሪት ሕዝብ ከሕወሓት መንግስት ነጻ እስካልወጣን ድረስ በነርሱ አንገዛም; ትግላችንም እስከመጨረሻው ድረስ ነው ሲል ቃል በመግባት መሪዎቹን መርጧል:: በየክልሉ ያሉ የነጻነት ታጋይ ሕዝቦች ከቋሪት ነዋሪዎች ተምረው እንዲሁ የራሳቸውን የጎበዝ አለቃ እንዲመርጡ በተደጋጋሚ በፖለቲከኞች ሲመከሩ እንደነበር አይዘነጋም::((ዘ-ሐበሻ) )

Ethiopian regime deploying massive military to the Amhara region as uprising continue unabated

Ethiopian regime deploying massive military to the Amhara region as uprising continue unabated
By Engidu Woldie
ESAT News (August 31, 2016)
Reports reaching ESAT from Ethiopia say the TPLF regime is deploying thousands of its troops and Agazi Special Forces to the Amhara region where uprising against the regime is gaining momentum as more towns and localities removed local administrations and the security, and replaced them with interim administrations elected by the people.
Thousands of troops in a dozens of convoys and heavy machinery were seen heading towards northern Gondar via Wuchale, Wollo as the alternative and direct routes were closed by protesters, according to a sources who spoke to ESAT.
ESAT is yet to verify the information but high ranking TPLF military and civilian officials led by chief of staff Samora Yunis have arrived in Gondar. Close observers of the new developments say the regime was heading towards forming military posts and putting in place a military administration as seen in the Oromo region of the country where a nine month protest has relatively quieted this month.
Deadly protests have however continued on Tuesday in Gondar and Gojam where seven protesters - three in Adet and four in Simada - were shot and killed by TPLF forces. Three people were also killed in Merawi.
In Bahir Dar, angry protesters went to the Sebatamit prison and freed 700 prisoners who were detained in the recent protests. Several people were injured in the shoot out to free the prisoners, according to hospital sources. Gun fire could be heard on Tuesday in the city of Bahir Dar which saw deadly protests on Monday as four people were killed and protesters attacked businesses belonging to the regime.
In Amba Giorgis, regime forces attacked residents who on Monday targeted businesses and set on fire houses belonging regime officials.
Tensions remained high in Fnote Selam that has seen deadly protests in recent days. Offices and businesses remained closed on Tuesday in Finote Selam.
Prime Minister Hailemariam Desalegn blamed the unrest on what he called “foreign forces” bent on distracting the country from its development and fomenting ethnic conflicts. He declined to name the “foreign forces” but went on to accuse them of providing financial support to Ethiopian opposition forces in the diaspora.
The Premier’s accusations did not come as a surprise to political observers who said that it has been customary for the regime to blame external forces for all its internal crises.
Meanwhile, human rights groups called for an independent investigations into the killings and incarceration of civilians by security forces in Ethiopia. Defend Defenders, Amnesty International, Ethiopian Human Rights Project, Frontline Defenders and FIDH called in a joint statement for the immediate cessation of the killings and detention of peaceful citizens and members of the civic society.
(Photo file of Samora Yunis)

በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ወንጀል ገለልተኛ አለም አቀፍ ቡድን እንዲመረምረው ተጠየቀ

በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ወንጀል ገለልተኛ አለም አቀፍ ቡድን እንዲመረምረው ተጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008)በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ክልሎች በመንግስት ጸጥታ ሃይሎች እየተደረገ ያለውን ግድያና፣ ሰቆቃ፣ እና እስራትን የሚመረምር አለም አቀፍ ገለልተኛ ቡድን እንዲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማህበራት ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።
የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ተከላካይ ድርጅት (ዲፌንድ ዲፌንደርስ)፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጄክት፣ Front Line Defenders, እና የሰብዓዊ መብት አለም አቀፍ ፌዴሬሽን (FIDH) በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎችና በሲቪል ማህበረሰብ አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ወከባና እስራት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ነሃሴ ወር ለምርምር የተሰማሩ 4 የሰብዓዊ መብት ድርጅት አባላት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ማሰሩ ታውቋል ። በዚሁ በነሃሴ ወር የሰብዓዊ መብት ምክርቤት አባላትና በምርምር ስራ ላይ የተሰማሩት እቶ ተስፋ ቡራዩ፣ አቶ ቡልቲ ተሰማና አቶ አበበ ዋከኔ፣ በኦሮሚያ ሲታሰሩ፣ አቶ ተስፋዬ ታከለ ደግሞ በአማራ ክልል መታሰራቸው ታውቋል።
እነዚህ በምርመራ ስራ ላይ እያሉ የታሰሩት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አባላት ክስ ሳይመሰረትባቸውና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እስካሁን ድረስ በወህኒ ቤት ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
የዕስሩ ምክንያት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየደረሱ ያሉትን ግድያዎች፣ ሰቆቃና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመመዝገብ ላይ መሰማራታቸውና ይህም መንግስት እያደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይጋለጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት አምነስቲ እንደሆነ በድረገጹ የተሰራጨው መግለጫ አትቷል።
በሰብዓዊ መብት ላይ ገለልተኛና ግልጽ ምርመራ ለማካሄድ ፍላጎት የሌለው የኢትዮጵያ መንግስት፣ በዜጎች ላይ ለደረሰው የሰብዓዊ ጥሰት ትክክለኛ፣ መረጃ ያወጣል ብለን አናስብም ሲል በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድረገጽ ላይ የተበተነው መግለጫ ያስረዳል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙትን አጣርቶ ከማሰር ይልቅ፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የምርምር ሰራተኞችን እያሰረ እንደሚገኝ ባወጣው መግለጫ አክሎ ገልጿል።
በሁለት ቀናት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከ100 በላይ ሰላማዊ ሰልፈኞች በመንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ተከትሎ የታሰሩት የሰብዓዊ መብት ሰራተኞች፣ የመንግስት ሃይሎች ያሰሯቸው ምክንያትም መረጃ የመሰብሰብ ሂደት ለማስተጓጎል በማሰብ እንደሆነ በድረገጽ ላይ የተሰራጨው መግለጫ ያስረዳል።
ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ በነሃሴ ወር ሶስት የውጭ ጋዜጠኞች ለ24 ሰዓታት በሻሸማኔ ከተማ ታስረው እንደተፈቱ የገለጸው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት፣ ከታሳሪዎች ውስጥ ለአፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ የምትሰራዋ ሃዳር አህመድ፣ የፒ ቢ ኤስ ሪፖርተሮች ፍሬድ ላዛሮ እና ቶማስ አዳኤር እንደሚገኙበት ዘርዝሯል።
ዲፌንድ ዲፌንደርስ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ፣ ፍሮንድ ላይን ዲፌንደርስ፣ እና የሰብዓዊ መብት አለም አቀፍ ፌዴሬሽን የተባሉት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የታሰሩትን የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአለም አቀፍ መርማሪ ቡድን ምርመራ ማካሄድ እንዲቻል ፈቃድ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።



በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው።




በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው።
#Ethiopia #Amharaprotests #BahrDar #AmharaResistance

 በባህር ዳር ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ታውቋል።ከባሕር ዳር 45 ኪሎ ሜትሮችን በምትርቀው የጉማራ መንደር እስከ ዛሬ ሌለት ድረስ በቆየ የተኩስ ልውውጥ 8 የወያኔ ፌደራሎች ተገድለዋል። 2 ዐማሮች በተጋድሎው ተሰውተዋል። የ8 ፌደራል ሙሉ ትጥቅ ገበሬው ተከፋፍሏል። መንገዶች ዝግ ሲሆኑ ሕዝቡም ራሱን እያስተደዳረ ነው።በባህር ዳር እና አዋሳኝ በሆኑ ከተሞች በህዝብና በወያኔ ቅልብ ወታደሮች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው፡፡


ከባህር ዳር ወደ ጭስ አባይና አዴት ሞጣ ቢቸና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው ሰባታሚት ላይ የአማራ ህዝብ ወያኔን በአኩሪ ጀግንነት እየተፋለመ ነው፡፡በባህር ዳርም ቀበሌ 7 እና 17 ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው። ወያኔ በማንኩሳ ዐማሮች ላይ ሙለ ጦርነት አውጇል።ከማንኩሳ አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች ሕጻናትን ጨምሮ በደካሞችና አዛውንቶች ላይ ሁሉ እያነጣጠሩ እየተኮሱ ነው።ማንኩሳ ማንኛውም ዓይነት መረጃ መለዋወጫ መንገድ ተዘግቷል። #ምንሊክሳልሳዊ

Tuesday, August 30, 2016

ሕዝባዊ እንቅስቃሴው በህወሓት የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ የኢኮኖሚ ጦርነት ሊጀምር ነው




በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር እና ጎጃም በደቡብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን አመጽ ጋር በተያያዘ በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት የፖለቲካ መናጋት እንደደረሰበት የሚወስዳቸው ግብታዊ ርምጃዎች ያመላክታሉ።


ምንም እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአማራም በኦሮሚያም የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢገደሉም ሕዝባዊ ተቃውሞው በተቃራኒ ጉልበቱን እያደሰ ስርዓቱን ግራ አጋብቶታል።

የህወሓትን ኢኮኖሚ አቋም ለማዳከም በሚመስል ሁኔታ በጎጃም ባህር ዳር ከስርዓቱ ጋር ንክኪ ያላቸውን የንግድ ተቋማት ዝርዝር የያዘ እና የኢኮኖሚ እቀባ የሚጠይቅ ጽሁፍ ተበትኗል። በጎንደር እና ሌሎች የጎጃም አካባቢዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድም ታውቋል። የኦሮሚኛ ተናጋሪ የፖለቲካ መሪዎች ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ጦርነት በህወሓት ተቋማት ላይ ለማድረግ እቅድ ነድፈው ወደ ስራ ለመግባት እንደተዘጋጁም ተሰምቷል።

ከህወሓት ጋር የፖለቲካ እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ያላቸው ወገኖች ያላአግባብ በመበልጸግ ሃገሪቷን ዘርፈዋል የሚል ተደጋጋሚ ክስ ከኢትዮጵያውያን ይሰነዘራል። ከጥቂት አመታት በፊት ኤፈርትን ጨምሮ ህወሓት እንደፓርቲ የሚያንቀሳቅሳቸው የንግድ ተቋማት ብቻ ከአምስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚገመቱ ባለስልጣናቱን በመጥቀስ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከዚህ በፊት የህወሓት ቁልፍ ሰው ናቸው ከሚባሉት ከስብሃት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስብሃት ህወሓት ግዙፍ ሃብት እንዳካበት ሳይደብቁ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ትላንት ቅሊንጦ እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት በቀለ ገርባን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች ባለፉት ጥቂት ወራት ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሶስት ቀን የሃዘን ቀን እንዲታወጅ እና ኢትዮጵያውያን ጽጉራቸውን በመላጨት የተገደሉትን ንጹሃን ኢትዮጵያውያን እንዲያስቡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን በመቀበል ጽጉራቸውን በመላጨት እና የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውን የተቃውሞ ምልክት የሆነውን የተሳሰረ እጂ በፎቶግራፍ በማሳየት ለጥሪው ምላሽ ሰጥተዋል።
ቦርከና14012564_10205198112430990_355381106_o

ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ለመውሰድ የህወሀት ደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት ያደረገው ዘመቻ ከሸፈ።


የሰሜን ጎንደር ዞን አድማ በታኝ ም/አዛዥ ኢንስፐክተር መልካሙ የሺዋስ ረዕቡ ዕለት ከስራ ተሰናበቱ። በአንገረብ ወህኒ ቤት ኮ/ል ደመቀን ለመውሰድ የተከፈተውን ዘመቻ ያከሸፈው የሰሜን ጎንደር ልዩ ሃይል አካል የሆነው የአድማ በታኝ ጦር ም/አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ ”ህዝባችን ላይ አንተኩስም” በማለት የሚመሩትን ጦር አቋም እንዲይዝ አድርገዋል። በዚህም ከስራ ተባረዋል። ጦሩ ግን ከጎናቸው ነው።
13702300_10205044758677242_799614874_o

Monday, August 29, 2016

አመፅ ቀስቃሽ ናቸው የተባሉ መጻሕፍት በመሸጥ የተጠረጠሩ አዟሪዎች ታሰሩ

14037783_10205234208373366_1048345346_o


ኅብረተሰቡን ለአመፅ የሚገፋፉና ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ መጻሕፍት በማዘዋወርና በመሸጥ የተጠረጠሩ መጽሐፍት አዟሪዎች፣ ከነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መታሰራቸው ታወቀ፡፡


ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ መጻሕፍት አዟሪዎች በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች መታሰራቸውንና በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ቤተሰቦቻቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አዟሪዎቹ የተጠረጠሩት ሕዝብ የሚያነሳሱና አመፅ የሚቀሰቅሱ መጣጥፎችን በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በማተም ክስ ተመሥርቶበት የሦስት ዓመታት ጽኑ እስራት የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ በቅርቡ ‹‹የፈራ ይመለስ›› በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፍ፣ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ‹‹የኦሮሞና አማራ የዘር ግንድ›› በሚል ርዕስ ያሳተሙት መጽሐፍና ጋዜጠኛ ሙሉ ቀን ተስፋው ‹‹የዘመኑ ጥፋት›› በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፍ በማዞር ሲሸጡ ስለተገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ቀደም ብሎ ክስ ተመሥርቶበትና ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት የተጣለበትን መጣጥፍና በድጋሚ በመጽሐፍ መልክ ያሳተመውን መጽሐፍ ማሠራጨት ወንጀል መሆኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱ ታውቋል፡፡ ሌሎቹም የተጠቀሱት መጻሕፍት አመፅ ቀስቃሽ መሆናቸውን በመግለጽ መሠራጨታቸው ተገቢ አለመሆኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቶ፣ መጻሕፍቱ ሲታተሙ ያተማቸው ማተሚያ ቤት በመጽሐፉ ላይ መግለጽ የነበረባቸው ቢሆንም ሳይገልጹ መቅረታቸውንም አክሏል፡፡ ይኼም ሆን ተብሎ መንግሥት ቁጥጥር እንዳያደርግ በድብቅ የሚሠራ ሕገወጥ ተግባር መሆኑን በማስረዳት፣ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ ተገልጿል፡፡

የተወሰኑ አዟሪዎች መጻሕፍቶች ተነጥቀው ሁለተኛ እንዳያዞሩ ፈርመው መለቀቃቸውንና ማተሚያ ቤቱን እንዲጠቁሙ ተገደው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መጻሕፍት አዟሪዎች ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ታውቋል፡

Sunday, August 28, 2016

በታላቁ የአባይ ወንዝ መነሻ በሰከላ ወረዳ ህዝብ ስልጣን ተረከበ

ከ22-12-2008 ጀምሮ በአደባባይ ላይ ባደረገዉ ትልቅ አመፅ ከዳር እስከዳር ወያኔን አንቀጠቀጠ ህዝቡ በድንጋይ የወያኔን መሳሪያ መከተ አንድነት ሃይል ነዉ በማለት በቀላል ዘዴ ወያኔን ከመሃል አድርገዉ አጣበቁት ከመሬት! እስረኞች ተፈቱ……………
በአደባባይ ከብአዴን ቢሮ ሰይጣኒዝሙ ባንዲራ ወርዶ ከእግዚያብሄር የተላከልን አባቶች የተሰዉላት ሰንደቅ በከፍታ ተዉለበለበች የወያኔ ታፔላ ሁሉም ተገነጠላ!
በዛን ሰአት ወያኔ በአስገባቸዉ ሰዉ በላ የጥይት ዶፍ በሰዉ ላይ ተከፈተ ህዝቡ ተበተነ ሁሉም በወኔ ምሽግ ያዘ! እንደገና ህዝቦ ተነሳ ”ነፃነት በነፃ አይገኝም” የሚል ሞፎክር አሰሙ! በዚ የተበሳጩት የወያኔ ቅጥረኞች ወጣቱን በጥቁር መዝገብ ላይ አሰፈሩ!
በ23-12-2008 እንደገና በጠዋቱ ተጀመረ የግሽ አባይ ምድር በ ሰንደቅ አሸበረቀ ሽንፈት በቃን አለ! የአባይ ወንዝ አጉረመረመ ሰማዬ ጠቆረ ህዝብ ስልጣን ተረከበ! በአሁኑ ሰአት በአገር ሽማግሌ እየተመራች ነዉ! ድል ለህዝብ ነዉ ትግላችን ይቀጥላል.
13942395_10205155496405616_1008799724_n

በርካታ ኢትዮጵያውያን በህወሃት/ኢህአዴግ ሃይሎች ለተሰው ዜጎች አጋርነታቸውን ለማሳየት ጸጉራቸውን እንደተላጩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ


ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008)
በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጋግሎ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በመንግስት ሃይሎች ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን አጋርነታቸው ለማሳየት ጸጉራቸውን መላጨታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
ኢትዮጵያውያን ጸጉራቸውን ሲላጩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ደረገጾች መለቀቃቸውን ያወሳው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት፣ የጸጉር መላጨት ድርጊት የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑን አስረድቷል።
በኢትዮጵያ ጸጉር መላጨት ሃዘንን መግለጽ ነው ያለው ሌላው የዚምባብዌ ጋዜጣ፣ ድርጊቱ በኦሮሞያና በአማራ ክልሎች በመንግስት ሃይሎች በተደረጉ ግድያዎች የሞቱትን ዜጎች ለማስታወስ የተደረገ መሆኑን ገልጿል።
በኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ከ500 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የገለጸው የአሜሪካ ሬዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት፣ ህዝባዊ ተቃውሞውን ያስተባብራሉ የተባሉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጭምር በጨለማ ወህኒ ቤት መወርወራቸውን አብራርቷል።
በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች መጠየቃቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ብሄራዊው የሃዘን ቀን በኦሮሚያና የአዲስ አባባና ፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንንነትና የድንበር መካለል ጉዳይ፣ በጋምቤላና በደቡብ ክልሎች፣ በኮንሶ ብሄረሰብ እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቷ ክፍሎችም የስርዓቱን አፈና በመቃወም ጥያቂያቸውን አንግበው አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ ዘግናኝና ጅምላ ጭፍጨፋ ለማስታወስ እንደታወጀ በእስር ቤት የሚገኙ እነ አቶ በቀለ ገርባ መጥራታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል ተገደለ

በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ ሲል የትህዴን ድምጽ ዘግቧል:: በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው ህዝብ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ ምክንያት በግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ተሳስሮ ሰዎች ሊጠረጥሩት ሞክረው ህዝቡ ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ምክንያት ገዳዩ ሳይታወቅ ዝምታን እንደመረጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በተመሳሳይ- በሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ሳዕስዕ ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ደስታ ጎቢጥ የተባለ የቀድሞ ታጋይ ባልታወቁ ሰዎች ነሃሴ 13 2007ዓ/ም በድንጋይና በዱላ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ተገድለዋል እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከአካባቢው ካድሬዎች ጋር ስምምነት ያልነበራቸውና ጥቅም ያጣላቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አክሎ ገልጿል።
13819494_611651515666849_1114674654_n

Saturday, August 27, 2016

ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ብራዚል ድረስ ሄደው ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጥብቅና እንደሚቆሙ ቃል ገቡ

አስደሳች ዜና – ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ብራዚል ድረስ ሄደው ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጥብቅና እንደሚቆሙ ቃል ገቡ
ጴጥሮስ አሸናፊ እንደዘገበው
ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ታላቅ ድል ካስመዘገበና ህወሃትና ታማኝ ጦሩ የሆነው አጋዚ በኢትዮጵያውያን በተለይም በታላላቆቹ የኦሮሞና አማራ ብሔረሰቦች ላይ የሚያካሂዱትን የዘር ማጥፋት፣ የመግደል፣ የማሰር፣ የመጨፍጨፍ፣ የማዋከብና የማሳድድ ተግባርን በአለም አቀፍ መድረክ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦች በኦሎምፒክ አደባባይ ከፍ አድርጎ በማሳየቱ የሃገራችን ሕዝቦች፣ የሃገራችን ወዳጆችንና በአምባገነኖች የሚረገጡና የሚጨቆኑ ጥቁር አፍሪካውያንን ያኮራ ታሪካዊ ጀግንነትን በመፈፀሙ ገድሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በአራቱም መዐዘን በመገናኛ ብዙሃን እየተነገረለት ይገኛል።
የወንዶች ማራቶን ውድድር በታላቁ የኦሎምፒክ መድረክ የመዝጊያ ቀን የሚካሄድ እንደመሆኑና ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የተሳታፊ ሃገሮች ተወዳዳሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላትም ወደየሃገራቸው ለመመለስ የሚዘጋጁበት ጊዜ በመሆኑ የኢትዮጵያን ኦሎምፒክ ቡድን የሚመሩት የህወሃት አባላት ጀግናውን አትሌት እንዳያዋከቡትና ወደ ሃገር ቤት እንዲመለስ ጫናና ግፊት እንዳያደርጉበት ኢትዮጵያውያንና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት አፋጣኝ እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመጎትጎት ላይ ይገኛሉ።
የጉዳዪን አሳሳቢነትና የሕዝባችንን ስጋት በመረዳት አሁን ማምሻውን በአጭር ጊዜ የተዋቀረ አለም አቀፍ ግብረ ሃይል አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ላይ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ያለውን የሙያተኞች ስብስብ በማስፋት ለጀግናው አትሌት የአለንልህ ጥሪውን ለማሰማት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በታላቅ ደስታ ይገልፃል።
እስካሁን መቀመጫቸውን በአሜሪካን ሃገር ሲያትል ዋሺንግተን ያደረጉት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ እንደ አጋጣሚም ፓስፖርታቸው ላይ የብራዚል ቪዛ ስላላቸው በራሳቸው ወጪ ወደ ሪዮ በመሄድ ለጀግናው አትሌት በነፃ ጠበቃው ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ሌሎችም የሕግ ባለሙያዎች እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።
የህወሃት መንግስት በነገው ዕለትና በመጪዎቹ ቀናት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ወደ ብራዚል እንደሚልክና ከብራዚል መንግሥት ተወካዮችም ጋር ግንኙነቶችን እንደጀመረ ምንጮች እየጠቆሙ ቢሆንም የብራዚል መንግሥት ሰላማዊ ዜጎችን በአደባባይ በጥይት ለሚገድለው ህወሃት አዎንታዊ መልስ ይሰጣል ተብሎ አይገመትም።
የህወሃት መንግሥት ከሁለት አመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን የመንገደኞች አውሮፕላን በመጥለፍና ጄኔቫ ስዊዘርላንድ በማሳረፍ የሥርአቱን ገመና ያጋለጠውን ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራን ከስዊዘርላንድ ወደ ኢትዮጵያ በማስመለስ ለማሰቃየትና ለመግደል አድካሚ የዲፕሎማሲ ጥረት ቢያደርግም በስዊዘርላንድ መንግሥት ጥያቄው በተደጋጋሚ ውድቅ እንደተደረገበትና የስዊዘርላንድም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኃይለመድኅንን በነፃ እንዳሰናበተው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች የህወሓትን መንግስት እየገመገሙ ነው::


በህወሓት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማቶች እየተገመገመ መሆኑ ተሰማ፡፡ በአዲስ አበባ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ ከልዩ የፖሊስ ኃይል በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ያለው የታጠቀ መከላከያ ሠራዊት ከተማዋን ወርሯት ነበር፡፡ ትላንት ይካሔዳል ተብሎ እቅድ ተይዞለት የበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ለዜጎቻቸው የተጠንቀቁ መልዕክት ያስተላለፉት የምዕራብ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ ወቅታዊውን የሀገሪቱን ሁኔታ በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግስት የተነሳበት ህዝባዊ ተቃውሞ በከፍተኛ መጠን እንደከበደው ይታያል፡፡ ከዚህ ቀደም በተወሰነ የፖሊስ ኃይል ይቆጣጠራቸው የነበሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች አሁን ላይ መከላከያ ሠራዊት እስከማሰለፍ አድርሶታል፡፡›› ሲሉ የገለጹት ዲፕሎማቶቹ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በመደጎም ግንባር ቀደም የሆኑ ሀገራት፣ ስርዓቱ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ወደ ድርድር እንዲገባ ግፊት ለማድረግ ነገሮችን እየገመገሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ፤ የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ዊስሊ ሬድ ‹‹ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማ እንደሚፈልጉ ተመልክተናል፡፡ በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉት እና በጎዳና ላይ ሰልፍ የወጡ ዜጎች እርስ በእርስ እንዲደማመጡ አሳስባለሁ፡፡ ሀሳቡን በመግለጹ ብቻ ማንም ሰው መሞት የለበትም፡፡›› ሲሉ አዲስ አበባ ተገኝተው አሳስበዋል፡፡
ሚስ ዌስሊ ሬድ ያስተላለፉት መልዕክት ሀገራቸው አሜሪካ በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያላትን አቋም የሚያመለክት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም እስከሚቀጥለው የካቲት 2017 ድረስ የሚቆይ የጉዞ እና የደህንነት ማስጠንቀቂያ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከተቃዋሚዎቹ ጋር ለድርድር እንዲቀመጥ ምዕራባውያን ሀገራት ጫና ለማድረግ እንደተዘጋጁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቢቢን

Friday, August 26, 2016

በፌዴራልና ክልል ከተሞች መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ተነገረ

በፌዴራልና ክልል ከተሞች መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ተነገረ
ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008)
በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና ክልሎች መደበኛ መንግስታዊ አገልግሎቶች በመስተጓጎላቸው የህዝቡን ምሬት እያባባሱ እንደሆነ ተገለጸ።
አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና የልል መንግስታዊ ተቋማት በመዘዋወር መረጃውን ያደረሱን የኢሳት ምንጮች፣ በመንግስታዊ ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚሄዱ ነዋሪዎች አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ በመፈጠሩ በስርዓቱ ላይ መማረራቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች በህዝባዊ እምቢተኝነቱ ምክንያት መንግስታዊ መዋቅሩና ጽ/ቤቶቹ በመዘጋታቸው መደበኛ ስራዎችና አገልግሎቶች ጭምር መቋረጣቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። በተለይም በጎንደር፣ ጮሂት፣ ጎርጎራ፣ ቆላድባ፣ ባህርዳር፣ ማጀቴ የመሳሰሉ አካባቢዎች የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ሁኔታ መፈጠሩ ታውቋል።
በየአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሹመኞችና ሰራተኞች ከነሃሴ 8 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ መንግስት የተነተሳብኝን ተቃውሞ ለማርገብ ያስችለኛል በሚል በየአዳራሹ በስብሰባ እየተጠመደ መሆኑን መመልክታቸው ገልጸዋል።
በስብሰባው የመንግስት ሰራተኞች የአካባቢውን ባለስልጣናት እና ካድሬዎችን “ህዝብ አንፈልጋችሁም ብሏል ለምን ስልጣናችሁን አትለቁም?” በሚሉ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን አስጨንቆ እንደያዛቸው ምንጮቻችን በስፍራው በመገኘት ለመታዘብ መቻላቸውን ገልጸዋል።
የየአካባቢው ባለስልጣናት ካድሬዎች ችግሩን የፈጠሩት “የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የማይቀበሉ የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” በማለት ውጫዊ ለማድረግ ቢሞክሩም የሰራተኛውን ጆሮ ለማግኘት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
በኢትዮጵያ የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥልና ሊስፋፋ እንደሚችል ባሳለፍነው ሳምንት የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

 2c159-avereg

በአዲስ አበባና በጎንደር ጉዟቸውን ሲጠባበቁ የነበሩ 9ሺ ቤተ-እስራዔላውያን ወደ እስራዔል ሊጓዙ ነው


ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008)
የእስራዔል መንግስት በቅርቡ እንዲዘገይ ያደረገውን እና ተቃውሞ አስነስቶ የነበረውን የዘጠኝ ሺ ቤተ-እስራዔላውያንን ጉዞ ከሶስት ወር በኋላ እንደሚጀምር ይፋ አደረገ።
በጎንደር እና አዲስ አበባ ከተሞች ለአመታት ጉዟቸውን በመጠበባቅ ላይ የንበርሩ ቤተ እስራዔላውያን በፊታችን ህዳር ወር ጀምሮ ወደ እስራዔል መግባት እንደሚጀምሩ የሃገሪቱ የቤተ እስራዔላውያን ኤጀንሲ መግለጹን ታይምስ ኦፍ እስራዔል የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
የእስራዔል የፋይናንስ ሚኒስቴር ወደ ዘጠኝ ሺ አካባቢ የሚጠጉትን ቤተ እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ በጀትን ያጸደቀ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በበጀት እጥረት በሚል ጉዞው እንዲዘገይ መደረጉ ይታወሳል።
ይሁንና፣ የሃገሪቱ መንግስት ያስተላለፈውን ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ በእስራዔላውያን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱ ከበጀት ችግር ጋር የተያያዘ ሳይሆን፣ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ከመጣው የዘረኝነት ጉዳይ ጋር የተገናኘ ነው በማለት ተቃውሞ ሲያካሄዱ ቆይተዋል።
ከኢትዮጵያውያኑ የቀረበውን ተቃውሞ ተከትሎ የእስራዔል ባለስልጣናት ጉዳዩን ዳግም በማጤን ቤተ እስራዔላውያን እንዲያጓጉዙ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ታውቋል።
ከመጪው ህዳር ወር ጀምሮ በየወሩ 100 የሚሆኑ ተጓዦች ወደ እስራዔል ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የጉዞ ሰነዳቸው ያለቀላቸው 90 ቤተ-እስራዔላውያን በቅርቡ ወደ ሃገሪቱ እንደሚገቡ ባለስልጣናት ለእስራዔል መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃገራቸው በጎንደር እና አዲስ አበባ ከተማ ለጉዞ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ቤተእስርዔላውያን በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥ እንደምታጓጉዝ ይፋ አድርገው እንደነበር የሚታወስ ነው።
የእስራዔል የገንዘብ ሚኒስቴር ወደ ዘጠኝ ሺ አካባቢ የሚሆኑትን ቤተ እስራዔላውያን ወደሃገሪቱ በማጓጓዝና ለማቋቋም ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ላይ ናቸው።
ከቤተሰቦቻቸው የተቆራረጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የእስራዔል መንግስት ጉዞው እንዲፋጠን በማድረግ ለአመታት ሲጠበበቁት የነበረው ጉዳይ ዕልባት እንዲያገኝ ጥሪ እያቀረቡ መሆኑም ታውቋል።
በተለያዩ ጊዜያት ወደ እስራዔል የተጓዙ ከ130ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ እንደሚኖሩ መረጃዎች የመለክታሉ።2c159-avereg

ስንታየሁ ቸኮል ያለበት ሊታወቅ አልቻለም!







ነሐሴ 16 ቀን 2008 ዓ.ም አራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርቦ በዋስ እንዲወጣ ብይን የተሰጠው ስንታየሁ ቸኮል፣ ከእስር ካለመለቀቁ በተጨማሪ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ያለበት ቦታ ሊታወቅ አልቻለም። በትላንትናው ዕለት የአራዳ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ስብሃት ገ/መድህን ከእስር ሊለቀቅ ያልቻለበትን ምክንያት በማስመልከት ላነሳልናቸው ጥያቄ “ሌላ የሚፈልገው አካል ስላለ ልንለቀው አንችልም!” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል። የሚፈልገውን አካል ማንነት ከመናገር የተቆጠቡት ኃላፊው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስንታየሁን ማዘዋወራቸውን በዛሬው ዕለት ገልፀውልናል። ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ ስንታየሁ፣ ወደዛ መዘዋወሩን ለማጣራት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የዕለት ሁኔታ ኃላፊ የሆኑት ሳጅን ለምለም አደምን፣ ያነጋገርን ሲሆን ስንታየሁ ቸኮል የተባለ እስረኛ ወደእነሱ አለመዘዋወሩን ገልፀው ወደ አረዳ ፖሊስ መምሪያ ሄደን እንድንጠይቅ ነግረውናል። ሁለቱም አካል እኛ ጋር የለም ማለታቸውን ተከትሎ ወደፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በማቅናት ወደዛ መዘዋወሩን ብንጠይቅም “እንደዚህ የሚባል እስረኛ አልተዘዋወረም!” የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል። (እዮኤል ዳምጤ)

Thursday, August 25, 2016

“የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይል እና የሚሊሻ ጦር ሰራዊት አባላት ሆይ! የምትሞቱት ለማን ነው?” ከአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ


አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በረሃ ወርዶ ነፍጥ በማንሳት ወደ ጦርት የገባው ተገዶ ነው፡፡ ያስገደደውም ተፋላሚው ቡድን አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ አገዛዝ ነው፡፡ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አገዛዝ ምን፣ ምን አይነት ግፍ እና በደል እያደረሰ እንደሚገኝና ምን አይነት መንግስታዊ ስርዓት እያራመደ እንዳለ ለእናንተ ለመከላከያ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለልዩ ኃይልና ለሚሊሻ ጦር ሰራዊት አባላት መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ምክንያቱም እናንተም የአገዛዙ የግፍ ሰለባ ሌላኛው አካል ስለሆናችሁና ፍዳውን እያየ ከሚገኘው ህዝብ አብራክ ስለተከፈላችሁ የህዝቡ ብሶት ብሶታችሁ ስለሆነ ነው፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የሚዋጋው በጉልበት ስልጣን ይዞ በመንግስትነት ስም ኢትዮጵያን እያዋረደ፣ ህዝቧን እየገደለ እያስገደለ፣ እያሰረ፣ እያሰደደ፣ እያስራበ እና እያሳረዘ የሚገኘውን ህወሓት የሚሰኝ ዘረኛ ቡድን በኃይል ደምስሶ ህዝቡን ብቸኛው ሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት ለማድረግ በማለም ነው፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 ህወሓትን በጥይት በመደብደብ ገድሎ ጉድጓዱን አርቆ በመቆፈር ከቀበረው በኋላ የሽግግሩን ሂደት ከማገዝና የህዝቡ የስልጣን ባለቤትነት በተግባር እንዲረጋገጥ ከማድረግ ውጭ በምርጫ ተወዳድሮ የመንግስት ስልጣን የመያዝ ዓላማ ፈፅሞ የለውም፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞካራሲ ንቅናቄ ስልጣን የህዝብ እና የህዝብ ብቻ አንዲሆን አንጂ አምርሮ የሚታገለው መንግስት የመሆን ምኞት ኖሮት አይደለም፡፡ በታሪክ እስካሁን ከተደረጉት የነፃነት ትግሎች የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ትግል ልዩ የሚያደርገው አንዱና ዋነኛው ጉዳይ ይሄ ነው፡፡
እኛም እናውቃለን፣ የኢትዮጵያ ህዝብም ያውቃል፣ እናንተም ታውቃላችሁ የአገሪቱን ሀብት እየዘረፉ በብልፅግና ላይ ብልፅግና እየተጎናፀፉ፣ ከመኪና መኪና እያማረጡ፣ በዲዛይነር የተሰራ ሱፍና ከረባት እየለበሱ፣ ጮማ እየቆረጡ ዊስኪ እየተራጩ፣ የተንደላቀቀ የቤተ መንግስት ህይወት የሚመሩት የህወሓት ባለስልጣናት ወደ ስልጣን ሲመጡ ምንም የከፈሉት ዋጋ የለም በድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ደም እንጂ፡፡ አሁንም ስልጣናቸውን ማስቀጠል የሚፈልጉት የደሃውን ህዝብ ልጅ ለጦርነት በማሰለፍ በእሱ ደም እንጂ እነሱና ዘመድ አዝማዶቻቸው ምንም የሚከፍሉት ዋጋ አይኖርም፡፡
መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ሆይ! በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሞትክ፣ በሶማሊያ ጦርነት ሞትክ፣ ኦጋዴን፣ ጋምቤላ፣ ሚዛን ቴፒ፣ አርማጭሆ… ላይ ደጋግመህ ሞትክ አሁን ደግሞ ትግራይ ክልል ውስጥ እየሞትክ ትገኛለህ፡፡ በአንተ ክቡር ህይወት፣ በአንተ ደምና አጥንት፣ በአንተ ታሪክ… ሊወድቅ የዘመመው የህወሓቶች የስልጣን ደሳሳ ጎጆ ለጊዜውም ቢሆን ተደግፎ ቆሞ አየህ እንጂ ለአንተ፣ ለቤተሰብህ፣ ለአገርህ ኢትዮጵያ፣ ለበቀልክበት ህዝብ ምን አተረፍክ? ባንተ ሞት እነማን ሹመትና ሽልማት እንዳገኙ ኑሯቸው እንደ ተቃና አንተው ራስህ ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ፡፡ የምትሞተው አንተ፤ የምትዋረደው አገርህ ኢትዮጵያ፤ የሚረገጠው የወለደህ ህዝብ፤ የምትሞትለት መልሶ እየገደለህ የሚገኘው አንተው ራስህን ነው፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረው ጦርነት የጥቃት ስልቱን እየቀያየረ ከህወሓት አድማስ ረቀቅና ወሰብሰብ ባለ መልኩ በኢትዮጵያ አራቱም ማዕዘናት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ነገር ግን ፍልሚያው አንደኛው ጭቆናን ለማስወገድ ሌላኛው ጭቆናን ለማስቀጠል ሲባል ጎራ ለይተው በተሰለፉ ሁለት ጭቁን ወንድምአማች ኢትዮጵያዊያን መካከል መሆኑ ግን አርበኞች ግንቦት ሰባትን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡ በመሆኑም ህወሓት በእናንተ ሞት ነግሶ ለመኖር አስታጥቆ ለእርድ ያሰለፋችሁ የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይል እና የሚሊሻ ጦር ሰራዊት አባላት የታጠቃችሁትን ጦር መሳሪያ አፈሙዝ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የእናንተ ጠላት ወደሆነው ህወሓት እንድታዞሩ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ አለበለዚያ ግን የምትከፍሉት ዋጋ ከመቸውም ጊዜ በላይ በእጅጉ የከፋ ነው የሚሆነው፡፡ ጦርነቱ በጣም ፈታኝ፣ ይህ ነው ተብሎ በቃላት ሊገለፅ የማይችል ዋጋ የሚያስከፍል፣ እስካሁን በተለያዩ ቦታዎችና ወቅቶች ሲደረግ ከነበረው የጎሬላ ውጊያ የተለየ የረቀቁ የውጊያ ስልቶችን የሚከተል መሆኑን ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፣ ማይ ሰገል፣ በዋል፣ ጓንጋ አሳግላ እና ማይ እምቧ ላይ በተደረገው ጦርነት በየዋህነት ተማግደው የተረፉ ጓዶቻችሁ ካሉ ጠይቃችሁ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡
ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብ በጠቅላላ አንቅሮ የተፋው የበሰበሰ ስርዓት መሆኑንም እንድታስታውሱ አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባችኋል፡፡
ዘረኛው የህወሓት ቡድን ያቋቋመው መንግስት በቅርቡ ብትንትኑ መውጣቱ አይቀርም የእናንተ ለስልጣኑ መጠበቂያ አሽከርነት ያቆማችሁ የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ ሰራዊት አባላት ከንቱ ሞት ግን አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄን ከወዲሁ በእጅጉ ያሳስበዋል ያሳዝነዋልም፡፡ ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች ሞት ለዘረኛውና ፋሽስቱ ወያኔ!

13942395_10205155496405616_1008799724_n

Wednesday, August 24, 2016

ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጠየቀ


ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሃገሪቱ የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና እስራትን በመቃወም የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እሁድ በሪዮ ኦሎምፒክ የተቃውሞ መልዕክቱን ያስተላለፈው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ጥሪውን አቀረበ።
እሁድ በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ስለሆነ የተቃውሞ ድርጊቱ ከኢሳት ጋር ቆይታን ያደረገው አትሌት ሌሊሳ በተለይ አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶች የገዢው የኢህአዴግ መንግስትን ግድያ እና አፈና በመቃወም ተመሳሳይ ድርጊትን እንዲወስዱ ጠይቋል።
ካገኘሁት ሜዳሊያ ይልቅ ያስተላለፍኩት መልዕክት ደስታን ሰጥቶኛል ሲል የገለጸው አትሌቱ እጁን በማጣመር ተቃውሞን በአለም አደባባይ ማቅረቡ ሃላፊነትን የመወጣት ድርጊት እንደሆነ አስታውቋል።
“ከአሁን በኋላ ብሞትም አይቆጨኝም ሲል በወሰደው እርምጃ እጅግ ደስተኛ መሆኑን የተናገረው አትሌት ሌሊሳ፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተረባርቦ ይህንን ስርዓት ማስወገድ አለበት” በማለት ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረገው ቃለምልልስ አስረድቷል።
በመንግስት እየተፈጸመ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለመግለጽ ቃል ያጥረኛል ያለው ወጣቱ አትሌት የታሰሩ ዘመዶቹን ለመጠየቅ እስር ቤት በሚመላለስበት ጊዜ በሚያየው ሁኔታ ሲያዝን መቆየቱን አስታውቀዋል።
ለሪዮ ኦሎምፒክ ከመታቀፍ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ያለውን ግድያና እስራት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማጋለጥ በዝግጅት ላይ እንደነበር የገለጸው ሌሊሳ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን እየረገፉ እንደሆነ አክሎ አስረድቷል።
ከባለፈው አመት ጀምሮ በበርሊንና ቶኪዮ ከተሞች በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድልን ተቀናጅቶ የነበረው አትሌት ሌሊሳ እሁድ በሪዮ ኦሎምፒክ በመዝጊያ ዝግጅት ወቅት በተካሄደ የማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል።
ይሁንና ወጣቱ አትሌት በእለቱ ያስተላለፈው ተቃውሞ ከድሉ ይልቅ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ ሰፊ ሽፋንን እንዲያገኝ ያደረገው ሲሆን፣ ሰኞ ድረስ በርካታ የአለም አቀፍ መገኛና ብዙሃን ድርጊቱን ሲዘግቡ ውለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሪዮ ስላለው ሁኔታ የተጠየቀው አትሌቱ ከተለያዩ ሃገራት በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ያላቸውን ድጋፍ እየገለጡለት እንደሚገኝና በጥሩ ስነልቦና ውስጥ መሆኑን ከዜና ክፍላችን ጋር በነበረው ቆይታ ገልጸዋል።
ዋሽንግተን ፖስት፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ቢቢሲ፣ ሮይተርስ፣ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ዴይሊ ሜይልን ጨምሮ ከ20 የሚበልጡ አለም አቀፍ አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና ጋዜጠኞች አትሌቱ የወሰደውን ድርጊት በማስመልከት በኢትዮጵያ ስላለው ተቃውሞ ሰፊ ዘገባን አቀርበዋል።

 2016 Rio Olympics - Athletics - Final - Men's Marathon - Sambodromo - Rio de Janeiro, Brazil - 21/08/2016. Feyisa Lilesa (ETH) of Ethiopia celebrates.   REUTERS/Athit Perawongmetha

Tuesday, August 23, 2016

ከ መቶ በላይ አለም አቀፍ ሚዲያዎች የ ሰሞኑን ትግል በአትሌት ፈይሳ በተያያዘ በስፋት ዘግባዋል

#‎ፈይሳ‬ ‪#‎ሌሊሳ‬ ይሄን ምልክት በኦሎምፒክ ባያሳይ ኖሮ የተቀረው አለም ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ችግር ሊሰማ እንደማይችል #ፎክስ ኒውስ የተሰኘው እና ከአለማችን ትላልቅ የዜና ዘገቢዎች መሃከል ስሙ ጎልቶ የሚወጣው ድርጅት ስለ ፈይስ ሌሊሳ እንዲህ ሲል ዘግቧል...  መቼም ብሄራዊይ ጀግናችን ለአለም ያሰማልንን የወያኔን ዘግናኝ ጭቆናና ግድያ የአለም ሚድያዎች 10,000 ኢትዮጵያንን እንኳ ፋሽስቱ ህዋሓት በገድል አይጮሁልንም ነብር ።ሽር አድርጉ ለጀግናዊ አትሌት ፋይሳ ሌስሳ
ይህ በእንድህ እንዳለ ከመቶ በላይ የአለማችን ታላላቅ ሚድያዎች ስለ ፈይሳ ሌሊሳ በስፋት ዘግባዋል እነሆ ተመልከቱ
100 Media reported on # Feyisa_Lilesa

1.www.washingtonpost.com
2.www.nytimes.com
3.www.cnn.com
4.europe.newsweek.com
5.www.theguardian.com
6.www.independent.co.uk
7.www.csmonitor.com
8.www.letsrun.com
9.www.nbcchicago.com
10.www.dailynews.com
11.www.nation.co.ek
12.www.nknews.org
13.www.latimes.com
14.www.huffingtonpost.com
15.www.standard.co.uk
16.www.dailymail.co.uk
17.www.cosmopolitan.com
18.www.sportingnews.com
19.www.si.com
20.www.espn.com
21.www.nbcnewyork.com
22.www.smh.com.au
23.www.usatoday.com
24.www.mirror.co.uk
25.www.flotrack.org
26.runningmagazine.ca
27.www.ibtimes.co.uk
28.www.bustle.com
29.www.foxnews.com
30.m.france24.com
31.www.irishtimes.com
32.www.the-star.co.ke
33.mashable.com
34.reuters.com time.com
35.www.runnersworld.com
36.www.jeuneafrique.com
37.www.wsj.com
38.www.bbc.com
39.www.thenational.com
40.fusion.net
41.www.globalnews.com
42.nzherald.co.nz
43.time.com
44.rrstar.com
45.allafrica.com
46.addisstandard.com
47.bbcafrica.com
48.focusafrica.com
49.www.youtube.com
50.opride.com
51.qz.com
53.www.upworthy.com
54.www.telegraph.co.uk
55.www.sbnation.com
56.www.abc.net.au
57.www.newsweek.com
58.deadspin.com
59.mic.com
69.www.yahoo.com
70.www.dailydot.com
71.www.voanews.com
72.www.infobae.com
73.www.dailymaverick.com
74.www.elsalvador.com
75.www.thesun.co.uk
76.uproxx.com
77.www.ledauphile.com
78.www.trackarena.com
79.zeenews.india.com
89.www.pri.org
90.www.givemesport.com
91.indianexpress.com
92.www.rfi.fr
93.www.lapresse.ca
94.www.lavanguardia.com
95.www.businessinsider.com
96.www.mediapart.fr
97.www.lastampa.it
98.ici.radio-canada.ca
99.www.sopitas.com
100.www.japantimes.co.jp
Via Xiixaa Buubaa Sardaa

2 አትሌቶች የወያኔን መንግስት ያጋለጡበት የኦሎምፒክ መድረክ -ዘአብርሃም


አትሌት  ፈይሳ ሌሊሴ እንዴት አድርጎ የወያኔን መንግስት አሳሪነት እንዳሳየ  እየተደመምን  እስቲ ደሞ አትሌት  ዮናስ ክንዴ የተባለ  ሌላ ጀግና እንዴት አድርጎ  በሪዮ ኦሎምፒክ  የወያኔን መንግስት አሳዳጅነት እንዳጋለጠ  እንመልከት።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ  በአለም ላይ ተሰደው የሚገኙ ሀገር አልባ ስደተኞችን ለማስታወሰ እና እነሱንም ወክሎ ከሌሎች ሀገራት እኩል የሚወዳደሩ 43 ሰዎችን በመጋቢት ወር መረጠ። ከነዚህም ውስጥ ስደተኛ በጣም የሚሰደድባቸው ሀገራት በሚል መስፈርት ከተለዩት ውስጥ ከሶርያ ጀርመን ና ቤልጅየም  የገቡ 2፣ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ  ወደብራዚል የተሰደዱ 2፣ ከደቡብ ሱዳን ኬንያ ካኩማ የስደተኞች ካምፕ የተጠለሉ 5 አትሌቶችና ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓዊቷ ሉግዘምብርግ የተሰደደው ዮናስ ክንዴ   በድምሩ 10 አትሌቶች ሪዮ ዴጄነሮ ብራዚል ለኦሎምፒክ ውድድር  አመሩ። ከመክፈቻው ዕለት አንስቶ ይዘውት የነበረው የተሰደዱበትን ሃገር ባንዲራ ሳይሆን   አምስቱ  ቀለበቶች ያሉበትን ነጩን የኦሎምፒክ አርማ ባንዲራ ነው።የሚወክሉት ሃገር ኣልባ የሆነውን ስደተኞችን ነው። Refugee Olympic Team/ROT/ በሚል መጠሪያ።
ቀውሱ በጣም ከፍተኛ ከሆነባቸው ከሶርያ አትሌቶች ፣ ከደቡብ ሱዳን ከ ደሞክራቲክ ኮንጎ   እኩል የዚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በሰደተኛች ቡድን መታቀፍ ሲዘገብ ከረመ። በአንጻሩ ከትዮጵያ የተሰደዱ ወገኖች  ያሳደዳቸው ምክንያት ከእነዚህ ሶርያዎች ወይም ደቡብ ሱዳኖች እኩል እንደሆነ ታየ። የወያኔው መንግስት እንደ ኮንጎዎቹ ዘረኛና እኩይ መሆኑ ተመሰከረ።



በዉሃ ዋና ትግሬ በመሆኑ ብቻ ተመርጦ ዉሃ ውስጥ  ያዋረደን የሮቤል ጉዳይ   በአለም ሚዲያ ሲዘገብ ከሰደተኞቹ ውስጥ ሁለቱ ሶርያውያን ራኒ ኣኒስ እና ያሱራ ማርዲኒ በሴቶች ውሃ ዋና ተወዳዳሪ ነበሩ።በአስራ ሰባት አመቷ  ከሶሪያ ተሰዳ  ከእህቷ ጋር  በባህር ሊሰምጡ የነበሩ 20 ሌሎችን በዋና ጠበቧ ታድጋ ጀርመን በርሊን የደረሰችው ይችው የሰደተኞች ተወካይ አትሌት  ተንደላቆ ተዳልቶለት በ አባቱ ዳኝነት ከተመረጠው  የሕወሃቱ ቦርጫም ዋናተኛ  ሮቤል የበለጠ ተዘግቦላታል።ስደተኞች ተዘግቦላቸዋል።        ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ረፐብሊክ ወደ ብራዚል  የተሰደዱት  ሁለቱ በጁዶ ስፖርት ሲሳተፉ ፣አምስት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሩጫ ሲወዳደሩ ሁሉ   የኢትዮጵያ ስም በስደተኛ አበርካችነቷ እየተጠራ ነበረ። እነ ፈይሳ ሌሊሴ በሪዮው ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ተብለው  ሰማቸው  ሲተዋወቅ  ዮናስ ክንዴ ከኢትዮጵያ ግን በሃገር አልባ ስደተኞች ማልያ  በማራቶን ተሰለፈ። ሁለት ኢትዮጵያውያን አንዱ በመንግስት ተወክሎ አንዱ በመንግስት ተፈናቅሎ። ዞሮዞሮ  ኢትዮጵያን ወክሎ ሁለተኛ የወጣው አትሌት እሱም ሰደተኛነቱን አስመሰከረ የታሰሩ የተገደሉ  የኦሮሞያ የጎንደር ወገኖቹን ደም ሲቃ እያየ ወደ ወያኔው የአትሌቶቹ ካምፕ መሄድ አልወደደም። በይፋ የለም ህዝብ በሙሉ በትኩረት እያየው ኢትዮጵያውያን ታስረዋል አለ። የኢትዮጵያ መንግስት አሳዳጅነት እና አሳሪነት ወትሮዉኑም ሲታወጅ የቆየ ነው አሁን ሰበብ ተገኘ።
ኤስቢ  ኔሽን የተባለው የዜና አውታር << Bringing athletes from war-torn countries to Rio>>  በጦርነት ከፈረሱ
ሃገሮች የመጡ አትሌቶች በሚል ርዕስ ስር  ነሃሴ መጀመሪያ ሳምንት ላይ ያወጣውን  ሃተታ በማየት ብቻ እንደምንረዳው   ከሶርያ ፣ከደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ እኩል ኢትዮጵያም በጦርነት ስር እንዳለች ለ አለም አስነብቧል።
የተባበሩትን መንግስታት የስደተኞች መስሪያ ቤትን ጠቅሶ  ኤስቢ  እንዲህ ሲል  << The civil war in Syria has been driving an outright refugee crisis in Europe. The United Nations Refugee Agency says there are 4.8 million Syrian refugees, plus an estimated 8.7 million people displaced inside Syria this year. Its count of refugees and asylum-seekers from South Sudan is 850,000. In the Democratic Republic of the Congo, it is more than 384,000 refugees and more than a million internally displaced persons. There are more than 700,000 Ethiopian refugees. This is just a sampling.>> ሰባት መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ የሚለው ይሄ የመጨረሻው አረፍተ ነገር የወያኔን መንግስት አጋኖ አጋለጠው እንዳንል እነ ቢቢሲ ሲኢኤን ኤን ኣልጀዚራ ወዘተ የተባሉት ዝነኛ ሚድያዎች ሳይቀሩ ኢትዮጵያን ከጎንደር ኦሮሚያ አመጽ እስከ ሪዮ ኦሎምፒክ የ አትሌቶች አመራረጥ አድልዎ እያብጠለጠሉ የመንግስትን ሙስና ሲዘግቡ ነበሩ።
በተለይ የሶርያ ቀውስ ጉዳይ አለም ኣቀፍ አጀንዳ ከመሆኑ ጋር እና ሁለት ሴት አትለቶቹ በዉሃ ዋና ሪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከተሳተፉ ቀን ጀምሮ የእያንዳንዱ ስደተኛ አትሌት የስደት መንስኤ በስፋት ተራግቧል። በሁሉም ዜናዎች የኛው አትሌት ዮናስ ክንዴ በፖለቲካ ምክንያት ከሃገር መባረሩን እና ለአትሌቶች ምቹ መንግስት እንደሌለ የገለጸው ለመላው አለም ህዝብ አይን እና ጆሮ ደርሷል።
በሉግዘምብርግ በታክሲ ሹፌርነት ኑሮውን የሚገፋው የ36አመቱ   ዮናስ 2ሰዓት ከ17 ደቂቃ ምርጥ የማራቶን ሰዐቱን በፍራንክፈርት በግል ያስመዘገበ ሲሆን  በሪዮው ኦሎምፒክ  ዘጠናኛ ወጥቶ  ስደተኞች  ከማንም እንደማያንሱ  አትሌቶችን ወክሎ የተናገረው ይጠቀስለታል።
ታዋቂው ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስሩ አትለቶች ከ ስልሳ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በ አለም ላይ የተበተኑ ስደተኞችን ይወክላሉ ሲል ከአስሩ ስድስቱ ወንዶች  አራቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም በሃገራቸው ባለ ግጭት  የተነሳ የተሰደዱ ናቸው  በማለት የአሜሪካው ኒውዮርከር  ድረገጽ ደሞ አትቷል። ኢትዮጵያዊው ዮናስ ክንዴ ከ ኢትዮጵያ የተሰደደው በ2013 ሲሆን በዛ ወቅት  አስከፊ ግጭት ነበረ ካለ በአሁን  ሰኣት ደሞ ያለውን ጄኖሳይድ ምን ብሎ ህወሃትን እንደሚያብጠለጥለው መረዳት አይከብድም ።http://www.newyorker.com/news/sporting-scene/the-refugee-olympians-in-rio
The ten team members—six men and four women—were announced in June. All have fled conflicts in their home countries. There are two swimmers from Syria, two judokas from the Democratic Republic of Congo, a marathoner from Ethiopia, and five middle-distance runners from South Sudan.
ህወሃት ወያኔ በሁሉም ቦታ ተዋረደ  አይቀናውም። በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አብዮትም በውጪ ሀገራትም። በሃገር ውስጥ ህዝቡ
በአንድነት ተነስቷል።  ከእንግዲህ ዘረኛ መንግስት ይብቃን ፋሺስት ወያኔ ይወገድ ብሏል ከጫፍ እስከ ጫፍ።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለህወሃት ያደሩ ካድሬዎቹ አምባሳደሮቹ ሳይቀር  የወያኔን ኤምባሲ ከድተው ለቀዋል። ህወሃት በየፊናው  እየተፍረከረከ ስለመሆኑ ከነሱም  ምስክር ሞልቷል። በውጭው ሃገራትም የህወሃት መንግስትን የሚያወግዙ ሰልፎች በኢትዮጵያውያን እየተስተጋባ ነው።
ሌላው የአለም ህብረተሰብም ገመናውን ከተረዱት ቆዩ።  ከነዚህም የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን  በ አማራ ክልልና እና ኦሮሚያ ክልል በግፍ ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን አጣሪ ኮሚቴ ይመደብ ማለቱ ፥ ግድያውንም እነ ቢቢሲ እና ሌሎች ተደማጭ ሚዲያዎች እያሳበቁት መሆኑ የሚጠቀስ ሲሆን የ አለም አይንና ጆሮ በሙሉ ወደ ብራዚሉ ኦሎምፒክ ትኩረት ባደረገበት ወቅት ላይም የዚህን አምባገነን መንግስት አሳሪነት በማራቶን ሁለተኛ የወጣው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ እጁን በማሳየት ተናግሯል። እየደጋገመ የዘገበውም ይሄንን ነው።
bbc marathon
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ  አመት ጀመረው ይሄ የ አለም ስደተኞችን ራሳቸውን ወክሎ ማወዳደር የሚበረታታ ተግባር መሆኑን  በመቶዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች አድንቀውታል። በዛው ልክ የተጠቀሱት ሃገራት ሶርያ፣ደቡብ ሱዳን፣ዲ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ያለባቸው የመንግስታት ችግር ሙስና በመላው አለም ታውቋል።
በዘንድሮው ኦሎምፒክ ከምንግዜውም በተለየ ህወሃት አንገቱን የደፋበት ሆኖ በማለፉ ደስ ይለናል።
እስከመጨረሽው ህወሃትን በአለም አቀፉ መድረክ እናጋልጣለን
ዘአብርሃም  ከጀርመን

Ethiopian marathon star cross his wrists in Rio to show solidarity with his people protesting a brutal regime

Ethiopian marathon star cross his wrists in Rio to show solidarity with his people protesting a brutal regime

feyisa lilesa 2
Photo: AP
Feyisa Lilesa
Photo: AFP
By Engidu Woldie
ESAT News (August 21, 2016)
Feyisa Lilesa crossed the finish line in the Olympic marathon on Sunday in Rio winning silver for his country and crossing his wrist above his head showing solidarity with his people protesting a brutal regime.
Feyisa later told journalists that he was showing the crossed wrist in solidarity with his fellow countrymen and women who were killed daily in his home country. “I was protesting for my people,” Feyisa was quoted by several media outlets as saying on Sunday.
He crossed his wrist high in the air one more time at the podium and told the crowd that more than a thousand people were killed in just nine months by the ruthless regime back in his country for demanding basic rights.
He told the press that he knew his actions would not be taken lightly by the tyrannical regime and he may face death or imprisonment if he were to return home.
“If I go back to Ethiopia maybe they will kill me. If I am not killed maybe they will put me in prison. [If] they [do] not put me in prison they will block me at airport,” he was quoted as saying by several international media outlets.
The silver medalist said he might consider moving to another country. “I have got a decision. Maybe I move to another country,” he told journalists.
Feyisa also ceased the opportunity to remind Western allies of the tyrannical regime that their support was enabling the killings in his country.
“It is a very bad government. Now America, England, France support this government when they give this support it buys machine guns then they kill the people,” said Feyisa who is now in the hearts and minds of Ethiopians fighting a ruthless regime.

በባህርዳር የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

በባህርዳር የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ
ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
በቅርቡ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጸሙ ድርጊቶችን በማውገዝ በተለያዩ ተቃውሞ ውስጥ የቆዩ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች እሁድ የጀመሩት ከቤት ያለመውጣት አድማ ሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ለኢሳት አስታወቁ።
ህዝበ ውሳኔ ተላልፎበት ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው ይኸው አድማ የከተማዋ ነዋሪ በመንግስት የሚፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን በፅኑ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።
የከተማዋ ነዋሪ የወሰደውን አድማ ተከትሎ የባህርዳር ከተማ ሙሉ ለሙሉ ጭር ብላ የምትገኝ ሲሆን፣ አድማውን በጣሱ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በነዋሪው ዘንድ ስምምነት መደረጉን እማኞች አስታውቀዋል።
ከቤት ያለመውጣቱንና የስራ ማቆም አድማውን በጣሱ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ እማኞች አስታውቀዋል።
ከቤት ያለመውጣቱና የስራ ማቆም አድማ መደረጉን ተከትሎ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ የግልና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ስራ አቁመው እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።
ከሁለት ሳምንት በፊት የከተማዋ ነዋሪ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ ለመግለጽ አደባባይ በወጣ ጊዜ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሃይል እርምጃ በበህር ዳር ከተማ ብቻ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በጎንደር ከተማ የተፈጸመን ግድያ በመቃወም የከተማዋ ነዋሪዎች ባለፈው ሳምንት የሶስት ቀን ከቤት ያለመውጣት አድማ ሲያደርጉ መቆየታቸውም የሚታወቅ ነው።
እሁድ በአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህርዳር ከተማ የተጀመረው ከቤት የለመውጣት አድማ እንዲያበቃ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ ቅስቀሳን ቢያደርጉም ነዋሪው እምቢተኛ መሆኑን ከነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል።
በባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በመካሄድ ላይ ያሉ ሰላማዊ ተቃውሞዎች በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው በየከተሞቹ ያሉ ነዋሪዎች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።
የተለያዩ አለም ቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሁለቱ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆናቸውን በመግለጽ ላይ ሲሆን ለወራት በኦሮሚያ ክልል ከዘለቀው ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በአጠቃላይ ከ500 በላይ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች ይገልጻል።

 

Sunday, August 21, 2016

ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘ – እጁን ወደላይ በማጣመር ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳየ

በሪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አገኘች:: ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በኬኒያዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ተቀድሞ 2ኛ ቢገባም ውድድሩን በሚያጠናቅቅበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ  ባለፈው 10 ወራት ካለማቋረጥ እየተጠቀመበት ያለውን እጅን ወደላይ ማጣመር በማሳየት ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳይቷል::

በዚህ የማራቶን ውድድር አሜሪካዊው ግሌን ሩፕ 3ኛ ሲወጣ ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረስላሴ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል::
ኬንያዊው አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ 2:08:44 ሲፈጅበት ኢትዮጵያዊው ፈይሳ 2:09:54 ገብቷል:: 3ኛ የወጣው አሜሪካዊው ግሌን 2:10:05 በመግባት 3ኛ ሆኗል::
ፈይሳ ዛሬ በብዙ ሚሊዮኖች በተከታተሉት የኦሎምፒኩ ሜዳ ላይ እጁን ወደላይ አጣምሮ መንግስትን መቃወሙና ከሕዝብ ጎን አጋርነቱን ማሳየቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የሰብ አዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲያደርጉበት የራሱን ጫና ያሳድራል::
 Lalisa

Saturday, August 20, 2016

ኢትዮጵያ የእርሻ ምርቷ ክፉኛ ጉዳት እንደሚደርስባት ተመድ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የእርሻ ምርቷ ክፉኛ ጉዳት እንደሚደርስባት ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008)
በተያዘው አመት የዝናብ እጥረት ምክንያት ለድርቅ አደጋ የተጋለጠችው ኢትዮጵያ፣ ዳግም በሚከሰት የቅዝቃዜ የአየር ንብረት ለውጥ የእርሻ ምርቷ ክፉኛ ጉዳት እንደሚደርስባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።
ሃገሪቱን ከጥቅምት ወር ጀምሮ ይመታታል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ለውጥ የእርሻ ምርት እንዲቀንስ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለምግብ ድጋፍ ይዳርጋል ሲል ድርጅቱ ማክሰኞ ባወጣው ማሳሰቢያ አመልክቷል።
ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ የገለጹት በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ የሆኑት አማዱ አላሁሪ በጥቅምት ወር ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ቀዝቃዛ የአየር ለውጥ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ጉዳትን ያስከትላል ተብሎ ስጋት መኖሩን እንዳሳሰቡ የአፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
በተያዘው አመት በስድስት ክልሎች ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ከ10 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መጋለጣቸው ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ድርቁ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ርብርብ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ ዳግም በቅዝቃዜ ሳቢያ ይደረጋል የተባለው የሰብል ምርት ችግሩን የከፋ ያደርገዋል ተብሎ ተሰግቷል።
በድርቁ ምክንያት የዘር እህሎቻቸውን ላጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የተለያዩ የእርሻ ግብዓቶችን ለማቅረብ በቀጣዮቹ አራት ወራቶች ብቻ ከ90 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሚያስፈልግ የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።
በሃገሪቱ ተከስቶ ያለው የድርቅ ጉዳት ለመቅረፍ ኢትዮጵያ አስቸኳይ የሆነ አለም አቀፍ ድጋፍን ትፈልጋልች ሲሉ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ የሆኑት አማዱ አላሁሪ አክለው አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ወደ አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት ተጋልጠው የሚገኙ ሲሆን፣ ከተረጂዎቹ መካከል ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸው ታውቋል።
ለምግብ እጥረቱ ተጋልጠው ከሚገኙት ስድስት ሚሊዮን ህጻናት መካከል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት በከፋ የምግብ እጥረት የተነሳ የአካልና የጤና ችግር እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ የመለክታል።
የአለም አቀፍ ተቋማት ድርቁ ወደ ከፋ ደረጃ ይሸጋገራል የሚል ተደጋጋሚ ስጋትን ቢገልጹም መንግስት ችግሩን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ነው ሲሉ ምላሽን ሰጥቷል።

Friday, August 19, 2016

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ጠየቁ

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ጠየቁ
ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008)
በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች ጠየቁ።
በአቶ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በጋራ ተጽፎ ለኢሳት የደረሰው ደብዳቤ፣ “ብሄራዊ የሃዘን ቀን የሚታወጀው የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ አንግበው የተሰው ወገኖቻችንን በልባችን ውስጥ ህያው ሆነው እንደሚኖሩ ለማረጋገጥና እነሱም የወደቁለትን አላማ በትግላችን እንደምናሳካው ቃል ለመግባት እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውም አጋርነታችንን ለማሳየት ነው” ሲል ያስረዳል።
በኦሮሚያና የአዲስ አባባና ፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንንነትና የድንበር መካለል ጉዳይ፣ በጋምቤላና በደቡብ ክልሎች፣ በኮንሶ ብሄረሰብ እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቷ ክፍሎችም የስርዓቱን አፈና በመቃወም ጥያቂያቸውን አንግበው አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ ዘግናኝና ጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄዷል እየተካሄደም ይገኛል ያለው ይህ ደብዳቤ፣ በዚህ የነጻነት ጥያቄ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች “ለሶስት ቀናት ከነሃሴ 19-21 ብሄራዊ የሃዘን ቀና በማወጅ እናስባቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ይላል።
“እኩልነት በህገ-መንግስቱ ተረጋግጧል ተብሎ በሚነገርበት ዘመን በተደጋጋሚ ህጋዊ ጥያቄዎችን አንግበው አደባባይ የወጡ ዜጎች በትግላችን ዴሞክራሲ አምጥተናል” በሚሉ ገዢዎች ትዕዛዝ በአደባባይ በጥይት ሲደበደቡና ድምጻቸው በአፈሙዝ ሃይል ሲፈተን ከሁለት አስተር አመታት አስቆጥሯል ያለው ከቂሊንጦ የወጣው ደብዳቤ፣ እንዳለመታደል ሆኖ በሃገራችን የገዳዮች ጀግንነት እንጂ የሟቾች ንጹህንነትና በግፍ መገደል የሚነገርበትና የሚጻፍበት ዕድል ባለመኖሩ ለህዝብ ጥያቄዎች ሲባል ህይወታቸውን ካሳለፉ ሰዎች መካከል ህይወታቸው በሰውለት ህዝብ የሃዘን ቀን ተወስኖላቸው እየታሰቡ የሚገኙ ጥቂቶች ሆኗል ብሏል።
በንጹህነታቸው በሞቱ ዜጎች ላይ ማላገጥና እነሱንም መኮነን እጅግ አሳፋሪ ታሪክ የማይረሳው ድርጊት በማለት የህወሃት/ኢህአዴግን ድርጊት የኮነኑት በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች፣ አምባገነን መሪዎች እነዚህ ንጹሃን ህይወታቸውን የሰውለትን ጥያቄ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ በሚቆጣጠሯቸው መገናኛ ብዙሃን በዜጎች ላይ የወሰዱት እርምጃ ትክክል እንደሆነ ህዝቡን በማስፈራራት ስራ ተጠምደዋል ሲል ከሷል።
የሃዘን ቀን በታወጀባቸው ሶስት ቀናት፣ ኢትዮጵያውያን ጥቁር የሃዘን ልብስ በመልበስ የፌስቡክ ፕሮፋይላቸውን በጥቁር ወይም በሟች ወገኖቻችን ፎቶ በመቀየር፣ በተሽከርካሪዎች ላይ ጥቁር ጨርቅ በማውለብለብ፣ የሻማ ማብራት ፕሮግራሞች የፓናል ውይይቶቻን በጋራ የህሊና ጸሎቶችን በማከናወን፣ በሃገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሟቾች ቤት በመሄድ አጋርነታቸው በመግለጽ፣ እንዲሁም በተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የተገደሉ ዜጎችን ሙሉ መረጃ እና ፎቶ በማህበራዊ ድረገጾች በተከታታይ በመለጠፍ የመንግስት ጥቃት ሰለባዎችን እንዲያስቧቸው ጠይቋል።
በተጨማሪም፣ “ህዝቡ ሃዘኑን እንዳያደርግ ለማስተጓጎል የሚደረጉ የመንግስት ተጽዕኖዎችን በተለያዩ የምስልና የድምፅ መረጃዎችን ለህዝብ በማቅረብ ለፍትህ ለነጻነትና እኩልነት ሲሉ ህይወታቸውን በሰጡ ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፈለን” ሲሉ እስረኞቹ ከቂሊንጦ ወህኒ ቤት በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያውያን የወገኖቻችን ህይወት የተሰዋበት አላማ እስኪሳካ ድረስ ትግሉን እንዲቀጥል በጋራ ቃል መግባት እንደሚኖርባቸው እስረኞቹ በዚህ ደብዳቤ ጠይቀዋል።

ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ካናዳ፣ አውሮፕላ እንዲሁም አፍሪካ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግድያና እስር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚደረገውን ግድያና እስር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008)
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ካናዳ፣ አውሮፕላ እንዲሁም አፍሪካ የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በመቃወም በሳምንቱ መገባደጃ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ።
በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማና አካባቢው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ህዝቡ ያቀረበውን ሰላማዊ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽን እንዲያገኝ ጠይቀዋል።
ሰላማዊ ጥያቄን እያቀረቡ ካሉ ዜጎች ጎን መቆማቸውን ሲገልጹ ያረፈዱት ሰልፈኞቹ በመግንስት የጸጥታ ሃይሎች እየተወሰደ ያለው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆምና መንግስት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ አስታውቀዋል።
ነዋሪነታቸው በአውሮፓዊቷ አገር ስዊድን መዲና ስቶኮልም ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መልኩ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍን በማካሄድ በተለያዩ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች በመፈጸም ላይ ያለን ግድያ አውግዘዋል።
በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ በካናዳ ኤድመንተን ከተማ እንድሁም በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ የምገኙ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መልኩ የተቃውሞ ዝግጅቶችን እንዳካሄዱ ከየከተሞቹ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመልክቷል።
በካናዳዋ ኤድመንተን ከተካሂደው የተቃውሞ ዝግጅት በተጨማሪ፣ ከካልጋሪ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ዝግጅት ሰሞኑን እንዳካሄዱ ተባባሪ ባልደርባችን ጸጋዬ ቦሬ ከስፍራው ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በዚሁ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በመቃወም ነዋሪነታቸው በብሪታኒያ ለንደን ከተማ እንዲሁም በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ሰኞች እንደተካሄደ አዘጋጆች ለኢሳት አስታውቀዋል።
በሁለቱ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመውንና እየፈጸመ ያለውን ግድያ በመቃወም ድርጊቱን እንደሚያወግዙ የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዳቀረቡ ታውቋል።
በሁለቱ ክልሎች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ተከትሎ ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ የሚናፖሊስ ግዛት ሚኔሶታ ከተማ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የተቃውሞ ትዕይንቶች መካሄዳቸው ይታወሳል።
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሁለቱ ክልሎች በተፈጸሙ የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ለወራት በኦሮሚያ ክልል በሰነበተው ተቃውሞ ከ400 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን አለም አቀፍ ተቋማት ይገልጻሉ።


 

የህዝብን የነፃነት ጥያቄ በጠመንጃ ማፈን አይቻልም!

ለዘመናት በአንድነቱና በነፃነቱ ጸንቶ የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ሃገር በቀል ወራሪዎች ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በመሪር አገዛዛቸው ሲቀጠቀጥና ሲታሰር፣ሲገደልና ሲሰደድ የአንድ ትውልድ ዕድሜ ነጉዷል። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእሳት ወደረመጡ እንዲሉ ዛሬ በዓለም መድረክ ሰቆቃ ከሚፈጸምባቸው ህዝቦች ቀዳሚው ነው ብንል አልተጋነነም።ትናንት በአባቶቻችን ዕድሜ ነጻነታቸውን ያገኙ የአፍሪካ ሃገራት ህዝቦች ነጻነትና ዲሞክራሲን ሲያጣጥሙ እኛ በባርነትና በጭቆና እየማቀቅን ለመሆኑ ዋቢ መጥራት አያስፈልገንም። ሃገራችን የጥቂት አምባገነኖች ንብረት ሆና ህዝባችን በረሃብና በበሽታ እንዲማቅቅ ተፈርዶበት፣ልጆቹ እንጀራ ፍለጋ በየሃገሩ ተሰደው ለአውሬና ለባህር ብሎም ለነፍሰ በላ አሸባሪዎች ህይወቱን የገበረው በዚህ ዘረኛ አገዛዝ ዘመን ነው። በየእስርቤቱ የሚማቅቁት ወገኖቻችን ሁሉ ለነጻነትና ለፍትህ በመሟገታቸው በፈጠራ ወንጀል ተከሰው በአድር ባይ ዳኞች ፍርደ ገምድል ውሳኔ በየማጎርያ ቤቱ የስቃይ ኑሮ የሚገፉት ለህዝባችን መብትና ነጻነት መረጋገጥ መሆኑን እንገነዘባለን። እኛም ከእናት ሃገራችን በግፍ ተሰደን በዩጋንዳ የምንኖር ስደተኞች በደረሰብን ወከባ ፣ስቃይና እንግልት ለስደት ተዳርገን የመከራ ህይወት የምንገፋው ሃገር አልቦች ሆነን ሳይሆን በዕኩልነትና በፍትሃዊነት የሚያስተዳድረን የመረጥነው መንግስት ባለመኖሩ ነው። ዛሬ ላይ በሃገራችን የተቀጣጠለው የህዝብ ብሶት የዘመናት የፍትና የርትዕ ዕጦት መሆኑንም እንረዳለን። ህዝቡ በወረቀት ላይ በሰፈረው ህገመንግስታዊ መብት ጥያቄዎቹን በማቅረቡ ገዢው ሃይል የሰጠው ምላሽ ጅምላ ግድያና እስር መሆኑ በዚህ ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን በጉልበት ህዝብን አንበርክኬ እገዛለሁ ማለት ትላንት በሰሜን አፍሪካ ተቀጣጥሎ የነበረው ህዝባዊ ማዕበል የቱንዚያን ንጉሳዊ አገዛዝ እንዳስወገደ፣የግብጹን ሆስኒ ሙባረክና የሊቢያውን ሙአመር ጋዳፊ ከተጣበቁበት ወንበር አሽቀንጥሮ ለውርደትና ሞት እንዳበቃ የወያኔ መንግስት እንዴት መገንዘብ እንዳቃተው ለሁላችንም እንቆቅልሽ ነው። የገዛ ህዝብን በሰራዊት ብዛት አስጨንቆና አሸማቆ ለዘመናት መግዛት አይቻልም።የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ አስተናግዶ ምላሽ መስጠት እንጂ በመሳርያ ተማምኖ ህዝብን መፍጀት መንግስት ከሆነ አካል የሚጠበቅ ተግባር ሳይሆን የአሸባሪዎች ድርጊት ነው። በመላ ኦሮሚያ ከመንፈቅ በላይ በዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ወጣት ተማሪዎችን በጥይት በመደብደብ ህዝባዊውን ንቅናቄ አዳፍናለሁ የሚለው የወያኔ የጉልበት ርምጃ ችግሮችን ከማባባስ በስተቀር የፈየደው ነገር የለም።ዛሬ ደግሞ መላው አማራ በደረሰበት ግፍና በደል ተማሮ አደባባይ በመውጣቱ ወገኖቻችን በግፍ እየተጨፈጨፉ መሆኑን በዓለም መገናኛ ብዙኃን እየተከታተልን ነው። በማንኛውም ወገናችን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ ፣እስርና ማሳደድ አጥብቀን እናወግዛለን።በሰላማዊው ህዝባችን ላይ በማን አለብኝነት ፍጅት እንዲካሄድ የሚያደርጉትን ወገኖች ከአፈራሽ ተግባራቸው ተቆጥበው የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ በሃይል በመጨፍለቅ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም እንደማይቻልና ውድቀትንም እንደሚያፋጥን ከታሪክ እንዲማሩ እናሳስባለን። በመላ አለም ላይ ያሉ ለሰዎች ልጆች ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆሩና የሚሟገቱ መንግስታት፣ሃገራትና ተቋማት እንዲሁም የዓለም መገናኛ ብዙሃን በህዝባችን ላይ የሚፈጸመው ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ከህዝባችን ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እያቀረብን በአምባገነኖች ትዕዛዝ ክቡር ህይወታቸውን ለተነጠቁ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ስንገልጽ ለዲሞክራሲና ነጻነት መረጋገጥ የህይወት ዋጋ የከፈሉ ሁሉ ጀግኖች ሰማዕታት በመሆናቸው በታሪክ መዝገብ ስራቸውና ስማቸው ህያው ሆኖ እንደሚኖር ጽኑ እምነታችንን ለመግለጽ እንወዳለን። በሰው ሃገር በስደት የምንኖር ወገኖች የመንከራተት ዘመናችን አብቅቶ ከህዝባችን ጋር ዳግም ተገናኝተን በነጻነት ፣በፍቅርና በአንድነት እናት ኢትዮጵያን ወደነበረችበት የክብር ሥፍራ ለመመለስ እንድንችል የአምላክ ፈቃዱ እንዲሆን ከልባችን እንመኛለን።

በዩጋንዳ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ማህበር ነሐሴ 9 ቀን 2008 ዓ/ም (ኦገስት 15, 2016)

wanted officials