Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 28, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም እንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ ነው

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም እንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አሥራ ስድስት ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞና ተቃውሞውን ተከትሎ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በእያመቱ ከ3 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ ገቢ የሚያስገኘውን የቱሪዝም እንዱስትሪ ክፉኛ እንደጎዳው ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።
ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ችግር የሌለባቸው በመሆኑ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚችሉ ቢናገርም፣ የውጭ አገር የአስጎብኝ ድርጅቶች አማካሪዎች ግን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በሁዋላ ሁኔታው አስፈሪ በመሆኑ ቱሪስቶች እንዳይጓዙ መክረዋል።
አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ ፣ እንግሊዝና ሌሎችም የአውሮፓ አገራት ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ያወጡት ማስጠንቀቂያ ገዢውን ፓርቲ በእጅጉ ያበሳጨው ሲሆን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቱሪስቶችን አይመለከትም የሚል መግለጫ አውጥቷል። ማንኛውም ዜጋ ዋና ዋና በሚባሉት መንገዶች እንዳይጓዝ ታግዶ ባለበት ወቅት እንዲሁም ቱሪስቶች ጉዳት ሲደርስባቸው እርዳታ ለመስጠት የሚችሉ የኢምባሲ ሰራተኞች ከአዲስ አበባ 40 ኪሎሜትር ውጭ እንዳይወጡ ታግደው በሚገኙበት ወቅት አዋጁ ቱሪስቶችን አይመለከትም መባሉ ግራ አጋብቷል።
የቨርሲክ ማፕል ክሮፍት የአደጋ ተንታኝ የሆኑት ኢማ ጎርዶን ፣ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ጸጥ ያለ ቢመስልም፣ ተቃውሞው ግን አልቆመም ብለዋል። የስራ ማቆም አድማ፣ ከተሞችን ሰው አልባ ማድረግ፣ እና ሌሎችም ሰላማዊ ትግሎች አሁንም ድረስ እየተካሄዱ መሆኑን የገለጹት ተንታኟ፣ እነዚህን ድርጊቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ሆነ በፖሊስ ለማስቆም እንደማይቻል ገልጸዋል።
ተቃውሞውን የሚያካሂዱ ወገኖች እንዴት አድርገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደሚቋቋሙት መላ ከዘየዱ በሁዋላ፣ በተለይም ማህበራዊ ሚዲያ መዘጋቱን፣ የፖለቲካ ውይይት መከልከሉንና ስብሰባ ማከሄድን አለመቻሉን አስመልክቶ መፍትሄ ከፈለጉ በሁዋላ አመጹ እንደገና ሊካሄድ ይችላል ብለዋል።  የውጭ አገር ኩባንያዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ተከትሎ በአገር ውስጥ በመቆየትና በመልቀቅ መካከል እየዋዠቁ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials