Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 31, 2018

አርበኛ መሳፍንት ‹‹በወልቃይት ጠገዴ ያልተነገረና የኢትዮጵያ ህዝብ በውል ያላወቀው መጠን የለሽ በደል ተፈፅሟል›› አሉ

Image may contain: 1 person, standing and outdoor


አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ህወሀት በትጥቅ ትግሉ ወቅት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረውን ግፍ በመቃወም በረሃ ገብተው ህወሃትን ሲፋለሙ በትግራይ የጉድጓድ እስር ቤት ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል፡፡ ይሁንና እስር ቤቱን ሰብረው በመውጣት እድሜያቸውን ሙሉ ሲፋለሙ የቆዩት እኚህ አርበኛ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ሰምተው በቅርቡ ከበረሀ ወጥተዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግል ጓዶቻቸውን ይዘው ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ወደጎንደርና ባህር ዳር መምጣታቸውን ከዚህ ቀደም በዘሃበሻ ዜናዎቻችን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አርበኛ መሳፍንት ዛሬ ለንባብ ከበቃውና በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ከሚዘጋጀው በረራ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡
በዚህ ቃለምልልስ ትግል ስለጀመሩበት ምክንያት ሲገልፁ ‹‹የህወሃት ሰዎች ለአካባቢው ህዝብ ያላቸው እይታ ገና ከጠዋቱ ጀምሮ በጥላቻ የተሞላ ነበር፡፡ በአማራ ላይ የነበራቸው ጥላቻ ጫፍ የደረሰ ስለነበር አንተ የመሳፍንት ዘር፣ የጨቋኝ ቤተሰብ ስለሆንክ ነው መሳፍንት የተባልከው እያሉ በጥላቻ ያዩኝ ነበር›› ካሉ በኋላ በዚህ መልኩ በእሳቸውና በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ሲበዛ በ22 አመታቸው ወደትግል መውጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ በትግል ትንሽ ከቆዩ በኋላ በህወሀት እጅ ወድቀው የስቃይና የመከራ ጊዜ እንዳሳለፉ የተናገሩት አርበኛ መሳፍንት መስከረም 17 ቀን 1981 ከለሊቱ ስምንት ሰአት አምልጠው እንደወጡም ገልፀዋል፡፡
ከእስር አምልጠው ዳባት ርቀው እየኖሩ እያለ ህወሀቶች በ1983 አገሪቱን እንደተቆጣጠሩና መሳሪያቸውን እንዲያወርዱ ተስማምተው የግብርና ኑሯቸውን ጀምረው እንደነበር አስረድተዋል፡፡ ይሁንና ግብርና እንደጀመሩ የቢሮክራት ልጅ ተብለው እርሻቸው እንደተቀማባቸው የተናገሩት አርበኛው ይህን በደል ችለው በመኖር በ1997 ቅንጅትን ወክለው ምርጫ መወዳደራቸውንም ያወሳሉ፡፡ በምርጫው በዳባት ሙሉ በሙሉ ምርጫውን ማሸነፉን ተከትሎ አፈሙዝ ሲነሳባቸው በድጋሚ ለትግል ወደበረሃ መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡ በረሃ ከገቡ በኋላም በህዳር ወር 1999 ህወሀት ሽፍታ በመላክ ልታስገድላቸው እንደሞከረችና በተአምር እንደተረፉ ያስረዱት አርበኛ መሳፍንት ሲናገሩ ‹‹ህዳር 19 ቀን 2009 ይፋዊ ውጊያ በህወሃት ተከፍቶብኝ ከእነሱም ከእኛም ወገን በርካታ ሰው ሞቷል፡፡ በዚያ ውጊያ የምወደው አባቴ ተታኩሶ በኋላም ተገድሎብኛል፡፡ እኔም ከብዙ ጡርነት ነው ያመለጥኩት›› ብለዋል፡፡ በዚህ ውጊያ ህወሃት ዲሽቃና ከባድ መሳሪያ ሁሉ ተጠቅሞ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
አሁን በምን ስምምነት ከበረሃ ወጥተው ከተማ እንደገቡ ሲጠየቁ በሰጡት ምላሽ ደግሞ ‹‹መሬት የያዘ ነገር የለም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል አመራሮች ከውጭ አገር እስኪመለሱ እየጠበቁ መሆኑን የተናገሩት አርበኛው ከበረሃ የመጣው ወጣት ሀይል እየተንገላታ በመሆኑም ቅሬታቸውን አሰምተው ‹‹ወደፊት በምን አይነት መልኩ ህዝብና አገር ሊጠቅም በሚችል ተግባር ላይ ልንሰማራ እንደምንችል በዝርዝር ተወያይተን ለህዝባችን እንገልፃለን›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተለይ በወልቃይት ጠገዴ ህወሃት የፈፀመውን ሲገልፁ ደግሞ ‹‹በወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ወጣቱን አጥፍተውታል፡፡ ነባሩን ህዝብ እያሰሩ፣ እያሳደዱና እየገደሉ ከርስቱ አፈናቅለው የራሳቸውን ህዝብ አስፍረውበታል፡፡ ያልተነገረና የኢትዮጵያ ህዝብ በውል ያላወቀው መጠን የለሽ በደል ተፈፅሟል›› ብለዋል፡፡

Sunday, December 30, 2018

አቡነ መልከጼዴቅ ነገ ኢትዮጵያ ይገባሉ


ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አንድ ከመጠቃለሉ በፊት በውጭ በነበረው ሲኖዶስ በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቡነ መልከጼዲቅ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኝተዋል:: ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::

አጭር የሕይወት ታሪክ
አቡነ መልከጼዴቅ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረታቦር አውራጃ  በፋርጣ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ መገንታ ቁስቋም በተባለ ሥፍራ ከአባታቸው ከቄስ ወርቅነህ ትኩና ከእናታቸው ከወ/ሮ አንጓች አታሌ እንደ ኢትዮጵያ አቶጣጠር በ1916 ዓ/ም ተወለዱ። ገና የአስራ አንድ ዓመት ልጅ እያሉ በ1927 ዓ.ም ማዕረገ ድቁናን ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ተቀበሉ፤ የአስራ አምስት ዓመት ወጣት ሳሉ ጣና በምትገኘው በክርስቶስ ሠምራ ገዳም መነኮሱ። በ1938 ዓ.ም ማዕረገ ቅስናን ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ተቀበሉ። ብፁዕ አባታችን ዘመናዊ ትምህርትን ከመንፈሳዊው ትምህርት ጋር አጠናክረው ለመማር በ1939 ዓ.ም ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ገብተዋል። ከወዳጅ ቤተ ክርስቲያን በተገኘው ከፍተኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ዕድል ቆስጠንጢንያ በሚገኘው የግሪክ ኦርቶዶክስ ኢኩሚኒካል መንበረ ፓትርያርክ ተልከው ልዩ ስሙ ሐልኪ በሚባለው የሥነ መለኮት (የቲኦሎጂ) ኮሌጅ በዲግሪ ተመርቀዋል። የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሥነ መለኮት (የቲኦሎጂ) ባለድግሪ ካህን በመሆንም በ1949 ዓ.ም. ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።
ብፁዕ አባታችን መደበኛ ሥራቸውን የጀመሩት አዲስ አበባ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በመምህርነት ተመድበው የተማሩትን በማስተማር ነበር። በ1950 ዓ.ም. የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ዳይሬክተርና መምህር ሆነው እንዲሠሩ ተመርጠውና ተሹመው ሙያቸውን በተግባር ገልጠዋል። በ1952 ዓ.ም. የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ልዩ ካቢኔ ሲቋቋም ለንጉሠ ነገሥቱ የሚቀርቡትን መንፈሳዊ ጉዳዮች ለማጣራት በኃላፊነት ተመርጠው የመንፈሳዊ ጉዳዮች መምርያ ዳያሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ወዲያውም የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀሥልጣናት ሆነው ተሹመው ሁለቱንም ከፍተኛ ኃላፊነቶች በመሸከም እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ለ14 ዓመታት ከፍተኛ የሥራ ውጤት አሳይተዋል።
ብፁዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ ፈጣሪ በሰጣቸው እውቀትና ጥበብ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ 21 መጻሕፍትን በተለያዩ ቋንቋዎች ደርሰው ያሳተሙ ሲሆን 11 የሚሆኑ ያልታተሙና ለህትመት የተዘጋጁ መጻሕፍቶችን ደርሰዋል። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በ1983 ዓ.ም. ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እጅ ጵጵስናን ተቀብለዋል።
ብፁዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ ላበረከቱት ከፍተኛ ሐይማኖታዊ፤ ሰብአዊና ሀገራዊ አገልግሎቶች ከሀገራችንና ከተለያዩ የውጪ ሀገራት በርካታ የክብር ሽልማቶችንና ልዩ የክብር አልባሳትን ተጎናጽፈዋል። ዋናዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህል፦
– የኢትዮጵያ የክክብር ኮከብ ባለ አምበል 1ኛ ደረጃ
– የዳግማዊ ምኒልክ የክብር ኮከብ ባለ አምበል 1ኛ ደረጃ
– የቅድሥት ሥላሴ ኒሻን የኮማንደር ደረጃ ባለ ፕላኩ
– የቅድሥት ሥላሴ ኒሻን የኮማንደር ደረጃ ከነ ፕላኩ
ልዩ ሽልማት፦
ከግሪክ መንግሥት
ከግሪክ ቤተ ክርስቲያን
ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን (በግሪክ)
የላዝሩስ ኒሻን ከኦስትርያ(ቪዬና)
ጥቄር ካባ ባለራስ ማዕርግ በሙካሽ የተሠራ፤
ቀይ ከፋይ ላይ ወርቅ የተጠለፈበት ካባ እንዲሁም በሙካሽ የተሰራ ቀሚስ
ከወርቅ የተሰራ የእጅ መስቀል ናቸው።
ብፁዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ ከሚወዷት ሀገር የተሰደዱት በሥርዓት መጓደል፣ በቀኖና መፍረስ፣ የመንግሥት ቀጥታ በሐይማኖት ተቋም ውስጥ ጣልቃ መግባትና ፓትርያርክ በሕይዎት እያለ በሌላ እንዲተካ ከማድረግ ጀምሮ ከተራ ንፍቀ ዲያቆን እስከ መንበረ ፓርትያርክ ያለው የሥራ ቦታ እየተቀማ ከሥራቸው እያባረረ በምትካቸው ብቃት የሌላቸውንና ከሃይማኖቱ ጋር ቁርኝት ያልፈጠረባቸውን ካድሬዎችን በማስገባት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግ ተጥሶ፣ ደንቡ ፈርሶ፣ ቀኖናው ተዛብቶ፣ ስርዓቱ ደፍርሶ የግፉ ዋንጫ ሞልቶ ሰለፈሰሰ ነበር።
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በስደት ዓለም በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ፓርቲያሪክ መሪነት እሳቸው ዋና ጸሐፊ በመሆን ሕጋዊው ሲኖዶስ በስደቱ ዓለም እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ ብርቱ ጥረት አድርገዋል። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሕጋዊው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የካሊፎርኒያ ግዛት ሊቀ ጳጳስ መደበኛ ጽሕፈት ቤታቸውን ካሊፎርንያ በርክሊይ በማድረግ እንደዘንግ እየተወረወሩ በመላው አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ የሩቅ ምሥራቅ፣ ኢሲያ፣ በመላው አውሮፓና በደቡብ አፍሪካ በመሄድ ወገኖቻቸውን አሰባሰቡ፤ አጽናኑ፣ አበረታቱ ገንዘብም ለምነው ቤተ ክርስቲያን አሳነጹ፣ በጸሎታቸውም ተጉ። እንደ ሐዋርያው ጳውሎስም ደጋግመው ጎበኟቸው። በፅኑ መሠረት ላይ የጸኑትን አብያተ ክርስቲያናት በሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንዲተዳደሩ አደረጉ።
ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ አማርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ግዕዝ፣ ግርክኛ፣ ቱርከኛ፣ አረብኛና ትግሪኛ ቋንቋ የሚችሉ በመሆናቸው መጽሐፍትን ለማንበብ፣ እንግዶችን ለማነጋገር፣ እንዲሁም በየቤተ ክርስቲያኖቻቸው ተጋብዘው ሲሄዱ በቋንቋቸው በመናገር ብዙዎቹን ያስደመሙ የቋንቋ ባለጸጋ ናቸው።
ብጹዕነታቸው በካሊፎርኒያ ግዛትና በአለም አቀፍ ደረጃ ላደረጉት ከፍተኛ ሐይማኖታዊና ሰብአዊ እንቅስቃሴ ስደተኛው እምነቱን እንዲያጸና፣ ሐይማኖቱን እንዲጠብቅ፣ በጥሩ ሥነምግባር እንዲታነጽ፣ ብርቱና ጠንካራ ሠራተኛ እንዲሆን፤ እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸውን በትክክለኛው ጎዳና እንዲያሳድጉ፤ ልጆችም በሐይማኖታዊ ምግባር ታንጸው ጠንካራና መልካም ዜጋ እንዲሆኑ በማስተማር ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከአምስት የካሊፎርንያ ግዛት ከንቲባዎች፦ ከኦክላንድ ሊቢ ሼፍ፣ ካሳንፍራንሲስኮ ኤድዊን ሊ፣ ከሳን ሆዜ ሳም ሊካርዶ፣ ከበርክሊ ቶም ባትስ፣ እና ከሳንታ ክላራ ሊዛ ጊልሞር ፤ ከሶስት የሕዝብ ተወካዮች፦ ከናንሲ ፐሎሲ፣ ከባርብራ ሊ፣ እና ከማይክል ሆንዳ፤ ከሁለት የጉባኤ አባላት፦ ከዳያን ፊንስታይን እና ከካሜላ ሃረስ እንዲሁም ከካሊፎርንያ ግዛት የሸንጎ አባል ሮን ቦንታ የምስክር ወረቀትና የከፍተኛ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ እንዲሆኑ ወስነው የትውልዳቸው ቀን ጁላይ 19 በየአመቱ የአቡነ መልከጼዴቅ ቀን እንዲሆን ሰይመውላቸዋል። በዚህም የተነሳ ብጹዕነታቸው ከትውልድ ሀገራቸው ውጪ በስደት ዓለም ፈጣሪያቸውን፣ ተከታይ የመንፈስ ልጆቻቸውን፣ ሀገራቸውን ያስከበሩ ምሉዕ አባት ናቸው።

ብጹዕ ሊቀጳጳስ አቡነ መልከጼዴቅ ለክርስቶስ ራሳቸውን የሰጡ፣ የጳውሎስን አረአያ የተከተሉ፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የተጋደሉ፣ የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነ የሰው ልጅ ምንም ዓይነት በደል እንዲደርስበት የማይፈልጉ፤ ኃጢያትን የሚጠየፉ፣ ከምንም በላይ ክርስቲያኖች እርስ በእርሳቸው ተከባብረው፣ ተፈቃቅረው፣ እራሳቸውን በመፅሐፍ ቅዱስ ቃል አንጸው፣ በፈጣሪ እምነት ጸንተው፣ እንዲቆዩ ያስተማሩ አባት ናቸው። በሕይወት ዘመናቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጸኦ ባይመጥንም ማስታወሻቸው ይሆን ዘንድ ይህንን ቤተ መጽሐፍት ወመዘክር የብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሊቀጳጳስ ቤተ መጽሐፍት እንዲሆን በእሳቸው ስም የተቋቋመው የመልከጸዴቅ ፋውንዴሽንና የኦክላንድ መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በወሰነው ውሳኔ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. (May 12, 2018) በብጹዕ አባታችን አቡነ መልከጼዴቅ ተመርቆ ተከፍቷል። መጻሕፍት ቤቱ ብጹዕ አባታችን ያነበቧቸውና የጻፏቸው መጻሕፍቶችና ማስታወሻዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትመራባቸውን ቀኖናዎች፣ ታሪኮች፣ የታተሙና ያልታተሙ መጻሕፍቶቿ የሚሰበሰቡበትና ለአንባቢ፣ ለአጥኝ፣ ለተመራማሪ እንዲመቻች ለመድረግ ነው። እንኳን ደስ ያላችሁ:
Condensed Biography of His Eminence Archbishop Abune Melketsedek
His Eminence Archbishop Abune Melketsedek was born in the locality of Megenta Kusquam, in the district of Debre Tabor, province of Gondar, Ethiopia, to his father Priest Workneh Teku and his mother Mrs. Anguach Atale on July 24, 1924. In 1935, at the tender age of eleven, His Eminence was ordained a deacon by Bishop Abune Abraham. Four years later, absolving himself of the secular life he never had much care for, he committed himself to the services of the Lord and became a monk at the age of 15 at the convent of Kristos Semra, near Lake Tana. He was ordained a priest in 1946 by His Eminence Abune Yishak.
In 1948, with the natural inclination to supplement his ecclesiastical training, His Eminence enrolled in Kidist Selassie Theological College. During his fourth year, under the auspices of the Greek Orthodox Ecumenical Patriarchate, he attended Holy Theological School of Halki, the Patriarchate’s main School of Theology in Turkey, and returned to his country in 1958 as the first Ethiopian theologian cleric.
His Eminence joined the workforce as an instructor at the Theological College of the Holy Trinity Cathedral in Addis Ababa, Ethiopia, where he was later appointed Director of Sewasew Berhan St. Paul School of Theology in 1958. In 1960, His Eminence was chosen to serve on Emperor Haile Selassie’s Crown Council as Director of Religious Affairs, overseeing the vetting of all religious matters that come before the Emperor. Immediately following this appointment, he was also appointed Arch-hierarch of Menbere Tsebaot Kidist Selassie Cathedral. He simultaneously filled both positions until 1974.
His Eminence is a prolific writer and a scholar who made a significant contribution to the Ethiopian Orthodox church by publishing canonical books that are fundamental to the Ethiopian Orthodox faith. He has authored 32 books, 21 of which were published, and 11 remain in manuscript form. In 1983, with His Holiness Patriarch Abune Merkoriwos officiating, His Emminence Abune Melketsedek was enthroned as Archbishop. In recognition of his tireless efforts His Eminence has received the following honorary awards and vestments from his country and different foreign countries over his lifetime.
The Order of the Star of Ethiopia (1st grade/Grand Cross)
The Order of Emperor Menelik II (1st grade/Knight Grand Cross)
The Order of the Holy Trinity (Commander Grade)
Honorary Awards from:
The Greek government
Church of Greece
Church of Alexandria in Greece
Lazarus Medal from Austria
Vestments including,
Gold-embroidered black velvet cloak
Gold-embroidered red velvet cloak and cassock
Gold blessing cross
His Eminence was exiled from his beloved country in 1992 after bearing witness to the upheaval that was brought on the church by the government; its interference with church governance, the enthronement of a new patriarchate while the incumbent patriarch was still alive, its replacement of clergy with unqualified persons and its egregious violation of the cardinal tenets of the Ethiopian Orthodox church. He openly criticized the government and produced writings of opposition along with other church leaders, which resulted in the government’s pursuit of him. Consequently, he fled the country on October 20th, 1992 taking refuge in the United States.
Along with a group of other exiled leaders including Abuna Zenamarkos, Abuna Elias and Abuna Gorgoriyos, with the partnership of Abuna Yishak, Archbishop of the Ethiopian Orthodox Churches in North America and Europe, and the leadership of the exiled Patriarch who was living in Kenya at the time, His Eminence ensured the continuation and expansion of the Ethiopian Orthodox Holy Synod despite its displacement from its home. Under the leadership of His Eminence as General Secretary, the Synod sought to console the distraught Christians in Ethiopia while seizing the opportunity to gather the multitude of Ethiopians who had migrated to North America and Europe since the 1970s.
As General Secretary of The Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church-In-Exile, His Eminence established his secretariat in Berkeley, CA, but traveled far, in the manner of the missionary journeys of the Apostle St. Paul, to Canada, Australia, the Middle East, Asia, Europe and South Africa to organize and nurture the ardent Ethiopian Christians, tirelessly soliciting for funds to build them church buildings.
In addition to his native Amharic, His Eminence speaks Geez (the ancient classical and liturgical language of Ethiopia), Tigrigna, English, Greek, Turkish, and Arabic, which has enabled him to read, interact with visitors and easily communicate whenever he is invited for a visit to places where these languages are spoken.
For his exceptional stewardship over his jurisdiction in California, the tremendous religious and social strides he made in providing spiritual guidance to the faithful Ethiopian immigrants at large and his invaluable services to the Ethiopian Orthodox Church, His Eminence is a recipient of certificates of recognition from United States Congressman Michael M Honda, United States Congresswoman Barbara Lee, 13th congressional district, United States Congresswoman Nancy Pelosi, 12th congressional district, United States senator from California, Kamala Harris, United States senator from California, Dianne Feinstein, Assemblyman Rob Bonta and The California Legislature Assembly. In addition, His Eminence also received certificates of declaration, proclaiming July 19th, his date of birth, Archbishop Melketsedek Workneh day, from Mayor Edwin Lee for City and County of San Francisco, Mayor Libby Schaaf for the City of Oakland, Sam Liccardo for the City of San Jose, Tom Bates for the City of Berkeley and Lisa M Gillmor for the City of Santa Clara.
His Eminence Abune Melketsedek devoted his life to Christ, advocated equal rights for all and tirelessly taught the paramount importance of Christians respecting and loving one another and modeling themselves after the gospel. Concerning the social and political challenges of his country, he preached intensely and tirelessly against religious and racial divide and urged all Ethiopians to live in peace and harmony with the understanding of their lineage to the holy land that is Ethiopia. He supplicated for the brutally murdered, the unjustly imprisoned, the impoverished and the sick, while persistently speaking out against perpetrators of evil.
Although not befitting his outstanding contributions, Mekane Selam Medhanealem Cathedral and Melketsedek foundation designate this museum library Archbishop Abune Melketsedek Library & Museum in commemoration of His Eminence’s legacy. It will serve as a repository of primary source materials on His Eminence, such as his written bodies of work, his personal library of books and memorabilia, among other archives. It is inaugurated with his benediction on this day May 12, 2018.

Saturday, December 29, 2018

የሻሸመኔ አሳዛኙ ክስተትና የደረሱኝ መረጃዎች | ከአህመዲን ጀበል



ዛሬ ጠዋት ላይ በፌስቡክ ወጣቶች አዛዉንቶችን ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ተመለከትኩ፡፡ አንዳንዶች አዛዉንቶቹ የእገሌ ብሄር(ዘር) ስለሆኑ ነው የሚደበድቧቸው እያሉ ሲጽፉ ሌሎች ደግሞ የተደብዳቢዎችን ማንነት ትተው ሽማግሌዎች መሆናቸውን ብቻ እየጠቀሱ አዝነው የጻፉትን አነበብኩ፡፡ ልክ ነው ያሳዝናል፡፡ በሀገራችን ባህል ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በእድሜ ከፍ ያለን ሰው ያውንም ወጣቶች እንኳንስ እያሳደዱ መደብደብ አይደለም አጓጉል ቃላት እንኳ መሰንዘር ነውር ነው፡፡ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በአንድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝና አስደንጋጭ የደቦ ፍርድና እርምጃ አስታዉሶኝ ጉደዩ አስደነገጠኝ፡፡ ችግር ቢኖር እንኳ ለህግ ማቅረብ እየተቻለ ስለምን የደቦ ፍርድ እዚያም እዚህም ይሰፍናል? ብዩ አዘንኩ፡፡ ቪዲዮውን በጥሞና ሳየው ደብዳቢዎቹም ተደብዳቢዎቹም ኦሮምኛ ቋንቋ እየተናገሩ እንደሆነ አስተዋልኩ፡፡

ከዚም ጉዳዮን አጣርቼ ለማወቅ ጥረት ጀመርኩ፡፡ የተለያዩ ሰዎች ጋር ደዋወልኩ፡፡ እንደተባለው ግጭቱ በሻሸመኔ እንደሆነና ስፍራው በሻሸመኔ ከተማ ቀበሌ 10 አሌሉ የሚባል ሰፈር ባለው የምዕራብ አርሲ ዞን የእስልምና ጉዳይ ጽ/ቤት (መጅሊስ) ቅጥር ጊቢ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ የተደበደቡት ሰዎች ጀማል መሀመድ፣ሁሴን አብዱልቃድር፣ ዑስማን፣ሙሀመድ አየለ (አልይ) እና አንድ ስማቸውን ማወቅ ያልቻልኳቸው እንደሆኑ ተረዳሁኝ፡፡ ክስተቱም ከ41 ቀናት በፊት በ6/3/2011 እንደተፈጠረ ሰማሁ፡፡ ጉዳዩም ከመጅሊስ ጋር ተያይዞ እንደተፈጠረና ከአንድ ወር በፊት የተደበዱ ሰዎች ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች አቤቶታ እንዳቀረቡም ሰማሁ፡፡ በሀገሪቷ በአንንዳንድ አከባቢዎች እየታየ ስላለው ግጭት የመፍጠር አዝማሚያ ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የፌደራል መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሀጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል በሻሸመኔ መጅሊስ ግጭት ተከስቶ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንደቀረበ የጠቀሱት ኋላ ላይ ትዝ አለኝ፡፡ ወደ ፌደራል መጅሊስ ደዉዩ እንዳረጋገጥኩ የሻሸመኔው ችግር ከ41 ቀናት በፊት የተከሰተው ራሱ መሆኑን አረጋገጥኩ፡፡ ወደ ሻሸመኔም ደውዩ ጠያየቅሁ ከመረጃ ምንጮቼ የተረዳሁትን ከጉዳዮ መነሻና የእለቱ ችግር እንዴት እንደተከሰተ ጭምር እንደሚከተለው በዝርዝር አብራራለሁ፡፡
የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ በከተማዋ በስልጣን ላይ የነበሩት የመጅሊስ አመመራሮችን አትወክሉንም ብሎ ይቃወም ነበር፡፡ በኋላ ላይ የህዝቡ ጫና ሲበዛባቸው በመጅሊስ መሪነት የነበሩ ሰዎች ከሕዝቡ ከምንጣላ ብለው በ15/10/2011 ከሥልጣን ለቀው የቢሮውን ቁልፍ ለሀገር ሽማግሌዎች አስረከቡ፡፡ ሽማግሌዎችና ዓሊሞች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ ሳለ በሰኔ 26 ቀን 2010 የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አሸማጋይነት ተቋቋመ፡፡ የመጅሊሱን ቢሮ ቁልፍ የተረከቡት ሽማግሌዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት ለዉጥ እስኪመጣ እንጠብቅ በሚል የሻሸመኔ ከተማና የምዕራብ አርሲ ዞን መጅሊስ ቢሮ ታሽጎ እንዲቆይ ይወስናሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከአምስት ወራት በፊት የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ ደብዳቤ በመጻፍ እነእገሌን በመጅሊስ መሪነት ሾሜያለሁ ብሎ ደብዳቤ አስይዞ ይልካል፡፡ የተላኩት ሰዎችም በተይም በረብሻው ስፍራ ቆሞ ለህዝቡ የሚናገረው ጀማል መሀመድ የተሾሙበትን ፖስታ ይዞው ለዞኑና የከተማው አስተዳደሮች ፖሊስና የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር ይሄዳል፡፡ ከአከባቢው ያገኘሁት መረጃ እንደሚለው ናደው የሚባለው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ጉዳዩ የህዝበ ሙስሊሙ እንጂ የኛ አይደለም፡፡ ሕዝቡን ጠይቅ እኛን አይመለከትም ይለዋል፡፡
ቀጥሎም በከተማዋ ታዋቂ የሆኑ ዓሊሞችን እነ ሼህ ሀጅ አደም፣ሼህ አሊ ቡታንና ሼህ መሀመድ በዳሶ ያናግራል፡፡ አግዙኝ ይላል፡፡ እነርሱም ‹‹ችግር ልትፈጥር ካለሆነ በቀር አርፈህ ተቀመጥ›› ይሉታል፡፡ የዚህ በዚህን ጊዜ የከተማው አስተዳደር ፖሊስና የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ችግር እንዳይፈጠር አርፈው እንዲቀመጡና ከህዝቡ ጋር እንዳትጋጩ ብለው ይመክሯቸዋል፡፡ የሻሸመኔ ከተማ የእስልምና ጉዳይ ጽ/ቤትን ከፍተው ለመግባት ስፍራው ከተማ መሃል ስለሆነና ቁልፉም በሀገር ሽማግሌዎች እጅ ስለሆነ ችግር ይፈጥርብናል ብለው ይሰጋሉ፡፡ ቀጥሎም የሻሸመኔ ከተማ መጅሊስ ቢሮ ተዘግቶ እያለ አዲሱን የሻሸመኔ መጅሊስን ቢሮ ወደ ምዕራብ አርሲ ዞን መጅሊስ ቢሮ ቅጥር ጊቢ አዙረናል፡፡ እኛም ተመርጠናል ብለው በከተማዋ መስጊዶች ማስታወቂያ ይለጥፋሉ፡፡
የተወሰኑ የሀገር ሽማግሌዎች ከዚህ በፊት በመጅሊስ ምርጫ ጊዜ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ነበረ የተባለው ጀማል መሁመድን ከዚህ በፊት በማንኛውም መልኩ የመጅሊስ አባል ሳትሆን እንዴት በመጅሊስ መሪነት ተመረጥኩ ትላለህ ብለው ያናግሩታል፡፡ ይኸው የኦሮሚያ መጅሊስ መርጦ ላከኝ ያለበትን ደብዳቤ ብሎ ያሳያቸዋል፡፡ ሽማግሌዎቹ ‹‹እውነት የኦሮሚያ መጅሊስ መርጦህ ቢሆን እንኳ ከህዝቡ ሁሉ ጋር ተጋፍጠህ አትችልም፤ ደብዳቤን ደብቀህ ኑሮህ ኑር›› ይሉታል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ እርሱም አሻፈረኝ ብሎ በመጅሊስ መሪነት ተሾመ የተባለው ጀማል መሀመድም በ02/3/2010 ደብዳቤ በመጻፍ (በኦሮምኛ የተጻፈው ይህ ደብዳቤ በእጄ ገብቷል) የሻሸመኔ ከሕዝበ ሙስሊም ስብሰባ ይጠራል፡፡ በዚህን ጊዜ የከተማው ሽማግሌዎችና ዓሊሞች በስብሰባው ቢገኙ ላልመረጧቸው የመጅሊስ መሪዎች እርቅና መስጠት ይሆናል ብለው ቀሩ፡፡ ሰዉም እንዲቀር ሲሉ በየመስጊዱ ለሕዝቡ አስተላለፉ፡፡ በዚህ ጊዜ የተወሰኑ ወጣቶች በስፍራው ተገኝተው ‹‹ማንናችሁ? በምን ስልጣን ጠራችሁን?›› ብለው እየጠየቁ ግርግሩና ድብደባው ተከሰተ፡፡ ይህንኑ የሚያሳየዉን ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡ ኦሮምኛ ለማትሰሙት ደግሞ በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚተላለፈውን ንግግር እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤያለሁ፡፡
– ተናጋሪ (በበረንዳው መድረክ ላይ የቆመው)፡- …መምጣት ስላልቻሉ…(ብሎ ቪዲዮው ይጀምራል)
– ከሰዉ መካከል፡- ማነው የጠራን?
– ተናጋሪ፡- እኔ ነኝ፡፡
– ከሰዉ መካከል፡- ለምን ጠራኸን? አንተ ማንነተህ?
– ተናጋሪ፡- እኔ ጀማል መሀመድ ጃርሶ እባላለሁ፤
– ከሰዉ መካከል፡- የሥራህ ድርሻ ምንድነው? ሚናህ ምንድነው? ለምን ጠራኸን?
– ከከመድረክ ተናጋው ጎን የቆሙት ሽማግሌ(በመጅሊስ መሪነት ተሸሙ የተባሉትና ኃላ ላይ ከተደበደቡት መካከል አንዱ ናቸው) ፡- ችግር የለውም ተራ በተራ ተናገሩ፡፡
– ከዉ መካከል፡- አንተ አያገባህም እንደፈለግነው እንጠይቃለን፡፡ ንግግራችን ከርሱ ጋር ነው፤ካንተ ጋር አልተነጋገርንም፡፡
– እንደፈለግነው እንጠይቃለን አያገባህም፡፡
– ከሰዉ መካከል፡- አንተ ሽማግሌ እርሱ እኔ ነኝ የጠረኻችሁ ብሏል አንተ ምንም አያገባህም ዝም በል፡፡
– ከመድረክ፡- ጌታችሁን ፍሩ
– ከሰዉ መካከል፤-አንተ ራስህ ጌታህን ፍራና ዉረድልን፡፡
– ከሰዉ መካከል፡- አንድ ሰው ሲጠይቅ ሌሎቻችሁ ዝም በሉ፡፡
– ከሰዉ መካከል፡- ዝም በል አፍህን አትክፈት፡፡
– ከሰዉ መካል፡- ምን ልትሆን ፈለግክ?
– ከሰዉ መካከል፡- አንተ ሕዝቡን የጠራህበትን ተናገር፡፡ ማን እውቅና እንደሰጠህ ተናገር፤ በህገወጥ መንገድ እዚህ ጊቢ ማን እንድትገባ እንደፈቀደልህ ተናገር፡፡ ይህ ጊቢ የሙስሊሙ ሕዝብ ነው፡፡ ከሌቦች እጅ ወስደን ቆልፈናል፡፡ ማን እንድትከፍት እንዳደረገህ ተናገር-ንገረን፡፡
– በዚህ ጊዜ በበረንዳው መድረክ ከጀርባ የቆመው ወጣት በመድረክ ላይ የቆመውን ተናጋሪ ከጀርባ ገፍቶ አስወረደው
– ከሰዉ መካከል፡ ተዉ ተዉ
– ምን ልትሆን ነው?
– ግርግሩና ድብደባ ተጀመረ፡፡
በዚህ መለኩ ግጭቱ ተፈጠረ፡፡ የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ፡፡ ጉዳዩን የሀገር ሽማግሌ የሆኑት ሼህ ተማም፣ሼህ አሊ ቡታ፣ ዉሽታና ዳንሱሬ በመያዝ በእርቅ እየፈቱት ነው፡፡ የተጎዱ ሰዎች ለመታከሚያ 200 ሺህ ብር ያስፈልገናል ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎቹ 10ሺህ ብር እንዲሰጥ ወስነዋል፡፡ ለአሁን የደርስኩበት መረጃ ይህን ይመስላል፡፡ እዚህ ላይ በግልጽ መጥቀስ የምፈልገው በአሁኑ ሰዓት ልክ በብሄርና ጎሳ ግጭት እየተፈጠረ እንዳለው በሃይማኖትም ግጭት ለመፍጠር አንዳንድ ሙከራዎች እንዳሉ እንደኮሚቴ በግልጽ ከመንግስት ጋር ተወያይተናል፡፡ መልኩን እየቀያየረ ቢመጣም ግጭት በተለይ በዚህ የሽግግር ወቅት ለማን እንደሚጠቅም ግልጽ ነው፡፡ ይህንን በመረዳት ኮሚቴው ከእስካሁኑ በተለየ መልኩና በፍጥነት መጓዝ እንደሚገባ ከሚመለከተው አካል ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህም ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ ኮሚቴው ይፋ የሚያደርጋቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ ይህን በመረዳት እያንዳንዱ ዜጋ ምንም ያክል ስሜት የሚነካ ነገር ቢከሰት የመፍትሄው እንጂ የችግሩ አካል እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባል፡፡
የሻሸመኔው ጉዳይ ላይም ምክንያት የሆኑ ሁሉ ከየትኛውም ወገን ይሁኑ ተለይተው ለህግ ማቅረብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይም እንደ ሙስሊምነታችን የሻሸመኔው ችግር በሙስሊሞች መካከል ያውንም አንድ ቋንቋ ተናጋሪ በሆኑ ወጣቶች በአባቶች ላይ መከሰቱ አሳፋሪና ብዙ የሚያስተምረን ሊሆን ግድ ይላል፡፡ የቱንም ያክል ልዩነት ቢኖር የሰውነት ክብር፣ የኢትዮጵያዊነት ባህልና የጋራ ማንነት ሉጋም ሆኖ ካልያዘን ከባድ ጊዜ ከፊታችን እንዳለ ያሳየናል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሰጋን በመሆኑ ስሜት ዉስጥ ገብተን ችግሩን ከማራገብ ቆም ብለን ዘላቂና ሀገር ዐቀፍ መፍትሄ እንድንሻ ሊገፋፋን ይገባል፡፡

ኢትዮጵያና ሱዳን በሶስት ሳምንት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኙ



የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በተቃውሞ እየታመሰች ባለችው ሱዳን ዛሬ ቆይታ አድርገዋል፡፡ በካርቱም ቆይታቸውም ከሱዳኑ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚነስትር ዶ/ር አል ድሪር ሞሃመድ ጋር መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ገልጿል።
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በውይይቱ ወቅት ሱዳን በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣት አገር ናት መሆኗን ጠቁመው ሁለቱ አገሮች ለሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ፍላጎት መሳካት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩና የሁለቱ አገሮች ህዝቦች መፃኢ ዕድልም ተመሳሳይ መሆኑን ገልፀዋል።
ጨምረውም ‹‹በሁለቱ አገሮች መካከል በከፍተኛ ደረጃ የተደረጉ የፖለቲካ ምክክሮች ሁለቱ ወገኖች ከፊት ለፊታቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና ለህዝባቸው ጥቅሞች በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ማሳያ ነው›› ብለዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር አል ድሪር ሙሀመድ በበኩላቸው ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው አዲስ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ ሱዳን ታደንቃለች›› ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም በሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ባለፈው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው የሁለቱን አገሮች ወንድማማች ህዝቦች ፍላጎት ለማሳካት በጋራና በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡
ሕወሓት ሱዳንን በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር አጋሩ መሆኗን ከገለጸ በኋላ በሁለት ሳምንት ውስጥ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ሱዳንን ሲጎበኝ ይህ ሁለተኛው መሆኑ ነው:: አልበሽር አዲስ አበባ መጥተዋል”” ከሳምንት በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት ሱዳን ሄደው የነበru ሲሆን ዛሬ ደግሞ ዶ/ር ወርቅነህ እዛ ናቸው:::
ኢትዮጵያና ሱዳን በሶስት ሳምንት ውስጥ ሶስት ጊዜ ተገናኝተዋል ማለት ነው::

Thursday, December 27, 2018

በኢትዮጵያ ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ ታወጀ



የሀይማኖት አባቶች በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየእምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንዲያደርጉ አወጁ፡፡ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች እና የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች አሁን በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው እለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤው ሁሉም ወገን ቅድሚያ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብአዊ ክብርና ሰላም በመትጋት የወገኖቻችን ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት በአፋጣኝ ማቆም ይገባዋል ሲል የተማጽዕኖ ጥሪም አቅርቧል፡፡ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ምንም አይነት ግጭት እና የሚተኮስ ጥይት ሊኖር እንደማይገባ አሳሰበው ጉባኤው ለመላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባለአስር ነጥብ የሰላም መልዕክት እና የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ግጭቱ ተወግዶ የታሰበው ሰላም እውን እንዲሆንም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየ ዕምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ጸሎትና ምሕላ ታውጇል ብሏል ጉባኤው፡፡

Wednesday, December 26, 2018

በኢትዮጵያ የታገቱትን 4 ህንዳዊያን ለማስለቀቅ 12.4 ሚሊዮን ብር ተጠየቀ



ከታገቱ በርካታ ቀናትን ያስቆጠሩት አራት ህንዳዊያን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ የተደረገው ድርድር ያለውጤት ተበተነ፡፡ ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አርብ ሲሆን በዚህ ድርድር ወቅት የህንድ ኤምባሲና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ተወካዮች ቢገኙም ምንም መስማማት ሊደረስ አልቻለም፡፡ ህናዳዊያኑ ሊታገቱ የቻሉት የሚሰሩበት የህንዱ የኮንስትራክሽን ድርጅት ለሰራተኞቹ ደመወዝ ሳይከፍል ወራትን በማስቆጠሩ ነበር፡፡

የህንዱ ቢዝነስ ላይን ጋዜጣ እንደዘገበው እነዚህን ህንዶች ለመልቀቅ የድርጅቱ ሰራተኞች 12 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ጠይቀዋል፡፡ ከታገቱት ውስጥ አንዱ የሆነው ቻይታነያ ሀሪ ሲናገር ‹‹የህንድ ኤምባሲ በህይወት እንደምንቆይ ብቻ ማረጋገጫ ሰጥቶናል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንም  እንደማንገደል ነግሮናል›› ብሏል፡፡ እነዚህ ሁለት አካላት የታገቱበትን ካምፕ ደህንነት ከማረጋገጥ ውጭ እነሱን ለማስለቀቅ የሚያስችል ምንም አቅም እንደሌላቸውም አስረድቷል፡፡

ጉዳዩ ከአቅም በላይ በመሆኑም የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጣልቃ እንዲገባም ታጋቹ ጠይቋል፡፡ የተጠቀሰው ገንዘብ እስካልተከፈለ ድረስ የመለቀቃቸው ነገር የማይታሰብ እንደሆነም ለዜና ምንጩ ተናግሯል፡፡ የህንዱ አይኤል ኤንድ ኤፍ ኤስ ኩባንያ የመንገድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን ደመወዝ ያልከፈለው በመክሰሩ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ዘግበን ነበር፡፡

Saturday, December 22, 2018

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ጸደቀ


 በኢትዮጵያ ከወሰንና ከማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚል የተዘጋጀው ረቂቃአዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ።
          በ33 ተቃውሞ የጸደቀው ይህ አዋጅ እንዳይጸድቅ 10 የሕወሃት የፓርላማ አባላት በፊርማ አስቀድመው ጥያቄ አቅርበዋል።
          ጥያቄያቸውም አዋጁ ሕገ መንግስቱን ይጻረራል የሚል ሲሆን የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ኮሚሽኑ የማማከር እንጂ የመወሰን ስልጣን ስለሌለው ሕገ መንግስት አይጻረርም በማለት ሞግተዋል።
          “የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ” በሚል ዛሬ ለፓርላማው የቀረበው አዋጅ ኮሚሽኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥናቱንና ምክረ ሃሳቡን እንደሚያቀርብ ያስረዳል።
          ኮሚሽኑ ከማንነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎችን የክልል፣የዞንና የወረዳ የአስተዳደር ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ ጥናት የሚመለከታቸውን ሁሉ በማሳተፍ ሞክረ ሃሳብ እንዲያቀርብ ስልጣን ተሰጥቶታል።
          ይህ ኮሚሽን የስልጣን ዘመኑ 3 አመት ሲሆን ዋናው ኮሚሽነርና ምክትሉ በፓርላማ እንደሚሰየምም ተደንግጓል።

Thursday, December 20, 2018

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ


 የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገቡ።
          የደርግንመንግስት በመቃወም ስርአቱን ከከዱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመጀምሪያው የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ1981 በኮለኔል መንግስቱሃይለማርያም ላይ የተካሄደው የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ላይ ከውጭ ሆነው ተሳታፊ እንደነበሩም መረዳት ተችሏል።
          ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ትላንት ከናሚቢያ ዊንዲሆክ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንደተቀበሏቸው ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።
          በአቀባበል ስነስርአቱ ላይ የቀድሞ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮለኔል ፍስሃ ደስታም መገኘታቸው ታውቋል።
          በአሜሪካ ኒዮርክ ከሚገኘው ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ 2ኛ ዲግሪያቸውን አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በደርግ መንግስት ውስጥ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ1979 ስርአቱን ጥለው በመውጣት፣በፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሆነው የደም እንባ የተባለ መጽሃፍ በመጻፍ የስርአቱ ጉድፍ ያሉትን አጋልጠዋል።
          በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በቋሚ ተጠሪነት የኤርትራ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪነትና በእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት በደርግ ስርአት ውስጥ ማገልገላቸው ታውቋል።
          ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ1981 የኮለኔል መንግስቱን መንግስት ለመገልበጥ በተደረገው ሙከራ ከውጭ ሆነው ተሳታፊ እንደነበሩም መረዳት ተችሏል።
          የኢትዮጵያ ወታደሮች ነጻ ንቅናቄን በመመስረት በግልበጣው ሒደት ተሳታፊ የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ መንግስት ከተገለበጠ በኋላ በሚደረገው ሒደት ውስጥ ሻዕቢያና ሕወሃት ተሳታፊ በሚሆኑበት መንገድ ላይ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቄና ከሕወሃት መሪዎች ጋር በወቅቱ መነጋገራቸውንም ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ መናገራቸው ይታወሳል።
          ለረጅም አመታት በተባበሩት መንግስታት ውስጥ በተለያየ የሃላፊነት ቦታ ያገለገሉት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ የሰላምና የጸጥታ ምርምር ተቋም የሚል ድርጅት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመመስረት በዋና ስራ አስፈጻሚነት እየመሩት እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።
          መቀመጫቸውን በአሁኑ ወቅት በናሚቢያ ዊንድሆክ ያደረጉት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከ33 አመታት በኋላ ትላንት ማምሻውን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
          ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ትላንት ከናሚቢያ ዊንዲሆክ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ተቀብለዋቸዋል።
          በአቀባበል ስነስርአቱ ላይ የቀድሞ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮለኔል ፍስሃ ደስታም መገኘታቸው ታውቋል።

በሱዳን የገዢው ፖርቲ ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ


ኢሳት
 ሱዳን ውስጥ ለተቃውሞ አደባባይየወጡ ወጣቶች የገዢውን ፖርቲ ጽሕፈት ቤት አቃጠሉ።
የተቃውሞው መነሻ በነዳጅ እና በዳቦ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ተቃውሞው የተነሳውና የተቀጣጠለው ከርዕሰ መዲናዋ ካርቱም 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አትባራ በተባለው ከተማ ሲሆን በተቃውሞው የሱዳኑ ገዢ ፓርቲ ናሽናል ኮንግረስ ጽሕፈት ቤት ከመቃጠሉ ባሻገር በጎዳናዎችም ላይ እሳት እያነደደ መገኘቱን አልጀዚራ ዘግቧል።
አንድ የሱዳን ፓውንድ ይሸጥ የነበረው ዳቦ ወደ 3 ፖውንድ ከፍ ማለቱና በተመሳሳይ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ መገኘቱ ለተቃውሞው መነሻ እንደሆነም ተመልክቷል።
ተቃውሞው ከአትባራ ወደ ሬድ ሲት ስቴት መሸጋገሩ የተገለጸ ሲሆን ተቃውሞው የአልባሽር መንግስት ከስልጣን ይውረድ ወደሚል ተሸጋግሯል።
ተቃውሞው በተጠናከረበት አትባራ ከተማና በአጠቃላይ በናይል ሪቨር ስቴት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የሰዓት ዕላፊም ተደንግጓል።
ከሰዓት 12 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ተደንግጓል።
የ74 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ኦማር አልበሽር በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙ የፊታችን ሰኔ 30 ዓመት ይሆናቸዋል።

ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ ህግ ወጣ


ከፊል አውቶማቲክ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ግለሰቦችና የግል ኩባንያዎች እንዳይጠቅሙ የሚከለክል መመሪያ የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አወጣ።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከመጋቢት23/2018 ጀምሮ መሳሪያዎቹን መጠቀም የተከለከለ በመሆኑ ግለሰቦችም ሆኑ አምራቾች እንዲያወድሙ አሊያም ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡትላንት መመሪያ ወጥቷል።
ከአውቶማቲክ መሳሪያዎች ውጭ ከፊል አውቶማቲክና አውቶማቲክ ያልሆኑ መሳሪያዎችን ገዝቶ መታጠቅ በማይፈቀድባት አሜሪካ የአሰቃቂ ግድያዎች እየጨመሩ መምጣት ብርቱ ተቃውሞን ሲያስከትል ቆይቷል።
በተለይም ከአንድ ዓመት በፊት የአሜሪካ የቁማርና የመዝናኛ ማዕከል በሆነችው ላስቬጋስ ከተማ በአንድ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የነበሩ 57 ሰዎች መገደል በጦር መሳሪያ መጠቀም መብት ዙሪያ ከፍተኛ ውይይት ቀስቅሷል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በጥቅምት ወር 2017 ስቴፈን ፓዶክ የተባለ የ64 ዓመት ሰው ላስቬጋስ ከተማ ከሚገኘው ማንዳሊ ቤይ ሆቴል 32ኛ ፎቅ ላይ ከያዘው መኝታው ክፍል ቁልቁል 22ሺህ ሰው በታደመበት የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በከፈተው ተኩስ 58 ሰዎች ሲገደሉ 489 የሚሆኑት ቆስለዋል።
ፖሊስ ከመድረሱ በፊትም ግለሰቡ ራሱን ያጠፋ ሲሆን በመኝታ ክፍሉ ውስጥም 23 የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸው ይታወሳል።
ይህንና መሰል ግድያዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መመሪያውን ትናንት እንደወጣ መረዳት ተችሏል።
ተጠባባቂ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ- ማቲው ዋይታከር መመሪያውን የፈረሙ ሲሆን እንደ አውሮፓውያኑ ከመጋቢት 23/2018 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
ቀደም ሲልም አውቶማቲክም ሆነ ማሽንጋን መሳሪያዎችን ግለሰቦች እንዳይጠቀሙ ህግ ይከለክላል።
በአዲሱ መመሪያ ከፊል አውቶማቲክ መሳሪያዎችም በዕገዳው ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል።
ሆኖም ሽጉጥና አውቶማቲክ ያልሆኑ መሳሪያዎችን ገዝቶ መጠቀም አልተከለከለም።
አዲሱን ዕገዳ ለማስቀልበስ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ከወዲሁ የተገመተ ሲሆን የመመሪያው አውጪዎች መመሪያው የሃገሪቱን ህግ መሰረት ያደረገ ስለሆነ እንሞግታለን ብለዋል።
ክልከላው በመላው አሜሪና ተፈጻሚ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ


(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2011) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ብር ጭኖ በሚጓዙ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች  ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመውጥቃት አንደኛው ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ተሽከርካሪዎቹ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ይዘው ሻኪሶ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለማድረስ እያመሩ እንደነበረ ታውቋል።
ሻኪሶ ከተማ ለመድረስ 20 ኪሎሜትር ሲቀራቸው ጥቃቱ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን ብሩን የጫነው አንደኛው ተሽከርካሪ አምልጦ ሻኪሶ በመግባት ገንዘቡን ማስረከቡን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲላ ቅርንጫፍ የኦፕሬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ አብዱልፈታህ አብራር ለኢሳት እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ነው።
ከዲላ ቅርንጫፍ ብር ጭነው ወደ ጉጂ ዞን ሃያዲማ ቅርንጫፍ ያመሩት የባንኩ ሰራተኞች በማግስቱ ከሃያዲማ ወደ ሻኪሶ የሚያደርሱት ገንዘብ እንደነበር ነው ሃላፊው የሚገልጹት።
6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ጭነው በ10 ወታደሮች ታጅበው ከሃያዲማ ወደ ሻኪሶ እያመሩ በነበሩት የባንኩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ሻኪሶ ለመድረስ 20 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው እንደነበርም ሃላፊው ገልጸዋል።
ማንነታቸው ያልታወቁ ባሏቸው ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከወታደሮቹ ሁለቱ ሲገደሉ የሁለተኛው ተሽከርካሪ ሹፌሩም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።
ታጣቂዎቹ ከሃያዲማ ቅርንጫፍ ወደሻኪሶ ገንዘብ ጭኖ የሚሄደውን ተሽከርካሪ በጥይት መትተው ጎማውን ቢያተነፍሱትም ሹፌሩ በወሰደው ቆራጥ ርምጃ ጎማ የሌለው መኪና እያሽከረከረ ሻኪሶ መግባቱንና ገንዘቡን ከዘረፋ ማስመለጡንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ይህን ተግባር የፈጸመው ሹፌር በተተኮሰበት ጥይት የተመታ ሲሆን ገንዘቡን ካስረከበ በኋላ ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና መግባቱንም ለማወቅ ተችሏል።
የታጣቂዎቹን ማንነት በተመለከተ ኢሳት ባደረገው ማጣራት በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚያሳዩ መረጃዎች ደረሰውታል።
ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የሻኪሶ ንግድ ባንክ ሰራተኛ የኦነግ እንቅስቃሴ ጎልቶ የሚታይበት አካባቢ በመሆኑ በባንኩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት የሰነዘሩትም የኦነግ ታጣቂች ናቸው ሲል ለኢሳት ገልጿል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኦነግ አመራሮች ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ የኦነግ ታጣቂዎች ጉጂና አማሮ በሚዋሰኑበት አከባቢ ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የገደሉበትን ጥቃት መፈጸማቸው የሚታወስ ነው።

አርበኛ መሳፍንት ተስፋ(ሰባ ጎራሽ) ከነሙሉ የጦር ሰራዊቱ እና ትጥቁ በዳባትና በጎንደር ከተሞች ደማቅ ህዝባዊ አቀባበል ተደረገለት።

አርበኛ መሳፍንት ተስፋ(ሰባ ጎራሽ) ከነሙሉ የጦር ሰራዊቱ እና ትጥቁ በዳባትና በጎንደር ከተሞች ደማቅ ህዝባዊ አቀባበል ተደረገለት።
የአርበኞች ግንቦት 7 በሀገር ውስጥ ካደራጀው ጦር አንዱ በአርበኛ መሳፍንት የሚመራው ጦር ሲሆን ትናንት በአማራ ክልል ፍትህ ተቋም በአቶ ፍርዴ ቸሩ ፊርማ የተረጋገጠ የምህረት የምስክር ወረቀት ለአርበኛ መሳፍንት እና ሙሉ ጦሩ ተሰርቶ ተልኮለታል።
የአርበኛ መሳፍንት ጦር ከህዝብ ዘንድ እያገኘ ያለውን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃግብር በድምቀት እየተቀበለ ለተሃድሶ ስልጠና በቅርቡ ወደ ካምፕ እንደሚገባ ይጠበቃል።Image may contain: 2 people, people standing, crowd and outdoor
Image may contain: 4 people, people standing

በወሊድ ወቅት በተሰጣት #የሰመመን_መድኃኒት ምክንያት ከሁለት ወራት በኋላም አለመንቃቷ አሳሳቢ ሆኗል

በወሊድ ወቅት በተሰጣት #የሰመመን_መድኃኒት ምክንያት ከሁለት ወራት በኋላም አለመንቃቷ አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በወሊድ ወቅት የተሰጣት የሰመመን መድኃኒት ከሁለት ወራት በኋላም እንድትነቃ አላደረጋትም፤ ይህም ባለቤቷ አቶ ይመስገን አልማውን እና ቤተሰቦቿን አስጨንቋል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ እታገኝ ባይሌ መስከረም 26 ቀን 2011 ዓ.ም የመውለጃ ቀኗ ስለነበር ወደ ፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሄዳ ነበር፡፡ ከረዥም ጊዜ ምጥ በኋላ በቀዶ ህክምና እንድጽገላገል ተወሰነና የስቃይ መቀነሻ የሰመመን መድኃኒት ተሰጣጽ፡፡ የሰመመን መድኃኒቱ (አንስቴዥያ) ግን ለከፍተኛ ስቃይ ዳረጋት፡፡ እስካሁንም ምግብ መመገብ፣ መናገርና መንቀሳቀስ አልቻለችም፡፡
ከወለደችበት መስከረም 26 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ በፍኖተ ሰላም ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲደርግላት ብትቆይም በጤናዋ ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል አልታዬም፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተላከች፡፡ ነገር ግን በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታልም በቂ ሕክምና ሳታገኝ ወራት ተቆጠሩ፡፡
ከባለቤቷ ከአቶ ይመስገን አልማው እና አባቷ አቶ ባይሌ ብርሃን ጋር ባደረግነው ቆይታ በሕክምና ስህተት በተፈጠረው ችግር በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ በግለሰቧ ላይ ደግሞ አሳሳቢ የጤና እክል እንደደረሰባቸው ነግረውናል፡፡ ‹‹እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በቀን እስከ ሁለት ሺህ ብርና ከዚያ በላይ በማውጣት ሊያነቃት ይችላል የተባለ መድኃኒት ሁሉ በመግዛት ሀብት ንብረቴን በሙሉ ጨርሻልሁ፤ ምንም የቀረኝ ንብረት የለም፤ በዚህ ሁኔታ ባለቤቴ የመዳን ዕድሏ ዝቅተኛ ነው›› ነው ያሉን ባለቤቷ ከእምባቸው ጋር እየታገሉ፡፡
የሕክምና ማስረጃዋ (ፋይሏ) ‹‹ሆን ተብሎ›› ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ላይ እንዲጠፋ መደረጉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸውም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ ሐኪሞችን ለማናገር ሞክረን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ባሁኑ ወቅትም በቅርብ ክትትል እንዲደረግላት በሚል ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆሰፒታል እንደተላከችና በጤናዋ ላይ መሻሻል አለመኖሩን ቤተሰቦቿ ነግረውናል፡፡
ዘጋቢ፡- አብዮት ከፋለ (አብመድ)
#መፍትሔ
የክልሉ ጤና ቢሮ፥ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የምመጤክአቁባ...የህክምና ሂደቱ እና ስነምግባር ላይ በቂ ምርመራ በማድረግ አስፈላጊው ህክምና እንዲደረግላት ማድረግና ስህተቱ/ችግሩ በባለሙያዎች ምክንያት ከሆነ በህጉ መሠረት እርምጃ መውሰድ!
በወሊድ ወቅት በተሰጣት #የሰመመን_መድኃኒት ምክንያት ከሁለት ወራት በኋላም አለመንቃቷ አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በወሊድ ወቅት የተሰጣት የሰመመን መድኃኒት ከሁለት ወራት በኋላም እንድትነቃ አላደረጋትም፤ ይህም ባለቤቷ አቶ ይመስገን አልማውን እና ቤተሰቦቿን አስጨንቋል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ እታገኝ ባይሌ መስከረም 26 ቀን 2011 ዓ.ም የመውለጃ ቀኗ ስለነበር ወደ ፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሄዳ ነበር፡፡ ከረዥም ጊዜ ምጥ በኋላ በቀዶ ህክምና እንድጽገላገል ተወሰነና የስቃይ መቀነሻ የሰመመን መድኃኒት ተሰጣጽ፡፡ የሰመመን መድኃኒቱ (አንስቴዥያ) ግን ለከፍተኛ ስቃይ ዳረጋት፡፡ እስካሁንም ምግብ መመገብ፣ መናገርና መንቀሳቀስ አልቻለችም፡፡
ከወለደችበት መስከረም 26 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ በፍኖተ ሰላም ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲደርግላት ብትቆይም በጤናዋ ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል አልታዬም፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተላከች፡፡ ነገር ግን በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታልም በቂ ሕክምና ሳታገኝ ወራት ተቆጠሩ፡፡
ከባለቤቷ ከአቶ ይመስገን አልማው እና አባቷ አቶ ባይሌ ብርሃን ጋር ባደረግነው ቆይታ በሕክምና ስህተት በተፈጠረው ችግር በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ በግለሰቧ ላይ ደግሞ አሳሳቢ የጤና እክል እንደደረሰባቸው ነግረውናል፡፡ ‹‹እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በቀን እስከ ሁለት ሺህ ብርና ከዚያ በላይ በማውጣት ሊያነቃት ይችላል የተባለ መድኃኒት ሁሉ በመግዛት ሀብት ንብረቴን በሙሉ ጨርሻልሁ፤ ምንም የቀረኝ ንብረት የለም፤ በዚህ ሁኔታ ባለቤቴ የመዳን ዕድሏ ዝቅተኛ ነው›› ነው ያሉን ባለቤቷ ከእምባቸው ጋር እየታገሉ፡፡
የሕክምና ማስረጃዋ (ፋይሏ) ‹‹ሆን ተብሎ›› ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ላይ እንዲጠፋ መደረጉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸውም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ ሐኪሞችን ለማናገር ሞክረን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ባሁኑ ወቅትም በቅርብ ክትትል እንዲደረግላት በሚል ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆሰፒታል እንደተላከችና በጤናዋ ላይ መሻሻል አለመኖሩን ቤተሰቦቿ ነግረውናል፡፡
ዘጋቢ፡- አብዮት ከፋለ (አብመድ)
#መፍትሔ
የክልሉ ጤና ቢሮ፥ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የምመጤክአቁባ...የህክምና ሂደቱ እና ስነምግባር ላይ በቂ ምርመራ በማድረግ አስፈላጊው ህክምና እንዲደረግላት ማድረግና ስህተቱ/ችግሩ በባለሙያዎች ምክንያት ከሆነ በህጉ መሠረት እርምጃ መውሰድ!

በወሊድ ወቅት በተሰጣት #የሰመመን_መድኃኒት ምክንያት ከሁለት ወራት በኋላም አለመንቃቷ አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በወሊድ ወቅት የተሰጣት የሰመመን መድኃኒት ከሁለት ወራት በኋላም እንድትነቃ አላደረጋትም፤ ይህም ባለቤቷ አቶ ይመስገን አልማውን እና ቤተሰቦቿን አስጨንቋል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ እታገኝ ባይሌ መስከረም 26 ቀን 2011 ዓ.ም የመውለጃ ቀኗ ስለነበር ወደ ፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሄዳ ነበር፡፡ ከረዥም ጊዜ ምጥ በኋላ በቀዶ ህክምና እንድጽገላገል ተወሰነና የስቃይ መቀነሻ የሰመመን መድኃኒት ተሰጣጽ፡፡ የሰመመን መድኃኒቱ (አንስቴዥያ) ግን ለከፍተኛ ስቃይ ዳረጋት፡፡ እስካሁንም ምግብ መመገብ፣ መናገርና መንቀሳቀስ አልቻለችም፡፡
ከወለደችበት መስከረም 26 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ በፍኖተ ሰላም ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲደርግላት ብትቆይም በጤናዋ ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል አልታዬም፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተላከች፡፡ ነገር ግን በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታልም በቂ ሕክምና ሳታገኝ ወራት ተቆጠሩ፡፡
ከባለቤቷ ከአቶ ይመስገን አልማው እና አባቷ አቶ ባይሌ ብርሃን ጋር ባደረግነው ቆይታ በሕክምና ስህተት በተፈጠረው ችግር በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ በግለሰቧ ላይ ደግሞ አሳሳቢ የጤና እክል እንደደረሰባቸው ነግረውናል፡፡ ‹‹እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በቀን እስከ ሁለት ሺህ ብርና ከዚያ በላይ በማውጣት ሊያነቃት ይችላል የተባለ መድኃኒት ሁሉ በመግዛት ሀብት ንብረቴን በሙሉ ጨርሻልሁ፤ ምንም የቀረኝ ንብረት የለም፤ በዚህ ሁኔታ ባለቤቴ የመዳን ዕድሏ ዝቅተኛ ነው›› ነው ያሉን ባለቤቷ ከእምባቸው ጋር እየታገሉ፡፡
የሕክምና ማስረጃዋ (ፋይሏ) ‹‹ሆን ተብሎ›› ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ላይ እንዲጠፋ መደረጉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸውም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ ሐኪሞችን ለማናገር ሞክረን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ባሁኑ ወቅትም በቅርብ ክትትል እንዲደረግላት በሚል ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆሰፒታል እንደተላከችና በጤናዋ ላይ መሻሻል አለመኖሩን ቤተሰቦቿ ነግረውናል፡፡
ዘጋቢ፡- አብዮት ከፋለ (አብመድ)
#መፍትሔ
የክልሉ ጤና ቢሮ፥ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የምመጤክአቁባ...የህክምና ሂደቱ እና ስነምግባር ላይ በቂ ምርመራ በማድረግ አስፈላጊው ህክምና እንዲደረግላት ማድረግና ስህተቱ/ችግሩ በባለሙያዎች ምክንያት ከሆነ በህጉ መሠረት እርምጃ መውሰድ!
በወሊድ ወቅት በተሰጣት #የሰመመን_መድኃኒት ምክንያት ከሁለት ወራት በኋላም አለመንቃቷ አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በወሊድ ወቅት የተሰጣት የሰመመን መድኃኒት ከሁለት ወራት በኋላም እንድትነቃ አላደረጋትም፤ ይህም ባለቤቷ አቶ ይመስገን አልማውን እና ቤተሰቦቿን አስጨንቋል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ እታገኝ ባይሌ መስከረም 26 ቀን 2011 ዓ.ም የመውለጃ ቀኗ ስለነበር ወደ ፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ሄዳ ነበር፡፡ ከረዥም ጊዜ ምጥ በኋላ በቀዶ ህክምና እንድጽገላገል ተወሰነና የስቃይ መቀነሻ የሰመመን መድኃኒት ተሰጣጽ፡፡ የሰመመን መድኃኒቱ (አንስቴዥያ) ግን ለከፍተኛ ስቃይ ዳረጋት፡፡ እስካሁንም ምግብ መመገብ፣ መናገርና መንቀሳቀስ አልቻለችም፡፡
ከወለደችበት መስከረም 26 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ በፍኖተ ሰላም ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲደርግላት ብትቆይም በጤናዋ ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል አልታዬም፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተላከች፡፡ ነገር ግን በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታልም በቂ ሕክምና ሳታገኝ ወራት ተቆጠሩ፡፡
ከባለቤቷ ከአቶ ይመስገን አልማው እና አባቷ አቶ ባይሌ ብርሃን ጋር ባደረግነው ቆይታ በሕክምና ስህተት በተፈጠረው ችግር በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ በግለሰቧ ላይ ደግሞ አሳሳቢ የጤና እክል እንደደረሰባቸው ነግረውናል፡፡ ‹‹እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በቀን እስከ ሁለት ሺህ ብርና ከዚያ በላይ በማውጣት ሊያነቃት ይችላል የተባለ መድኃኒት ሁሉ በመግዛት ሀብት ንብረቴን በሙሉ ጨርሻልሁ፤ ምንም የቀረኝ ንብረት የለም፤ በዚህ ሁኔታ ባለቤቴ የመዳን ዕድሏ ዝቅተኛ ነው›› ነው ያሉን ባለቤቷ ከእምባቸው ጋር እየታገሉ፡፡
የሕክምና ማስረጃዋ (ፋይሏ) ‹‹ሆን ተብሎ›› ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ላይ እንዲጠፋ መደረጉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸውም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ ሐኪሞችን ለማናገር ሞክረን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ባሁኑ ወቅትም በቅርብ ክትትል እንዲደረግላት በሚል ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆሰፒታል እንደተላከችና በጤናዋ ላይ መሻሻል አለመኖሩን ቤተሰቦቿ ነግረውናል፡፡
ዘጋቢ፡- አብዮት ከፋለ (አብመድ)
#መፍትሔ
የክልሉ ጤና ቢሮ፥ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የምመጤክአቁባ...የህክምና ሂደቱ እና ስነምግባር ላይ በቂ ምርመራ በማድረግ አስፈላጊው ህክምና እንዲደረግላት ማድረግና ስህተቱ/ችግሩ በባለሙያዎች ምክንያት ከሆነ በህጉ መሠረት እርምጃ መውሰድ!
Image may contain: 1 person, smiling, sleepingImage may contain: 1 person, standing and indoor

Tuesday, December 18, 2018

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ


 በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ብር ጭኖ በሚጓዙ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተሽከርካሪዎች  ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመውጥቃት አንደኛው ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ተሽከርካሪዎቹ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ይዘው ሻኪሶ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለማድረስ እያመሩ እንደነበረ ታውቋል።
ሻኪሶ ከተማ ለመድረስ 20 ኪሎሜትር ሲቀራቸው ጥቃቱ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን ብሩን የጫነው አንደኛው ተሽከርካሪ አምልጦ ሻኪሶ በመግባት ገንዘቡን ማስረከቡን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲላ ቅርንጫፍ የኦፕሬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ አብዱልፈታህ አብራር ለኢሳት እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ነው።
ከዲላ ቅርንጫፍ ብር ጭነው ወደ ጉጂ ዞን ሃያዲማ ቅርንጫፍ ያመሩት የባንኩ ሰራተኞች በማግስቱ ከሃያዲማ ወደ ሻኪሶ የሚያደርሱት ገንዘብ እንደነበር ነው ሃላፊው የሚገልጹት።
6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ጭነው በ10 ወታደሮች ታጅበው ከሃያዲማ ወደ ሻኪሶ እያመሩ በነበሩት የባንኩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ሻኪሶ ለመድረስ 20 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው እንደነበርም ሃላፊው ገልጸዋል።
ማንነታቸው ያልታወቁ ባሏቸው ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከወታደሮቹ ሁለቱ ሲገደሉ የሁለተኛው ተሽከርካሪ ሹፌሩም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።
ታጣቂዎቹ ከሃያዲማ ቅርንጫፍ ወደሻኪሶ ገንዘብ ጭኖ የሚሄደውን ተሽከርካሪ በጥይት መትተው ጎማውን ቢያተነፍሱትም ሹፌሩ በወሰደው ቆራጥ ርምጃ ጎማ የሌለው መኪና እያሽከረከረ ሻኪሶ መግባቱንና ገንዘቡን ከዘረፋ ማስመለጡንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ይህን ተግባር የፈጸመው ሹፌር በተተኮሰበት ጥይት የተመታ ሲሆን ገንዘቡን ካስረከበ በኋላ ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና መግባቱንም ለማወቅ ተችሏል።
የታጣቂዎቹን ማንነት በተመለከተ ኢሳት ባደረገው ማጣራት በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚያሳዩ መረጃዎች ደረሰውታል።
ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የሻኪሶ ንግድ ባንክ ሰራተኛ የኦነግ እንቅስቃሴ ጎልቶ የሚታይበት አካባቢ በመሆኑ በባንኩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት የሰነዘሩትም የኦነግ ታጣቂች ናቸው ሲል ለኢሳት ገልጿል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኦነግ አመራሮች ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ የኦነግ ታጣቂዎች ጉጂና አማሮ በሚዋሰኑበት አከባቢ ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የገደሉበትን ጥቃት መፈጸማቸው የሚታወስ ነው።

Saturday, December 15, 2018

በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነው ተባለ


በተለያዩ የትግራይ እስር ቤቶች ከ750 በላይ የራያ ተወላጆች ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ።
የራያ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ለኢሳትእንደገለጸው ተቃውሞ ከተነሳበት ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ በተወሰደ የጅምላ እስር 761 የራያ ተወላጆች ታስረውበአራት የትግራይ እስር ቤቶች ውስጥ ታጉረዋል።
ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ የሚገልጸው ኮሚቴው አንድ ሰው በድብደባ ምክንያት ህይወቱ ማለፉን አስታውቋል።
ከታሰሩት በተጨማሪ በርካታ የራያ ተወላጆች ደብዛቸው እንደማይታወቅም ተገልጿል።
መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በትግራይ እስር ቤቶች የሚደርሰውን የራያዎች ስቃይ እንዲያስቆም ኮሚቴው ጥሪ አድርጓል።
የራያ ማንነት ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደጀኔ አሰፋ ለኢሳት እንደገለጹት በአራት የትግራይ እስር ቤቶች 761 የራያ ተወላጆች በስቃይ ላይ ይገኛሉ።
በመቀሌ፣ በማይጨው፣ አዲሸሁና ኩይሃና እስር ቤቶች ውስጥ የታጎሩት የራያ ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ መረጃው እንዳላቸው ነው አቶ ደጀኔ የሚገልጹት።
ከአራቱ እስር ቤቶች በተጨማሪ በትግራይ በድብቅ ቦታዎች የሚገኙ እስር ቤቶች መኖራቸውን እናውቃለን ።
በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እንደሚፈጸሙት የስቃይ አይነቶች በእነዚህ የትግራይ ስውር እስር ቤቶችም የራያ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመባቸው ነው ብለዋል አቶ ደጀኔ።
ካለፈው ጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ በአላማጣና በሌሎች የራያ አካባቢዎች እንደአዲስ የተቀጣጠለውን ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ የተሰማራው የትግራይ ልዩ ሃይል በየዕለቱ የራያ ወጣቶችንና ተጽዕኖ ይፈጥራሉ የተባሉ ግለሰቦችን እያፈነ በመውሰድ ላይ እንደሆነም አቶ ደጀኔ ይገልጻሉ።
በትግርይ በሚገኙ እስር ቤቶችና ስውር የማሰቃያ ቦታዎች የተወሰዱት የራያ ተወላጆች ባለፉት ሁለት ወራት የተፈጸሙባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሰቃቂ ናቸው ያሉት አቶ ደጀኔ ብልት ላይ የሃይላንድ ውሃ ከማንጠልጠል ጀምሮ ከፍተኛ ድብደባና ስቃይ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
በአሁኗ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ በተዘጋበት ዘመን የራያ ተወላጆች በትግራይ ክልል ውስጥ እየተሰቃዩ እንደሆነ የገለጹት አቶ ደጀኔ አንድ የራያ ተወላጅ በድብደባ ብዛት ህይወቱ ማለፉንም ጠቅሰዋል።
የትግራይ ክልል መስተዳድር ራያ የማንነት ጥያቄ የለውም በሚል ጥያቄውን ያነሱትን በሙሉ በእስርና ወከባ እያሰቃየ እንደሆነም ተመልክቷል።
በትግራይ እስር ቤቶች በስቃይ ላይ ከሚገኙት በተጨማሪ ከ500 በላይ የራያ ተወላጆች ተፈናቅለው በራያ ቆቦ ተጠልለው እንደሚገኙም ተገልጿል።
በየእስር ቤቱ የሚገኙት የራያ ተወላጆች ፍርድ ቤት ሲቀርቡም ጉዳዩን የሚመለከቱት ዳኞች የህወሃት ሰዎች በመሆናቸው በፍርድ ቤት ያለው መጉላላትና የሰብዓዊ መብት ጥሰትም ለራያ ተወላጆቹ ከፍተኛ ፈተና እንደሆነባቸው አቶ ደጀኔ ገልጸዋል።
ይህ ሁኔታ እየከፋ በመምጣቱ የፌደራሉ መንግስት አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጥ የራያ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪ አድርጓል።

Thursday, December 13, 2018

መሸፈት ደግ ነዉ ለስልጣን ያሳጫል

ሰመረ አለሙ semere.alemu@yahoo.com
እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሺ ቀርቶ የገደለሺ በላ የሚባለዉ አባባል ለረጂም ዘመን ስሜት ሳይሰጠኝ ቆይቶ ዛሬ ተግባራዊነቱ ላይ ደርሻለሁ።
ቀደም ባለዉ ጊዜ ሰርቶና ጥሮ ግሮ መኖር ያልሆነለት  ዋልጌ ወሮበላ ሰርቶ አዳሪዉን ቀምቶ፤ ገበያተኛዉን አድፍጦና አስበርግጎ፤ መተዳደሪያዉን ነጥቆ፤የሀገር ሰላም አደፍርሶ በዚህም ተፈርቶና ተጠልቶ ተረግሞ ይኖር ነበር። ተፈጥሯዊ ህግ ነዉና በዚህ ዉንብድናዉ እስከ መጨረሻዉ መቀጠል ባለመቻሉ በመጨረሻዉ  የሰዉ እርግማንና ጥላቻ ተደማምሮበት የክፉ ስራዉ  ስበቱ ሲያመዘን በዱላ፤ በገመድ ከቀናዉም በጥይት ተደብድቦ ሳይሰቃይ ያልፋል ሬሳዉም ሰብአዊ ክብር ሳይሰጠዉ በመንገድ ተጎትቶ ለሌላዉ በመቀጣጫነት ያገለግል  ነበር። ልቡ በቁጭት የነደደዉ የባህር ዳር ወጣትም  በረከት ስምኦንን አለበት በተባለዉ ቦታ ቢያገኘዉ እጣ ፈንታዉ ከዚህ የተለየ አይሆንም ነበር።  

ወደዚህኛዉ ዘመን ስንሸጋገር ደግሞ ሺፍትነት የሚጀምረዉ ከጫካና ከመንደር ሳይሆን ከትምህርትና ከነገድ ተቋማት ነዉ። ጥቂት ጀብደኞች አብዛኞቹ በእጽ ሀይል ተገፋፍተዉ ትምህርቱም ሲከብዳቸዉ ሌላ ሀገር የተደረገዉ እኛስ ለምን ይቅርብን በሚል ፉክክር ትርፍ ያመጣል ብለዉ ያሰቡትን ርእስ/ብሶት/ጭቆናን ፈጥረዉ የራሳቸዉን ትርክት ጨምረዉ ተረታቸዉን በእዉቀት ለተጎዳዉና ማገናዘብ ለቸገረዉ ዜጋ በማር ለዉሰዉ ይግቱታል።  ቆየት ብለዉ  ሀይል ሲያገኙ ደግሞ እንደ ህወአት፤ ኦነግ፤ ኦብነግ፤ ኤነግ …ግ  በተራቸዉ አልቀበል ያላቸዉን በጥይት/በዱላ/በቡጢ ደብድበዉ ሃሳባቸዉን አፍንጫዉን ይዘዉ ይግቱታል።ጥቂቶች በግል የጀመሩት ብሶት፤ አመጽ፤ትርክት በግድ ህዝባዊ መልክ እንዲኖረዉ ይደረጋል ከድግግሞሽ  ብዛት ሳናዉቀዉ እኛም የህዝብ ተወካዮች አድርገናቸዉ ትርክታቸዉ ዉስጥ እንወድቃለን። ይህ ነዉ የሆነዉ ባለፉት 40 እና 50 አመታት። ይህ ባይሆን የትግራይ ህዝብ  በአእምሮዉ ለማሰብ እድሉ ቢሰጠዉ እንዴት ህወአትን ሊቀበል ይችላል? ኦሮሞም የእነ ዳዉድ/ሌንጮ/በያን ሀሳብ ከነገረሱ ዱኪ ከራስ ጎበና በላይ ባላከበረዉ ነበር።  እዉነት ለትግራይ ነገድ የአልቤኒያ ኮሚኒዝም በነመለስ የታዘዘለት ከኢትዮጵያዊነት በልጦበት ነዉ አረጋዊ በርሄን አምኖ የህወአትን ትርክት የተጋተዉ? እዉን የኤርትራስ ህዝብ የአፈወርቂና መሰሎቹ ተረት ከታላቅ አገር ዜግነት በልጦበት ነዉ? ጊዜ  እየመለሰዉ ነዉ ወደፊትም ብዙ እናያለን።
ዶ/ር አብይ ስለ ምርጫዉ ተቃዋሚ ተብዬዎችን ሰብስቦ ሲያናግራቸዉ አንዳንዴም እየተቁነጠነጡ አንዳንዴም ከዶ/ር አብይ ቀድመዉ ሃሳብ እንስጥ የሚሉ የዶ/ር አብይ ወዳጂ መስለዉ ክሬዲት ለማስቆጠርና ለመታጨት የሚጨናነቁት ከመግቢያዉ ላይ ከጠቀስነዉ  ሺፍቶች ብዙም የተለዩ አይደሉም። ልዩነታቸዉ  ጸጉራቸዉ የተበጠረ ነዉ፤ ሱፍ ይለብሳሉ፤እንደ ዘመኑ አቀራረብ እንግሊዝኛ ጣል ጣል ያደርጋሉ። ሆኖም የእዉቀታቸዉን ልክ የሚለካ የምርምር ስራዎቻቸዉን ግን  አስነብበዉን  አያዉቁም ብቻ ህዝቅኤል ጋቢሳ ስለ ጫት መጻፉን በአንድ ወቅት አንድ ጽሁፍ ላይ የተነበበ ይመስለኛል ከዚህ በተረፈ የነሱ ልዩ እዉቀትና ስልጠና በተስፋዬ ገ/አብ ትእዛዝና ትምህርት ዜጋን ከዜጋ ማጋጨት እንደምንም ተንሸራቶ ፖለቲካ ዉስጥ ተሸጉጦ መተዳደሪያቸዉን ማመቻቸት ነዉ። 
 ዲማ ነገዎ እሱም ፕሮፌሰር ነዉ መሰል በአንድ የቴሌቭዥን ገለጻዉ በጸጸት ” የአድዋዉን ፊታዉራሪ ገበየሁ ባልቻን አንዴት ኦሮሞ መሆኑን እንዳልሰማ  ሀዘኑን በቁጭት ገልጿል”።ፊታዉራሪ ገበየሁ ባልቻ ነገዱን  ሳይጠየቅ እነ ዲማ ነገዎ በጭራቅ ምስል የሳሏቸዉ አጼ ምንሊክ የኢትዮጵያን ጦር እንዲመራ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ አድርገዉ  ሹመዉት ነበር።ነገዱ ሳይሆን ሀገሩ ለሰጠችዉም ክብር ተመሳሳይ ዋጋ ለመስጠት ገበየሁ የሚያዝዘዉ ጦር እንደ መላላት ሲል የተሰጠዉ ክብርና ሃላፊነት ስለ ከበደዉ ለተዋጊዉ ምሳሌ ለመሆን “ስለ እኔ ወደ ሸዋ በህይወት የሚመለሱ ይናገሩ” በማለት ፈረሱን የሽምጥ ጋልቦ የጦርነቱ እሳት  ላይ ወደቀ እነ ዲማ/ሌንጮ/ዳዉድና መሰሎቻቸዉም አዉሮፕላኑን ከጭብጥ ገንዘብ ጋር አስቀዝፈዉ በስምምነት ወደ ሚያመቻቸዉ አገር ነጎዱ። ገበየሁ ዉድ ህይወቱን  ሳይሳሳ ለነገዱ ሳይሆን ለሀገሩ ሰጠ፤ ምሳሌነቱም ሀገሩን በሚወድ ዜጋ ዘወትር  ሲታሰብ ይኖራል። ከአድዋዉ ድል በሗላም ንጉሰ ነገስቱና የኢትዮጵያ ጦር በገበየሁ ሞት  ከልብ አዘኑ የጦርነቱን ድልም ድባብ ጣለበት።ገበየሁ ከነ ዲማና ከእነ አረጋዊ በርሄ  በላይ በኢትዮጵያዉያን ይከበራል ይዘከራል ኢትዮጵያ ትኖራለች እስካለችም ድረስ ትዉልድ እየተቀባበለ ዉለታዉን ያስታዉሰዋል እነ ዲማና ሌንጮ አረጋዊ ግን በህይወት እያሉ ተረስተዋል። 
በአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ እንጂ ዘሩ ባለመጠየቁ የተደራጀዉን የጥልያን ጦር  ዉጊያ ደረማምሶት ገባ በነዲማ/ዳዉድ/በያን ሱጳ፤ሌንጮ/አረጋዊ  ዘመን ግን ሰዉ በነገዱ ስለተሸነሸነ ትንሿን የዚያድ ባሬን ጦር መቋቋም ተስኖን የሆነዉን አሁን ያለዉ ትዉልድ የሚረዳዉ ይመስለኛል።በእንደነዚህ አይነት የአንድነት ጠላቶችና በክፉ የተመረዙ ግለሰቦች የወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቋጭ ዝግጂቱን ማየት በእጅጉ ያሳስባል። ዲማና መሰሎቹ  ሳያዉቁት የሚነገሩን በዘር ልክፍት በመለከፉቸዉ ምክንያት መሳሪያና ወታደሩን ከመቁጠር ይልቅ  ማን የማን ነገድ መሆኑን አድዋ ጦርነት ላይ እንድንመዘግብላቸዉ ነበር የፈለጉት እንዲህ አይነቱን ሰዉ ነዉ ፈረንጂ ዶፍቶር/ፕሮፌሰር እያደረገ ለአፍሪካ የሚልከዉ።
ወገኖች ኦነግን የትኛዉ የኦሮሞ ነገድ ተሰብስቦ ነዉ አንተ ምራን ብሎ ሌንጮን ወይም ዳዉድን የጠየቀዉ? አረጋዊና ህወአትንስ የትኛዉ ትግሬ ነዉ እናንተ ካልመራችሁን ብሎ በድምጽ ብልጫ የተማጸናቸዉ? ኦጋዴንም ሌላዉንም። ዶ/ር አብይ እንዳለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተቃዋሚ ነን ብለዉ እንቅስቃሴ ያደረጉት መሪዎቹ አንዱም አልሞቱም ተምረዉ ተመችቷቸዉ ሀብት ይዘዉ ይኖራሉ የሞተዉ የድሀ ልጅና እነሱን አምኖ የተመመዉ የዋሁ ወጣቱ ነዉ በአባባሉ እስማማለሁ። ታድያ ይህን ባለ ማግስት እነዚህ መሰሪዎች እነዚህ የህዝብ ዉክልና የሌላቸዉ ወንጀለኞችን ከፊት ለፊቱ ቁጭ አድርጎ ስለ ምርጫ ሲያናግራቸዉ ማየት ትንሺ ግር ያሰኛል።
እስቲ ሁሉም ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም አረጋዊ በርሄን ነጥለን እናዉጣዉ። ዶ/ር አብይ አንዳንዴ እንደ ኮሜድያን ነዉ ቀልድ በጣም ይችላል አቶ አረጋዊ በርሄ ብሎ በስብሰባዉ ላይ ሲጠራዉ ያለምክንያት አልነበረም። አረጋዊ በርሄ የዱፍትርና መመረቂያዉን የጻፈዉ ህወአት ስለተባለዉ ወንጀለኛ የናዚ ስብሰብ የመላእክት ጥርቅም ለኢትዮጵያ ደግ አሳቢ አድርጎ ስሎ ነዉ  እንዲህ አይነት ጥናትና ትርክት ለእዉቀት አስተዋጽኦ ባይኖረዉም ፈረንጆቹ አረጋዊ ስለ ኢትዮጵያ የሚፈልጉትን ሁሉ ካቃበላቸዉ በሗላ ደስ ይበለዉ ብለዉ ወረቀቱን ወርዉረዉለት ይሆናል። ምናልባትም አበበ ገላዉ ምርመራዉን ቢያጠናክር ላይኖረዉም ይችላል። ለማንኛዉም ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም አይንህ ላፈር ስላሉት እስቲ ማን ማንነቱ በማይታወቅበት ትልቅ ሀገር ሂጄ እድሌን ልሞክር በማለት ወደ አሜሪካ አቀና። እዛም ሳይጠራ በየስብሰባዉ አዘጋጆቹ ጎን በመቀመጥ ከአጀንዳዉ ጋር ያልተያያዘ ጥያቄ በመጠየቅ በማሳከር ወደ ሚዲያ ተቋማት እየደወለ ጠይቁኝ እያለ በማሰልቸት የፖለቲካ ተክለ ሰዉነቱን ገነባ። ተቃዋሚ ነኝ ብሎ በተገኘበት ቦታ ሁሉ መለስ ዜናዊን እንጂ ህወአትና አስነዋሪ ስራዉን ሳይተች ለዳግም ጥፋት የመለሰን ሌጋሲ በእሱ መንገድ ሊያስቀጥል ወደ ዶክተር አብይ ጉባኤ አቀና። 
በተመሳሳይ ሁኔታ ናቅፋ ላይ 5000 የትግሬን ወጣት መርቶ የኢትዮጵያን ወታደር ለእርድ ያቀረበ አርከበ እቁባይ 6 ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ዶፍቶር ተብሎ መመለሱ ተነግሮናል የመመረቂያዉ ጽሁፉም  ኢፈርት ስለተባለ የዘረፋ ቡድን እንደሆነ ይነገራል።  ይህ የሌባ ድርጅት ህገወጥ ስምምነቶችን አድርጓል፤ የተበደረዉን የህዝብ ገንዘብ መጥፎ ብድር በማለት አሰርዟል፤በጠራራ ጸሀይ ቡና ከዲፖ አሰርቋል፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁሉ ወስዶ ለራሱ አድርጓል።  ምርመራዉ ሲጀመር  የአርከበ ጥናታዊ ጽሁፍም ከግምት ይገባል የሚል እምነት አለን አርከበም በጻፈዉ በራሱ ማስረጃ ወደ ቃልቲ ይወረወራል (ፍትህ በኢትዮጵያ መጥቷል ከተባለ) ፈረንጅም የጋዳፊን ልጅ የሀሰት ዱፍትርና እንደቀማዉ ሁሉ ከአርከበም ተቀምቶ ዶክተር የሚለዉ ያለችሎታዉ የተሰጠዉ ማእረግ በሚገባዉ ማእረግ በአቦይ  ይተካል።
ወገኖች በጣም ያሳዝናል በኢትዮጵያ ዉስጥ  እየተሺከረከረ ብሄራዊ ባህላችን የሆነዉ የገደለንን ሀገር ላይ ያመጸን የከዳን ባንዳ ማክበርና ማባባል ነዉ። አጼ ሐይለ ስላሴ ባንዳ ሆዳም ነዉ ምቾት ይወዳል ጥልያን የሰጠዉ ምቾት ቢቀርበት እራሱን ይሰቅላል አገር ጤና ይነሳል ብለዉ በማሰብ የአንድነት ሀይሉ የትም አይሄድም አገሩን ይወዳል በሚል መንፈስ ባንዳዉን ሲንከባከቡት የአንድነት ሀይሉ አኩርፎ የሰሜን የአገራችንን ከፍልና የባህር በራችንን በኩርፈኞች ተነጠቅን። ለዚህም አረጋዊ በርሄና ድርጅቱ ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።
በዶር አብይ ዘመንም  በመጥፎ ሃሳብ የተመረዙ ተቃዋሚ ነን ባዮችን በመለመን፤ በማክበር፤ ሆቴልና ዊስኪ በማቅረብ ፤ ወደ ሀገር ቤት በማስገባት ህዝቡ ተስፋ የጣለበት የቲም ለማ ራእይ እንዲጨልም ሆነ። ይህ በመሆኑም ዳዉድ ኢብሳ በድፍረት ማን ማንን ትጥቅ ያስፈታል ብሎ በድፍረት ተናገረ ሁለተኛ መንግስት መሆኑንም ጠቆመ ራቅ ብሎ ያልቻለዉን ከዉስጥ እንዲበትነን ህጋዊ ፈቃድ ተሰጠዉ። ኦቦ ጁዋር መሀመድም ከፈለግሁ ኦሮምያን መገንጠል ማን ከለከለኝ ብሎ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ደሰኮረ የህወአትን ማኒፌስቶ የቀረጸዉ አረጋዊ በርሄ  ከዶር አብይና ከበታች ሹማምንት ቀድሞ ሀሳብ ሰጭ ሁኖ ተገኘ፤’ ከጅምሩ የወደፊቱ ጉዟችን ተስፋ መጨለሙም በገሀድ ታየ። እነዚህ ግለሰቦች በሺፍትነቱ ዘመን በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ ህይወት የቀጠፉ ወሮበሎች  ቤታቸዉ ቃልቲ መሆን ሲገባዉ መፍሄ ፈላጊ ሁነዉ መታየታቸዉ እዛ አገር ምን እየተሆነ እንደሆን መረዳት ይከብዳል። 
አረጋዊ በርሄ የህወአት ፈጣሪ፤መሪ፤የወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ሁኖ በሰራበት የሽፍትነት ስራዉ በትግራይ የሚኖሩ አፍቃሪ ኢትዮጵያዉየንን ከመፍጀት ባሻገር የመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ በደልና ዘረፋ የፈጸመ  የዜጋን ህይወት በመቅጠፍ ቀጥተኛ አመራር በመስጠት የተሳተፈ መሆኑ እየታወቀ ሰዉ እንደጠፋ ሁሉ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሃሳብ ሰጭ ሆኖ ስናየዉ ልባችን አዝኗል።  ጌታቸዉ አሰፋን እያደኑ አረጋዊ በርሄን ህገ መንግስት አርቅቅ፤ ሀሳብ ስጥ፤ በፖለቲካ ተሳተፍ ብሎ መጋበዝስ ምን የሚሉት ትያትር ነዉ? ለመሆኑ አረጋዊ በርሄ ድርጂት አለዉ ወይ? ግደይ ዘርአጽዮን አንዱ ወንጀለኛ የድርጅቱ አባል ነዉ ሁለት ሰዉ ድርጅት ሁኖ እንዴት የኢትዮጵያን መጻኢ ጊዜ ከሌሎች ጋር በግርግር ተቀላቅሎ እንዲወስን ይፈቀድለታል? ጎበዝ የሰዉ ደሀ አይደለንም ከታሪክ እንማር እንጂ ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ስተቀላቀል እንደነዚህ አይነት መርዘኛና ወንጀለቾችን ከአንድነት ሀይሉ በላይ ክብር ሰጥተን በመፍትሄ አሳትፈን ችግሩ ለዚህ ትዉልድ ተረፈ። በነ አረጋዊና በእነ ሌንጮ/ዳዉድ… ስንገረም እነ ስለሺም ሰብሰብ ብለን ድርጅት እንፍጠር ብለዉ ተሰባስበዋል መሰል ወይ ጣጣ ስንቶቻችን እናዉቃቸዋለን እነዚህን ሰዎች?።
ጎበዝ ስለ ቤተሰብ አይደለም የምንመክረዉ አረገዊ በርሄና ግደይ ዘራጽዮን በክብር ተጠርተዉ የወንጀላቸዉ ተጠቃሚ ሲሆኑ ከነሱ በተጻራሪ ከኢትዮጵያዊነት ጋር የቆሙ ህወአት በነብስ የሚፈልጋቸዉ እነ አቶ ገ/መድህን አርአያ እነ አቶ ጌታቸዉ ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)  ምን ይሰማቸዋል?  በነገራችን ላይ ከ30ሚሊዮን በላይ የአማራን ህዝብ በስምም ሆነ በመልክ የማያዉቀዉን አማራን በጠላትነት ፈርጆ በፖሊሲ ደረጃ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ የህወአቱ አረጋዊ በርሄና የህወአትን አስተሳሰብ ተግተዉ ስፍር ቁጥር የሌለዉን አማራ የፈጁ እነ ዳዉድ ኢብሳንና ሌሎች ኦነጎችን ጨምሮ  በዚያ መድረክ ላይ መገኘት አሁንም የአማራን ህዝብ ከመጥላትና ከመናቅ የመጣ ስለሆነ የአማራ ነገድ ለሚመጣዉ ክፉ ዘመን እራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል እላለሁ። 
ምንም እንኳን አበክረን ይህ የነገድ አስተዳደር ጥቅም እንደሌለዉ ብንገልጽም ዶ/ር አብይ  በአንድ ስብሰባ  ጁዋር መሀመድና ኦነጋዉያን  በተደጋጋሚ እንደሚነግሩን ስልጣን ለመያዝ የብሄር ስብጥር በግድ መኖር አለበት  ብለዉናል። ይህ አካሄድ አሁንም ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን  በተደጋጋሚ ያለመሰልቸት  ብዙ ወገኖች በምሁር እይታ ስጋታቸዉን ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከተከበረና ከተካበ ነገሮች ሁሉ በዜግነት እሳቤ ከገቡ ኢትዮጵያዊ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌልኛዉ ጫፍ አገሬ ነዉ ብሎ ካመነ የዘር ኮታ ከሚሰጠዉ በላይ የዜግነት እሳቤ ጥቅም መስጠቱን በተለያዩ አስተዳደሮች ተመልከትናል። ሐኪም ወርቅነህ፤ቡልቻ ደመቅሳ፤ክፍሌ ዳዲ፤ኮማንደር ዘለቀ፤ዳዊት ዮሀንስ፤ጸሀዩ እንቁስላሴ ፤ ገርማሜ ነዋይ ከብዙ በጥቂቱ  በተመደቡበት አካባቢ ለትዉልድ ቀያቸዉ ከሰጡት አገልግሎት በላይ ታላቅ ስራ በመስራታቸዉ ስማቸዉ ዘወትር በአካባቢዉ ነዋሪ ከሚዘከርላቸዉ ስመ ጥር ዜጎች ጥቂቶቹ  ናቸዉ። ይህ በብሄርና በሀይማኖት ስብጥር የሚደረገዉ አስተዳደር ለሃሳቡ አራማጆች መተዳደሪያ ይሰጥ ካልሆነ በስተቀር  ለአንድነትና ለመልካም አስተዳደር ምንም ጥቅም እንደሌለዉ እያሳሰብን እንግለዞችና ፈረንሳዮች በመካከለኛዉ ምስራቅ በነገድና በሀይማኖት አቧድነዉ አካባቢዉ ምስቅልቀሉ ሲወጣ እነሱ ዳኛም ፤ አስታራቂም፤ መሳሪያ ሻጭና ህንጻ ገንቢም  ሁነዉ ከወንጀሉ ተጠቃሚ ሆኑ እንጂ አካባቢዉ አሁንም የጦር አዉድማ ከመሆን በስተቀር የተፈለገዉ ሰላም አልመጣለትም ።
 ዶ/ር አብይ፤ ገዱ አንዳርጋቸዉ፤ለማ መገርሳ፤ብርቱካን ሚደቅሳ  ጊዜ ወስደዉ እነዚህ የጦር ወንጀለኞችን የዜጋን ህይወት በጥይት የቀጠፉትን፤ በዘረፋ የተሳተፉትን  እንደ ነጻ አዉጭና ተቃዋሚ ሁነዉ የቀረቡትን ድርጅቶች በገፍ እንደ ተቃዋሚ ድርጅት ከመዉሰዽ ይልቅ  የኢትዮጵያ ህዝብ መክሮበት ፕሮግራማቸዉ ታይቶ የአባሎቻቸዉ ብዛት  ተቆጥሮ በዘመናቸዉ ከወንጀል ነጻ መሆናቸዉ ተረጋግጦ በግልጽ ሃሳቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተሺጦ ተቀባይነት ካገኘ በሗላ በዚህኛዉ ሳይሆን ለወደፊት በሚመጣዉ ምርጫ እንዲሳተፉ እንዲደረጉ እንደ ዜጋ እያምላከትኩ ይህ ባለመሆኑ ግን  እስከ መርዛቸዉ ገብተዉ እንዲያቦኩ ከተፈቀደ ነገሩ ሁሉ ታጥቦ ጭቃ ከመሆኑም በላይ  ዉጤቱም ያለ ጥርጥር የከፋ ይሆናል። ተስፋ የተጣለባቸዉ መሪዎቻችንም በእጅ ጠምዝዝ ፖለቲካ እጅ መስጠት እንደሌለባቸዉም ከወዲሁ ማመላከት እንወዳለን። 
ዶ/ር አብይ ገዥም ተቃዋሚም ሁኖ ለነዚህ በሀሳባ ለተጎዱ ተቃዋሚ ነን ባዮች ሰብሰብ በሉ 3 በቂ ነዉ ብሎ ሃሳብ ሲሰጥ ጩሉሌዉ አረጋዊ በርሄ ዶር አብይ ከመጨረሱ  ምናልባት ሃሳቡን ሊለዉጥ ይችላል ብሎ በመስጋት  ሃሳቡን የተቀበለዉ ያለምክንያት አልነበረም። ሰዉየዉ ተንኮልን ተክኖበታል የድርጅት አባላትም የሉትም አረናል ትግሬ ከተባለዉ የአብረሀ ደስታ ድረጅት ጋር ካልተደመረ በስተቀር። አረጋዊ ሁለት መሰረታዊ ፕሮግራሞች አሉት አንዱ ጊዜ ጠብቆ እርቅና ሰላም የሚለዉን ከማንም በላይ አጉልቶ ማጮህ ነዉ በዚህም ሁለት ጥቅሞችን ያገኛል ይኸዉም የህወአት ወንጀለኞችን ከህግ ተጠያቂነት ማዳን ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ እሱም በዚህ ግርግር ከሰራዉ ወንጀል ነጻ ሁኖ የፓርላማ ወምበረን በማግኘት ዶ/ር አብይን በመማጸን ያሰበዉን ክፉ ስራ ማስፈጸም ይሆናል። ጎበዝ ደቡብ አፍሪካ ሌላ ኢትዮጵያ ሌላ በደቡብ አፍሪካ ወንጀለኞች ወንጀላቸዉ ተፍቆ ቀደም ሲል የያዙትን እንደያዙ ሳይሳቀቁ ተንደላቀዉ እየኖሩ ነዉ የሞተዉ የቆሰለዉ አካሉ የጎደለዉ ከነ ስቃዩ ይኖራል የእነ አረጋዊ ፕላንም በዚህ መልኩ እንዲቀጥል ነዉ። ፍትህ ለያንዳንዱ ዜጋ መድረስ አለበት የሺብሬ ደሳለኝን መስዋትነት አንርሳ። 
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ መሪ ይሄዳል ይመጣል መሪዎች የሚያደርሱት በደል መከራዉ ላንተ ነዉ ይህ እንዳይሆን መሪዎችህን ከመምረጠህ እድሉን ከመስጠትህ በፊት የሀገርና የአንድነት ፍቅራቸዉን ካደረጉት አስተወጽኦና ከሰሩት ወንጀል ጋር በማነጻጸር በድምጽህ ቅጣቸዉ እምቢ በላቸዉ አንተ አምጽ እንጂ እነሱ እንዲያምጹብህ እድል አትስጣቸዉ ስንቴ ያታልሉሀል ቀላማጂ ምላሳቸዉን ሳይሆን ስራቸዉን መርምር። ሐይል የህዝብ ነዉ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Tuesday, December 11, 2018

ገነት ዘውዴ እና ሙሉ ሰለሞን እንደ አናቃቂ ተናጋሪ (Inspirational speakers)


ገነት ዘውዴ እና ሙሉ ሰለሞን እንደ አናቃቂ ተናጋሪ (Inspirational speakers)
ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ
ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ህዳር 28፣ 2011ዓ.ም. (Ensuring sustainable development through empowering women academicians) በሚል ርዕስ በግዮን ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት መድረኮች ወጣት ሴት ተማሪዎችን፣ መምህርትን እና ሴት ተመራማሪዎችን የሚያበረታታ ስለሆነ ጉዳዩ ወቅታዊና ተገቢ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ አምባሳደር ዶ/ር ገነት ዘውዴ፣ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን፣ ፕሮፌሰር አለምፀሀይ እና ዶ/ር አስቴር ፀጋዬ አናቃቂ ተናጋሪዎች ሁነው ተጋብዘው ነበር፡፡ሁሉም ተናጋሪዎች ግሩም የሆነ የህይውት ተሞክሮዓቸውን ለወጣት ሴት ተማሪዎችና ሴት መምህራን አካፍለዋል፡፡
በተለይወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን እጅግ ግሩም የሆነች ተናጋሪ ከመሆንዋ በላይ ለሴት እህቶቻችን ጥሩ ምሳሌ መሆን የምትችል እህት ነች፡፡ የማትሰለች፣ አንደበተ-ርቱዕ፣ ድንቅ ኢትዬጲያዊ ነች፡፡ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን በተለያዩ መድረኮች በየክፍለ-ሀገሩ እና በየ-ትምህርት ተቋማት እየተዘዋወረች ንግግር ብታደርግ የበርካታ ኢትዬጲያዊ ሴቶችን ግንዛቤ የመቀየር እምቅ አቅም ያላት ፍቅር የሆነች ሴት ነች፡፡ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን የመምህርትን ባህሪ የተላበሰች፣ አቀራረብ የምትችል፣ ለዛ ያላት አስተማሪ ነች፡፡
አምባሳደር ዶ/ር ገነት ዘውዴም ንግግር ካቀረቡ ምሁራን አንዷ ነበሩ፡፡ አምባሳደር ዶ/ር ገነት ዘውዴን ለመጠየቅ ዕድል አግኝቸ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው የበፊቱ የኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የአሁኑ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ስመ-ጥር የሆነ የመምህራን ማፍለቂያ ተቋም ነበር፡፡ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ከሆነ ጊዜ ጀምሮ ግን እንደ ሌሎች የፊዴራል ዩኒቨርስቲዎች በሚጠበቅበት ደረጃ አለማደጉ የዶ/ር ገነት ዘውዴ የፖለቲካ ውሳኔ እንደ ነበር እና በኢትዮጲያም ለሚታየው የትምህርት ስርዓት ውድቀትም እንደ ሚኒስተር የዶ/ር ገነት ዘውዴ አስተዋፅዎ ከፍተኛ እንደነበረ እና ለነዚህ ጉዳዬች በምን ያህል መጠን እንደሚፀፀቱ ጥያቄ አንስቸላቸው ነበር፡፡ ዳሩ ግን ዶ/ር ገነት ዘውዴ የሚፀፀቱ ሰው እንዳልሆኑ ከንግግራቸው ለመረዳት ችያለሁ፡፡

የዶ/ር አብይ አስተዳደር ሁሉንም ነገር በይቅርታ እና በፍቅር ለማለፉ የሚያደርገውን ጥረት ከባንዳዎች ጋር ሁነው አገርን የዘረፉ፣ ትውልድን ያመከኑ፣ የበፊቱ ስርዓት ባለሟሎች ያጠፉት ጥፋት ሊታያቸው አለመቻሉን በዶ/ር ገነት ዘውዴ መልስ ለመረዳት ችያለሁ፡፡በህግ መጠየቅ እና እስር ቤት መግባት የነበረባችው የበፊቱ ስርዓት አጋፋሪዎች የመልካም ስራ ተምሳሌት ሁነው መቅረባቸው ምን ያህል የሞራል ልዕልናቸው እንደወረደ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን የበፊቱ አስተሳሰባቸው ምን ያህል ወደ ኃላ እንደሚጎትታቸው የተረዳሁበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ሰው ባጠፋው ጥፋት ተፀፅቶ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ይቅርታ መጠየቅ ሰብዓዊ ባህሪነው፤ ባጠፋው ጥፋት መታበይ ግን አላዋቂነት ነው፡፡አጥፊ ከሆነ ስርዓት ጋር ወይም ህዝባዊ ድጋፍ ከሌለው መንግስት ጋር ህዝቡን ሲበድሉ፣ ሲያሳዝኑ፣ሲዘርፉ፣ሲገሉ እና በትውልድ ህይወት ላይ ሲያፌዙ የነበሩ ግለሰቦችን እንደ ምሳሌ አድርጎማ ቅረብ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው መልዕክት ተጠያቂነት ከሌለው ስርዓት ጋር መወገን ምንም አይነት ዋጋ እንደማያስከፍል እና የአድርባይነትን ሰብዕና እንዲላበሱ ነው የሚያደርጋቸው፡፡ የመልካም ነገር ተምሳሌት መሆን የማይችሉ ዜጎችን ምሳሌ አድርጎ ማቅረብ የግለሰቦችን ደካማ ባህሪ ዕውቅና መስጠት እና ሌሎች እንዲጋሩት መጋበዝ ነው፡፡
ምሳሌ መሆን የሚችሉ ድንቅ ሴት ኢትዮጲያውያን ባልጠፉበት ሀገር የጥፋት ተልዕኮ ከያኒያንን የሆኑ ምሁራን እንደ አናቃቂ ተናጋሪ አድርጎ መጋበዝ የፖሮግራሙ አዘጋጆች ችግር ቢሆንም ለወደፊት መታረም ያለበት ክፍተት ይመስለኛል፡፡ ማንኛውም ዜጋ መመዘን ያለበት በደረሰበት የትምህርት ደረጃ እና በነበረው ስልጣን ልክ ሳይሆን ለወገን፣ ለሀገር፤ ለትውልድ ብሎም ለምድሪቱ ባበረከተው አስተዋፅኦ መሆን አለበት፡፡

Sunday, December 9, 2018

የቴዲ አፍሮ የኮንሰርት ትኬት ፎርጂድ ተሰራ


 ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለማቅረብ ፍቃድ አግኝቶ በኋላም ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ መንግስት አዳራሹን ይፈልገዋል በሚል ኮንሰርቱ ለአንድ ሳምንት የተራዘመበት ቴዲ አፍሮ የቡራዩ እልቂት እንደተከሰተ “ወገኖቼ እየሞቱ አሁን መዝፈን አልችልም” በማለት ኮንሰርቱን ማራዘሙ ይታወሳል:: : (ይህን ዜና በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ)
በተለይም ይህ የተሰረዘው ኮንሰርት ትኬት ተሽጦ ያለቀ በመሆኑ; ትኬት የገዙ ሰዎችን ፍላጎት ለመሙላት ድምጻዊው ከዚያም በኋላ ኮንሰርቱን ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በአዲስ አበባ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ የኮንሰርት ፈቃድ ሳያገኝ መቅረቱን ዘ-ሐበሻ እየተከታተከ ሲዘግብ ቆይቷል::
በሚሊዮን ብሮች የወጣበት ይኸው ኮንሰርት ጥቅምት 24, 2018 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንዲካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈቃድ የሰጠ ሲሆን ተሽጦ አልቋል የተባለው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ትኬት በፎርጂድ መታተሙና ፎርጂድ ትኬቱም እየተሰራጨ መሆኑ ስለተደረሰበት ከዚህ ቀደም ትኬት የገዙ ወገኖች ከነገ ጀምሮ በሚኒሊየም አዳራሽ በመገኘት ትኬታቸውን እንዲያስቀይሩ ጥሪ ቀርቧል::
በከተማው ፎርጂድ የኮንሰርት ትኬቶች በመሠራጨታቸውም ሕዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠይቋል::

source (ዘ-ሐበሻ)


በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትሰራ የነበረች አንዲት ቻይናዊት ሆስተስ በፖሊስ ከአገር ተባረረች

ዋንግ ዤንግዢያን የምትባለው የ28 አመት ሆስተሷ ባለፈው እሁድ ከስልጠና መባረሯን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአየር መንገዱ የደረሳት ሲሆን ይህን ተከትሎ በንዴት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ለማወቅ ችለናል፡፡ ደብዳቤው እንደደረሳት በአጠገቧ የነበረውን አውሮፕላን መስታወት ከመሰባበሯም በላይ ወደ እንግዳ መቀበያ ዴስክ በመሄድ ጠረንጴዛውን ገልብጣ ሌሎች ሰልጣኞች ላይ ጉዳት ልታደርስ ስትል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለች ምንጮች አስረድተውናል፡፡ አየር መንገዱ ለፖሊስ እንዳስታወቀው በወቅቱ በዚህች ቻይናዊት ድርጊት የተነሳ ከ580 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ተጎድቷል፡፡ ካለፈው ሁድ ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረችው ቻይናዊቷ ራሴን አጠፋለሁ ብላ ስለዛተች 24 ሰአት ሙሉ ፖሊስ ጥብቅ ቁጥጥር ሲያደርግባት መቆየቱን ከምንጮቹ ለመረዳት ችለናል፡፡ ቻይናዊቷ ድርጊቱን የፈፀመችው በመተጥ ሀይል ተገፋፍታ እንደሆነ የተናገረች ሲሆን ትላንት አርብ ከእስር ተለቃ ወደቻይና መባረሯን ለማወቅ ችለናል፡፡

የአዲስ አበባ ሁሉን-አቀፍ ንቅናቄ (አሁን) ምስረታ መግለጫ


ይህ መግለጫ የአዲስ አበባ ሁሉን-አቀፍ ንቅናቄ (አሁን) ምስረታን ያበስራል። አሁን ‘የአዲስ አበባ ባለቤትነት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው’ የሚልን መሪ ሃሳብ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ የተመሰረተ ሲሆን – የምስረታውም ዋነኛ ዓላማ ይህን እሙን ሃቅ በሃገራችን ፖለቲካዊ፥ ኢኮኖሚያዊና፥ ማህበራዊ መስተጋብር ይረጋገጥ ዘንድ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር ነው።

የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ ያገለገለችው አዲስ አበባ ሰበአዊነትን፥ አብሮነትን፥ መከባበርን፥ መወዳጀትን፥ መፋቀርን፥ መዋለድን እና መወሃድን በጎሳና ሃይማኖት ሳትገደብ ከሁሉም ማንነት በጎ በጎውን ወስዳ አዲስ የበለጸገ ማንነት (ዜግነት)ለሁሉም ያለ ልዩነት ያጎናጸፈች፣ እነዚህን ድንቅ እሴቶች የተላበሰ ‘አዲስአበቤ’ ማንነትም መፍጠር የቻለች የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ልብ የሆነች ከተማ ናት፡፡
ሆኖም ግን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት መሰረት፤ በቋንቋ ላይ የተመሰረተው “የብሔር-ፌደራሊዝም” መዋቅር፤ የአዲስ አበባን ሕብረ-ብሔራዊነት እና ብሔር ዘለል ሕብረ-ቀለማዊ ማንነት የሚያስተናግድበት አስተዳደራዊም ሆነ ርዕዮት-ዓለማዊ ማዕቀፍ የለውም፡፡ አገሪቱን በብቸኝንት ሲገዛ የኖረው የሕውሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ቡድንም ይህንኑ የመዲናይቱን ህልው እና ብዝሃ-ስብጥራዊ ማንነት በመካድ የዘረጋው የመዲናይቱ የአስተዳደርና የአገዛዝ ቀመር፤ በብሔር ተዋፅዖ እየተሰላ የሚሰፈር፤ ከላይ ወደታች፤ የሆነ ሹመት መሆኑ በሚገባ ይታወቃል። አዲስአበባም በዚህ ህገመንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ሳብያ በአሁን ወቅት በዘውጌ የፖለቲካ ቡድኖች ወዲህና ወድያ የምትላጋ፣ ስለእራሷ የማትወስን ከተማ ናት፡፡ ስለሆነም፣ ነዋሪዎቿ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ተነጥቀዋል፡፡ በፈቃዳቸው የሚሾሙትና የሚሽሩት እነርሱን የሚመስልና ተጠያቂነቱ ለእነርሱ የሆነ አስተዳደር እንዳይኖራቸው ሆነዋል፡፡ ህልውናቸውና ማንነታቸው ከህግና ከፖለቲካ ምህዳር ላይ ተፍቋል፡፡ ከገዛ ከተማቸው ባለቤትነትም ተሽረዋል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ አዲስ አበባን ብሎም ነዋሪዎቿን ዜጎች እንዳልሆኑ ሁሉ፣ በሰፋሪነት የመፈረጅ፣ በጠላትነት/ደመኝነት የመመልከት ክፉ አባዜ በሰፊው “የአክራሪ ብሔረተኛ የፖለቲካ ኃይሎች” ዘንድ ገኖ ይታያል። ይህም በከተማዋና ነዋሪዎቿ ላይ አብይ የደህንነት ስጋት ደቅኗል፡፡ የአዲስ አበባን ህብረ-ቀለማዊ ማንነት እና የአዲስአበቤዎችን ከተማ ወለድ እሴቶችንና ፍላጎቶችን ከግምት ያላስገባ (ያላገናዘበ) የፖለቲካ አስተዳደር ዛሬም የአዲስአበቤዎች ተግዳሮት ሆኖ ቀጥሏል።
ይህንን ሁናቴ በሚገባ በመረዳትና ከመደራጀት በቀር ምርጫ አለመኖሩን በመገንዘብ የአዲስአበባ ሁሉንአቀፍ ንቅናቄ አ.ሁ.ን የተሰኘ የአዲስ አበባን እና የነዋሪዎቿን ሁሉን አቀፍ መብት፥ ፍላጎት፥ ጥቅምና ውክልና የሚያረጋግጥ፤ ኢትዮጵያውያንን የመዲናቸው ባለቤት ለማድረግ የሚሰራ አለም-አቀፍ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ንቅናቄ ተመስርቷል። ከእዚህም አላማው በመነሳት፣ አ.ሁ.ን አዲስአበባን የተመለከቱ ታሪካዊ ምርምሮችን ለህዝብ ተደራሽ የማድረግ፥ በከተማዋ ጉዳዮች ዙርያ የተለያዩ ዕውቀት የማሰራጫና ግንዛቤ መፍጠርያ መድረኮችን የማዘጋጀት፣ የከተማዋንና የነዋሪዎቿን አንገብጋቢና ዘላቂ አጀንዳዎች በመለየት እነኝያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሰላማዊ ዘመቻዎችን አስተባብሮ የመምራት ስራ ያከናውናል። ሌሎች እዚህ ላይ ያልተመለከቱ አላማውን ለማሳካት የሚያግዙ በርካታ ተግባራትንም ለመፈጸም አቅዷል፡፡ አ.ሁ.ን ለአዲስአበባና አዲስአበቤ መብትና ጥቅም ለታመኑና ቁርጠኛ ለሆኑ ለማናቸውም አደረጃጀቶች ሁሉንአቀፍ ድጋፍ የሚያደርግ አለምአቀፍ ንቅናቄ ነው፡፡
አ.ሁ.ን በሁሉም የአለም ክፍሎች ወኪሎች የሚኖሩት ሲሆን በምስረታው ወቅት ወደ 2000 የተጠጉ አባላት አሉት። በቀጣይነትም ማንኛውም ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአባልነት እንዲመዘገብ፥ በጊዜ፥ በክህሎትና በገንዘብ በመደገፍ ለአላማችን ከግብ መድረስ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ እናቀርባለን።
የአዲስአበባ ሁሉንአቀፍ ንቅናቄ አ.ሁ.ንን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ማግኘትና የንቅናቄው አባል መሆን የምትሹ በሚከተሉት አድራሻዎች ልትጽፉልን ትችላላችሁ፤
1. contactAhunUS@gmail.com
2. contactAhunEU@gmail.com
3. contactAhunETH@gmail.com
በአንድነት አዲስ አበባንና አዲስአበቤነትን እንታደግ!
አዲስአበቤነት ይለምልም !!
ኢትዮጵያ ምንጊዜም በክብር ትኑር !!
የአዲስአበባ ሁሉንአቀፍ ንቅናቄ (አሁን)

Thursday, December 6, 2018

በቀድሞው የስለላ እና የጥርነፋ አሰራር የተዋቀረውን የኢትዮጵያን ኤምባሲዎች ሰራተኞች ላይ ቁጥር ቅነሳ እንዲካሄድ በጀርመን ኢትዮጵያውያን መግለጫ አወጡ



“በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ኤምባሲዎች ግንኙነት በሚመለከት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ በተግባር እንዲተረጎም እንጠይቃለን አብረንም ለለውጥ እንተጋለን።” ሲሉ በጀርመን በርሊን እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  መግለጫ አወጡ::
መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል::
በዋናነት የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት እስከ ቅርብ ጊዜ ለውጡ እስከመጣበት ወቅት ድረስ ታዋቂ ተግባር ኢትዮጵያውያኖች ለዲሞክራሲ እና ለሰባዊ መብት መከበር በሚያደርጉዋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ዝግጅቶች ስብሰባዎች ላይ የተሳታፊዎችን አስተሳሰባቸውን በነጻ የገለጹትን ለመብት እና ለህግ የበላይነት የታገሉትን በተለያየ አጋጣሚ ሃሳባቸውን በግል በነጻ የሚገልጹትን በወኪሎቻቸው አማካኝነት በመስማት መረጃ በመሰብሰብ ድምጾች በመቅዳት ፎተግራፎች በማስነሳት ቪዲዮ በማስቀረጽ ኢትዮጵያውያንን በጥቁር መዝገብ ላይ በማስፈር ወደ አገር ቤት የአገር ውስጥ እና ውጭ ደህንነት መስሪያ ቤት ማስተላለፍ ነበር። 
ብዙዎች የደረሰባቸው የስነልቡና ጭነት እና የመብት ጥሰት ብናስታውስ ፍርሃት እንዲሰፍን አገራቸውን እንዳያዩ ቤተሰብ እንዳይገናኙ ዘመድ እንዳይቀብሩ ማስፈራሪያዎች ለዘመድ ለጓደኞቻቸው ለቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ የተደረጉ እና የተሞከረባቸው ጥቂት አይደሉም።
የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት በዚህ ተግባር ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ከለውጡ በኋላ በይቅርታው ጉዞ በዝምታ ቢታለፍም ስነልቦናዊ ለውጥ ያልታየበት አሰራሩን ቀጥሎበት በፍራንክፈርት ጠ/ሚኒ አብይ አህመድ ከኢትዮጵያውያኖች ጋር በአደረጉት ስብሰባ ዝግጅት ላይ ተሳታፊዎችን ቁጥር የቀነሰ ያጒላላ እና የተሰራ ዝብርቅርቅ እስከ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ዋናው ተጠያቂው የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ሃላፊነት አልወሰደም። ሙሉ በሙሉም ይቀርታ እስከ አሁን ድረስ በግልጽ አልጠየቀም።
ከዚህ በታች እንደሚከተለው ከ1-5 ያሉ ጥያቄዎችን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እናቀርባለን።
(1).በጠ/ሚ አብይ አህመድ የፍራንክፈርት ስብሰባ ላይ በተሳታፊዎች ላይ ለደረሰው መጉላላት እና የዝግጅቱ መተረማመስ የፍራንክፈርቱ ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት ሙሉ ሃላፊነት እንዲወስድ በግልጽ በዋናነት ሙሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ እንጠይቃለን።
(2.)የፍራንክፈርቱን ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት የሃገር ሃብት ብክነት አስራር  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲመረምር እንዲሁም ለዝግጅቱ የወጣው ጠቅላላ ወጭ በፍራንክፈርቱ ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት በዝርዝር በግልጽ ባስቸኳይ ይፋ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
(3.)የሃገር ሃብት አውዳሚ የሆነው በቀድሞው የስለላ እና የጥርነፋ አሰራር የተዋቀረውን በርሊንም ኤምባሲ ሆነ በፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽ/ቤት ሰራተኞች ላይ ቁጥር ቅነሳ እንዲካሄድ እንጠይቃለን።
(4.) በበርሊንም ኤምባሲ ሆነ በፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽ/ቤት እውቅና በሌለው የጎንዮሽ ግንኙነት ያለ ሃቅ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት እንዲቀር እና የድብቅ ጥሪ ሆነ ወይንም ማንኛውም የድብቅ ማደራጀት እንዳይኖር እንጠይቃለን።
(5.)በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመት የተሰጣቸው ዳይሬክተር ጄኔራሎች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መካከል እኚሁ የፍራንክፈርት ቆንስል ጀነራል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ አገሮችና የአውሮፓ ህብረት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሆነው መሾማቸው አጠያያቂ ነው እንላለንል። የፍራንክፈርት ቆንስል ጀነራሉ ለሃገር እና ለወገን በዚህ ቦታ የሚሰሩትን ዲፕሎማሲ ካሳለፍነው ልምድ በከፍተኛ ጥረጣሬ እንመለከተዋለን። ለተቃና የውጭ ግንኙነት በቦታው በማሳደድ ዲፕሎማሲ የልተካፈሉ ሙያተኞች እንዲመደቡበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እንጠይቃለን።
የበርሊን እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን

Saturday, December 1, 2018

“በ21 አክሱም ጺዮን በ22 ደብረጺዮን!”


ከደብረ ጺዮን ወደ አክሱም ጺዮን | ክንፉ አሰፋ
መቀሌ ለደበቀቻቸው “ጀግኖች” ባለ ውለታ ናቸው። ከዚህም በላይ ይገባቸዋል የሚሉ አሉ። እምነት ለነሱ ኢምንት ነው። ሃይማኖት ደግሞ ፖለቲካ። ልብ ያለው ፈጣሪን ያስባል። ይሉኝታ ያለው አምላኩን ይፈራል። ህሊና ያለው ደግሞ የእግዚአብሄርን ስም ይጠራል። ይህ ሁሉ የሌለው ግን በባዶነቱ ዝም ብሎ ይቁነጠነጣል። ይህ አዲስ አይደለም። ራስ እንጂ ጭንቅላት ከሌለው ሰው ተቃራኒው ቢፈጸን ነበር የሚደንቀው።
አንዱ ሰው ጓደኛውን ይጠይቀዋል። “እስኪ ለአፍታ አስበው በጫቃ መሃል ውስጥ ነህ። አንበሳ ሊበላህ አሰፍስፎ ይጠብቅሃል። ምን ታደርጋለህ?”
ልጁ መለሰ። “ማሰብ አቆማለሁ!”
እያወራን ያለነው በአንበሶች ተከብበው ማሰብ ስላቆሙ ሰዎች ነው።
ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል የቤተ ክርስትያንዋን ካባ ይልበሱ። ባለ ልዩ ማዕረጉን አክሊልም ይድፉ። ይህ የሆነው ከንሰሃ በፊት ይሁን ወይንስ ከንስሃ በኋላ ግልጽ አልሆነልንም። ከካይሮ እስከ ቡሳን፤ ከባንኮክ እስከ ዱባይ፣ ከናይሮቢ እስከ ቬጋስ በጉዞ ላይ የፈጸሙዋቸው የዝሙት ነውሮች ለዚህ ሽልማት ሊያበቁ እንደማይችሉ ቤተ ክርስትያን ሳታውቅ ቀርታ አይደለም። ከቶውንም ዝሙት እና ሌብነት ለተክሊል የሚያበቁ ጀብዶች እንደማይሆኑ ግልጽ ነው።
አክሱም ጺዮን በኢትዮጵያ ክርስትና ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ትይዛለች። ሰለሞናዊው ስርወ መንግስት ንግስና የሚጸናውም በዚያ ስፍራ ነው። የታሪክ መዛግብት እንደሚነግሩን፤ ሁለት መቶ ሃያ አምስቱ የሰለሞናዊ ነገስታት ከንግስናቸው በኋላ ወደ አክሱም ጺዮን መሄድ እና ስልጣናቸውን ማጽናት ግድ ነው።
አቡነ ማትያስ ስለ ዶ/ር ደብረጺዮን ንግስና የነገሩን ባይኖርም፤ በዚያ ታሪካዊ ቀን ይህንን የማድረጋቸው ምክንያት ግልጽ ይመስላል። ንጉሰ ነገስት ህወሃት ዘማሌሊት።
ነብሳቸውን ይማርና አቡነ ጳውሎስ ቢዮንሴን ባስተናገዱ ግዜ
“በ7 ስላሴ፣
በ8 ቢዮንሴ
በዘጠኝ እኔ ራሴ” እያለ ሕዝብ ሲቀልድባቸው ነበር።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዶ/ር ደብረጺዮንን በህዳር ጺዮን ማርያም ሲያነግሱ፤
“በ21 አክሱም ጺዮን
በ22 ደብረጺዮን!” ተብሏል።
ችግሩ ከአልባሳቱ ላይ አይደለም። ስብዕናው የወረደ፤ በሙስና እና በዝሙት የሚከሰስን አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ፤ በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ በዚህች ታሪካዊ ስፍራ ላይ ያላግባብ ከፍታ ላይ ማስቀመጡ የማድረጉ እንደምታ ነው። ቤተ-ክርስትያንዋን ለማርከስ ከመሞከር በላይ ይህ ጉዳይ ትልቅ ትርጉም አለው።
ጠባብ የክልል አስተሳሰብ ይዘው መጡ። ሰላማዊ ሕዝብ ላይ እንደ ማሽላ ዘሩት። በሲስተሙ ሰው ሲባላ እነሱ ግን ኖሩበት። በመጨረሻ የለኮሱት እሳት ራሳቸውኑ መብላት ሲጀምር፤ ዳግም መቀሌ ላይ ተሰበሰቡ። ገዳዩም፣ ዘራፊውም፣ ቄሱም፣ ጳጳሱም፣ …. መክረው የመጀመርያ የሆነውን ንግስና እውን አደረጉት።
እርግጥ ነው ነፍጥ አንጠንጥሎ እንደፈለጉ የማድረጉ ሰዓት አሁን ረፍሮበታል። በዳዩ፣ ከሳሹ፤ ምስክሩ እና ዳኛው አንድ የነበረበት ዘመን እንደ ዋዛ አልፏል። የፖለቲካ ቁማራቸውን በቤተ-እምነትን ውስጥ ይዞ ብቅ ማለት ግን ወንድ ልጅን አስገድዶ ከመድፈር የላቀ ወንጀል መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም።
አይቶ የማይመለከት፣ ረግጦ የማይቆምና ይዞ የማይጨበጥ የዥዋዥዌ ፖለቲካውን ባናቱ ላይ ተሸክሞ ሲቁነጠነጥ የነበረው ሰውዬ፤ ዛሬ ወደ አክሱም ጺዮን ብቅ ብሏል። አካሄዱ ረጋ ያለ የኤሊ ጉዞ ቢሆን ኖሮ ከጀርባ ያዘለውን ጉድ በጥርጣሬ የሚያየው አልነበረም። ሩጫው የብርሃን ፍጥነት ሆነና ሕዝበ አዳምን “ጉድ” ማሰኘቱ አልቀረም።
አሁን ለታ ቤተ-ክርስትያንዋ ዶ/ር አብይ እና ባለቤታቸውን ጠርታ የክብር ካባ አልብሳ ሸልማቸው ነበር። አግባብ ያለው ሽልማት። በሁለቱ ሲኖዶስ እርቅ ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነበር የተሸለሙት።
ዶር ደብረ ጺዮን የግፈኞች እና ሌቦችን እየተንከባከቡ በመቀሌ ዋሻ ከማቆየት ውጭ። ተጠርጣሪን አሳልፌ አልሰጥም ከማለት ውጭ የትኛውን ጽድቅ ስራ ሰርተው ለዚህ ክብር እንደበቁ ግልጽ አይደለም።
የማሌሊት መጥምቀ-ዮሃንስ፣ የአልባንያ ኮምኒዝም ሃዋርያ፣ የሂትለሩ ጎብልስ ደቀ መዝሙር ናቸው ደብረጺዮን። በርዕሰ አድባራት ፅዮን ማርያም በር ላይ እንኳ ለመድረስ ይዳፈራሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም። ጽዮን ማርያም ታሪካዊ ናት። ኢትዮጵያ ክርስትናን ለመጀመሪያ ይዞ በገባው በአቡነ ሰላማ ዘመን የተገነባች ጥንታዊ ቤ/ክርስቲያን። አስርቱን የፈጣሪ ትእዛዛት የያዘው የሙሴ ጽላት በሚገኝባት።
በሃይማኖት ሸፋን የፖለቲካ ጨዋታ ለመጫወት መሞከሩ አንድ ነገር ነው። ገና መዳህ ሳይጀምር በማርክሲዝም ሌኒንዝም ርዕዮት ደደቢት በረሃ ለተጠመቀ ሰው የተክሊል ቆብ መጫን፤ ከፖለቲካ ውጭ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም።
ኮምፒዩተሩ ሃክ ተደርጎ የሰውየው መረጃ መንገድ ላይ ተሰጥቶ ባየን ግዜ አማትበናል። አሁን ግን ሃክ የተደረገው ኮፒዩተር ሳይሆን የዘውድ አክሊል የጫኑለት አባቶች ጭንቅላት ነው። መቼም አንጎላቸው ሃክ ተደርጎ ካልሆነ በስተቀር በጽድቅ እና በኩነኔ፤ በሃላል እና በሃራም መሃል ያለው ልዩነት አይጠፋቸውም። አልያም የዘር ካርድ ከልመዘዙ በአንድ ፖለቲከኛ ክንድ ብቻ አይዘወሩም።
በመጀመርያ ለዝሙቱ እና ለሌብነቱ ሃፍረት መሸፈኛ መንገድ ሳይቀይስ የህዝብን አንጀት መብላት መሞከር በራሱ ጅልነት ነው።
ብዙ የፖለቲካ ዚግዛግ አይተን ይሆናል። የደብረ ጺዮኑ አይነት ግን የተለየ ነው። በፖለቲካ ግራና ቀኝ እርግጫ አስገርሞን ሳያበቃ ቤተ ጸሎት ዘው ብለዋል። ሁለት ባላ ትከል። አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል አይነት ነው። ንጋት ላይ ሌባን ስለማጥፋት ሲነግሩን ቆይተው ምሽት ላይ “የምን ሌባ” ይሉናል። በዚህ ተደንቀን ሳንጨርስ ደግሞ የሌቦችን ቀን መቀሌ ያከብሩልናል። በአድዋና በአዲግራት ላይም ይደግሙልናል። ግራ ገብ ነገር!
አበው ሲተርቱ ሳይቸግር ጤፍ ብድር ይላሉ። ሰዎቹ መቀሌ ላይ በሸሸገቻቸው ግፈኞች ሳብያ ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ናት። ችግሩ በጫጫታና በትእይንተ ሕዝብ አይፈታም። የጦርነት ከበሮ መደለቅም መፍትሄ አይሆንም።
ደብረጺዮን በዚህ አቋማሜ የት ድረስ ልሄድ እችላለሁ የሚለው ጥያቄ ሃሳብ ሊገባቸው ይችላል። የሚሄድበትን ለማያውቅ፤ ሁሉም መንገድ ይወስደዋል። ግራ ገብ ተጓዥ ወደ ጥፋትም ይሁን ወደ ልማት፣ ሽቅብ ይሁን ቁልቁለት ዝም ብሎ ይሄዳል። ምክንያቱም አይን የለውም። ልብም የለውም። ሕዝቡን እሱ ወደሚጓዝበት ይመራዋል። ወደየት እና የት ድረስ እንደሚሄድ ግን የሚይውቅ የለም።
የቱንም ያህል ይወዛወዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጋር መጻፈጡ ግን ወጋ ከማስከፈል ውጭ ትርፍ አያመጣለትም። የመኒ-ቴክ (ይቅርታ ሜቴክ) ሃላፊን ለማስመለጥ ሞክረው አልተሰካም። ሌላዎቹን እስከ መቼ መደበቅ እንደሚችሉ ይታያል።
እንደ ናይጄሪያው የሽብርተኛ ቡድን መሪ ቦኮ ሀራም በረሃ ካልገባ በቀር ሁሉም የፍትህን ደጃፍ ይረግጣታል። መተናነቁ ያለው ከመቶ ሚሊየን ከሕዝብ ጋር መሆኑን ለአፍታም ባይዘነጉት መልከም ነው። ጆ ቢደን እንዳሉት “ሌብነትን መዋጋት መልካም መስተዳደር ማምጣት አይደለም። ራስን መከላከል እንጂ”
ካልተያዙ በስተቀር ሌብነት ሥራ ነው የሚለው የሙዚቃ ሪትም አሁን ሲያከትም፤ እነሱ በተራቸው ሰልፍ ተማሩልን። ቅኝቱን ሲለውጡት ደግሞ የዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን ንግስና አበሰሩን።
እስቲ ይሁና። የጀርመኑ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ እንዲህ ይላል። “ቢያስሩን እና ሊገድሉን ካልቻሉ የበለጠ ጠንካራ ያደርጉናል።”
ሌላው ጎርፍ ነው። ይሄዳል
Image may contain: 3 people

የምትመለከቱት አፅም በአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን የሚገኝ የፊታውራሪ ገበየሁ ነው።



ይሄ ክቡር የሆነ አፅም አንተ ሰው ሆነህ በሰውነትህ እንድትኮራ የተከሰከሰልህ አፅም ነው።የአፅሟ ፍንካች የነጻነት ምልክት ናት።ጫት ይዘህ መፈረሻ ላይ እንደ ድመት ስትድበለበል ከመዋል፥ጃቦ ከምትገለብጥ መፅሐፍ ግዛና አንብብ!!
ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) በ25 አመቱ ጀብድ የፈጸመ ብላቴና ነበር።
"ያ ጎራው ገበየሁ
አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው
ለምሳም ሳይደርሱ ቁርስ አደረጋቸው"ተብሎ የተገጠመላቸው ፊታውራሪ ገበየሁ በእንዳ ኪዳነ ምህረት በኩል የመጣውን እና በጄኔራል አልበርቶኒ የሚመራውን የጠላት ጦር አፈር ደም አስግጠው ለእናት ሀገሩ በለጋ ዕድሜው የተሰዋ አጸበራቂ ኮኮብ ነበር።
ከዓድዋ ድል በኋላ በጃንሜዳ የጦር አበጋዞች በፈረስ ሲያልፉ የፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው ፈረስ ብቻውን ከፊት ሲያልፍ ያዩት አፄ ምኒልክ ተንሰቅስቀው ያለቀሱት ገብርዬን እንዳአጡት አጼ ቴዎድሮስ ያን ትንታግ የ25 አመቱን ወጣት ገበየሁን በማጣታቸው ነው።
የምትመለከቱት አፅም በአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን የሚገኝ የፊታውራሪ ገበየሁ ነው።

ሰባት ህንዳዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ታግተናል አሉ

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ስራ ላይ የተሰማራው il&FS አይኤል ኤንድ ኤፍኤስ የተሰኘው የህንድ ኩባንያ ሰራተኛ የሆኑት ህንዳዊያን እንደታገቱ ገለፁ፡፡ ከታጋቾቹ አንዱ እንደሆነ የገለፀው ኒራጅ ራጉዋንሺ በትዊተር ገፁ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው እሱን ጨምሮ ሰባት ህንዳዊያን ከታገቱ አራት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ኩባንያው ለሰራተኞቹ ደመወዝ ባለመክፈሉና ያለበትን እዳም ሊከፍል ባለመቻሉ ኢትዮጵያዊያኑ ሰራተኞችና አበዳሪዎች እገታውን እንደፈፀሙም አስረድቷል፡፡
ኩባንያው ከሁለት አመት በፊት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አማካኝነት የወጣውን አለም አቀፍ ጨረታ አሸንፎ ወደስራ የገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት እንደከሰረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የሰራተኞቹ ደመወዝና ያለበት እዳ እንዲከፈል በተደጋጋሚ ለኩባንያው ጥያቄ ቢያቀርብም ከኩባንያው አጥጋቢ ምላሽ ሊያገኝ እንዳልቻለ የጠቆመው ራጉዋንሺ መልእክቱ ለጠ/ሚ/ር ናሬንድራ ሞዲ እና ለካቢኔያቸው እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ታጋቹ ግለሰብ በተከታታይ ትዊት ያደረገ ሲሆን በእነዚህ ትዊቶቹም ‹‹አሁን ከታገትንበት ብንለቀቅም የአካባቢው ባለስልጣናት እስር ቤት ያስገቡናል፣ ወይንም ኩባንያው በፈጠረው ስህተት የአካባቢው ነዋሪ ይገድለናል›› ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡ በመልእክቱ እንዳስረዳው የታጋቾቹ ጥፋት ለኩባንያው ታማኝ በመሆን ፕሮጀክቱን ለመጨረስ መስራታቸው ነው፡፡ እነዚህ ህንዳዊያን ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር ተገናኝተው እንደነበር የተናገሩ ሲሆን የባለስልጣኑ ሰራተኞችም እርምጃ ከሚወስዱባችሁ በፊት የአካባቢውን ነዋሪ ወዝ አደር ደመወዝ መክፈል አለባችሁ የሚል ምክር እንደሰጧቸው አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲም ተመሳሳይ ምላሽ እንደሰጣቸው ነው የተናገሩት፡፡
አሁን ከወደ ህንድ በሰማነው ዜና ደግሞ ኪሳራ ደርሶበት አክሲዮኑ በሀራጅ እየተሸጠ ያለውን ይህን ኩባንያ እያስተዳደረ ያለው ተቋም ስለጉዳዩ ሰምቶ ከኢትዮጵያ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ድርድር ጀምሯል፡፡ ለዚህ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ዋስትና የሚሰጥ የህንድ ድርጅት ካለ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ታጋቾቹ የሚለቀቁበትን መንገድ ሊፈልግ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ኩባንያው ከነቀምት እስከ ቡሬ ያለውን ከ160 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ በስምንት አመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ኮንትራቱን የወሰደው በ223 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ይህም ገንዘብ የተገኘው ከአለም ባንክ ከተገኘ ብድር እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡

ጋናዊው የእግር ኳስ ተጨዋች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እየተፈለገ ነው

ኪንግ ፋይሳል የተሰኘው የጋና ክለብ አጥቂ የነበረው ሞሪሰን ኦሲይ በተቃጠለ ቪዛ አገር ውስጥ በመቆየቱና በሆቴል እዳ በኢትዮጵያ ፖሊስ እየተፈለገ ነው፡፡ ራሱ ተጨዋቹ ለጋና ጋዜጦች እንዳስታወቀው ከኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጋር የነበረው ኮንትራት ከተቋረጠ በኋላ ላለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል፡፡ ሲናገርም ‹‹እኔ ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ኢትዮጵያ ቡና ክለብን ለመቀላቀል ነበር፡፡

ነገር ግን እኔን ያስፈረሙኝ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ወደአገራቸው መመለሳቸውን ተከትሎ ክለቡ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ክፍያ ሳይፈፅምልኝ ኮንትራቴን ሊያቋርጠው ችሏል›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹በዚህ የተነሳ ሌላ ክለብ እያፈላለኩ እያለ ቪዛዬ ለወራት ያህል ተቃጥሎብኛል፡፡ እንዲሁም የሆቴል ወጪዬንም ክለቡ ሊከፍልልኝ ፈቃደኛ አልሆነም›› ሲል ለጋና ጋዜጦች ዛሬ በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል፡፡ በመሆኑም ያረፈበት ሆቴል አስተዳደር እዳውን መክፈል ስላልቻለ ስለሁኔታው ለፖሊስ በማመልከቱ መታሰርን ፈርቶ ከአዲስ አበባ ውጭ ሌላ ከተማ መደበቁን ተጨዋቹ አስረድቷል፡፡
ደብዳቤውን በመቀጠል ‹‹አሁን የኢትዮጵያ ፖሊስ እያሳደደኝ ነው፡፡ አንዳንዴ የምደበቅበት ቦታ እያጣሁ መኪና ስር የማድርበት ጊዜም አለ፡፡ አሁን ከኢትዮጵያ ለመውጣት 3ሺህ 500 ዶላር ለኢምግሬሽን አገልግሎት መክፈል ይጠበቅብኛል፣ ግን ምንም የለኝም›› በማለት አትቷል፡፡
ሞሪሰን ኦሲይ በእስያ ፕሮፌሽናል ሆኖ የተጫወተ ሲሆን ከዚያ ቀደም ሲልም በኸርት ኦፍ ላየንስ ክለብ ተሰልፎ በጋና ፕሪምየር ሊግ ተጫውቶ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ደረሰላቸው



በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ ኬቭ ላይ ይፋለማሉ፡፡
የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜን ውድድር ለመከታተል ደጋፊዎች በዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭ መከተማቸው ተነግሯል፡፡
የዘንድሮውን የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሪያል ማድሪድ የሚያነሳ ከሆነ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፥ እንዲሁም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ለማሸነፍ ነው የሚፋለመው፡፡
ሊቨርፑል ዋንጫውን የሚያነሳ ከሆነ ደግሞ በታሪኩ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳ ተብሎ ታሪክ ይጻፍለታል፡፡
አስገራሚው ዜና ይህ ነው:: ዛሬ ቅዳሜ ምሽት በኪየቭ ዩክሬን ለሚደረገው የሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ውድድር፣ የሊቨር ፑል ደጋፊዎች የሚወስዳቸው አውሮፕላን እጥረት ተፈጥሮ ነበር። ነገር ግን በከተማውና በቡድኑ ጥረት ለሚታወቁ አየር መንገዶች ኮንትራት በመስጠት ጉዞውን ለማቀላጠፍ ጥረት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ከተመረጡት መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንዱ ሆኖ፣ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ዛሬ ዓርብ ጠዋት ከሊቨርፑሉ ጆን ሌኖን አየር ማረፊያ ኪየቭ ዩክሬን ድረስ አመላልሷል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ደረሰላቸው ተብሏል::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ 100 አውሮፕላን በመጨመር ከአፍሪካ ቀዳሚነቱን አረጋግጧል።

በመቱ ከተማ ሰልፍ ተካሄደ | በቤኒሻንጉል 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ



በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር ከተሞች አካባቢ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች እና የክልሉ ፖሊሶች መገደላቸውን ተከትሎ በም ዕራብ ኦሮሚያ የሚደረገው ሰልፍ ቀጥሏል:: በዛሬው ዕለት በመቱ ከተማን ጨምሮ በሌሎችም የም ዕራብ ወለጋ ከተሞች መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ የሚጠይቁ ሰልፎች ሲካሄዱ ውለዋል::
ኦዴፓ በዜጎች ላይ ደም ማፍሰስ የፈጸሙትን እና ሌቦችን የገቡበት ገብቼ እይዛቸዋለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ ነበር::
በሌላ ዜና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፥ ፖሊስን ጨምሮ በአካባቢው የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል:: የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::
ከቤኒሻንጉል ሳንወጣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካመሸ ዞን የቀጠለውን አለመረጋጋት የሸሹ ወገኖች ዛሬ ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ መምጣታቸውን የአማራ ቲቪ ዘግቧል። ተፈናቃዮቹ በእግራቸው በመጓዝ የመጡ ሲሆን፣ የሞቱ ሰዎችን መንገድ ላይ ማየታቸውን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ቢኖርም ካማሸ ዞንን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ አለመከፈቱም ተገልጿል። መንገዱ ከተዘጋ አራት ወር አልፎታል::
ከካማሺ ዞን ‹‹ያሶ ወረዳ›› አካባቢያቸውን ትተው ቻግኒ ከተማ የገቡት እነዚሁ 45 የሚሆኑ ወገኖች ችግሩ እየከፋ በመምጣቱ ስጋት ውስጥ መግባታቸውንና በዚህም አካባቢውን ለቀው መምጣታቸውን ; ሌሎችም እየተከተሉ መሆኑን ገልጸዋል::
ተፈናቃዮቹ በቻግኒየከተማ አሥተዳደሩ ቢሮ ውስጥ ተጠልለዋል፡፡ ከሁለት ቀናት በፊትም ከካማሺ ዞን ሸሽተው የመጡ 69 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች በዚሁ ሥፍራ ተጠልለው እንደነበር የቻግኒ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አረጋየሁ ወረደ ተናግረዋል::
ቤኒሻንጉል ዜጎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ሆነዋል፤ የዕለት ምግብ ፍጆታቸውንም ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡ የቤኔሻንጉል ክልል መንግሥትም ከአቅሜ በላይ ነው ብሏል፡፡

Wednesday, November 28, 2018

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ነዳጅ በመጥፋቱ ከፍተኛ የመኪናዎች ሰልፍ እየታየ ነው፡፡ ለእጥረቱ ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተጠየቁት የሚመለከታቸው ባለስልጣናት እጥረቱ የተከሰተው ህገወጥ የነዳጅ ገበያ በመጨመሩ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ለሪፖርተር ጋዜጣ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለእጥረቱ ዋነኛ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እየተቀዳ በየመንደሩ ስለሚሸጥ ነው ብለዋል፡፡ ይህን ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ እጥረቱ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ከማደያዎች ውጪ በተለይ ቤንዚን በኪዮስኮች ጭምር እየተሸጠ ነው›› ያሉት ሃላፊው ይህንን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለ ጥረት የላላ መሆኑ ደግሞ ችግሩን እንዳባባሰው ጠቁመዋል፡፡
ይህ አንዲህ እንዳለ የመስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ህገ ወጥ የነዳጅ ሽያጩ የተባባሰው ወደጎረቤት አገራት ስለሚሸጥም ነው ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም ከጎረቤት አገራት ጋር ያለው የንግድ ግንኙነት ገደብ ሊበጅለት እንደሚገባ የጠቆሙት ህዝብ ግንኙነቱ የትኛው ጎረቤት አገር እንደሆነ አልገለፁም፡፡ ይሁንና ኤርትራን ማለታቸው እንደሆነ ይታመናል፡፡

Tuesday, November 27, 2018

የብርቱኳን ዉለታ አለብን ከሳዲቅ አህመድ

ከሳዲቅ አህመድ
ብርቱኳንን የተዋወኳት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊዎች በታሰሩበት ሰሞን ነው።እራሷ ናት የደወለችልኝ። ስለታሰሩት ኮሚቴዎች ጠየቀችኝ።ስለ እስር ቤት አሰከፊነትም አጫወተጭኝ።ከድምጿ አዘኔታን፣ ርህራሄን ሰምቻለሁ። አቅሟ በቻለው መጠንም ማድረግ የሚገባትን እንደምታደርግ ቃል ገብታ ነበር።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል ዋሽንግተን ዲሲ መጥተን በህገወጥ መንገድ ስለታሰሩት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እንድናስረዳ ብርቱኳን ሁናቴዎችን አመቻቸች። በቀነ ቀጥሮውም መሰረት እኔና አብዱሰላም (የደስደስ) ያሲን ቦታው ላይ ተገኘን። ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ከብርቱኳን ጋር በግል ተወያየን።በወቅቱ ስለ ኮሚቴው የምንሰማው ነገር እንዳለ ጠየቀችን።እኔ ማስረዳቱን ስቀጥል ብርቱኳን ድንግጥ አለች።ስቅጥጥ ሲላትም አየሁ።በጣም የምትንሰፈሰፍ ሆና አገኘኋት። እስር ቤት የሚጎዳና የሚሰብር ነው። ብርቱኳን ሚደቅሳ ላሸባሪዎቹና ለማፍያዎቹ ህወሃቶች ሳትሰበር የነርሱን የተፈረካከሰ እኩይ ተግባር ለማድቀቅ የበቃች ጀግና ሴት በመሆኗ ሁሌም አክባሪዋ ነኝ። የህግ ባለሙያ የሆነው አብዱሰላም (የደስደስ) ከህግ አንጻር የኮሚቴውን እስርና በፍትህ ስርአት ዉስጥ የተፈጸመውን ሸፍጥ በተዋጣለት መልኩ አስረዳ።ተሰብሳቢው በተመስጥኦ አዳመጠ።አብዱሰላም (የደስደስ) ንግግሩን ሲጨርስ ጭብጨባው ጎላ ያለ ነበር።
በግዜው የአሸባሪነት ትርክት ( narrative) በአለም የመገናኛ ብዙኋን ላይ ናኝቷል።አሸባሪው ህወሃት በኢትዮጵያዊ ዉስጥ አሸባሪነትን ፈብርኮ የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ለማስመታት ይጥራል።ያሰራቸውን ኮሚቴዎች ጂሃዳዊ ሐረካት በሚባል የሐሰት ዘጋቢ ፊልም ባሸባሪነት ፈርጆ የምእራብን ምጽዋት ለማግኘት ይንደፋደፍ ነበር-ህወሃት። ዛሬ መቀሌ በሽፍታነት የገባው የነ ጌታቸው አሰፋ ቡድን ከዚህ እኩይ ተግባር ያንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ይህንን ሴራ ለማክሸፍ ብርቱኳን ሚደቅሳ ባደባባይ ወጥታ ባትናገርም በውስጥ የተቻላትን አድርጋለች።ከተለተለያዩ አለምአቅፍ ተቋማትም ጋር ትገናኝ ነበር።በተለያቱ ግዜያትም ብርቱኳን እየደወለች ስለኮሚቴው ስትጠይቅኝ ኮሚቴዎቹ በእስር ቤት ውስጥ የሚተነፍሱትን የስቃይ ትንፋሽ እየተነፈሰች እንደሆነ ይሰማኝ ነበር።

ብርቱኳን ከህወሃት እስር ቤትና የሽብር ጥቃት ተርፋ፣ መንፈሷን በለውጥ እሳቤ አጎልብታ፣ አሜሪካ በቆየችባቸው አመታቶች በትምርቷ ተራቃ የመጠቀች ድንቅ ሴት ናት።ብርቱኳን ለብዙ ሴት እህቶች #የይቻላል መንፈስን የለገሰች፣በትግል ጣራ ላይ ወጥታ ሌሎች ሴቶችን የሳበች የሴት ተምሳሊት ናት።ዛሬ ሴቶች አገሪቷን ለመምራት ግማሹን ካቢኔ ሲረከቡ፣ሴቶች በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ ሲቀመጡ በውስጣቸው ብርቱካናዊ ቁርጠኝነት፣ብርቱካናዊ የአላማ ጽናት አለ ቢባል የእብለት አይሆንም።ብርቱኳን የምርጫ ቦርድን መምራቱ ቢያንሳት እንጂ አይበዛባትምና ልብ ያለው ልብ ይበል።
ይህ ብርቱካናዊ የትግል ጥላ አሁንም ባሉ፣ገና በሚወለዱ ሴት ልጆች ላይ አርፎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች እርሷን መስለው ከርሷ በላይ ይሆኑ ዘንድ ምኞቴ ነው።እኛም ወንዶች ከርሷ ጥንካሬ ብዙ የምንማረው ነገር አለ ስል ብርቱዋን ብርቱካን መልካም የስራ ዘመን ይሁንልሽ እያልኩ ነው።
በዚህ አጋጣሚ ከላይ የጠቀስኩትን የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ስብሰባም ይሁን ሌሎች የዲፕሎማሲና የላቢ (lobby) ስራዎች ላይ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ የኔ ብሎ ሚዲያ ላይ ሳይወጣ በውስጥ ብዙ ስራዎችን ሲሰራ የነበረውን ዝምተኛውን ጀግና ከባዱ በላቸው ሳላመሰግን አላልፍም።

Monday, November 26, 2018

ኦነግ አዲስ ፓርቲ አይደለሁም እንደ አዲስ አልመዘገብም አለ

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) ከምርጫ ቦርድ ጋር የጀመረው ውዝግብ ቀጥሏል፡፡ ከውጭ አገር የገቡ ፓርቲዎች በሙሉ በቦርዱ እንዲመዘገቡ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ኦነግ ግን አልመዘገብም ብሏል፡፡
ለዚህ ያቀረበው ምክንያት ደግሞ በ1983 የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የተመዘገብኩ ስለሆነ ድጋሚ መመዝገብ አያስፈልገኝም የሚል ነው፡፡ ይህንኑ ምክንያት ጠቅሶ ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ማመልከቻው ውድቅ እንደሆነበት ከምንጮች ሰምተናል፡፡ አሁን በስራ ላይ ባለው የቦርዱ ህግ መሰረት አንድ ፓርቲ ለሁለት የምርጫ ወቅቶች ካልተወዳደረ ምዝገባው እንደሚሰረዝ መደንገጉን ለማወቅ ችለናል፡፡
በመሆኑም ፓርቲው እንደአዲስ እንደሚመዘገብ በህጉ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንደአዲስ ለመመዝገብ መተዳደሪያ ደንብ ማቅረብ፣ ጠቅላላ ጉባኤ ማከናወን፣ አባላትን ማሳወቅና ሌሎችም ሂደቶችን ማለፍ ይጠይቃል፡፡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ግን የቦርዱን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ገልፀው ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል፡፡

Thursday, November 8, 2018

"ያለማንነቱ በግድ በአጋሜዎች የተጨፈለቀው የኢሮቭ ብሔረሰብ ኢሮብ እንጅ ትግሬም ኤርትራዊም አይደለሁም "አለ።







"ያለማንነቱ በግድ በአጋሜዎች የተጨፈለቀው የኢሮቭ ብሔረሰብ ኢሮብ እንጅ ትግሬም ኤርትራዊም አይደለሁም "አለ።
-------------------------------------------------------------------
ኦሮባ – ኢሮብ – ‹‹ወደ ቤት ግቡ ›› ማለት ነው!


የኢሮብ ህዝብ በትግራይ ክልል ጉሎ መኸዳ ወረዳ የሚኖር፣ ራሱን የቻለና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነም የራሱ የሆነ ማንነትና ቋንቋ ያለው: ኢትዮጵያዊ ነገድ ነው።

ኢሮብ በትግራይ ክልል፣ ምሥራቃዊ ዞን የሚገኝ ሲሆን በምሥራቅ አፋር፣ በሰሜን ደግሞ ኤርትራ ያዋስኑታል፡፡

ብዙዎቻችን የኢሮብን ህዝብ ልክ እንደ ህውሓት ወይም እንደ ትግሬ በመቁጠር ለጉዳዩ ትኩረት ሳንሰጥ እንዲሁ ስናላግጥ ውለናል።
የኢሮብ ህዝብ ልክ እንደ ወልቃይት ዐማራ በትግሬዎች የተዋጠ ነገድ ነው። ትግርኛ አይናገሩም። የራሳቸው ቋንቋና ባሕል ያላቸው። በታሪክ አጋጣሚ ግን ከባንዳዎች መሃል ሳንድዊች ሆነው የተገኙ ምስኪን ማህበረሰቦች ናቸው።

በ2007ዓም በተደረገው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መሠረት የኢሮብ ብሔረሰብ ብዛት ህውሓት አውቃ በሴራ ካልቀነሰችው በስተቀር 33407 እንደሆኑ ነው የማእከላዊ እስታስቲክስ መሥሪያቤት ሪፖርት የሚያመለክተው።

"ኢሮብ "የሚለው መጠሪያ ነገዱም ወረዳውም ይጠራበታል።

¶ ይህ ነገድ በውስጡ ሦስት ዓይነት ማኅበረሰቦች ያሉት ሲሆን :-

1•አንደኛው "ቡክናይታ" ይባላል፡፡

2•ሁለተኛው ማኅበረሰብ "ሀሳበላ" ይባላል።

3•ሦስተኛው ማኅበረሰብ ደግሞ "እንዳልገዳም" (አድጋዲ ዓረ) ይባላል፡፡

ህውሃቶች "ኢሮብን " ለኤርትራ ሽጠው ህዝቡን በወልቃይት ለማስፈር ነው ዋነኛ እቅዳቸው ። የትግሬ አንባገነኖች በግድ ከ50 ዓመት በላይ የተጨፍለቁት ኢሮቦች እንደ ዐማራው ህውሓት እንዲጠፍ ከወሰነችባቸው ነገዶች ውስጥ ቀዳሚ ናቸው ።

ይህ ነገድ ልክ እንደወልቃይት ዐማራ በትግራዮች በግድ ማንነቱን ነጥቀው እንዲጠፋ የተፈረደበት ምስኪን ነገድ ነው።

"ሳሆ ብሔረሰብ"
ከኢሮብ ህዝብ ከሚናገረው ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቋንቋ ያለው ነገድ" ሳሆ "በመባል የሚታወቀውና አሁን በኤርትራ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ብሔር ብቻ ነው።

" የኢሮብና የሳሆን ብሔረሰቦች" የሚለያያቸው የሚከተሉት እምነትና የኢኮኖሚ መሰረታቸው ብቻ ነው።

በአፋር ግዛት አካባቢ የሚገኙ የኢሮብ ነገድ አባላት ናቸው። ቋንቋቸው ግን አንድ ነው።

የኢሮብ ህዝብ እኔ ነኝ ያለ አራሽ ገበሬ ነው፡፡ ልክ በደቡብ ኢትዮጵያ እንደሚኖሩት " የኮንሶ" ነገዶች ተራራውን በእርከን አሳምረው ምርት የሚያፍሱ ታታሪ ገበሬዎች ናቸው ኢሮቦች።

እነ "ኢህአፓ" የትጥቅ ትግላቸውን ሲጀምሩ በኢሮብ አካባቢው ካሉት ተራሮች መካከል " አሲምባ " የሚባለውን ተጠግተው ነበር የትጥቅ ትግላቸውን የጀመሩት። ኋላ ላይ ህውሓት አርዳ በልታ ድራሻቸውን አጠፋቻቸው እንጂ። ከመታረድ የተረፉትን እነ ተፈራ ዋልዋ ፣ እነ በረከት ስምኦን ፣ እነ አዲሱ ለገሰን በራሷ አምሳል " አራጅ " አድርጋ እስክትፈጥራቸው ድረስ የኢሮብን ህዝብ ቀለብ ተሻምተው የሚበሉ ነበሩ። ኢሮብ ለበድኑ ብአዴንም ባለውለታ ነገድ ነው።

"ዳውሃን "የኢሮብ ነገድ ዋና ከተማ ሲሆን፤ ኢትዮ አሜሪካዊው 6 ተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ኢትዮጵያዊው አትሌት ምሩጽ ይፍጠርም የኢሮብ ነገድ አባላት ናቸው። ነፍሱን ይማረውና ምሩጽ በደህና ጊዜ ይህን ጉድ ሳይሰማ አርፏል። ይብላኝ ለቅዱስ ፓትሪያርኩ አይናቸው እያየ ነገዳቸው በቁሙ ተሽጦ ኤርትራዊ ነህ ለተባለው።

ይኽ ነገድ ባለፉት 50 ዓመታት የአካባቢው የተፈጥሮ ሁኔታና የትግራይ ትግሪኝ የፖለቲካ ኤሊቶች ኅብረት ፈጥረው ከምድረ ገጽ ድምጥማጡን ሊያጠፉት የወሰኑበት አሳዛኝና ምስኪን ሀዝብ ነው። ኢሮብ በሰሜናዊ ምስራቅ ትግራይ የሚኖር ብሔረሰብ ነው።

ሻአቢያና ህውሓት ደግሞ ይኼንን ብሔር በኢትዮጵያዊነቱና ኢትዮጵያዊነቱን በማቀንቀኑ ይጠየፉታል። አሁን ግን በሁለቱ ምክክር ከነ አካቴው ህውሓትና ሻአቢያ ተባብረው ድምጥማጡን ለማጥፈት የወሰኑና የቆረጡ ይመስላል።

ተመልከቱ አንድም የትግሬ ህውሓት ባለሥልጣን ወጥቶ ከጎናቸው ሊቆም አልፈቀደም። የራያ ዐማራውና ፆታውን ቀይሮ ህውሓት የሆነው ደፋሩ ጌታቸው ረዳ ሊያናግራቸው በኼደ ጊዜ የኢሮብ አባላት " ትግርኛ ስለማንሰማ በዐማርኛ " አውራን እንዳሉትም ይነገራል። ለዚህም ነው እንደ ባርያ እንዲሸጡ የተፈረደባቸው።

ዛሬ የኢሮብ ህዝብ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ለሻአቢያም እንዲሁም ለህውሓትም ግልጽ የሆነ መልእክት አስተላልፏል። እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ኤርትራውያን አይደለንም። አራት ነጥብ ብለው ወስነው እርግጡን ተናግረዋል። በሌላም በኩል በዛሬው ዕለት በዓዲግራት ከተማ የሚኖሩ የኢሮብ ነገድ አባላት ታሪካዊ የሆነ ኃይለኛ ስብሰባ ከማካሔድ አልፈው በቀጣይም ለሚያደርጉት ትግል በከተማ ደረጃ 9 ኣባላት ያለው ኣስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም ሰብሰባቸውን አጠናቅቀዋል።

የኢሮብ ህዝብ በየትኛውም ክፍለ ዘመንና በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ የኤርትራ አካል ሆኖ ኣያውቅም "ኢሮብ ኢሮብ እንጅ ትግሬም አይደለም" ።

እናም ጎበዝ ይኼን እንደ ወልቃይት ፣ እንደ ጠገዴ፣ እንደ ራያና እንደ አላማጣ ህዝብ በግድ ትግሬ ነህ ተብሎ የህውሓት በትር የሚያርፍበትን ህዝብ ቢያንስ በሞራል ከጎኑ ልንቆም ይገባል።

ነገዱን ሁለቱ ሻአቢያና ህውሓት በረቀቀ ጥበብ ሊያስወግዱት የሚፈልጉት ነገድ ነው። እናም ይኽን ከፍተኛ የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቶ ያለውን የኢሮብ ውሁድ ነገድ ለማዳን ድምፅ እንሁናቸው።

-ትግራይ ውስጥ "ኩናማ " ምዕራብ ትግራይ ሸራሮ አካባቢ እስከ ተከዜ ወንዝ በስፋት ይገኛል
-አሳሁርታ/ሳሆ/ቢሄረሰብ ከአክሱም ሰሜን ከራማ ምዕራብ እስከመረብ ወንዝ በስፋት ይገኛል
-ኢሮፕ አዲግራት ጉሎመከዳ አውራጃ እስከ አሲምባ ተራራ ድረስ ይገኛል ።

በጣም የሚያሳዝነው እነዚህ ታላላቅ ቢሔረሰቦች የራሳቸው ልዩ ዞን የላቸውም በቋንቋቸው አይማሩም እንደኔ እንደእኔ አዲግራት የኢሮፓውያን ዋና ከተማ መሆን አለባት አክሱም የአሳውርታዎች ሸራሮ የኩናማ ዋና ክልላዊ ከተማ መሆን አለባቸው ታዲያ የእውነት ፍትህ ካለ ነው::

ቀጣይ ትግራይ ውስጥ ያለንማንነቱ እየተጨፈለቀ ስላለው

"ዋጅራት ብሔረሰብ "በቅርቡ ይጠብቁን።

#ልሣነ-ዐማራ
#Amharapress

የራያ እና የወልቃይት የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን አስመልክቶ ከሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የተሰጠ መግለጫ




~"ራያ ቀደም ሲል በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውሰጥ የነበረ ሲሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ተጠቃሎ በአሁኑ ሰዓት በትግራይ ክልል አስተዳደር ስር ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎ ለበርካታ አመታት በቋንቋቸውና በባህላቸው የመታወቅ ብሎም የመጠቀም፣ የማዳበር እና የማስፋፋት ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደተጣሰ በአዲስ አበባ የሚገኙ የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሰመጉ አስረድቷል"


~"በወልቃይት ጠገዴ የሚኖሩ ዜጐች በአማርኛ ቋንቋ እንዳይነጋገሩና የአማርኛ ሙዚቃ እንዳይሰሙ እየተከለከሉ ነው፤ ይህንን ትዕዛዝ ጥሶ የተገኘ ሰው እየተደበደበና እየታሰረ ይገኛል"

(ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ.ም)

በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ የራያን ህዝብ የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ይዘው ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓም ሰልፍ በወጡ ዜጐች ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል በወሰደው የሃይል እርምጃ ቢያንስ 9 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸውን፤ 16 ወጣቶች በጥይት መቁሰላቸውን፤ እንዲሁም ከ50 በላይ ወጣቶች እየተደበደቡ ታፍነው መወሰዳቸውን ምንጮች ለሰመጉ አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም ከ500 በላይ የሚሆኑ የአላማጣ ወረዳ ወጣቶች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ከተገደሉት ሰዎች መካከል፡

1)ነጋሲ እዮብ
2)ካሳ ንጉስ
3) መሀመድ ዋከዬ
6) ሞላ አብርሃም እንደሚገኙበት የሰመጉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ራያ ቀደም ሲል በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውሰጥ የነበረ ሲሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ተጠቃሎ በአሁኑ ሰዓት በትግራይ ክልል አስተዳደር ስር ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎ ለበርካታ አመታት በቋንቋቸውና በባህላቸው የመታወቅ ብሎም የመጠቀም፣ የማዳበር እና የማስፋፋት ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደተጣሰ በአዲስ አበባ የሚገኙ የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሰመጉ አስረድቷል፡፡ የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ለሰመጉ እንደገለፁት ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እየተፈፀሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን ለጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ ቢያሳውቁም መንግስት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት በመንፈጉ ችግሩ ተባብሶ እዚህ ደረጃ ደርሷል፡፡

ራያ አላማጣ


የፌደራል መንግስት የራያ ህዝብ ያነሳውን ህገ- መንግስታዊ የማንነት ጥያቄ እና ከጥያቄው ጋር ተያይዞ እየተከሰቱ ያሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሰከነ ሁኔታ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በተከተለ መንገድ እንዲፈታ ሰመጉ ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም መንግስት ከራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የዜጐችን በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት እና የነፃነት መብቶች ላይ ጥሰት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ ሰመጉ ይጠይቃል፡፡

በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ከዚህ ቀደም ”በኢ.ፌዲሪ ሕገ-መንግስት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጐች ላይ የሚፈጸመው ግድያ፣ ሕገወጥ እስራት፣ አፍኖ መሠወር፣ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ 141ኛ ልዩ መግለጫውን ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓም ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ሰመጉ በመግለጫው የመጀመሪያ ክፍል የአማራ ብሔረተኝነት የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት 34 የወልቃይት ተወላጆች መገደላቸውን፣ 93 ሰዎች ታፍነው የደረሱበት አለመታወቁን ጨምሮ በተለያዩ ሰዎች ላይ ድብደባ ማሠቃየት፣ ሕገ ወጥ እስራቶች መፈፀሙን እና የእርሻ መሬት፣ መኖሪያ ቤትና ንብረታቸውን መነጠቃቸውንና ዜጎች መፈናቀላቸውን ዘርዝሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የወልቃይትን ሕዝብ የማንነትና የታሪክ ጥያቄ ለማጥፋት የአካባቢውን ነባር የቦታ ሥያሜዎች በአዲስ ሥያሜዎች መቀየራቸውን የኮሚቴው አባላት መግለፃቸውን ጠቅሶ ሰመጉ በሪፖርቱ ይፋ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ከ141ኛ ልዩ መግለጫ በኋላም የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በተለያዩ ጊዜያት በወልቃይት ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለሰመጉ ሲያመለክቱ ቆይተዋል፡፡

ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለተለያዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማትና ለኤምባሲዎች የተነጠቀ የአማራ ማንነታችን እንዲመለስልን ለ6ኛ ጊዜ የቀረበ አቤቱታ በማለት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡ ኮሚቴው ከ1974 ዓም ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ግፍና በደል ሲፈፀምበት ቢቆይም ለሕዝቡ ጩኸት መንግስት የሚጠበቅበትን ምላሽ እንዳልሰጠ አስረድቷል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ ለማፈን እያጋጠሙ ያሉ ወቅታዊ ችግሮች ናቸው በማለት ኮሚቴው በአቤቱታው ላይ ከዘረዘራቸው ችግሮች መካከል፤



ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትን በፀረ ሽብር ሕግ በመክሰስና በማሰር ከቆየን በኋላ መንግስት ለሰላም ሲል በወሰደው እርምጃ ከእስር የተፈታን ቢሆንም አሁንም የኮሚቴው አባላት በየሄዱበት እየታሰሩ ነው፤ ሌሎች አባላትም ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸዉ በስደት ላይ ይገኛሉ፤

ከዚህም በተጨማሪ በወልቃይት ጠገዴ የሚኖሩ ዜጐች በአማርኛ ቋንቋ እንዳይነጋገሩና የአማርኛ ሙዚቃ እንዳይሰሙ እየተከለከሉ ነው፤ ይህንን ትዕዛዝ ጥሶ የተገኘ ሰው እየተደበደበና እየታሰረ ይገኛል፤

ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙ ወጣቶችና እና የማንነት ጥያቄ የሚያቀርቡ አዛውንቶች እየተደበደቡና እየታሰሩ እንዲሁም ከአካባቢያቸዉ እንዲሰደዱ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በተለይ በአሁኑ ሰዓት ጥያቄያችንን ለማዳፈን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ:: በዚህም ምክንያት ሕይወታችንና እንደ ህዝብ የመቀጠል ህልውናችን አደጋ ውስጥ ገብቷል በማለት የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጠያቂ ኮሚቴ አባላት ለሰመጉ በአካል ቀርበው አመልክተዋል፡፡ በዚህም መሠረት የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ አካባቢውን ጥሎ እንዲሰደድ የተለያዩ ጫናዎች እየተፈፀሙባቸው እንደሚገኝና የመከላከያ ሃይልና የፌዴራል ፖሊስ በቦታው ተሰማርቶ ከተጋረጠብን ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ሊጠብቀን ይገባል ብለዋል፡፡

ሰመጉ የፌዴራል መንግስት ለወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር በአስቸኳይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ፤ እንዲሁም የሰው ህይወት ያጠፉ፣ አካል ያጎደሉና ንብረት ያወደሙ አካላትን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ፤ ለተጐጂዎች ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈልና የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ በማቋቋም ወደቀያቸው እንዲመልስ፤ ለደህንነታቸውም ዋስትና እንዲሰጥ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት አመታት የራያ እና የወልቃይት ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የማንነት እና እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን በስፋት ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ለእነዚህ የማንነት ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሁሉንም የፖለቲካ አካላት እና የዜጎችን ገንቢ ተሳትፎ ማረጋገጥ ለሀገር አንድነት ወሳኝ መሆኑን ሰመጉ ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም ለአመታት በአፈሙዝ ተዳፍነው የቆዩ ጥያቄዎችን በጥይት ሳይሆን በሕግ እና በስርዓት መፍታት ለዜጐች ሁለንተናዊ መብቶች መከበር ብቸኛው አማራጭ መሆኑን በመገንዘብ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሰመጉ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም፤ መንግስት ለሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር እንዲሁም ለህግ የበላይነትና የፍትሕ ስርዓቱን ለማሻሻል የገባውን ቃል እንዲተገብርና የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶችን እንዲያከብርና እንዲያስከብር ሰመጉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

wanted officials