Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 25, 2017

በአቶ ደመቀ መኮንንና በዶ/ር ደብረጺዮን መካከል የተጀመረው ጥል ወደ ሃይል እርምጃ ተሸጋገረ

በአቶ ደመቀ መኮንንና በዶ/ር ደብረጺዮን መካከል የተጀመረው ጥል ወደ ሃይል እርምጃ ተሸጋገረ
በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።
ባለፈው ሰኞ አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት
“ዶ/ር ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለአቶ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ዶ/ር ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣
አቶ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ። እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው ፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን ፣ በመሃሉ ዶ/ር ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በአቶ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን ፣ አቶ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር አቶ በረከትና አቶ ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
በዶ/ር ደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው አቶ ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም ” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን ፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።
የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials