Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, August 6, 2017

የአባባ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ መድረክ ውስጥ የቆዩትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለይም በልጆች ፕሮግራም እጅግ ታዋቂ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ በ93 አመታቸው ባለፈው እሁድ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሲፈጸም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
አቶ ተስፋዬ ሳህሉ በተዋናይነት፣በግጥምና ዜማ ጸሃፊነት እንዲሁም በድምጻዊነት በኪነጥበብ ዘርፍ ውስጥ ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
የዛሬ 11 አመት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተባረሩትና ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ በዚሁ ተቋም ለ42 አመታት ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ ሰኔ 20 ቀን 1916 በቀድሞው መጠሪያው በባሌ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ ኮዶ በተባለ ስፍራ መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
ከአባታቸው ከአቶ ኤጀርሳ በዳኔና ከእናታቸው ወይዘሮ ዮንዢ ወርቅ በለጠ የተወለዱት አባባ ተስፋዬ በኪነጥበብ መስክ እንዲሁም በልጆች ፕሮግራም ላደረጉት አስተዋጽኦ ከቀድሞው ንጉስ አጼ ሃይለስላሴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልመዋል።
በ1950ዎቹ በኮሪያ ዘመቻ በሙያቸው ላደረጉት አስተዋጽኦና በዘመቻው ተሳታፊ በመሆናቸውም የሃምሳ አለቅነት ማእረግ እንደተበረከተላቸው በቀብር ስነስርአታቸው ላይ የተነበበው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
በሙያቸው ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ከኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ከአለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ያገኙት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ የ2 ልጆች አባት ነበሩ።5 የልጅ ልጆችንም አይተዋል።
እኚህን አንጋፋ፣ ባለሙያና ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ረቡእ ከቀትር በኋላ 9 ሰአት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።Image may contain: 1 person, smiling

No comments:

Post a Comment

wanted officials