Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 16, 2017

በዶ/ር ደብረጺዮንና ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መደባደባቸው ተነገረ






በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።

ባለፈው ሰኞ አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት፣ “ዶ/ር ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለአቶ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ዶ/ር ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣ አቶ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ።

እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን፣ በመሃሉ ዶ/ር ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በአቶ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን፣ አቶ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር አቶ በረከትና አቶ ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።


በዶ/ር ደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው አቶ ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።

የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials